tgoop.com/tesfa_biranaye/3003
Create:
Last Update:
Last Update:
ባኢስ!
ብዙ ግዜ የቲክቶክ ቪዲዮ ስመለከት ባኢስ የተባለ ሰው አያለሁ።
በባኢስ ውስጥ ነገን አያለሁ፤ ከቀልዱ እና የማስታወቂያ ስራው ባለፈ ህይወቱን እንማርበት:-
ምናልባት ከቅርብ ግዜ በፊት ባኢስን ከቅርብ ወዳጂ ዘመዶቹ ወይም የአካባቢው ሰዎች ውጭ የሚያውቀው ይኖራል ብዬ አልገምትም ፤ የሚያውቁትም ከዚህ እድሜው በኋላ ህይወቱ በዚህ ልክ ይቀየራል ብለው ይጠብቃሉ ብዬ አላስብም።
አሁን ግን በፊልም፣ ሙዚቃ ወይም ሌሎች እውቅና ሊያመጡ በሚችሉ ዘርፎች ከተሰማሩ ግለሰቦች ያልተናነሰ እውቅና ሲኖረው በስራዎቹም ኑሮዉን በጥሩ ሁኔታ እየመራ እንደሆነ ያስታውቃል።
እኔም ፈጣሪ እድሜ ይስጠን እንኑር እንጂ የቀረ፣ የቆመ፣ ያበቃ ነገር እንደሌለና ሁሉም ነገር የዘገዬ ቢመስልም በግዜው ውብ ይሆናል፤ የረፈደ ነገር የለም ብዬ እንዳስብ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ተስፋ የቆረጥን የባኢስ ህይወት፣ የእኛ ቀን እንደሚመጣ እና ነገን ተስፋ እንድናደርግ ያደርገናል።
በተስፋ ነገን ለማየት እንጓጓ መቸም ቢሆን ከዛሬ ነገ የተሻለ ነው።
Join us...
✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
BY Tesfa
Share with your friend now:
tgoop.com/tesfa_biranaye/3003