tgoop.com/tmhrtegeeze/10264
Create:
Last Update:
Last Update:
ቅዱስ ጳዉሎስም “የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸዉን እየለወጡ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞ ሠራተኞች ናቸው። ይህም ድንቅ አይደለም ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለዉጣልና” ብሏል /2ቆሮ.11፥13-15/። ሐዋርያት ሁሉ በየመልእክቶቻቸው ከሐሰተኞች አስተማሪዎች እንድንጠበቅ ደጋግመው አሳስበዋል። ብዙ ሰው ግን በየዋሕነት ስለሚጓዝ የነዚህ ተኩላዎች ሰለባ ሆኗል።
ጊዜው ክፉ ነውና የሐሰተኞች ነቢያት መረብ ጠልፎ ወደ ሐሰተኞች ክርስቶሶች እንዳይወስደን በጥንቃቄ መጓዝ ይጠበቅብናል። ሐዋርያዉ ቅዱስ ይሁዳም በመልእክቱ ቁ3 “ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ” ሲል እንደመከረን በተቀደሰ እምነታችን እስከመጨረሻ ጸንተን እንጋደል።
በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች፦
-፩ኛ ተሰ ፬፥፲፫ እስከ ፍጻሜ
-፪ኛ ጴጥ ፫፥፯-፲፭
-የሐዋ ሥራ ፳፬፥፩-፳፪
ምስባኩም፦ መዝ ፵፱፥፫
"እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽዕ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ"
"እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይቃጠላል"
ወንጌሉም፦ ማቴ ፳፬፥፩-፴፮
https://www.tgoop.com/tmhrtegeeze
BY ✝️(ትምህርተ ግዕዝ)✝️
Share with your friend now:
tgoop.com/tmhrtegeeze/10264