Telegram Web
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update

በትላንትናው ዕለት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ "ጎቱ ኦኖማ" በተባለው አከባቢ ከሰዓት 10 ሰዓት አከባቢ በተራሮች ላይ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱ መገለጹ ይታወሳል።

ወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ደቂቃዎች በፊት ባወጣው መረጃ መሰረት አደጋው በመንግስትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን አስታውቋል።

ቢሮው እንዳስታወቀው ባጋጠመው የእሳት አደጋ ​​በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አለመድረሱን ገልጿል።

@tikvahethmagazine
#ጎንደር

ጥምቀት በዓል በጎንደር በቅዱስ ፋሲለደስ ጥምቀተ ባሕር በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። የሀገሪቱን ርዕሰ ብሔር ጨምሮ በርካታ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች በየዓመቱ ይታደሙታል።

በጎንደር ታቦታትን ወደ ባሕር ማውረድ የተጀመረው በቀዳሚ አድባራት ቀሃ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ ይነገራል፡፡

በኋላም ዐፄ ፋሲል ጎንደርን መስርተው መንግሥታቸውን ካደላደሉ በኋላ 7 አብያተ ክርስቲያናትን ተክለው በቀሃ ወንዝ ዳርቻ ማክበሩን የቀጠሉበት ሲሆን ታሪኩን ለመጠበቅም በቦታው የጥምቀቱን ግንብና ታቦት ማደሪያ አስገንብተው አጽንተውታል።

በተለምዶ “አርባ አራቱ ታቦት” የጎንደር መገለጫ ቢሆንም በጥምቀት በዓል ወደ ፋሲለደስ መጠመቂያ ግንብ የሚወርዱት የተወሰኑ ታቦታት ናቸው። ይህም የሆነው የቦታ ጥበት እንዳይኖር በማሰብ ዐፄ ፋሲለደስና ሊቃውንቱ ተመካክረው ነው።

በዓለ ጥምቀቱን ተምሳሌታዊ በሆነ መልኩ እንዲገልጽም ቀሃ ኢየሱስና መንበረ መንግስት መድኃኔዓለም ተጠማቂውን በማስመልከት፣ እልፍኝ ጊዮርጊስ ከሰማዕታት ወገን፣ አጣጣሚ ሚካኤልና ፊት ሚካኤል ከመላዕክት ወገን፣ አባጃሌ ተክለ ሃይማኖትና ቅዱስ ፋሲለደስ ከጻድቃን ቅዱሳን ወገን እንዲሁም አጥማቂው ደብረ ጽጌ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ በምዕመናን ታጅበው ወደ ባህረ ጥምቀቱ ይወርዳሉ፡፡

አርባ አራቱ ታቦታተ ጎንደር የሚባሉት ጎንደር የመንግሥት ከተማ ከሆነችበት እስከ ጎንደር ዘመን ማክተሚያ ፈፃሜ መንግሥት አፄ ተክለ ጊዮርጊስ (1772-1777) ድረስ በነገሱ 18 ነገሥታት የታነጹ ቤተ-ክርስቲያናት ቁጥርን ለማመልከት የተቀመጠ መሆኑ ይነገራል።

ፎቶ: የጎንደር ከተሞ ኮሙኒኬሽን ቢሮ
Credit : SBS Radio

@tikvahethmagazine
#ምንጃር_ሸንኮራ

በሀገራችን ኢትዮጵያ የጥምቀት በዓል በደመቀ ሁኔታ ከሚከበርባቸው ቦታዎች አንዱ በምንጃር ሸንኮራ ኢራንቡቲ ነው። በዓሉ በዚህ አከባቢ መከበር ከጀመረ ዘንድሮ ለ623 ኛ ጊዜ መሆኑ ተነግሯል።

በተለይም የሸንኮራ ወንዝ ዳርቻ ባለው ኢራንቡቲ 44 ታቦታት በአንድነት የሚያድሩበት ልዩ ጥምቀተ ባህር መሆኑ ይነገርለታል።

ቀደምት አበው ይህን የሸንኮራ ወንዝ ዳርቻ ለባህረ ጥምቀትነት የመረጡበትን ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ማምራቱን በማሰብ ተፈጥሮአዊ ወንዝ ፍለጋ እንደሆነ የአካባቢው የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ይገልጻሉ።

የሸንኮራ ወንዝ ለጥምቀተ ባህርነት ሲመረጥ ወንዙ እንደ ዮርዳኖስ ከላይ ከመነሻው አንድ ሆኖ መሀል ላይ ለሁለት ተከፍሎ ዝቅ ብሎ የሚገናኝ፣ ውኃውም ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የሚፈስ መሆኑ ከዮርዳኖስ ወንዝ ጋር ስለሚያመሳስለው እንደሆነም ይነገራል።

በተጨማሪም ከመነሻው ጀምሮ የ44ቱም ታቦታት ጸበል መኖሩ ለጥምቀቱ ያለውን ተምሳሌትነት ከፍ ያደርገዋል

ለአከባቢው ማኅበረሰብ የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ በዓልነቱ በተጨማሪ ያለፈውን በሙሉ የሚጋብዝበትና ማኅበራዊ እሴቱን የሚያሳይበት በዓሉ ነው።

ለወትሮው ከሌሎች አከባቢዎች የሚመጡ በርካታ ጎብኚዎችን የሚያስተናግደው ኢራንቡቲ ዘንድሮ ካለው የጸጥታ ችግር ምክንያት በርካታ ምዕመኖችን በስፍራው አልተገኙም።

ፎቶ: ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኮሚኒኬሽን
Credit: SBS Radio

@tikvahethmagazine
#UAE 🇦🇪

የጥምቀት በዓል ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው የውጭ አገራት በልዩ ልዩ ኃይማኖታዊ ክዋኔዎች በድምቀት ይከበራል።

በዓሉ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች በሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በአልዐይን ከተማ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተከብሯል።

Credit : Ethiopian Embassy - UAE

@tikvahethmagazine
#እምድብር

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በእምድብር ቅዱስ እንጦንዮስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተከብሯል።

ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የእምድብር ሀገረስብከት ጳጳስ በመሩት መስዋዕተ ቅዳሴ የተጀመረው በዓል ወደ ጎገብ ወንዝ በመውረድና በመባረክ በዓሉ ተከብሯል። (ሰላም ካቶሊክ ቲቪ)

@tikvahethmagazine
2025/02/02 20:46:35
Back to Top
HTML Embed Code: