‘ኦሪት ማለት ዋዜማ ማለት ናት፤ ዋዜማ ፍጹም በዓል ማለት አይደለችም፡፡ የእስራኤል ትልቁ ችግራቸው የኦሪቱን የዋዜማ ድግስ ከበቂ በላይ በልተው ሆዳቸው ስለሞላ ታላቁ የሐዲስ ኪዳን በዓል አምልጧቸዋል፡፡ ዛሬም ኦሪት ላይ ተቸክረው የቀሩ፣ በጽድቄ፣ በገድሌ በትሩፋቴ እድናለሁ ብለው እንደኩራት የሚናገሩ፣ የእግዚአብሔርን ልጅ ደም የዘነጉና የረሱ ብዙዎች አሉ፡፡ ይኸንን ታላቁን የሰባ ግብዣ ከዚህ መመገብ ያቃታቸው፡፡’
እዚህ ላይ ዋዜማን በኦሪት፣ በዓልን ደግሞ በወንጌል መስለው ከተናገሩ በኋላ ከላይ እንዳልኩት ወደ ሐሜት ነው የገቡት፡፡ በመሠረቱ የአይሁድ ችግራቸው ሊቀ ጳጳሱ እንዳሉት ዋዜማውን ‘ከሚገባው በላይ በልተው በመጥገባቸው’ አይደለም፣ ዋዜማውማ የሚያጠግብ ቢሆን ምን ችግር ነበረው? ጉዳዩ ዋዜማው ያጠግብ ነበረ ወይ ነው? ያ ማለት ኦሪት ሰዎችን ማዳን ወይም መቤዥች ችላ ነበረ ወይ? የኦሪት ድግሱስ አንዴ ተበልቶ ለዘላለም የማያስርብ ነበረ ወይ? ኦሪት ካጠገበችማ የወንጌል መምጣት ለከንቱ ሆነ፡፡ ባይሆን አይሁድ ዋዜማውን አክብረው ዋናውን በዓል ሳያከብሩ ቀሩ ወይም በዋዜማው በቃቸው ቢሉ ያማረ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ከደቂቃዎች በፊት ‘ኦሪት ጨካኝ ናት’ ያለ ሰው ኦሪትን ዋዜማ፣ ወንጌልን ደግሞ በዓል ሲያደርቸው፣ ዋዜማን ጨካኝ እያላት እንደሆነ እንዴት ይዘነጋል? ዋዜማ ዋናውን በዓል መቀበያ ናት፣ መቆያ፣ ኦሪትም ዋናዋን እናት ወንጌልን ለመቀበል የቆየንባት ሞግዚት ሕግ ናት ቢሉ ያማረ ነበር፡፡
ሌላው በዚህ ክፍል ያቀረቡት ዘለፋ ነው፡፡ ‘ዛሬም ኦሪት ላይ ተቸክረው የቀሩ፣ በጽድቄ፣ በገድሌ በትሩፋቴ እድናለሁ ብለው እንደኩራት የሚናገሩ፣ የእግዚአብሔርን ልጅ ደም የዘነጉና የረሱ ብዙዎች አሉ፡፡’
ይኸ ተሐዲሶና ፕሮቴስታንት ኦርቶዶክስን በተመለከተ የሚናገሩት እንቶፈንቶ የሆነ ሐሜት ነው፡፡ ይኸ ጽንፍ የያዘ ምልከታ እኛን አይመለከተንም፡፡ ሊቀ ጳጳሱን ከውጭ ወደ ውስጥ የጮኩት ያስባለን ይኸን መሰሉ ነው፡፡ አባታችን የአይሁድን ክፋትን ደግነት ባነጻጽሩበት ክፍል ላይም ሌላ ስሕተት ሠርተዋል፣ እንዲህ ይላሉ፣
‘እኔ መቼም የአይሁድ ከክፋታቸው ደግነታቸው በጣም ይከፋል፣ ከክፋት የከፋ ደግነት! ምን አሉ? ውኃ ጠማኝ ባለ ጊዜ ጉሮሮን የሚሰነጥቅ መራራ ሐሞት አቀረቡለት፡፡ እርሱን በመስቀል ላይ እየሰቀሉ፣ ይኸንን የመሰለ፣ ሥረ ወጥ የሆነ ልብስ መቀደድ የለበትም፡፡ ይልቁንም ለደረሰው ይድረሰው ብለው በልብሱ ላይ እጣ ተጣጣሉ፣ ያ ማለት ዐይንን አጥፍቶ ለግንባር እንደመጨነቅ፣ እግር ቆርጦ ለጫማ እንደማሰብ ማለት ነው፡፡ እነሱ ፍርፋሪ፣ ጨርቅ ላይ ነው የሚጣሉት፣ እኛ የጨርቅ ጉዳይ ሊያነጋግረን አይችልም፣ እኛ ጨርቅ ላይ አይደለንም፣ ዋናው ላይ ነው፣ መድኃኒቱ ላይ ነው፣ ፀሐይ ላይ ነው ያለነው፣ እኛ በጨረቃና በከዋክብት አንጨቃጨቅም፣ ዋናው ጸሐይ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነሆ በቀራንዮ የተደገሰው ታላቁ ግብዣ፣ ሥጋየን ብሉ ደሜንም ጠጡ ብሉ ብሎ አሳልፎ የሰጠን በእውነት፡፡’
ይኸ ንግግራቸው በተጣርሶ የተሞላ ብቻ ሳይሆን ከቅዱሳት መጻሕፍት ከሊቃውንቱ ብሎም ከፈጣሪ ጋር የሚያጣላቸው ነው፡፡ ሲጀምር አይሁድ ‘ተጠማሁ’ ሲላቸው ሆምጣጣ ማምጣታቸው ክፋታቸው እንጂ ደግነታቸው አይደለምና አባታችን በንጽጽሩ ለከንቱ ደከሙ፡፡ ሲቀጥል ልብሱን ሲካፈሉ አሁንም የክፋታቸውን ጥግ የሚያሳይ እንጂ እንዳልኩት ‘ዐይንን አጥፍቶ ለግንባር እንደመጨነቅ’ እንዳሉት ያለ ቅንጣት የመጨነቅ መንፈስ የለውም፡፡ ለአባታችን ችግር የሆነባቸው ንግግሩ የሳቸው ሳይሆን፣ የተሐዲሶ የፕሮቴስታንት እና ከውጭ ወደ ውስጥ የተጮኸ መሆኑ ነው፡፡
‘እኛ ጨርቅ ላይ አይደለንም’ ምን ማለት ነው? የክርስቶስ ጨርቁ ዋጋ የለውምና አይሁድ በመከፋፈል ደከሙ እያሉ ነው? አባታችን በርካቶች የቅዱሳንን ጥላቸውን፣ ጨርቃቸውን እየነኩ የሚፈወሱ መኖራቸውን አላነበቡም ይሆን? ወይስ ማጣጣል የፈለጉት ምንድነው? ‘ፀሐይ ላይ ነው ያለነው፣ እኛ በጨረቃና በከዋክብት አንጨቃጨቅም’ ማለትስ ምንድነው?
