tgoop.com/tikvahethmagazine/24012
Last Update:
#GlobalBank
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የዲጅታል ባንኪንግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።
አገልግሎት መስጠት የጀመረው የዲጂታል ባንኪንግ ማዕከል የባንክ ሂሳብ መክፈት፣ ገንዘብ ገቢ ማድረግና ወጪ ማድረግ፣ ቀሪ ሂሳብና የሂሳብ መግለጫ ማሳየት፣ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን መመንዘር፣ የተለያዩ ክፍያዎችን መፈፀም ያስችላል ተብሏል።
በተጨማሪም ያለ ኤቲኤም ካርድ አገልግሎት ማግኘት፣ ቼክ መመንዘርና ገቢ ማድረግን ጨምሮ ደንበኞች የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት መጠቀም በሚፈልጉበት ወቅት በማዕከሉ በመገኘት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጁ ታብሌቶች መጠቀም እንደሚችሉም ገልጿል፡፡
ባንኩ በመግለጫው ማዕከሉ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ክፍል ያለው መሆኑንና ተቀዳሚ (corporate) ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው የቪዲዮ ባንኪንግ አገልግሎት ማገኝት የሚያስችላቸው አገልግሎትም እንደሚሰጥ ጠቅሷል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ይህ ማዕከል ሥራ መጀመሩ ባንኩ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከማድረጉም ባሻገር የባለአክሲዮኖችን ጥቅም ከፍ ከማድረግ እና የሀገርን ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል።
ባንኩ በዘንድሮው አመትም ከታክስ በፊት ብር 757.6 ሚሊዮን ማትረፉን የገለጸ ሲሆን የቅርንጫፍ ብዛቱንም ወደ 238( ሁለት መቶ ሰላሳ ስምንት ) ከፍ ማድረግ ችሏል። በአሁን ሰዓትም ባንኩ ከ 1.7 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉት አሳውቋል፡፡
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ደ/ር ተስፋዬ ቦሩ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የባንክ ካፒታል ዕድገት ዝቅተኛ ጣሪያ በቀረው ጊዜ ውስጥ እንደሚያሳካ ገልጸዋል።
ባንኩ የተቀማጭ ሂሳቡን ከ 20.6 ቢሊዮን ብር በላይ ያደረሰ መሆኑንና የባንኩ ጠቅላላ ሃብት ደግሞ ከ 26.6 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱንም አስታውቋል።
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሜክሲኮ አካባቢ ለዋና መ/ቤት ግንባታ በተረከበው 5,550 ካ.ሜ ቦታ ላይ የወደፊት የዋና መ/ቤት ህንፃ ለመገንባት በሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ እየሰራ እንደሆነም ለማወቅ በላከልን መግለጫ ጠቅሷል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine