Telegram Web
ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ወደ ውጪ በሚላከው የነዳጅ ምርት ክፍያ ላይ አልተስማሙም ተባለ።

የባህር በር የሌላት ደቡብ ሱዳን የምታመርተውን ነዳጅ በሱዳን በኩል ለውጪ ገበያ የምታቀርብ ሲሆን ለዚህም በምትከፍለው ክፍያ ዙሪያ ከሱዳን ጋር ከስምምነት መድረስ አልቻለችም።

ደቡብ ሱዳን ነዳጇን በፖርት ሱዳን በኩል ስትልክ ትከፍል የነበረው ክፍያ ላይ ሱዳን ከሎጅስቲክስ ወጪ የተነሳ ማሻሻያ ማድረጓ ሃገራቱ እንዳይስማሙ አድርጓቸዋል ተብሏል።

በጦርነቱ ምክንያት የነዳጅ ምርቷን ለአለም ገበያ ማቅረብ ያልቻለችው ደቡብ ሱዳን በ2024 በኢትዮጵያ አድርጋ በጂቡቲ ለመላክ የሚያስችላትን የነዳጅ ቱቦ ለመስራት ማቀዷን መግለጿ ይታወሳል።

Source :Oilprice

@Tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
#Coffee ☕️ በዓለም አቀፉ የቡና ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ የታየ ዝቅተኛው የቡና ዋጋ ተመዝግቧል። ለዋጋው መቀነስ ምክንያት ከሆኑት ውስጥ አንዱ የአረቢካ ቡናን በዋነኝነት በምታመርተው ብራዚል በቂ ዝናብ በመኖሩ ካለፈው አመት  የተሻለ የቡና ምርት በመጠበቁ ነው። የቡና ዋጋ ባለፈው ሚያዝያ ወር በፓውንድ ሪከርድ የሆነ 4.11 ዶላር ደርሶ እንደነበር ሲታወስ ቡና ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ዋጋው በሚቀጥሉት…
#Coffee ☕️

"ባለፉት 11 ወራት ብቻ  409 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጪ ሀገር ተልኳል፣ በቀጣይ አመት 1.3 ሚሊዬን ቶን ቡና ለማምረት እየተሰራ ነው"

"በየሳምንቱ ዝቅተኛ የመሸጫ ዋጋ ተመን እየወጣ ለቡና ላኪዎች ማኆበር በየሳምንቱ መረጃ ይሰጣል" - ቡናና ሻይ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በመጭው አመት 1.3 ሚሊየን ቶን የቡና ምርት ለማግኘት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ዑመር የቡና ምርትን ከማሳደግ አንፃር በርካታ ስራዎችን እየተሰሩ መሆኑን እና ውጤታማ መሆን መቻሉን አንስተው ባለፉት 11 ወራት 409 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዝርዝር ምን አሉ?

የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሰፊ ስራዎችን ተሰርተዋል። ላለፉት በርካታ አመታት በየአመቱ ከ400 እስከ 500 ሺህ ቶን ብቻ ነበር ማምረት የተቻለው። በዘንድሮው አመት ግን 1.1 ሚሊየን ቶን ማምረት ተችሏል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የምርት ትንበያ ከየትኛውም አለም ሀገሮች በተሻለ ሁኔታ እየተሰራበት ነው። የትኛው አካባቢ ምርታችን ሊቀንስ እንደሚችል፣ በምርት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመለየት እና ምን ያክል ምርት ሊገኝ እንደሚችል የትንበያ ስራዎች ይሰራሉ።

አሁን ላይ ያለውን የቡና ምርት መጨመር የተቻለው በመንግሰት ኢንሼቲቭ ላለፉት ሶስት አመታት ከ8 ቢሊየን በላይ የቡና ችግኝ በመተከሉ ነው። ከእነዚህ ውስጥም ግማሽ የሚሆነው ወደ ምረት እየገባ ነው።

ከወቅታዊ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የሎጅስቲክ ችግር በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አገሮች ይከሰታል። አሁንም ሊከሰት ይችላል፣ ባለፈው ዓመትም በዚሁ ጉዳይ ተመሳሳይ ችግር ገጥሞን ነበር። አሁን ላይ ግን ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው።

ወደ ውጪ አገር የሚላክ የቡና ምርት በከፍተኛ ሁኔታ ሲጨምር የኮንቴይነር እጥረት ይከሰታል። ችግሩ በያዝነው ወርም ገጥሟቸው እንደነበር እና ከጅቡቲ ባዶ ኮንቴይነር በማስመጣት ፈተናል።

በተጨማሪም ከቡና ምርት በተያዘው አመት 2.44 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። ኢትዮጵያ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ ዝቅተኛ የቡና ዋጋ ተመን ስሌለላት ማግኘትን የሚገባትን የውጭ ምንዛሬ እና ገቢ ሳታገኝ ቆይታለች
ሲሉ ተናግረዋል።

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የገበያ አማራጭ ግብይትና ኮንተራት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ትዛዙ ኢዶሳ በበኩላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በየሳምንቱ ዝቅተኛ የመሸጫ ዋጋ ተመን እያወጣ መሆኑን እና ተመኑንም ለቡና ላኪዎች ማህበር በየሳምንቱ መረጃው እንድኖራቸው ይሰጣል ብለዋል።

የዋጋ ተመን ማውጣት ያስፈለገው የሀገርን ገቢ ለማሳደግ እና ነጋዴዎች ተከራክረው ከፍ ባለ ዋጋ መሸጥ እንዲችሉ ነው፤ ነጋዴዎች የሽያጭ መረጃ እያገኘን አይደለም የሚሉት ተቀባይነት የለውም፣ ምክንያቱም በየጊዜው Update እያደረግን በማህበራቸው በኩል እያሳወቅን ነው። መረጃ አልደረሰኝም የሚል ካለ ቢሮ እየመጣ መውሰድ ይችላል ነው ያሉት።

በየሳምንቱ የሚወጣውን ዝቅተኛ የዋጋ ተመን ለሁሉም ሰው ይፋ የማይደረገው የውጪ አገር ነጋዴዎች ኢትዮጵያ የቡና መግዣ ዋጋ ተመን አውጥታለች በማለት በዝቅተኛው የዋጋ ተመን ነው የምንገዛው እንዳይሉ እና ማግኘት ያለብንን ገቢ ላለማጣት ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎬 Day 2 Recap – A Hub of Deals, Products & Possibilities.Big 5 Construct Ethiopia and East Africa Infrastructure & Water Expo delivered another impactful day of business, innovation, and opportunity at Millennium Hall, Addis Ababa. Exhibitors from 20+ countries showcased cutting-edge products, live demos, and tailored solutions. Tomorrow is the final day — don’t miss out. https://www.big5constructethiopia.com/Tikvah_Magazine
#ጥቆማ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አገልግሎቱ ኳታር መቀመጫውን ያደረገ ኩባንያ ኢትዮጵያዊያንን ለመቅጠር ፍላጎት እንዳለው መግለጹን አስታውቋል።

ኩባንያው በሞግዚትነት ( Nanny ) መስራት የሚፈልጉ 80 ሴት ኢትዮጵያዊያን አሰልጥኖ ማሰራት እንደሚፈልግ ነው የገለፀው።

በዚህም ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት፣ የአእምሮ እና የጤና እክል የሌለባት፣ ጥሩ ስነ-ምግባር ያላችሁ፣ ታማኝ እና ቀልጣፋ፣ በዐረቢኛ ቋንቋ መግባባት የምትችሉ እና እድሜያችሁ ከ 18 እስከ 40 ያላችሁ መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል።


ጥቅማ ጥቅም :-

➯ ለ6 ተከታታይ ወራት በኳታር የሞግዚት ማሰልጠኛ አካዳሚ /Qatar Nanny Training Academy/ ስልጠና፣
➯ በስልጠና ቆይታቸው፤ መጠለያ እና ምግብ፣ የጤና ኢንሹራንስ፣ አበል፣ እና የቲኬት ወጪ ሙሉ በሙሉ በማሰልጠኛ ተቋሙ ይሸፈናል፣
➯ ከስልጠና በኋላ በማሰልጠኛ ተቋሙ በሚደረግ የቅጥር ምደባ ወደ ስራ የሚገቡ ይሆናል።
➯ በስራ ላይ ሆነው ሙሉ የጤና ኢንሹራንስ ቀጣሪው ድርጅት የሚሸፍን ይሆናል።   

ለማመልከት ይህን ሊንክ መጠቀም ትችላላችሁ። (https://forms.gle/KrTZS97Snc9rCeFo6)

ምዝገባ የሚያበቃበት ቀን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰባት ተከታታይ ቀናት ብቻ ነው።

ምንጭ: የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

@TikvahethMagazine
#ተመራቂና_ደራሲ_ፉኣድ_ረሻድ👏

" መጥላት የቻለ ልብ ፍቅርን/መዋደድን መለማመድ አያቅተውም " - በምረቃ ቀኑ ' ዘረኛው ልባችን ' የተሰኘ መፅሐፍ ያስመረቀው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ

በማተሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪግ ትምህርት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመረቀው፤ በተመሳሳይ በምረቃ ቀኑ " ዘረኛው ልባችን " የተሰኘ መፅሐፍ ያስመረቀውና በእለቱ መፅሐፉን ተዘዋውሮ ሲሸጥ የተስተዋለው ወጣት ሁዋድ ረሻድ የብዙኃኑን ቀልብ ስቧል።

ትምህርትና ድርሰቱን በአንዴ እንዴት እንዳስኬደው፣ ለድርሰቱ ምን እንዳነሳሳው በመጠየቅ ቲክቫህ ወጣቱን አነጋግሮታል።

ፉኣድ ረሻድ ፦

" አማርኛ ቋንቋ ሙሉ ለሙሉ ለመናገር የሚቸገር አንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የጤና እክል ገጥሞት ክሊኒክ ሄዶ ነበር። በወቅቱ ያገኛቸው የክሊኒኩ ሰዎች ደግሞ ከአማርኛ ውጪ ሌላ ቋንቋ ስለማይናገሩ ተማሪው የህመም ስሜቱን ለማስረዳት በተቸገረበት ቅጽበት መመልከቴ የድርሰቱ መነሻ ሆኖኛል።

ከዘር ፓለቲካ በመነሳት ተማሪዎች ከየተወለዱበት ክልል ስሌላኛው ክልል ስለሚሰሙት ነገር በአእምሯቸው የሚቀርጹት አመለካከት ጤነኛ ባለመሆኑ ይሄው ተማሪም ይህ አይነት እሳቤ ስላለው የክሊኒኩን ሰዎች ለደኀንነቱ በመስጋቱ የሚችለውን ቋንቋ እንኳ ደፍሮ ለመገር አልፈቀደም።

በወቅቱ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተግባብተን ታማሚውን ረዳውት።

ተማሪው ባጋጣሚ የዶርም ጓደኛዬ ሆነ፤ ከተግባባን በኋላ በጣም ልብ የሚነካ ነገር አጫወተኝ። ግቢ እንደገባ ዶርም ውስጥ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ የማይተኛ እንደነበርም ነገረኝ። የማይተኛው ሰዎች 'ሊገድሉኝ ቢሞክሩ እንኳ ገድዬ እሞታለሁ ' በሚል እሳቤ ነው።

'ከብሔሬ ውጪ ያሉ ሰዎችን በብሔራቸው ለይቼ ብቻ አሳድጀ ገርፌ አውቃለሁ' ብሎ እየጸጸተ አጫውቶኛል።

ይህ ሰው ይህን ያደረገው የተነገረውን መጥፎ ታሪክ ሙሉ ለሙሉ ስላመነበት ነው። ስለዚህ ታሪክ አእምሮን ሼፕ ያደርጋል፤ ሌሊቱን ሙሉ እስካለመተኛት ያደረሰው የተየገረውን ነገር በማመኑ ነው።

ከዚህ በመነሳት የሰው ልጅ መጥፎ ታሪክ በተነገረውና ወደ ውስጡ ባሰረጸው ቁጥር መጥፎ አስተሳሰብ እንደሚላበሰው ሁሉ ጥሩ ነገር ቢነገረው ጥላቻን ተጸይፎ እንዲኖር ማድረግ ይቻላል። በዚሁ አውድ ነድ ' ዘረኛው ልባችን ' በሚል ርዕስ መፅሐፍ ለማሳተም የበቃሁት። " ብሏል።

በመፅሐፉ ምን ሊያስተምረን እንደፈለገ የተጠየቀው ወጣቱ እንዲህ ሲል አብራርቷል።

" የሰው ልጅ ጊዜና ቦታ ሳይገድበው ማዳንም ሆነ መግደል፤ መውደድም ሆነ መጥላት ይችላል። መጥላት የቻለ ልብ ፍቅርን/መዋደድን መለማመድ አያቅተውም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ መውደድ በልቡ ዙፋን ማንገስ የሚፈልግ ሁሉ ዘረኛው ልባችን መፅሐፍን ያንብብ።

በብሔርተኝነት በመከፋፈል፣ አንዱን እንግዳ ተቀባይ፣ አንዱን ዘራፍ ባይ ሲደርግ ይስተዋላል። ለምሳሌ የድሬና የጎንደር ሰው ተጫዋች አድርገን እንወስዳልን በተለምዶ፤ ግን አንተ ነህ አካባቢውን የምትመስለው፤ ባሕር ዳር አንድ ቀን አድሬ ጅማ የምመለስ ከሆነ አንተን ካገኘሁ ባሕር ዳርን የምመስላት በአንተ ነው። ሰዎች ክልልን፣ ብሔርን እየገለጹ ያሉት ባገኙት ሰው ልክ ነው።

ለልብ የሚከብደው መጥላት ነው። ሰው መጥላት ከቻለማ መውደድ አያቅተውም። "

ደራሲው በመፅሐፉ፣ ዘረኝነት በሰዎች አመለካከት የሚመጣ በመሆኑ አመለካከታችን ከተቀየረ በብሔር ያለመሳቀቅ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ይቻላል የሚል ሙሉ ተስፋ አለው።

ደራሲውን ለማግኘት ይደውሉ 0924807351

@tikvahethmagazine
🛑ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከስቱድዮ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች

🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት

🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
💎 ባለ 1 መኝታ በ 504,767 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

🛍️🛒ሱቆች ከ 50 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው

ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097

#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#whatsapp
#4thhachaluhundessaaward

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ 5ኛው የሙት ዓመት መታሰቢያ እና 4ኛው ዓመት " የሃጫሉ አዋርድ " የሽልማት መርሃ ግብር ትላንት ምሽት በአዲስ አበባ እስካይ-ላይት ሆቴል ተካሂዷል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና በርካታ የጥበብ አፍቃሪያን ታድመዋል።

የ4ኛው አመት ሃጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ አሸናፊዎ፦

አንጋፍው አርቲስት አብዱላሂ ጂርማ የህይወት ዘመን ተሸላሚ ሆኗል።

ምርጥ የሙዚቃ ጠባቂ /music Care/- አርቲስት አሜ ጢቃ

ምርጥ ኬሮግራፈር -አርቲስት አለማየሁ ዳቢ
ምርጥ ሲኒማቶግራፈር- አርቲስት ሽመልስ ታደሰ

ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ - አርቲስት ዘመን እሼቱ
ምርጥ የሙዚቃ አቀናባሪ- አርቲስት ሚራ ትሩቼልቫም

ምርጥ አዲስ ዘፋኝ-አርቲስት አሳንቲ አስቹ

ምርጥ ሴት ዘፋኝ-አርቲስት ለምለም ሀ/ሚካኤል
ምርጥ ወንድ ዘፋኝ-አርቲስት አንዱዓለም ጎሳ

ምርጥ የግጥ ዜማ- አርቲስት ለሊሳ እድሪስ (ቢሊሌ)

ምርጥ የባህል ዜማ -አርቲስት አደም ሙሀመድ እና ሀሊማ አብዱራህማን (ሹቢቶ)

ምርጥ ዘመናዊ ዜማ - አርቲስት ጉቱ አበራ(ኢዮሌ)

ምርጥ አልበም- አንዱዓለም ጎሳ

ለአሸናፊዎች የዋንጫና ከ50ሺ እስከ 100ሺ ብር የንዘብ ሽልማት ተበርክቷል።

የቀድሞ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ደ/ር  ታደሳ ቀነኣ አመራር ላይ በነበሩ ጊዜ የሀጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት ዩኒቨርስቲው ውስጥ ላይ በማቆም ላደረጉት አስተዋጽኦ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የአርቲስት ሀጫሉ ባለቤት ወ/ሮ ፋንቱ ደምሰው እንደተናገረችው "…ሽልማቱ አርቲስቶችን ለማበረታታት ያለመ ነው። …የተረሱ አርቲስቶችም ይበረታቱበታል። የሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ሀጫሉ የጀመራቸውን ስራዎች እና ያለማችውን ስራዎች ከግብ ለማድረስ አላማ አድርጎ ይሰራል" ብላለች።