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታቱ ‘ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ፣ ዘአኰነኖ መዓልተ ለፀሐይ ከመ ያብርህ ለነ ውስተ ጠፈረ ሰማይ’ ካለ በኋላ ‘ፀሐይ ይበቃል’ ብሎ አልተወውም፡፡ ይልቁንም ‘ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ዘአኰነኖሙ ለወርኅ ወለከዋክብት ከመ ይሰልጡ ግብሮሙ በሌሊት’ በማለት ያመሰገነው፣ ያደነቀው፡፡ አስተውሉ ሊቁ በጥንቃቄ ነው ግብሮም በማለት ሥራቸው በሌሊት ይፈጽሙ ዘንድ አሠለጠናቸው ያለው፡፡ ‘ብርሃናቸውን ያበሩልን ዘንድ’ አላለም ሊቁ፣ የብርሃናቸው ምንጭ ፀሐይ መሆኑን ያውቃልና ሚና አላቀያየረም ወይም አልተምታታበትም፡፡ የጨረቃና የከዋክብት ግብራቸው ከፀሐይ የተቀበሉትን በሌሊት መግለጥ ነው፡፡ ፀሐይ የክርስቶስ፣ ጨረቃና ከዋክብት ደግሞ የቅዱሳኑ ምሳሌ የሆኑት በዚህ ንጽጽር ነበር፡፡ ጨረቃና ከዋክብት ከምንጩ ፀሐይ የተቀበሉትን ብርሃን በሌሊት ጨለማ እንደሚገልጡ፣ ቅዱሳንም ከፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ የተቀበሉትን ክብርና ጸጋ በሌሊት በሚመሰል ጨለማ ዐለምን ለማብራት ነው የሚተጉት (ከመ ይሰልጡ ግብሮሙ በሌሊት)፡፡ ‘ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ’ ያላቸው ደግሞ ራሱ ባለቤቱ ነው፡፡ ‘እኔ የዐለም ብርሃን ነኝ’ ካለ በኋላ ‘’እኔ ዐለምን ስላበራሁ እናንተ ምንም አታድርጉ’ አላለም፡፡ ይልቁንም ‘ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ። መልካሙን ሥራችሁን ዐይተው አምላካችሁን ያመሰኙ ዘንድ’ እያለ አባታቸው ቅዱስ እንደሆነ እነሱንም ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ አዘዛቸው እንጂ፡፡ ለዚያ ነው ይኸ የተቆነጸለ ትችትዎት ከመላዋ ወንጌል ጋር ያጋጫዎታል የምንለው፡፡ ለዚያ ነው ጩኸቱ ከንቱ የሆነ የተሐዲሶና የፕሮቴስታንት እንቶፈንቶ ነው ያስባለን፡፡
2ኛ ከ20ኛ ደቂቃ ጀምረው ‘ነይ ነይ እምየ ማርያም ቤዛ ነሽ አሉ ለዓለም፣ እመቤታችን ቤዛ አይደለችም፣ ቤዛ ልጇ ነው፤ አትደንግጡ፣ ቤዛ ልጇ ነው፡፡ ነይ ነይ ቤዛ ነሽ አሉ ለዐለም ተብሎ አይሰበክም፣ ቤዛ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ የእግዚአብሔር ልጅ ብቻ ነው፣’ የሚለው ንግግራቸው ነው፡፡ በዚህ ላይ ብዙዎች አስተያየት ስለሰጡበት በዚህ ጽሑፍ አልሄድበትም፡፡
3ኛ የክርስቶስን ፈራጅነትና አማላጅነት በተመለከተ ያለውን ፕርቶቴስታንታዊና ተሐዲሶዊ ትችት ከስብከታቸው ጋር የግድ የሚላቸው ባይሆንም ዐላማቸው ቤተ ክርስቲያንን መጎንተልን ከውጭ ሆኖ መተኮስ ነውን? በሚያስብል መልኩ ሮሜ 8፡34 አንሥተዋል፡፡ እንዲህ ይላሉ፣
‘አሁን በእኛ ቤትና በሌላ ቦታ እንደትልቅ መጨቃጨቂያ ተደርጎ በሮሜ 8፡34 ምን የሚያከራክር ነገር አለው? መጽሐፍ ቅዱሱ የሚያከራክር ነገር የለምኮ፣ አባ ስረይ ሎሙ እስመ በዘኢየአምሩ ይገብሩ፣ አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው፣ በሉቃ 23፡ 34 ላይ ይኸ የተናገረው የይቅርታና የምልጃ ቃል ለዘላለሙ ሲያድን ይኖራል፡፡ እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ይናገራል፣ አንድ ጊዜ የተናገረው ቃል ለዘላለሙ ይሠራል፡፡’

ይኸንንም ያነሡት ከውጭ ያሉት አካላት ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያነሡትን ለማጥራት ቢሆን ኖሮ ባላስነቀፋቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ‘‘አሁን በእኛ ቤትና በሌላ ቦታ እንደትልቅ መጨቃጨቂያ ተደርጎ’ የሚለው አባባል ራሳቸውን ሦስተኛ ወገን አድርገው ያቀረቡት፣ ኦርቶዶክስ ይኸንን የማታምንና የማታውቅ አስመስለው የሚከሱትን ክስ ያስተጋቡበት ሌላው ስሕተታቸው ነው፡፡ በመሠረቱ ለማብራሪያነት ያቀረቡት ጥሩ ቢሆንም በሌላው ቤት ‘አማላጅ ነው’ ሲሉ ምን እያሉ እንደሆነና ለምን እንደምቃወም ላይናገሩ ነገር ነው ጥቅሱን ለክስ ያነሡት፡፡
4ኛ ከ40ኛው ደቂቃ ጀምሮ ስለፍያታዊ ዘየማን ያንሡበትና በዚያው ላይ የትርጓሜ ባሕልና ትውፊትን አጥብቀው የተቃወሙበት ክፍል ነው፡፡ ቀደም ብሎ ከ37ኛ ደቂቃ ጀምሮ በሰሙነ ሕማማቱ የምናደርጋቸውን መከራውን ማሰብን፣ ስግደቱን፣ ምንብባቱን የሚቃወም የሚመስል ንግግር ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን እኔን በጣም ያስገረመኝና በሕስተት የተሞላው ንግግራቸው ያለው በሚከተለው ውስጥ ነው፣
‘እንኳን ለእኛ ይቅርና በቀኙ የተሰቀለው ፍያታዊ ዘየማንን ታስታውሱታላችሁ? ሉቃ 23፡39 ላይ ያለው፣ ተዘከረኒ እግዚኦ አመ ትመጽእ በመንግሥትከ በጣም ነው የምወደው ይኸን ሰው እኔ፡፡ እኛ በእንደዚህ ዐይነት መከራ ተይዘን ሳለን፣ በውኑ እግዚአብሔርን አትፈራውምን? እኔና አንተ የሚገባንን ቅጣት ተቀብለናል፣ ይኸ ግን ኃጢአት የለበትም፣ ማን ገለጸለት? ማነው ልቡን ያበራው? ማነው ዐይኑን ያበራው? ሌላ ነገር አይደለም፡፡ ሰማዋ፣ አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው የሚለውን ቃል ነው፡፡ ሌላውን ድርሰት ተረት ተውት፡፡’
