tgoop.com/tikvahethmagazine/23808
Last Update:
የኢትዮጵያዊያን ኤንዶስኮፒክ እና ላፓሮስኮፒክ ቀዶ ጥገና ማህበር ተመስርቷል።
የኢትዮጵያዊያን ኤንዶስኮፒክ እና ላፓሮስኮፒክ ቀዶ ጥገና ማህበር (SEELS) በዛሬው ዕለት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ውስጥ መመስረቱን ማኅበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላከው መረጃ ያሳያል።
ማህበሩን የመሰረቱት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ተቋማት ውሰጥ የሚሰሩ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች በጋራ ተሰባስበው እንደሆነ በምስረታው ወቅት ተገልጿል።
በምስታው ላይ የተገኙት የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ዋና ፕሮቮስት የሆኑት ዶክተር አንተነህ ምትኩ ማኅበሩ በኢትዮጵያ ለሚደረጉ የቀዶ ጥገና ሕክምናዎች በጎ ተጽእኖ ከፍ ያለ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
ለማኅበሩ መመስረት አንበሳውን ድርሻ ከተጫወቱት መካከል ዶክተር ሱራፌል ሙላቱ በበኩቻቸው የቀዶ ጥገና ሐኪሞች በጋራ መሰባሰብ በመጠነኛ ቀዶ ጥገናና በመሳሪያ በመታገዝ የሚደረግን ቀዶ ጥገናን ከፍ ወዳለ ደረጃ እንደሚያሳድገው እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
የኤንዶስኮፒክ እና ላፓሮስኮፒክ ቀዶ ጥገና ማህበር (SEELS) መመስረት አገልግሎቱን ለሚፈልጉ፣ የዚህ ሙያ ባለሙያ መሆን ለሚፈልጉ ሐኪሞች፣ ለኢትዮጵያ የሕክምና እድገት አዲስ በር የከፈተ እና ተስፋ ሰጪ መሆኑም ተገልጿል።
✍ Dr. Zelalem Chimdesa/#TikvahFamily🩵
@tikvahethmagazine
BY TIKVAH-MAGAZINE
Share with your friend now:
tgoop.com/tikvahethmagazine/23808