tgoop.com/tesfa_biranaye/2983
Create:
Last Update:
Last Update:
ይህ ሰው ዋሬን ቡፌት ይባላል የካፒታሊስቶች ቁንጮ የዓለማችን ቁጥር 1 በቢሊየን ዶላር የሚያንቀሳቅስ ባለሃብት ነው።
ይህ ሰው አሁን ላይ እድሜው እየገፋ ሲሄድ ሞት እንደቀረበው አውቀ። እናም "ራቁቴን ተወለድኩ ስሞትም ራቁቴን እሄዳለሁ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ወሰደ። (ኢዮብ 1:21) የሚለው የመጽሐፍ ቃል ትዝ አለው በገዛ ፈቃዱ ወሰነ የሃብቱን 99.5 ከመቶ ለበጎ አድራጎት ለማዋል ቃል ገባ ይህም 150 ቢሊየን ዶላር ገደማ ማለት ነው።
ሐብቴ ለልጆቼ ለዘመዶቼ ሳይሆን ለወደቁት እና ለተራቡት ይሁንልኝ አለ መኖር ማለት ገንዘብ መሰብሰብ በድሎት መኖር እና መሞት ብቻ አለመሆኑን ገብቶታል መኖር ትርጉሙ መስጠት መሆኑ ገብቶታል
ዋሬን ቡፌት ይህን ሁሉ የወሰነው በጣም አንባቢ እና የመጽሐፍ ወዳጅ ስለሆነ ነበር በቀን ውስጥም ብዙ ሰዓቱን በንባብ የሚያሳልፍ ባለጠጋ ነበር "የንባብ ኃይልን "እዚህ ጋር ታዩታላችሁ በሉ በቀን 1 ሰዓት ለንባባችሁ ስጡ ለመንፈሳዊ ሕይወታችሁ ሲጨንቃችሁ ሲከፋችሁ የሕይወትን ቃል ታገኛላችሁ እና አንብቡ ኑሮንስ ለመሻሻል ለቢዝነሳችሁም ለስራችሁ ለእድገታችሁ ቢሆን አንብቡ
እናንብ በጎውን እናስብ መልካም ቀን፡፡
Join us...
✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
BY Tesfa
Share with your friend now:
tgoop.com/tesfa_biranaye/2983