ሊቀ ጳጳሱ ይኸንን የሚሉት ስለፍያታዊ ዘየማን በትርጓሜው ውስጥ ያለውን ማንነቱን በተመለከተ የተቀመጠውን ታሪክና ሐተታ ነው ‘ድርሰትና ተረት’ የሚሉት፡፡ ይኸ የጥራዝ ነጠቆቹ የተሐዲሶን የፕሮቴስታንት ክስ ነው፡፡ ሊቀ ጳጳሱ ንግግራቸውን ይጨርሱና ስለምንተቸው አሁን አባን እንስማቸው፣
‘ስለዚህ ምን አለ ተዘከረኒ እግዚኦ አመ ትመጽእ በመንግሥትከ፣ ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ፡፡ አሳስብልኝ አላለም፡፡’
‘አሳስብልኝ አላለም፡’ ሲሉ አማላጅነትን እየተቃወሙ መሆኑን ልብ አድርጉ፡፡ ድምጹ የተሐዲሶና የፕሮቴስታንት ነው ያልነው ይኸንንና መሰሉን ይዘን ነው፡፡ አሁንም እንስማቸውማ፣
‘በዚያ ያን የተዋረደውን፣ የተሰቀለውን፣ እርቃኑን እንደሱ የተሰቀለውን፣ የመንግሥት ባለቤት መሆኑን አውቆ መለኮታዊ እግዚአብሔር መሆኑን አውቆ፣ ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ፣ እስኪ እንደሱ እንሁን፣ እግዚአብሔር የዚህ ሰው እድል ይስጠን በእውነት፡፡ በጣም እድለኛ ሽፍታ ነው፡፡ እኛ መቀባባት ስለምንወድ፣ እንደዚህ፣ ተሸክሞ፣ ምርኩዙ ተሰብሮበት፣ እርሱ አይቶትም አያውቅም፣ እንዴ የት ያየዋል? እውነቱን ነው እንጂ መናገር! ጌታን የዛን እለት ብቻ ነው ያየው፤ ክርስቶስ እኮ ልዩነት ነው፣ ሁለቱ ሽፍቶች እንኳን ተለያዩ በክርስቶስ፣ ለመግደል የተባበሩ ነበር፣ ለመስረቅ አይለያዩም ነበር፤ ለመድፈር አንድ ነበርሩ፤ ችግር አልነበረባቸውም፣ ግን በክርስቶስ ተለያዩ፣ ለምን? ክርስቶስ እውነት ነዋ፡፡ እውነት አንዲት ቅንጣት፣ የማትከፈል፣ ጥያቄ የማይነሣባት፣ ኮሜንት የማይሰጥባት እውነት፣ ጌታው በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ፡፡ በዚህ ደረጃ የተዋረደውን ሰው፣ እውነተኛ አምላክ መሆኑን አውቆ ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለ፡፡ ቤተልሔም ሲወለድና ሰብአ ሰገል ወርቅ እጣን ከርቤ ስያቀርቡለት አልነበረም፣ ፍያታዊ ዘየማን፣ ወደ ግብጽም ሲሰደድ አላየም፣ አልነበረም ፍያታዊ ዘየማን፣ ቃና ዘገሊላ ላይም አልነበረም በቀኝ የተሰቀለው ሽፍታ፣ ደብረ ታቦር ላይ ብርሃነ መለኮቱን ሲገልጥ አልነበረም፡፡ ሲጠመቅና አባቱ የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው ሲል አላየም አልነበረም፣ ነገር ግን ቀን አገናኛቸው፡፡’
አሁን ይኸንን በስሕተት የተሞላ ንግግራቸው እንተቸው፣ ‘እኛ መቀባባት ስለምንወድ፣ እንደዚህ፣ ተሸክሞ፣ ምርኩዙ ተሰብሮበት፣ እርሱ አይቶትም አያውቅም፣ እንዴ የት ያየዋል? እውነቱን ነው እንጂ መናገር!’ የሚለው ንግግራቸው ፍጹም ሰፊ ችግር ያለበት ቁንጽልና ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ የተሐዲሶና የፕሮቴስታንት ጩኸት ነው፡፡ ‘እኛ መቀባባት ሰለምንወድ እንጂ’ ያሉት የፍያታዊ ዘየማን ታሪኩ በትርጓሜ መቀመጡንና መነገሩን ነው፡፡ ‘ፍያታዊ ዘየማን እመቤታችን ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ ላይ ካገኟት ሽፍቶች አንዱ ነበር’ የሚለውን ነው፡፡ አሁን ሊቀ ጳጳሱን ጥያቄ መጠየቅ ይቻላል፣ ለመሆኑ እርስዎ ይኸንን ከመጻሕፍት ስላላገኙት አልቀበሉም እንበል፣ እርስዎስ ‘እርሱ አይቶትም አያውቅም፣ እንዴ የት ያየዋል? እውነቱን ነው እንጂ መናገር! ጌታን የዛን እለት ብቻ ነው ያየው’ ያሉት በምን ማስረጃ ነው? የዛን ቀን ብቻ ያየው መሆኑን ከየት አገኙት? ሁለቱ ሽፍቶችስ ሲሰርቁ ይተባበሩ እንደነበር አብረው አልነበሩ፣ ከየት አገኙት? የግል ትርጉምና ፍልስፍናዎትን ለማስተላለፍ የተጻፈንና ታሪክን ማጣጣል ምን የሚሉት ነው? ተቃርኖ አይታይዎትም ወይ? ሽፍታው ስለክርስቶስ አይቶም ይሁን ሰምቶ የማያውቅ መሆኑን ከየት ያለተጻፈ ነውና ከየት አመጡት? የሚሉ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ያስገድደናል፡፡ አምስት ገበያ ሕዝብ የሚያክል ይከተለው የነበረን ጌታ፣ የአይሁድና የሮማውያን አለቆች ‘ሕዝቡን ሁሉ ወሰደብን’ ብለው የቀኑበትን እርሱን፣ ሲወለድ የጥበብን ሰዎች ኮከብ የመራቸው እርሱን፣ በመወለዱ የተቆጣ ሄሮድስ ‘እገድለዋለሁ’ ብሎ 2000 ሕጻናትን የፈጀበትንና በይሁዳ ምድር ዐዲስ ክስተት የሆነውን እርሱን፣ ለምድራውያኑ ነገሥታቱ የሥልጣናቸው ተጋሪ መስሎ ጭንቅ የሆነባቸው እርሱን ከሕዝብ ወገን የሆነው ፍያታዊ ዘየማንን እንዲያ በጨበጣና በቆረጣ ‘እርሱ አይቶትም አያውቅም፣ እንዴ የት ያየዋል? እውነቱን ነው እንጂ መናገር! ጌታን የዛን እለት ብቻ ነው ያየው’ ሲሉ አልዘገነነዎትም ወይ? ፍያታዊ ዘየማን እኮ ጎልማሳ፣ ሽፍትነቱን ሐዋርያት ሳይቀሩ የመሰከሩበት ታሪክ ያለው በምድር ላይ የኖረ ሰው ነበር እንጂ በእለተ ዐርብ ድንገት ከዐለት ሥር የበቀለ አይደለም፡፡ ያንን የሽፍታውን የቀደመ ታሪኩን ፈልጎ መዝግቦ ከሥሩ ለማስረዳት ሊቃውንቱ ያደረጉት ጥረት የሚያስደንቅ እንጂ እንዴት የሚያስተች መሰሎት? የዚህ ሁሉ ጣጣ ከውጭ ሆነው ወደ ቤተ ክርስቲያን ስለጮኹት፣ ጩኸቱን የአባት ሳይሆንና ለተሐዲሶና ፕሮቴስታንት በውክልና የተጮኸ በመሆኑ ነው፡፡
5ኛ በመጨረሻው ከ 47፡20 ጀምሮ ስለመስቀል ያላቸውን ተቃውሞ ያሳዩበትና በትርጉም ከመናፍቃኑ ጋር የተስማሙበት ጠባብ የሆነ ትርጉም ያለበትን ንግግር የተናገሩበት ነው፡፡ ይኸንን ብዙም አልሄድበትም፡፡ ልክ እንደቤዛ ትርጉም መስቀልንም መከራ ብቻ ተብሎ እንድተረጎምና ዕፀ መስቀል ትርጉም የሌለው አስመስለው የተናገሩበት ክፍል ነው፡፡

👍4
በጠቅላላው ስብከታቸው በርካታ ችግሮች ያሉብት፣ ከውጭ ወደ ውስጥ የተጮኸ፣ ውጫዊ አካልን ለማስደሰት ወይም የሆነ አኩይ ዐላማን ለማስፈጸም የሚመስል ነቀፋ፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ የተደረገ፣ አሉባልታ ወይም የስሕተት ትምህርት ነው፡፡ ከላይ ትችት ያቀረብንባቸውን ንግግሮች ሳይጨምሩ የሰበኩት ስብከት ቢሆን ኖር ስብከታቸው እንዴት ያማረ በሆነላቸው ነበር፡፡ ዳሩ ግን ዋና በሚመስለው ስብከታቸው አስታከው ሊያስተላልፉት የፈለጉት ሌላ ‘ዋና መልእክት’ ከላይ የተቸነው በመሆኑ ምንም እንኳን ውድ ጊዜችንን ቢሰዋብንም፣ ምንም እንኳን ትችቱም ሽቅብ ቢሆንብንም ይኸንን ማድረጋችን ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን ደኅንነት ሲባል የተጋባ ነበር፡፡ መሰል ክሶችን፣ ጩኸቶችንና ቁንጽላዎችን መታግስ ዋጋ አስከፍለውን ስለተማርን ወደፊትም ይኸንን በማድረጋችን እንቀጥላለን፡፡
ይኸው ነው አለ
©ዶ/ር አረጋ አባተ !!!
ይኸው ነው አለ
©ዶ/ር አረጋ አባተ !!!
❤1💯1
+ + ምን፣ በማንና እንዴት ይደረግ ? + + +
፨ ፨፨ ፨
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “እመቤታችን ቤዛዊተ ዓለም” አትባልም የሚል ግልጽ ተሐድሷዊ ኑፋቄ አስተምረዋል። እዚሁ ላይ ደግሞ በቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ትምህርት ላይ በሊቃውንት መካከል የአተረጓጉም ይትበሃል ልዩነት (Hermeneutical divisions) እንደሌለ እያወቁ፥ ይህን ኑፋቄያዊ ትምህርታቸውን የአተረጓጉም ይትበሃል ልዮነት አድርገው ለማቅረብ ሞክረዋል። ይህ በራሱ ተጠያቂነትን ያመጣል።
ኑፋቄያዊው ትምህርት የተሰጠው ደግሞ የብፁዕነታቸው የዘወትር የኑፋቄ ማሰተላለፊያ መድረክ ሆኖ በማገልገል ላይ በሚገኘው የ“ፍኖተ ጽድቅ” ማኅበር የሠራተኛ ጉባኤ ላይ ነው። ይኼው የኑፋቄ ትምህርት የተላለፈው በ“ፍኖተ ጽድቅ” ሚዲያ ነው። ይህን ተከትሎ በርካታ መምህራ ድንቅ ድንቅ ምላሽ ስጥተዋል። እንደ መምህር አረጋ አባተ (ዶክተር ) ያሉት ደግሞ ምላሾቹን ምሉዕ የሚያደርግ ዘለግል ያለ እና የተተነተነ ሂሳዊ ትችቶችን አቅረበዋል።
በዚህ ሂደት ሁሉ ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ የሚገባቸው የቤተ ክርስቲያናችን ሦስት ዋና ዋና መዋቅራት የሉም። የመጀመሪያው የቤተ ክርስቲያንን መሠረት እምነት፣ ሥርዓት አምልኮና ትውፊት ማስጠበቅ ያለበት በብፁዕ ወቅዱስ ርእስ መንበርነት የሚሰበሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ሁለተኛ በቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓት አምልኮና ትውፊት ላይ ኑፋቄ ሲሰጥ የተብራራ እና የተተነተነ ኦርቶዶክሳዊ ምላሽ መስጠት የሚጠበቅበት የሊቃውንት ጉባኤ፤ ሦስተኛ ማኅበራትን የመመዝገብ፣ ፈቃድ የመስጠት፣ የመቆጣጠርና በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥፋት ፈጽመው ሲገኙ ፈቃድ የመሰረዝ ሓላፊነት የተሰጠው የማኅበራት ምዝገባ፣ ማደራጂያና ክትትል መምሪያ ነው።
ኑፋቄያዊ ትምህርቱ የተሰጠውና የተላለፈው በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ባሉ ብፁዕ አባት እና ማኅበር ጋርዮሻዊ የታቀደ ቅንጅት እና የታሰበ ስምምነት መሆኑ ግንዛቤ ተወስዶበት፤ የተሰጡት ምላሾች እና የቀረቡት ሂሳዊ ትችይች እንደተጠበቁ ሆነው፥ ሦስቱ የቤተ ክርስቲያን መዋቅራት የሚከተሉትን ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው ፦
፨ ቋሚ ሲኖዶስ
***
“እመቤታችን ቤዛዌት ዓለም” አትባልም ብለው ግልጽ ተሐድሷዊ ኑፋቄ ያስተማሩት አባት በማዕረገ ጵጵስና ያሉ በመሆናቸውና ሕገ ቤተ ክርስቲያን በማዕረገ ጵጵስና ያለ አባት መጠየቅ ያለበት በቅዱስ ሲኖዶስ እንዳአለበት ሰለሚደነግግ፥ በዚሁ ሕግ መሠረት ሊቀ ጳጳሱን ጠርቶ መጠየቅና ተገቢውን ቀኖናዊ የእርምት እርምጃ መውሰድ አለበት።
፨ የሊቃውንት ጉባኤ
******
ጉባኤው በሕገ ቤተ ክርስቲያን በተሰጠው ሥልጣን እና ሐላፊነት መሠረት የሊቀ ጳጳሱን ኑፋቄ፤ ከኦርቶዳክሳዊ መሠረት እምነት፣ ሥርዓት አምልኮና ትውፊት ጋር ያለውን ግልጽ ተቃርኖ በማሳየት እና ቅዱሳት መጻሕፍትን እና የአበውን ትምህርት ማዕከል ያደረገ የተብራራ ምላሽ መስጠት አለበት። ለቅዱስ ሲኖዶስም የውሳኔ አሳብ ማቅረብ ይኖርበታል።
