TIKVAHETHMAGAZINE Telegram 23791
በኡጋንዳ የተከሰተውና ሴቶችን ነጥሎ ስለሚያጠቃው በሽታ እስካሁን ምን ይታወቃል?

በ2023 ለመጀመሪያ ጊዜ እንደታየ የሚነገረውና በኡጋንዳዊያን ዘንድ በተለምዶ ‹Dinga Dinga› ማለትም የሚያንዘፈዝፍ/የሚያስደንስ በማለት የሚጠሩት በሽታ ሴቶችንና ህፃናትን እያጠቃ ይገኛል ተብሏል።

በሽታው እስካሁን በኡጋንዳ ቡንዲቡግዮ ወረዳ  300 የሚጠጉ ሰዎችን ያጠቃ ሲሆን ምንም አይነት ሞት ግን አልተመዘገበም።

የዲንጋ ዲንጋ ምልክቶች ምንድ ናቸው?

በዲንጋ ዲንጋ በሽታ የተያዙ ታካሚዎች የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ፦

► የዳንስ እንቅስቃሴዎችን የሚመስል ከመጠን ያለፈ የሰውነት መንቀጥቀጥ/መንዘፍዘፍ፤

► ትኩሳት እና ከፍተኛ ድካም፤

► የመራመድ ወይም ሰውነት ያለመታዘዝ ችግር፤

የኡጋንዳ ሚዲያዎች እንደዘገቡት፣ አንዳንድ ሰዎች ሰውነታቸው ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ስለሚንቀጠቀጥ በእግር ለመራመድ በበሽታው ለተያዙት የማይቻል ነው ይላሉ።

ፔሸንስ ካቱሲሜ የተባለች ታካሚ በበሽታው ስትያዝ ያጋጠማትን  ለመገናኛ ብዙኃን ስትገልጽ፦

"ድካም ተሰማኝ እና ሰዉነቴ አልታዘዝ አለኝ፣ ለመራመድ ስሞክር ሰውነቴ ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መልኩ ይንቀጠቀጣል፣ በጣም ይረብሸኝ ነበር።" ብላለች።

የጤና ባለሞያዎች ምን እያሉ ነው?

የወረዳው የጤና ኦፊሰር የሆኑት ዶ/ር ኪይታ ክርስቶፈር፥ የዲንጋ ዲንጋን መንስኤ ለማወቅ እየሞከሩ መሆኑን ገልጸው የታካሚዎች ናሙናም ወደ ኡጋንዳ ጤና ሚኒስቴር ለምርመራ ተልኳል ብለዋል።

ዶ/ር ክርስቶፈር፥ የበሽታው የማገገሚያ ፍጥነት ከፍተኛ መሆኑንና አብዛኞቹ ታካሚዎች ተገቢውን ህክምና በወሰዱ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ማገገም መቻላቸውን ተናግረዋል።

አክለውም በባህላዊ መንገድ የተቀመሙ መድኃኒቶችን ለዚህ የጤና ችግር ጠቃሚ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምንም ዓይነት ሳይንሳዊ ማስረጃ ስለሌለ እንዳይወስዱ አስጠንቅቀዋል።

በሽታው በአንቲባዮቲክስ መድኃኒቶች ሊታከም ይችላል ሲሉም ያክላሉ።

በማኅበራዊ ሚዲያ የተለቀቁ ቪዲዮዎች በበርካቶች እይታ ቢያገኙም እስካሁን ድረስ የኡጋንዳ ጤና ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም።

ዲንጋ ዲጋን ምን ሊያስከትል ይችላል?

ዲንጋ ዲንጋ ትክክለኛ መንስኤ አሁንም እንቆቅልሽ ነው። ባለሙያዎች ከቫይረስ ኢንፌክሽን እስከ የአካባቢ ሁኔታዎች ድረስ የተለያዩ መላምቶችን ያስቀመጡ ሲሆን ነገር ግን እስካሁን የተረጋገጠ ነገር የለም።

አንዳንዶች ይህንን ክስተት በ1518 በፈረንሳይ ስትራስቡርግ ከተማ ሰዎች ባልታወቀ ምክንያት ለቀናት ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መልኩ ያስጨፍር ከነበረው ታሪካዊው የዳንስ ቸነፈር ጋር እያመሳሰሉትም ይገኛሉ።

@tikvahethmagazine

tgoop.com/tikvahethmagazine/23791
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-MAGAZINE

Share with your friend now:
tgoop.com/tikvahethmagazine/23791

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Your posting frequency depends on the topic of your channel. If you have a news channel, it’s OK to publish new content every day (or even every hour). For other industries, stick with 2-3 large posts a week. The optimal dimension of the avatar on Telegram is 512px by 512px, and it’s recommended to use PNG format to deliver an unpixelated avatar. Activate up to 20 bots More>> Read now
from us

Telegram TIKVAH-MAGAZINE
FROM American