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"በሚቀጥሉት 40 ወራት ውስጥ አፍሪካ በማዳበሪያ እራሷን ትችላለች"- አሊኮ ዳንጎቴ

ናይጄሪያዊው የአፍሪካ ቁጥር አንድ ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ አፍሪካ በመጪዎቹ 40 ወራት ውስጥ በማዳበሪያ ምርት እራሷን ትችላለች አሉ።

ዳንጎቴ የማዳበሪያ ፋብሪካው ላይ የ2.5 ቢሊየን ዶላር ማስፋፊያ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን ይህም አፍሪካ ከውጪ የምታስገባውን ምርት በእጅጉ ይቀንሳል ተብሏል።

ቢሊየነሩ" አፍሪካ ከ40 ወራት በኋላ ከየትኛውም ቦታ ማዳበሪያ አታስገባም፤ 40 ወራት ብቻ ስጡኝ፥ ዳንጎቴ ከኳታር የበለጠ የዩራያ አምራች እንዲሆን እናደርገዋለን" ብለዋል።

አፍሪካ በአሁኑ ጊዜ ከ6 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በላይ በአመት ከሌላው አለም እያስገባች ሲሆን አሁን ያለው የዳንጎቴ ፋብሪካ በአመት 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የማምረት አቅም ገንብቷል።

የዳንጎቴ ፋብሪካ የድርጅቱን 37 በመቶ ምርት ለአሜሪካ ገበያ እያቀረበ መሆኑን ጠቅሶ ከማስፋፊያው በኋላ ምርቱን በእጥፍ በመጨመር የአፍሪካን ፍላጎት ያሟላል ተብሎ ይጠበቃል።

እንደ ግዙፉ የአፍሪካ ኤግዚም ባንክ ሪፖርት አፍሪካ በ2021 ከማዳበሪያ ሽያጭ 8.9 ቢሊየን ዶላር ገቢ ስታገኝ ትልቁን ድርሻ የሰሜን አፍሪካ ሃገራት ይይዛሉ ተብሏል።

ሞሮኮ እና ግብፅ 70 በመቶ የአፍሪካን የማዳበሪያ ሽያጭ ሲይዙ በድምሩ 6.23 ቢሊየን ዶላር አግኝተዋል።

ምንም እንኳን የተወሰኑ ሃገራት በማዳበሪያ እራሳቸውን የቻሉ ቢሆንም አብዛኞቹ አሁንም ከውጪ በሚገባ ምርት ላይ ጥገኛ ናቸው።

የዳንጎቴ የማዳበሪያ ፋብሪካ በሚቀጥሉት ሁለት አመታትም በቀን 7 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን ቢሊየነሩ ገልፀዋል።

በ2022 ስራውን የጀመረው የሌጎሱ የዳንጎቴ የማዳበሪያ ፋብሪካ በናይጄሪያ የምግብ እጥረትን ለመቀነስ በዝቅተኛ ዋጋ እየሸጠ ሲሆን የናይጄሪያን የ1.5 ሚሊየን ቶን አመታዊ የማዳበሪያ ፍጆታም ለመሸፈን እየሰራ ነው።

በአመት ከ400 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ የሚያስመጣው የማዳበሪያ ፋብሪካው የናይጄሪያን የውጪ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው።

የአፍሪካ የማዳበሪያ ዋጋ ከ15 ቢሊየን ዶላር የተሻገረ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2030 ወደ 20 ቢሊየን እንደሚያድግ ይገመታል።

በምግብ እጥረት እና በውጪ ምንዛሬ ለምትፈተነው አፍሪካ የዳንጎቴ ፋብሪካ ሁነኛ መፍትሄ እንደሚሆን ሲጠቆም ቢሊየነሩ ዳንጎቴ የአህጉሪቱ መሪዎች የአህጉሪቱን ሃብትና ኢንቨስትመንት ባማከለ መልኩ አፍሪካን ተቀዳሚ አድርገው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