፨ የማኅበራት ምዝገባ፤ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ
************
ቅዱስ ሲኖዶስ በአወጣው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበራት አስተዳደር ደንብ ቁጥር 3/2015 ዓ.ም መሠረት፥ “ፍኖተ ጽድቅ” ጠቅላላ ማኅበርን ሕጋዊ ማኅበር አድርጎ የመዘገበ እና የዕውቅና የምስክር ወረቀት የሰጠው ይህ መምሪያ ነው። ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበርም በመተዳደሪያ ደንቡ በግልጽ እንደአሰፊረው፤ የቤተ ክርስቲያንን መሠረት እምነት፣ ሥርዓት አምልኮና ትውፊት ጠብቆ እና አስጠብቆ ለማገልገል ደንግጓል። ሆኖም ግን የቤተ ክርስቲያንን መሠረት እምነት፣ ሥርዓት አምልኮና ትውፊት ጠብቄ አሰጠብቃለው ያለውን ሕግ በመተላለፍ እና በመጣስ በራሱ መድረክ ላይ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ የኑፋቄ ትምህርት እንዲሰጥ አድርጓል። ይባስ ብሎም በዚህ የኑፋቄ ትምህርት ከጉባኤው ውጭ ያሉ ምእመናንን ለመበከል በሚመስል ዕቅድ በሚዲያው አሰተላልፏል። የተቀሰቀሰውን ቁጣም ተመልክቶም እሰከ አሁን ከሚዲያው አላወረደም። እናም መምረያው የማኅበሩን የታሰበበት ኑፋቄን የማዛመት ድርጊትና ኦርቶዶክሳዊ መሠረት እምነት፣ ሥርዓት አምልኮና ትውፊት ጠብቄ አስጠብቃለ ብሎ የደነገገውን ሕግ ተላልፎ መገኘቱን ከግምት ውስጥ በማስገባት በማኅበሩ ላይ አፋጣኝ የእርምት እርምጃ መውሰድ አለበት።
ከዚህም ባሻገር በአንድም ሆነ በሌላ “ፍኖተ ጽድቅ” ማኅበር ከዚህ በፊት ለፈጸማቸው ጥፋቶቹ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅና በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓት አምልኮና ትውፊት ያለውን ግልጽ እምነት እንዲገልጽ ጫና የፈጠሩ መምህራን እና በማኅበራዊ ሚዲያ የዕቅበተ እምነት ሥራዎችን የሚሠሩ ወንድሞች፤ ሰለፍኖተ ጽድቅ ሥራዎች የዘገቡ የቤተ ክርስቲያን ሚዲያዎች እና ለሚዲያው የዘገባ ፈቃድ የሰጠው የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ፤ በፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው አህጉረ ስብከት፣ መንፈሳዊ ኮሌጆች፣ ገዳማት፣ አድባራትና ማኅበራት፥ ይህን ድርጊት በይፋ ማውገዝና ማኅበሩ ወደ መስመር እንዲገባ ጫና ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
ሁሉም በየደረጃው በዚህ መልኩ ሓላፊነቱን ካልተወጣ፥ የእሰከ አሁኑ ከሚመጣው ታላቅ የኑፋቄ ማዕበል በፊት የመጣ ታናሽ የኑፋቄ ማዕበል ነው። ጳጳስ የሆነ እና ገንዘብ ያለው ሁሉ ኑፋቄ የመዝራት መብት ያለውም ያስመስላል። አርአያነቱም ጥሩ ስለማይሆን በጊዜ መታረም አለበት። ይቆየን።
© መምህር ታደሰ ወርቁ

❤2🍌1
ቅዱስ ሄሬኔዎስ(St. Irenaeus : C.130 - 202 AD) ስለ እመቤታችን የሔዋን ምትክነት(ቤዛነት) እንዲህ ብሏል፦ "Just as Eve was still a Virgin and became by her disobedience the cause of death of herself and whole Human race; so Mary too, espoused yet a Virgin, became by her obedience the cause of salivation of both herself and whole Human race. - ሔዋን ድንግል ሳለች ባለመታዘዟ ለራሷና ለሰው ልጆች ሁሉ የሞት ምክኒያት ስትሆን፥ ማርያም ግን ድንግል ሳለች በመታዘዟ ለራሷና ለሰው ልጆች ሁሉ የመዳን ምክኒያት ሆናለች።'' (Against the Heresies 3.22.24)።
በሊቁ እንደተብራራ በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው የሔዋንና የእባቡ ንግግር ወደ ሞትና ጥፋት እንዳደረሰን በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 1 የተጻፈልን የእመቤታችንና የመልአኩ ንግግር ወደ ሕይወት መርቶናል። ይልቁንም እመቤታችን "እንደ ቃልህ ይሁንልኝ" ብላ የመልአኩን ቃል መቀበሏ የሰው ልጆችን ሁሉ ወክላ ከእግዚአብሔር ዓለምን የማዳን ሐሳብ ጋር የተባበረችበት ቁልፍ የነገረ ድኅነት መሠረት ነው። በዚህም የሰው ልጆች "የባሕርያችን መመኪያ" እንላታለን።
ቅድስት ድንግልን "ቤዛዊተ ዓለም" ስንላት ለዓለም ሁሉ ድኅነት ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ፍጹም ቤዛ ከሆነን ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አስተካክለን ሳይሆን በመዳናችን ውስጥ "ዳግሚት ሔዋን" በመሆን ያደረገችውን ሱታፌ ለመግለጽ ነው።
© በአማን ወላዲተ አምላክ

👍6🙏1
+ ከእነሆኝ እስከ እነኋት +
ማርያምና ሙሴን ምን አገናኛቸው?
