tgoop.com/tesfa_biranaye/2967
Last Update:
በ1950ዎቹ በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ በተደረገ ጥናት ዶር ከርት ሪቸተር ሶስት አይጦችን ወስዶ ውሃ በሞላበት እቃ ውስጥ አስቀመጣቸው::
አይጦቹ ምን ያክል ከውሃው ለመውጣት ወደ ላይ ይዋኛሉ የሚለውን መፈተን ነበር የዚህ ጥናት ዓላማ::
በአማካይ ከ15 ደቂቃ በሗላ አይጦቹ ተስፋ በመቁረጥ ውሃው ውስጥ ይሰጥሙ ነበር::
ተመራምሪዎች ሌሎች አይጦች አምጥተው አይጦቹ ተስፋ ቆርጠው ከመስጠማቸው በፊት በእጃቸው ጠልቀው ያወጧቸውና አድርቀው ለጥቂት ደቂቃዎች እንዲያፉ ያደርጏቸዋል::
ከዛም በሗላ ለሁለተኛ ዙር ወደ ውሃው ውስጥ ይጨምሯቸዋል::
በሁለተኛው የሙከራ ጊዜ አይጦቹ ውሃ ውስጥ ለመውጣት ለምን ያክል ጊዜ የሞከሩ ይመስላችህሗል? አስታውሱ: ተስፋ እስከመቁረጥ የዋኙት ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት ነው...
ምን ያክል ጊዜ የዋኙ ይመስላችሗል?
ሌላ 15 ደቂቃ? 10 ደቂቃ? 5 ደቂቃ? አይደለም! 60 ሰአት!
ይሄ በስህተት የተከሰተ አይደለም። እውነት ነው ለ60 ሰአት ከውሃ ውስጥ ለመውጣት ዋኝተዋል.
ከዚህ የተወሰደው መደምደሚያ ምንድነው; አይጦቹ ሊያድናቸው የሚመጣ እንዳለ ሲያምኑ ሰውነታቸውን በመጀምሪያው ዙር አይቻልም ብለውት ከነበረው ገደብ በብዙ አልፈው መግፋት ችለዋል::
ከዚህ ሃሳብ ጋር እተዋችሃለሁ:
ተስፋ የደከሙ አይጦችን 60 ረጅም ሰአት እንዲዋኙ ካስቻላቸው, እኛ ፈጣሪ አንድ ቀን እንደሚደርስልን ብናምን, ምን ያክል ልንጏዝ እንችላለን?
የፈጠራችሁ አምላክ አንድ ቀን እንደሚደርስላችሁና እንደማይረሳችሁ አስታውሱና በርትታችሁ ተስፋ ባለመቁረጥ የህይወትን የውጣ ውረድ ዋና ዋኙ! በርቱ!
Join us...
✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
BY Tesfa
Share with your friend now:
tgoop.com/tesfa_biranaye/2967