tgoop.com/tesfa_biranaye/2994
Create:
Last Update:
Last Update:
#self_confidence
ናይጄሪያዊው ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋች ቪክቶር ቦኒፌስ ለባየር ሊቨርኩሰን የፈረመ ሰሞን አስቤዛ ለመግዛት ጀርመን ውስጥ የሚገኝ አንድ የቱርክ ሱፐርማርኬት ይገባል።
እና የሚፈልገውን የምግብ አይነት እያነሳ በያዘው ዘምቢል ውስጥ እያስቀመጠ እያለ የሱፐርማርኬቱ ተቆጣጣሪ ከኋላው ሆኖ ሲከተለው ተመለከተ።
ቪክቶር የሱፐር ማርኬት ተቆጣጣሪ ተመድቦ የሚከተለው እሱን ብቻ እንደሆነ ተረድቷል። በሱፐር ማርኬቱ ያለው አንድ ጥቁር እሱ ነው፡ ለዛም ነው የሚከተለው።
ይህን እንደተረዳ ወደ ተቆጣጣሪው ዞሮ "እንካ ያዝ" ብሎ ዘምቢሉን ዘረጋለት : ተቆጣጣሪው አልገባውም
ቪክቶር ደገመለት "ጠባቂዬ እንደመሆንህ ዘምቢሉን የመያዝ ግዴታ አለብህ፡ የጋርድ ስራህን አትርሳ እንጂ" አለው።
በዚህ ጊዜ የሱፐር ማርኬቱ ተቆጣጣሪ በንዴት "ማነው ያንተ ጋርድ ያደረገኝ ?"
ቪክቶር እየሳቀ "ታዲያ የኔ ጋርድ ካልሆንክ ምን በሄድኩበት ትከተለኛለህ" ሲለው፡ ተቆጣጣሪው በመጣበት እግሩ ሀፍረቱን ተከናቦ ጥሎት ሄደ
ቪክቶር ቦኒፌስ በከለሩ ምክንያት ሊያሸማቅቀው የመጣውን ሰው በራስ መተማመን ስሜት በዚህ መልኩ የመልስ ምት ሰጥቶ የሚፈልገውን ገዝቶ ወጣ።
Join us...
✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
BY Tesfa
Share with your friend now:
tgoop.com/tesfa_biranaye/2994