ሰሞኑን ‘ድንግል ማርያም ቤዛ ትባላለች ወይንስ አትባልም?’ በሚለው ተዋስኦ ላይ በበርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ‘ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው’ የሚለው ከሌሎች ጥቅሶች ጋር እንደ አንድ ማስረጃ ‘ሙሴ ቤዛ ከተባለ ድንግል ማርያም እንዴት አትባልም?’ ተብሎ ሲጠቀስ ሰንብቶአል፡፡ [ቤዛ የሚለው ቃል መጽሐፍ ቅዱሱ በተጻፈበት የግሪክ ቋንቋ ‘Iytroten /ransom-bringer, redeemer/’ በግእዙ መድኅን በእንግሊዝኛው deliverer ተብሎ ተተርጉሞአል] (ሐዋ. 7፡35) የነገሩ ተቃዋሚዎች ደግሞ ታዲያ ‘ምን ያገናኘዋል? የማይገናኝ ነገር አታገናኙ! ሙሴ ቤዛ ተባለ እንጂ ማርያም ቤዛ ተባለች ወይ?’ ብለው ሲከራከሩና ሲሳለቁ ነበር፡፡ ስለዚህ ጉዳዩን የበለጠ ማብራራት ግድ ይላል፡፡
በመጀመሪያ ‘ያ እንዲህ ከሆነማ ይሄ እንዴት አይሆንም’ የሚለው የሙግት አገባብ እኛ የፈጠርነው አገላለጽ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የአመክንዮ ቅርጽ ነው፡፡ በረበናተ አይሁድ ዘንድ አገባቡ qal va chomer (የቀላልና ከባድ ንጽጽር) የሚባል ሲሆን ሁለት ክስተቶችን ግራና ቀኝ አስቀምጦ አንዱን አቃላይ ሌላውን አክባጅ (fortiori) መንገድ የሚከተል የረበናት አመክንዮ (rabbinic logic) ነው፡፡
ይህንን የሙግት ስልት የናዝሬቱ ረቢ መድኃኔዓለም ክርስቶስም ከፈሪሳውያን ጋር ሲነጋገር በሚገባ ተጠቅሞበታል፡፡ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ በማለቱ በተቃወሙት ጊዜ ክርስቶስ እንዲህ ሲል ጠይቆአቸው ነበር፡፡
በመዝሙረ ዳዊት ፦ ‘እኔ ግን፦ አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ አልሁ’ ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (መዝ. 83፡6) ጌታችን ይህንን እውነታ ተጠቅሞ እንዲህ አላቸው፡፡
‘ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ እኔ፦ አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን? መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፦ ትሳደባለህ ትሉታችሁን?’ (ዮሐ. 10፡35-36)
ጌታ በዚህ ቦታ ላይ ሁለት ነገሮችን እንደ ቀላልና ከባድ አድርጎ አነጻጸረ፡፡ በመዝሙር ካህናትና ሌዋውያን ‘አማልክት ፣ የልዑል ልጆች ’ ተብለው ከተጠሩ አብ የቀደሰኝን ፣ ወደ ዓለም የላከኝ እኔን የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልኩ እንዴት ‘ትሳደባለህ ትሉኛላችሁ’ ብሎ ትንሹን የካህናት አማልክት መባል ከእርሱ የእግዚአብሔር ልጅ መባል ተገቢነት ማስረገጫ አደረገው፡፡
ጌታችን ይህንን የትርጓሜ አመክንዮ በሌላ ጊዜም ደጋግሞታል ፦
‘ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበት በጉድጓድ ቢወድቅበት፥ ይዞ የማያወጣው ሰው ማን ነው? እንግዲህ ሰው ከበግ ይልቅ እንደምን አይበልጥም!’ ሲል ትንሹን በግ ከትልቁ ሰው ጋር አነጽጽሮአል ፡፡ (ማቴ. 12፡11-12)
‘እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው?’ ብሎ ትንሹን የምድር ወላጆችን ሥጦታ ከታላቁ የሰማያዊ አባት ሥጦታ ጋር አነጻጽሮአል፡፡ (ሉቃ. 11፡13)
የኦሪት ምሁሩ ቅዱስ ጳውሎስም በዚሁ ስልት ‘የሙሴን ሕግ የናቀ ሰው ሁለት ወይም ሦስት ቢመሰክሩበት ያለ ርኅራኄ ይሞታል ፤ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?’ ብሎ ትንሹን ሕገ ሙሴን ከትልቁ ደመ ክርስቶስ ጋር አነጻጽሮ ሞግቶአል፡፡ (ዕብ. 10፡29)
ብሉይ ጠቅሶ ለሐዲስ ማስረጃ ማድረግ ፣ የሚያንሰውን ጠቅሶ ለሚበልጠው መከራከሪያ የማድረግ አመንክዮ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተገኘ logical method እንጂ ‘ምኑን ከምኑ’ የሚያሰኝ ነገር አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱ አነጋገር አዲስ የሚሆንበት ሰው ለመጽሐፍ ቅዱስ አዲስ የሆነ ብቻ ነው፡፡
ሙሴና ድንግል ማርያምን ምን አገናኛቸው? ለሚልም ሰው የሙሴ ትንሽነትና የማርያም ትልቅነት ‘ሙሴ ቤዛ ከተባለ እሷ ለምን አትባልም?’ ብሎ ለመሟገት ሲሆን በደንብ ይገናኛሉ፡፡ ሙሴና ማርያምን በአንድ ወገን ለመነጻጸር የሚያስችል ደግሞ ብዙ ነገር መጥቀስ ይቻላል፡፡
የእግዚአብሔር ቃል የተጻፈበትን ጽላት የታቀፈ ሙሴ ቤዛ ከተባለ የእግዚአብሔርን ቃል ራሱን የታቀፈች ድንግል እንደምን ቤዛ አትባልም? የፋሲካውን በግ አሳርዶ መቃኑና ጉበኑን የቀባው ሙሴ ቤዛ ከተባለ የፋሲካውን በግ የወለደች ድንግል እንደምን ቤዛ አትባልም?
እውነት ነው ሙሴ በእስራኤል መዳን ላይ ወሳኝ ሰው ነበርና ቤዛ መባል ይገባዋል፡፡ በሲና ተራራ እግዚአብሔር በመልአክ የተነገረውን ቃል ሰምቶ ወደ ፈርኦን ሔዶ የታገለ ፣ ብዙ የተሟገተ ፣ እስራኤልን መርቶ ከግብፅ ያወጣ ሙሴ ቤዛ ቢባል አያንስበትም፡፡ በመላኩ ብሥራት ‘እነሆኝ የጌታ ባሪያ’ ብላ ራስዋን አሳልፋ ለፈጣሪ የማዳን እቅድ የሠጠችው ድንግል ማርያም ከሙሴ በላይ ዋጋ አልከፈለችምን?
አዎ ሙሴ ለተጠማ ሕዝብ ድንጋይ በበትር መትትቶ ውኃ አፍልቆ አጠጥቶ ነበር፡፡ ‘ያ ዓለት ክርስቶስ ነበረ’ የተባለለት ልጅዋ በጦር ሲወጋና ሕይወት የሚሠጥ ደሙ ሲፈስስ ያየችው ድንግልስ ከሙሴ አትበልጥምን? ሙሴ ዓለቱን በበትር ሲመታ አልሳሳም ነበረ፡፡ ልጅዋ በበትር ሲመታ በነፍስዋ ሰይፍ ያለፈው ድንግል አትበልጥምን? ባሕር ከከፈለና ካሻገረው ሙሴ ይልቅ የድንግልናዋን ባሕር ሳይከፍል ዓለምን ያሻገረውን ጌታ የወለደችው ድንግል አትበልጥምን?
