tgoop.com/tikvahethmagazine/23806
Last Update:
የ5 ዓመት ህፃን ልጅ የደፈሩ 2 ግለሰቦች ፍርድ ቤቱ በ19 ዓመት እስራት ቀጥቷቸዋል።
በጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ አስተዳደር በ 5 ዓመት ህፃን ልጅ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በ 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ወስኖባቸዋል።
ወንጀሉ የተፈፀመው በወናጎ ከተማ አስተዳደር ቱቱፈላ ቀበሌ ኦዶላ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ሲሆን ተበዳይ የሆነችው የ5 ዓመት ህፃን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ዳቦ ለመግዛት በሄደችበት ነው ጥቃቱ የተፈጸመባት።
ጥቃቱን ያደረሱት አቶ ኤልያስ ኤቶ እና አቶ ታምሩ ንጋቱ የተባሉ የዳቦ መጋገሪያ ቤቱ ሰራተኞች ናቸው።
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞቹ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።
🔴 3 ዓመት ከ 6 ወር ህጻን መድፈር ሙከራ ያደረገው ግለሰብ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል።
በዚያው ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ቀን በዋለው ችሎት ተከሳሽ ወጣት ኤርምያስ ፀጋዬ 3 ዓመት ከ 6 ወር በሆነችው ተበዳይ ህፃን ከምትጫወትበት ቦታ ወደ ኤት ኤል ትምህርት ቤት ይዞ በመሄድ የመድፈር ሙከራ ማድረጉን በምስክር ያረጋገጠው ፍርድቤት #በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
@tikvahethmagazine