#ጎንደር
ጥምቀት በዓል በጎንደር በቅዱስ ፋሲለደስ ጥምቀተ ባሕር በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። የሀገሪቱን ርዕሰ ብሔር ጨምሮ በርካታ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች በየዓመቱ ይታደሙታል።
በጎንደር ታቦታትን ወደ ባሕር ማውረድ የተጀመረው በቀዳሚ አድባራት ቀሃ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ ይነገራል፡፡
በኋላም ዐፄ ፋሲል ጎንደርን መስርተው መንግሥታቸውን ካደላደሉ በኋላ 7 አብያተ ክርስቲያናትን ተክለው በቀሃ ወንዝ ዳርቻ ማክበሩን የቀጠሉበት ሲሆን ታሪኩን ለመጠበቅም በቦታው የጥምቀቱን ግንብና ታቦት ማደሪያ አስገንብተው አጽንተውታል።
በተለምዶ “አርባ አራቱ ታቦት” የጎንደር መገለጫ ቢሆንም በጥምቀት በዓል ወደ ፋሲለደስ መጠመቂያ ግንብ የሚወርዱት የተወሰኑ ታቦታት ናቸው። ይህም የሆነው የቦታ ጥበት እንዳይኖር በማሰብ ዐፄ ፋሲለደስና ሊቃውንቱ ተመካክረው ነው።
በዓለ ጥምቀቱን ተምሳሌታዊ በሆነ መልኩ እንዲገልጽም ቀሃ ኢየሱስና መንበረ መንግስት መድኃኔዓለም ተጠማቂውን በማስመልከት፣ እልፍኝ ጊዮርጊስ ከሰማዕታት ወገን፣ አጣጣሚ ሚካኤልና ፊት ሚካኤል ከመላዕክት ወገን፣ አባጃሌ ተክለ ሃይማኖትና ቅዱስ ፋሲለደስ ከጻድቃን ቅዱሳን ወገን እንዲሁም አጥማቂው ደብረ ጽጌ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ በምዕመናን ታጅበው ወደ ባህረ ጥምቀቱ ይወርዳሉ፡፡
አርባ አራቱ ታቦታተ ጎንደር የሚባሉት ጎንደር የመንግሥት ከተማ ከሆነችበት እስከ ጎንደር ዘመን ማክተሚያ ፈፃሜ መንግሥት አፄ ተክለ ጊዮርጊስ (1772-1777) ድረስ በነገሱ 18 ነገሥታት የታነጹ ቤተ-ክርስቲያናት ቁጥርን ለማመልከት የተቀመጠ መሆኑ ይነገራል።
ፎቶ: የጎንደር ከተሞ ኮሙኒኬሽን ቢሮ
Credit : SBS Radio
@tikvahethmagazine

tgoop.com/tikvahethmagazine/23894
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-MAGAZINE
Share with your friend now:
tgoop.com/tikvahethmagazine/23894