ቢሊየነሩ አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት መስማማታቸው በቅርቡ ይፋ መደረጉም ይታወሳል።

Source: Reuters, Africa Fertilizer Watch

@TikvahethMagazine
🛑ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ  ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከስቱድዮ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች

🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት

🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
    💎 ባለ 1 መኝታ በ 504,767 ብር
    💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር  ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

🛍️🛒ሱቆች ከ 50 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር  የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው

ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097

#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#whatsapp
#ሱስ

"ባለፉት 3 አመታት ከ19 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የሱስ ተጠቂዎች ስልጠና ቢሰጥም ከእነዚህ መካከል 1 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ከሱስ የወጡት" - በዘርፉ ላይ የሚሰራ ተቋም

"የማህበራዊ ሚዲያ ሱስ የቤተሰብን ትስስር ወደ ሚበጥስበት ደረጃ ላይ ደርሷል" - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

"እረፍት የሥነ ልቦናና ምክር አገልግሎት ማዕከል" ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት በሆነበት የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ካሂዷል።

በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱም የማዕከሉ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ መጋቢ ቢኒያም አዴሎ ባለፉት 3 አመታት በ "አይሰለጥንብኝም" ፀረ-ሱስ ንቅናቄ ማህበር" የተሰሩ ስራዎችን አስመልክተው ሪፖርት አቅርበዋል።

ሪፖርቱ ምን ይላል ?

በሪፖርቱ በሶስት አመታት ውስጥ በሀገራችን 19 ሺህ ለሚሆኑ በተለያዩ ሱሶች ለተጠቁ ዜጎች የስነልቦና ማማከር አገልግሎት እና ከሱስ እንዲወጡ ስልጠና መስጠታቸውን ገልፀዋል።

ከእነዚህ መካከል 1 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ከነበሩበት የሱስ ህይወት ወጥተው የተሻለ ህይወት እንድኖሩ ማድረግ መቻሉን እና በዛሬው እለትም የንቅናቄው አንድ አካል በማድረግ ማዕከል መክፈት መቻላቸውን ተናግረዋል።

ከ19 ሺዎች ውስጥ 95 በመቶ የሚሆኑት ወጣቶች፣ 3 በመቶ እማወራና አባወራዎች፣ ከ1 በመቶ በታች የተሀድሶ ታካሚዎች እና 1 በመቶ ወላጆችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት ማግኘታቸው ተመላክቷል።

በአገራችን ካለው የዜጎች ቁጥር ውስጥ ወደ 50 በመቶ የሚጠጉ ዜጎች በተለያዩ የሱስ አይነቶች እየተጠቁ ነው ያሉ ሲሆን በቀጣይ ሶስት አመታት ውስጥ 30 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ከሱሰኝነት እንዲላቀቁ አቅደን እየሰራን ነው ብለዋል።

ማኅበሩ እስካሁን ባካሄደው ንቅናቄ ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያ ሱስ በዋናነት እየተጠቁ ነው ያሉ ሲሆን ይህም የተማሪዎችን ትኩረት ነስቷል፣ የእርስበርስ ግንኙነትን አበላሽቷል፣ ብዙ ሰዎችን ስሜታዊ እያደረገ ወደ ተለያዩ የሱስ አይነቶች እንደዲገቡ እያደረገ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

በአገራችን የሱሰኞችን ቁጥር ለመቀነስ የቤተሰብ፣ የሃይማኖት፣ የትምህርት እና የመንግስት ተቋማት እርብርብ እያደረጉ ቢሆንም ውጤቱ ግን አመርቂ አይደለም የተባለ ሲሆን ውጤት ለማምጣት የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል እርብርብ ያስፈልጋል ነው የተባለው።

ከሥነልቦና እስከ ፖሊሲ ልንጠቀምባቸው የሚገቡ መሳሪያዎች በተቀናጀ ሁኔታ አለመኖራቸው እና የግብአት አቅርቦት ማነስ የሱሰኞችን ቁጥር ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ላይ ተግዳሮት መሆኑን ተጠቅሷል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ምን አሉ ?

