TIKVAHETHMAGAZINE Telegram 23774
"በሰርግ መልሳችን ቀን ግን ይሆናል ብዬ አሰቤ አላዉቅም ነበር" - ዶክተር በየነ አበራ

በሰርጉ ማግስት የሙሽሪት ቤተሰቦች ከጠሩት የመልስ ፕሮግራም ላይ ላይ ተነስቶ በመሄድና የተሳካ ቀዶ ጥገና በማድረግ እናትና ልጅን የታደገዉ ዶክተር በብዙዎች ምስጋና ተችሮታል።

ይህ የሚያስመሰግን ተግባር የተፈጸመው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው።

በሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር በየነ አበራ በትላንትናው ዕለት በሰርጉ ማግስት የሙሽሪት ቤተሰቦች በጠሩት የመልስ ዝግጅት ላይ ነበር።

በዚህ ዝግጅት ላይ እንዳለ ነው እንግዲህ ከሚሰራበት ሆስፒታል የስልክ ጥሪ የደረሰው። የስልክ ጥሪውም እናትና ልጅን እንዲታደግ የቀረበ ነበር።

ዶክተር በየነ ስለሁኔታው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲናገሩ "መልስ በሀገራችን ባህልና ወግ ትልቅ ቦታ እሚሰጠዉ አዉቃለሁ በዕለቱ አማቾቼ አክብረው ጠርተዉን ፕሮግሙ እየተካሄደ ነበር ስልክ የተደወለልኝ" ሲል ያስረዳል።

"የመጀመሪያዉ ዙር አላነሳሁም! በድጋሚ ሲደወልልኝ አነሳሁት አንዲትን እናት ምጥ እንዳስቸገራትና ቀዶ ሕክምና የግድ እንደሚያስፈልጋት  ተነገረኝ፤ አላመነታሁም!" በማለት የመልስ ዝግጅቱን አቋርጦ ለመሄድ መወሰኑን ነግሮናል።

ይህንን ጉዳይ እንዴት ለሙሽሪት እንዳስረዱና እንዳሳመኗት ጠይቀናቸዋል፤ እሳቸው ሲመልሱም፦

"በፍቅር ሕይወታችን ወቅት የትዳር አጋሬን በተደጋጋሚ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በተደጋጋሚ እነግራት ነበር፤ በሰርግ መልሳችን ቀን ግን ይሆናል ብዬ አሰቤ አላዉቅም ነበር" ሲሉ ሁኔታውን ይግልጻሉ።

ከዚያም "ለሙሽራዋ ባለቤቴና ለሚዜዎቼ ነገርኳቸዉና ወደ ሆስፒታሉ አመራሁ። የሙሽራዋ ባለቤቴን ጨምሮ ጓደኞቼና ጓደኞቿ ለሙያው ያለኝ ፍቅርና ቁርጠኝነት ስለሚያዉቁ ሊጫኑኝ አልፈለጉም፤" ያሉት ዶክተር በየነ "ቤተሰቦቿን ግን ተመልሼ ይቅርታ ለመጠየቅ ወስኜ ነበር ወደ ሆስፒታል የሄድኩት" ይላሉ።

አክለውም "ወደ ሆስፒታሉ ስደርስ የቀደ ጥገና ቲሙ ዝግጁ ስለነበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጌ ቀዶ ሕክምናውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል" ብለዋል።

ዶክተር በየነ አበራ የመጀመሪያ ዲግሪያቸዉን በሕክምና ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የስፔሻሊቲ  መርሐግብራቸዉን ደግሞ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ሰርተዋል።

ዶክተር በየነ አበራ እናመሰግናለን 👏

#TikvahEthiopia

@TikvahethMagazine

tgoop.com/tikvahethmagazine/23774
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-MAGAZINE

Share with your friend now:
tgoop.com/tikvahethmagazine/23774

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Developing social channels based on exchanging a single message isn’t exactly new, of course. Back in 2014, the “Yo” app was launched with the sole purpose of enabling users to send each other the greeting “Yo.” As the broader market downturn continues, yelling online has become the crypto trader’s latest coping mechanism after the rise of Goblintown Ethereum NFTs at the end of May and beginning of June, where holders made incoherent groaning sounds and role-played as urine-loving goblin creatures in late-night Twitter Spaces. Hui said the messages, which included urging the disruption of airport operations, were attempts to incite followers to make use of poisonous, corrosive or flammable substances to vandalize police vehicles, and also called on others to make weapons to harm police. You can invite up to 200 people from your contacts to join your channel as the next step. Select the users you want to add and click “Invite.” You can skip this step altogether. Although some crypto traders have moved toward screaming as a coping mechanism, several mental health experts call this therapy a pseudoscience. The crypto community finds its way to engage in one or the other way and share its feelings with other fellow members.
from us

Telegram TIKVAH-MAGAZINE
FROM American