ሙሴ ራሱ ያወጣውን ሕገ ኦሪት እንኳን መጠበቅ አቅቶት ከከነአን ቀርቶአል፡፡ ኢትዮጵያዊው ቆስጠንጢኖስ ይህንን ሲያብራራ ‘ከማርያም በቀር ዐሠርቱ ቃላትን የፈጸመ ማንም የለም’ ‘ወባሕቱ አልቦ ዘፈጸመ ዐሠርተ ቃላተ ዘእንበለ ማርያም ድንግል’ ብሏል፡፡ (መጽሐፈ ብርሃን ዘጸሐፈ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ 85) ለሙሴ የተገባ ‘ቤዛ’ የሚል ቃል ለእርስዋ አይገባትም ሲሉን የማንሰማው ለዚህ ነው፡፡
ከመጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳንን ቀድዶ ጥሎ ፣ የክርስቶስን አካል ጥላ ቢስ አድርጎ ከሚረዳ ሰው በቀር የሙሴና የማርያም ንፅፅር ለሁሉ ግልፅ ነው፡፡ ቤዛ መባሉን ይዘን ከሙሴ ብቻ ጋር አነጻጸርናት እንጂ እርስዋ እንኳን በእኛ ዓይን ባሕር የከፈለች የወንድሙ የአሮን በትር ፣ በ‘ንሴብሖ’ ፈንታ ‘ታዓብዮ’ ያለች ማርያም ፣ የእግዚአብሔር ቃል የወረደባት የሲና ተራራ ፣ የቃሉ ሰሌዳ ጽላት ፣ የመብራት ማቆሚያው መቅረዝ ፣ የጽላቱ ማደሪያ ታቦት ፣ የዕጣኑ መሠዊያም ፣ ደብተራ ኦሪትም እርስዋ ናት፡፡ Typology ከማይገባቸው ሰዎች ጋር መነጋገር ሆነብን፡፡
ሙሴ ለእስራኤል ቤዛ የተባለው እግዚአብሔር እስራኤልን አልተቤዠም ለማለት አይደለም፡፡ የፈጣሪን ቦታ ለመተካት ወይም ለመገዳደርም አልነበረም፡፡ የእግዚአብሔር እስራኤልን የማዳን ሥራ ላይ ሙሴ በቀዳሚነት ስለታዘዘና ሕይወቱን ስለሠጠ ነው፡፡ ይግረማችሁና ‘ሕዝቡም በእግዚአብሔርም በባሪያውም በሙሴ አመኑ’ ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ዘጸ.

👍3
14፡31) ይህ ማለት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ነው ማለት አይደለም፡፡ በሙሴ ማመን በላከው ማመን ስለሆነ ነው፡፡ ድንግል ማርያም ቤዛ ስትባልም ‘በደሙ በተደረገ ቤዛነት’ ያዳነንን አምላክ ለመገዳደር ሳይሆን ‘የጌታ ባሪያው’ ብላ ራስዋን ሠጥታ ፣ ይዛው ተሰድዳ ፣ እስከ መስቀሉ ድረስ ተከትላው ነው፡፡ እርስዋ ‘እነሆኝ’ ሳትል የተጀመረ ድኅነት የለም ፤ ልጅዋም ‘እናትህ እነኋት’ ሳይልም የፈጸመው ድኅነት የለም፡፡ የሰው ልጅ የመዳን ታሪክ በእነሆኝ ተጀምሮ በእነኋት የተጠናቀቀ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ሙሴ ለእስራኤል ቤዛ ሲሆን የበጉ እናት ደግሞ በደሙ ለዳኑ ሁሉ ቤዛ ናት፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ልዳ ጊዮርጊስ
ሚያዝያ 2017 ዓ.ም.
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ልዳ ጊዮርጊስ
ሚያዝያ 2017 ዓ.ም.
❤5
ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶ የነበረው
የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው ታግዷል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚሰሩ ኦርቶዶክሳውያን የሚዲያ ተቋማት በአንድ ማዕከል እንዲያገለግሉ፣ የመረጃ ፍሰቱ ወጥነት ያለውና ተቋማዊ መሆን ይችል ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቶ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብረው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ ማከናወን የሚችሉበት ፈቃድ ከመምሪያው መሰጠቱ ይታወሳል።
ከእነዚህ የሚዲያ ተቋማት መካከልም የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን አንዱ ሆኖ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።
ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት "ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም።" በሚል ርእስ የተላለፈው ትምህርትን ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያችን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን እንገልጻለን።
ሚያዚያ ፲፭ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብዙኃን መገናኛ አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር የአየር ሰዓት አጋርቶ የነበር ቢሆንም፣ ነገር ግን እመቤታችን ቤዛ አይደለችም የሚል ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ውጭ የሆነ ትምህርት በፍኖተ ጽድቅ ሚዲያ የዩቲዮብ ገጽ ማስተላለፉን ተከትሎ የድርጅታችን የአስተዳደር ጉባኤ ሚያዝያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ ባካሄደው ጉባኤ፣ በቀጣይ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ለማኅበሩ ተሰጥቶ የነበረው የአየር ሰዓት በእግድ እንዲቋረጥ ውሳኔ አስተላልፏል ።
እንኳን ለዳግም ትንሳኤው በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ፤ ማለት ሲገባኝ .......። አንዳንድ ድርጅቶች እና አንዳንድ አስመሳይ ሰዎች ክህደትን እና የደም ዋጋን የሚያሳንስ እጅግ በጣም መራር ነገር በማር ለውሰው እንጋታችሁ ሲሉ ይህንን ለመጻፍ ተገደድኩ ፡፡
=========================================
+ አርእስት ፦ "" መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና ፤ አሁን ግን አየነው ወልዶ ከብዶ ገና ""
+ ዓላማ ፦ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ሁለንተና በመጨፍለቅ ፤ ቤተክርስቲያን ለትውልድ ፣ ለሀገር እንዲሁም ለዓለም ያበረከተችውን እጅግ ከፍተኛ በምንም ሊተመን የማይችል አስተዋጾ ጥላሸት የሚያለብስ .... አባቷን አታውቅ አያቷን ትናፍቃለች አይነት እጅግ አስነዋሪ ፤ ሥጋን ቁጠር ቢሉት ጣፊን እንደ ሙዳ አይነት እጅግ ዘኛኝ እና ትውልድ የሚቀጩ ድርጊቶችን ለሚያስተላልፉ ሚዲያዎች በተለይ ኢቲቪ እና ሌሎች ላይ የመፋረጃ ሰነድ እንዲሆን ፡፡
+ የሚመለከተው ፦ ሁሉም የዚች ሀገር ዜጋ
+ ማስረጃ ፦ ምንጩን በማጠቃለያው ላይ እንደ ጉድ ተዘርግፎ ያገኙታል

ክፍል አንድ ፦ " ተኩላው ማነው ......... ? " ፤ ምልክቶቹ ............