በዕለቱ የተገኙት ሚኒስትሯ ሱስን መከላከል የሚያስችል አዋጅ መውጣቱን አስታውሰው፥ በአዋጁ ላይ የፖሊሲ ክፍተት ያለው በመሆኑ ጠቅሰዋል።

አክለውም፥ ፖሊሲውን ከማስፈፀሚያ ስልቶች ጋር የተዋሃደ እንዲሆን የህግ ድንጋጌዎች እንዲወጡ የማድረግ ስራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የማህበራዊ ሚዲያ ሱስ የቤተሰብን ትስስር ወደ ሚበጥስበት ደረጃ ደርሷል ያሉ ሲሆን የሚዲያ አጠቃቀም እውቀት እና ክህሎት ላይ ማዕከሉ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"የእናቶች እና ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት የሞት ምጣኔ ላይ ከፍተኛ መቀነስ ቢታይም አሁንም በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው" ‎- የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት(EPHI)

‎የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ‎ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ የእናቶች እና ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት የሞት ምጣኔ ላይ ከፍተኛ መቀነስ ቢታይም አሁንም በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሆነ ገልጿል።

ይህንንም ኢንስቲትዩቱ በጥናት ማረጋገጡን የተናገሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ፥ በኢትዮጵያ የእናቶችና ህጻናት የሞት መንስኤዎች እና አጠቃላይ የበሽታ ሥርጭት ትክክለኛ ቁጥራዊ መረጃዎች አለመገኘታቸው እንቅፋት መሆኑን ነው የተናገሩት።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፥ ‎የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ውስጥ የሚገኘው የብሔራዊ መረጃ አስተዳደር ቅመራና እና ትንተና ማዕከል (NDMC)  ለሀገር አቀፍ ጤና አገልግሎት ግብዓት የሚሆኑ  ማስረጃዎችን በመመርመር ሲያቀርብ የቆየ ቢሆንም አብዛኛዎቹ የመረጃ ምንጮች ሙሉነትና ወጥነትና የጎደላቸው መሆናቸውን ነው ያነሱት።

የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር መርጋ ደረሳ በአገራችን ከ1ሺህ እናቶች ውስጥ 200 የሚሆኑት እናቶች በወሊድ ምክንያት እንደሚሞቱ የዓለም አቀፍ ጥናቶች ያሳያሉ ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አክለውም በክልሎች ላይ ያሉ የጤና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ተገቢውን መረጃ በአግባቡ ባለማስቀመጣቸው ቁጥሩን እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም ያሉ ሲሆን ነገር ግን የሞት ምጣኔው ይቀንስ እንጂ አሁንም ችግሩ አለ ሲሉ አስረድተዋል።

የማኅበረሰቡ አኗኗር፣ የጤና ህክምና ፍላጎት አለመኖር፣ የጤና ተቋማት አስፈላጊ የሆነ ግብአት አለመኖር፣ የእርግዝና ክትትል በበቂ ሁኔታ አለመኖር ለእናቶች ሞት በሚፈለገው ልክ አለመቀነስ እንደምክንያት ይጠቀሳል።

የህፃናቶችን ሞት ማቆም ያልተቻለው ህፃናቶች በእናታቸው ማህፀን ውስጥ እያሉ ተገቢውን ክትትል አለማግኘታቸው እና ከተወለዱ በኋላም ያለው የአመጋገብ ሥርአት ዘልማዳዊ መሆኑ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ጤና ቢሮ ሃላፊዎች ጋር የእናቶችን እና የህፃናትን የሞት ምጣኔ ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ይህ የመግባቢያ ስምምነት የናሙና ምዝገባ ሥርዓት SRS መዘርጋት ሲሆን ዓላማው በኢትዮጵያ የእናቶችና ሕጻናት ሞት እና የሞት መንስኤዎችን እንዲሁም አጠቃላይ የበሽታ ስርጭት መለየት እና ያሉትን የክትትል ሥርዓቶች ለማጠናከር  ያሰበ ነው።

በስምምነቱ መሰረት በጤና ነክ ዙሪየ ያሉትን ችግሮች ለመለየት በሃገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልልሎች በተመረጡ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ላይ ጥናት ለማካሄድ መታቀዱ ተጠቁሟል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@TikvahethMagazine
2025/07/02 00:14:45
Back to Top
HTML Embed Code: