❗ ታህሣሥ 3 በዓታ ለማርያም ❗ ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,🔴 👉 ታህሣሥ 3 በዚህች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት ነው ምክንያቱም እርሷ ለእግዚአብሔር የስዕለት ልጅ ነበረችና።🔷 👉 ታዲያ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት ነው ብለን ብቻ ማለፍ ሳይሆን እንዴት እንደገባች ማወቅ ያስፈልጋልና አጠር አድርገን እንመለከታለን። 🔴 👉 የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወላጅ እናት ቅድስት ሐና ትባላለች። እናታችን ቅድስት ሐናም አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግሥት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ ኢያቄም ጋር አጋቧት።🔴 👉 እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሐና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሂደው ሲጸልዩ ሲያዝኑ ዋሉ። ሀዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ፡- ኢያቄም፡- "አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ጸሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለዐይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ/ች ወንድ ወይም ሴት ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ። ሐናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ፤ ስማኝ ለዐይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማኅጸኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች።🔷 👉 እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት ዐይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች። ከሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ፣ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ (ውሃ) ቀድታ፣ መሶብ ወርቅ ሰፍታ፣ መጋረጃ ፈትላ፣ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ። ዘካርያስም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው።🔷 👉 ከዚያም በኋላ ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም ዕለቱኑ ራዕይ ዐይተው ነገር አግኝተው አደሩ። ራዕዩም ኢያቄም “ርኢኩ በህልምየ እንዘ ይትረኀው ሰባቱ ሰማያት - ፯ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” አላት ፤ ወፍ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ነጭነቱ ንጽሐ ባሕሪው ነው፤ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ ዐየሁ ማለቱ፤ አምላክ የኢያቄምን ( የሰውን) ባሕርይ ባሕርይ እንዳደረገው ሲያጠይቅ ነው፤ ፯ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባሕርይው፣ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩ መንግሥቱ ናቸው።🔴 👉 ሐናም እኔም አየሁ አለችው፤ ምን አየሽ ቢላት፤ “ዖፍ ጸዓዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርዕስየ ወቦአት ውስተ ዕዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርስየ - ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅጸኔ ስትተኛ አየሁ” አለችው። ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት። ነጭ መሆንዋ ንጽህናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ድንግልናዋ ነው። ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማሕጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መጽነሷን ነው። ይህንኑም ራዕይ ያዩት ሐምሌ ፴ (ሠላሳ) ዕለት ነው። 🔷 👉 እነሱም እንዲህ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሔዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ ፯ ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ። በነሐሴ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁና ዛሬ በሩካቤ ሥጋ ተገናኙ ብሏችኋል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሐና ነገራት። በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ነሐሴ ፯(7) ቀን ተፀነሰች።🔴 👉 እመቤታችን ከተፀነሰች በኋላ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው። ከቅናትም የተነሳ ሊገድሏቸው ይፈልጉ ነበርና በመልአኩ ትዕዛዝ ሸሽተው በሊባኖስ ተራራ ላይ እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ፱(9) ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት ፩(1) ተወለደች። 🔴 👉 የእመቤታችን እድሜ ሦስት ዓመት ሲሞላው ጠቢቡ ሰሎሞን “ሰነፎች ደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልኽ ጊዜትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ የተሳልኸውን ፈጽመው ተስለህ የማትፈጽም ብትኾን ባትሳል ይሻላል” መክ 5፡4-5 ብሎ የተናገረውን በማሰብ ባሏ ኢያቄምን ይኽቺ ብላቴና የብጽአት ገንዘብ እንደኾነች ታውቃለኽ ወስደን ለቤተ እግዚአብሔር እንስጣት አለችው፡፡ 🔷 👉 እርሱም ፍቅርሽ ይለቅልሽ ብዬ ነው እንጂ እኔማፈቃዴ ነው አለ፤ ኢያቄም ይኽነን ማለቱ ሐና እመቤታችንን በመካንነት ኑራ ያገኘቻት አንድያ ልጇ ናትና ከፍቅሯ ጽናት የተነሣ ተለይታት አታውቅም ነበርና ነው፡፡ ከዚህም በኋላ ቅድስት ሐና ከቅዱስ ኢያቄም ጋር በመሆን ካህኑ ዘካርያስ ወደሚገኝበት ቤተመቅደስ ልጃቸውን ወሰዷት፡፡ ኢያቄምና ሐና እግዚአብሔርን በማመስገን ካህኑ ዘካርያስን ‹‹ይህቺ ብላቴና ስዕለት ተስለን አምላካችን በቸርነቱ የሰጠን ናትና ተቀበለን›› አሉት፡፡ እርሱም ቢያያት እንደ ፀሓይ የምታበራ እንደመብረቅ ግርማዋ የሚያስፈራ የምታበራ ዕንቈ ባሕርይ መስላታየችው፡፡🔴 👉 ወደ ቤተመቅደስ በወሰዷት ወቅትም እርሱም በአድናቆት ይህቺን የመሰለች ፍጥረት ምን እናደርጋታለን፣ ምን እናበላታለን፣ ምንስ እናጠጣታለን፣ ምን እናነጥፍላታለን፣ ምን እንጋርድላታለን ብሎ ሕዝቡን ሰብስቦ ሲጨነቁ ሳለ ለእስራኤል ደመና ጋርዶ መናን አውርዶ የመገበ፤ ለኤልያስም በመልአኩ እጅ በመሶበ ወርቅ ኅብሥት የመገበ፤ ለዕዝራ ሱቱኤልም በመልአኩ በቅዱስ ዑራኤል እጅ መልኩ እሳት የሚመስል ጽዋዐ ልቡና ያጠጣው ልዑል እግዚአብሔር ለእናትነት ወደ መረጣት ወደ እናቱ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤልን ላከላት (ዘፀ 16፡ 31፤ 1ኛነገ 19፡6፤ ዕዝ. ሱቱ. 13፥38-41)::🔷 👉 በዚያን ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ወረደ፤ ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ሊቀበል ቢነሣ ወደ ላይ ሰቀቀበት፤ ያን ጊዜ ጥበበ እግዚአብሔር አይመረመርምና ለዚህች ብላቴና የመጣ ሀብት ይኾናል እስኪ እልፍ አድርጋችኊ አኑሯት አለ፤ እልፍ አድርገው ቢያኖሯት እመቤታችን እናቷን ስትከተል መልአኩ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንዱን ክንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያህል ከፍ ብሎ ኅብስቱን መግቧት ጽዋውን አጠጥቷት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡❗ የእናታችን የቅድስት በዓታ ለማርያም ረድኤት በረከቷ ይደርብን❗ ❗ ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ❗ ።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።። ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።። ።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
tgoop.com/tmhrtegeeze/11725
Create:
2024-12-11 Last Update: 2025-01-07 09:26:42

BY ✝️(ትምህርተ ግዕዝ)✝️
Share with your friend now:
tgoop.com/tmhrtegeeze/11725
Telegram News
So far, more than a dozen different members have contributed to the group, posting voice notes of themselves screaming, yelling, groaning, and wailing in various pitches and rhythms. As of Thursday, the SUCK Channel had 34,146 subscribers, with only one message dated August 28, 2020. It was an announcement stating that police had removed all posts on the channel because its content “contravenes the laws of Hong Kong.” On Tuesday, some local media outlets included Sing Tao Daily cited sources as saying the Hong Kong government was considering restricting access to Telegram. Privacy Commissioner for Personal Data Ada Chung told to the Legislative Council on Monday that government officials, police and lawmakers remain the targets of “doxxing” despite a privacy law amendment last year that criminalised the malicious disclosure of personal information. Hashtags SUCK Channel Telegram
from us