ተኩላው እጅግ በጣም ዘገምተኛ ነገር ግን ድምጹም ፣ ቁመናውም ፣ አለባበሱም ከመንጋው ጋር የሚመሳሰል እና አደገኛ ነው ፡፡ ይህ ተኩላ ሃይማኖት የለውም ነገር ግን ሃይማኖት ሲሰብክ እና ባለ ሥነ ምግባር ሊያደርግክ ይሞክራል ፡፡
ምሳሌ አንደ ፦
1። "በቫቲካን የሚገኘው የኢትዮጵያ አሻራ ምንድን ነው ? ETV | EBC | EBCDOTSTREAM " በሚል ዶክመንተሪ ከአራት ቀን በፊት ሰርቶ ኢትዮጲያውያን ወደ ቫቲካን አይናቸውን እንዲተክሉ ለማድረግ እና ልክ በለሱን ሳትበላው "ኦሪት ዘፍጥረት 3፥6 ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ " የተባልለውን መልክ ቀይረው የሞት ዶክመንት የጋቱን አይነት ነው ፡፡
++ የሚገርመው ፦ ቫቲካን በኢትዮጲያ ህዝብ ላይ በተለይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ያደርሰችው ለዘመናት ያላቋረጠ የግፍ ዓይነት እንደ ኢያን ካምፕቤል የዘገበልን ማን አለ ? ከአራቱ መጽሐፍቶቹ በተለይ "Holy War: The Untold Story of Catholic Italy's Crusade Against the Ethiopian Orthodox Church" የተባለው አንባቢ ቢችል ገዝቶ ቢያነበው ግድ ይላል ፡፡ እንኳን ወደ ቫቲካን ልናይና አሻራ ልንሻ የአባቶቻችን ደም በእምነት ፣ በመንፈስ ፣ በሥጋ እሾክ ሆኖ ይወጋናል ፡፡
ጥላቻ መስሎክ እንዳትታለል ...... የብራና መጽሐፍቶችክ ፣ ሰነዶችክ ምናልባት ለዚህ ትውልድ ትልልቅ መፍትሄ የሚሆኑ የጥበብ ቀመሮችህ ቫቲካን ዘግተው ቆልፈው እንኳን አንተ ባለቤቱን ሌላንም አያስነኩም ፤ ቀለበቱን ስመክ እንኳን ካቶሊክ ብትሆን ሲያምርክ ይቀራል አታገኘውም ፡፡ ድንቄም አሻራ !!!
++ አባዜው ፦ ኢትዮጵያ እያሉ ጠቅልለው ይናገሩታል እንጂ ካቶሊኮቹ ፤ ኢትዮጵያው የሆኑት መጽሐፍቱን እና ጥናታዊ አውደርእያቸውን እንኳን እውቅና አይሰጡም ፤ እውቅና የሚሰጡት መቼ ብቻ ነው ........፤ ካቶሊክ እንዳደረጉህ ሊነግሩህ እና ሊነግሩልክ ሲፈልጉ ነው ልክ እንደ አሻራው ፡፡ ባዶ አዳራሽ እና የምንፍቅና ትምህርታቸው ያታለላቸው ጥቂቶች ማስደሰቻ ፡፡ ለሌላው ዓለም ግን ኦርቶዶክሳዊነትህን ያደበዝዙበታል ትልቅ ፖለቲካ ነው ይሄ ከገባክ ፡፡
==========
ከምሳሌው የምንረዳው
1. የተኩላው = ካቶሊክ
2. ድምጹ = ታላቂቷ ኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያውያን
3. ቁመናው = ድንበር የተሻግረ ቅርስ አለክ የሚል ፌዝ
4. አለባበስ = ክርስትና
5. ዝምድናው = ከገዳይ ፣ ከሌባ ፣ ከመናፍቅ ፣ ከሰይጣን ደቀ መዝሙር ጋር አንሶላ መጋፈፍ
6. ሴራው ምንድነው = "ሴራው ግብጽ ከምታገሳበት ከዴር ሱልጣን ፣ ይሄ ይቀርብካል የሚል ትውከት " ፤ " ዲማ ጊዮርጊስን በድሮን አፍርሼ ፣ ቫቲካንን በድሮን ቀርጬ ላሳይክ አይነት ድድብና " ፤ " የዝቋላን ጫካ ከቃጠሎ ከማድን ፣ መከኮሳቱን ከገዳይ ከምጠብቅ ... ልሻገር ቫቲካን ባህር አቋርጬ ልቅረጽና ልላክ ዶክመንተሪ አይነት ጊልዶ የቀረው የሰዶም ዘፈን "
7. ጋብቻውን የሚያስፈጽሙት = ዶክመንተሪ የሚሰሩ ፣ መጽሐፍ የሚጽፉ ባንዳዎች ፣ የምንግስት አካላት ፣ የማያፍሩት ተኩላው ተቋማት !
=========================
ለአዛኝ ቅቤ አንጓቾች .........
1። ዴር ሱልጣን ይከበርልን ፤ የወሰዱትን ድርሻችንን ይመልሱልን !!!
2። ቫቲካን የቆለፈችውን ከፍታ ፤ መዛግብቶቻችን ይመለሱልን !!!
3። የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን እውቅና የነፈገ ምንም አይነት ፕሮግራም ለኢትዮጵያውያን መቅረብ የለበትም እንዳያቀርቢ ራሳቸውን ያግዱልን !!!
=========================
ክፍል ሁለት ይቀጥላል ....
©ሰናይ ጥበቡ

ሊቀጳጳስ በማኅበራዊ አገልግሎት ላይ
የጌዲዮ፣ቡርጅ እና አማሮ ዞኖች ሀገረስብከት ብፁዑ አቡነ ገሪማ ነድያን እና የጎዳና ተዳዳሪዎችን በመሰብሰብ በማጽዳት፣አልባስ በማልበስ እና ምገባ በማከናወን የማኅበራዊ አገልግሎት ፈጽመዋል።
ወደ ድሆች ዝቅ ብሎ የሚውል ክርስቶስን ጋር ይውላል። ለተጣሉት ሐዘኔታ ያሳዬ ልብ የደስታ መጨረሻ ይገባዋል።
እንዲህ ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት ወደ ታችኛው ማኅበረሰብ ወርደው ሲያገለግሎ መመልከት የሃይማኖት አባት ግዴታቸው ቢሆንም ብርቅ ከመሆኑ የተነሳ እንደነቅበታለን።
©Kune
እኛ እባቶቻችን እንዲህ ዝቅ ብለው በስጋ የወደቁትን የጎሰቆሉትን በነፍስ ተስፋ እንዲኖራቸው የሚያደርጉትን ማየት ነው።

👍7❤3