Telegram Web
አክፍሎት ከጤናም ከኑሮ ሁኔታም አንጻር ማክፈል ለሚችሉ አማኞች ነው የትንሣኤ ዕለት የሚቆርቡ ሁሉ የግድ ማክፈል አለባችሁ በማለት ሰዎችን ከሥርዓተ ቁርባን አናርቃቸው በተለይ በሰው ቤት ብዙ አድካሚ ሥራ የሚሠሩ በአረብ ሀገር ያሉ እህቶቻችን በዚህ ጉዳይ የግድ ማክፈል አለባችሁ በሚል የአንዳንዶች የግዴለሽነት ትምህርትን አክብረው ለመቁረብ እየሄዱ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሳይቀር እራሳቸውን እንደሚስቱ እንሰማለን
እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥም ብዙ ሰዎች የፋሲካ ሌሊት ደክመው ሰው ሲደግፋቸው ወዘተ እናያለን እነዚህ ሰዎች ከተቀበሉ በኋላም ከታመሙ ከቁርባኑን አላማ እንዲርቁ ሊያደርጋቸው ይችላል

አንድ ቆራቢ ሰው ከመቁቡ በፊት መጾም ያለበት ለ18 ሰዓት ነው እንደ ፋሲካ ያለ ቀን ሲሆን ግን ቢቻለው ያከፍላል ባይቻለው ግን የግድ ሐሙስ በልተህ ነው የምትቆርበው ተብሎ ስላላከፈልህ መቁረብ አትችልም አይባልም በዚህ የግዴለሽነት መመሪያ መሠረት ብዙ ሰዎች ከቁርባኑ ይርቃሉ በተለይ የጤና እክል ያለባቸውና አድካሚ ሥራ የሚበዛባቸው ሰዎች ደግሞ ወይ እራሳውን ከልክ በላይ ጎድተው ከአቅማቸው በላይ መጾም እራሳቸውን እስከመሳት በሚያደርስ መልኩ ቆይተው ይቆርባሉ አሊያም ከሥርዓተ ቁርባኑ ለመራቅ ይገደዳሉ።
አንዳንዶች መቁረብ እፈልግ ነበር ግን ማክፈል ይከብደኛል ብለው በውስጥ ይጠይቃሉ ስለዚህ በሰዎች ላይ ሸክም እያበዛን ከሥጋ ወደሙ እንዳናርቃቸው እናስተውል!
የምንችል ሁሉ የክርስቶስን መከራና ስቃይ እያሰብን አክፍለን እንቁረብ የማንችል ደግሞ ማክፈል ባንችል እንኳን ለ18 ሰዓታት ነገረ ሕማሙን እያሰብን ጾመን እንቁረብ።

👉 መጋቤ ሐዲስ ዘላለም ሐሳቤ
👍3
ሚያዝያ 10 በሊቢያ በአክራሪዎች ሰማዕት የሆኑ ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ

"የክርስቶስን አምላክነት የእናቱን አማላጅነት አትክድም?"

"የለም አልክደውም"

"አልክደውም ካልክ በሰይፍ ታርደህ ህይወትህን እንደምታጣ ታውቃለህ?"

"ህይወቴ ክርስቶስ ነው እናቱ ደግሞ እናቴና አማላጄ ናት የአለም ህይወቴን ባጣ ዘላለማዊ ህይወትን እርሱ ያድለኛል "

እያንዳንዱን ሰማዕታት አረመኔዎቹ አራጆች እንዲህ ያሏቸው ይመስለኛል እነርሱ ግን "እንሞታለን እንጂ አንክድም" አሉ ለተመረጡት ንዑዳን ክቡራን የአምላክ ወዳጆች ብቻ በተገባው የሰማዕትነት ህልፈት ሊያልፉ ተመርጠው ነበርና

ሰማዕትነት እድል ነው መመረጥ ነው ደግሞም ለቅድስና መታጨት ነው ይህን እድል ብዙኃን አበው የሚመኙት ነገር ግን የተመረጡ ቅዱሳን ብቻ የሚያገኙት ልዩ ሽልማት ነው

ቅዱሳን ሰማእታት ሆይ ደጉ አምላካችን የእናንተን የክብር ሞት ያድለን ዘንድ ቸሪቱ አማላጅቱ እናታችንም በእቅፏ ትቀበለን ዘንድ ለምኑልን በረከታችሁ በላያችን ይደር

አሜን

👉መሪጌታ ብርሃኑ
❤‍🔥6
✍️ ቀኖና ዘሐዋርያት ቀዳም ሥዑርን(የተሻረች ቅዳሜ) የዓለማት ፈጣሪ በከርሰ መቃብር የተቀበረበት ዕለት በመኾኗ ቀኑን ሙሉ የምትጾም መኾኑን ሲገልጹ፦ "ነገር ግን በእናንተ ዘንድ በዓመቱ አንድ ብቻ ቀዳም ሰንበት አለች። እርስዋም ጌታችን በመቃብር የኾነባት ዕለት ቀዳም ሥዑር ናት፤ ሰዎች ሊጾሙበት የሚገባው በዓል እንጂ በዓለ ፍስሐ አይደለችም።..."

''But there is one only Sabbath to be observed by you in the whole year, which is that of our Lord's burial, on which men ought to keep a fast, but not a festival. For inasmuch as the Creator was then under the earth, the sorrow for Him is more forcible than the joy for the creation; for the Creator is more honourable by nature and dignity than His own creatures."[𝐀𝐩𝐨𝐬𝐭𝐨𝐥𝐢𝐜 𝐂𝐨𝐧𝐬𝐭𝐢𝐭𝐮𝐭𝐢𝐨𝐧𝐬 (𝐁𝐨𝐨𝐤 𝐕𝐈𝐈), 𝐒𝐞𝐜𝐭𝐢𝐨𝐧 𝟐, 𝐗𝐗𝐈𝐈𝐈].
👍2
የኦርቶዶክስ በዓላት በመጡ ቁጥር የሚጠየቁ ጥያቄዎች ምን ያህል ከኦርቶዶክሳዊ ኅሊና እንደራቅን ማሳያዎች ይመስሉኛል። ይህንን ያህል ከኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት፣ ከቤተክርስቲያን ኅሊና፣ ከኦርቶዶክሳዊው አእምሮ በጣም ሩቅ ነን።እውነት ለመናገር በጣም ያሳዝናል።

መምህራኑን ስለበዓሉ ስንት ጠለቅ ያለ ነገረ መለኮታዊ ጉዳይ መጠየቅና መጠቀም ሲኖርብን በዓል በመጣ ቁጥር እርድ መቼ ነው፣አሳ በጾም ይበላል አይበላም፣ ገና ገሀድ አለው የለውም ወዘተ አይነት ጥያቄዎች በየዓመቱ መጥመድ በጣም ያልተገባና መስተካከል ያለበት ነገር ነው።

አጥንት ልንቆረጥም በምንችልበት እድሜ እና ሁኔታ ሁሌ ወተት ጋቱኝ ማለት ጤነኝነት አይደለም።

👉ስምዐ ጽድቅ ኤልያስ እንደጻፈው
የጌታን ጎን በጦር የወጋ፤ ዃላም ጎኑን ለወጋው ጌታ ሰማዕትነት የተቀበለ የሮማ ወታደር፤

ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ ይህም 9 ሰዓት ሲሆን ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ ለይቷል። ዃላም ከሮማ ወታደሮች አንዱ ‹‹ ቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው›› ከወታደሮቹ አንዱ የሆነው ለንጊኖስ የጌታችንን ጎን ቢወጋው ከጎኑ ትኩስ ደምና ውኃ ፈሷል፡፡

ለንጊኖስ ማለት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስብከት ዘመን የዺላጦስ ወታደር የነበረ ሰው ነው። ለንጊኖስ አንድ ዓይኑ የጠፋ ሰው ሲሆን ጌታችን በተሰቀለበት የጌታችንን ጎን ሲወጋው የደሙ አንዷ ፍንጣቂ ሔዳ የታወረች ዐይኑ ላይ ዐርፋ ዓይኑ በራለት፡፡ ከጌታችን ጎን የፈሰሰው ደም እንደ ''ለ'' ቅርጽ በመሆን በሁለት ወገን ደምና ውኃ ሆኖ ፈሰሰ፡፡ ከጌታችንም የፈሰሰውን ትኩስ ደም መላእክት በጽዋ ብርሃን ቀድተው በምድር ላይ ረጩት፤ ይህ መሠረት ሆኖ ዛሬ ቤተ ክርስቲያን የሚታነጸው እግዚአብሔር ባወቀ ደሙ የነጠበበት ቦታ ላይ ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ነው፤ ቅዱስ መጽሐፍ ‹‹እግዚአብሔር በደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን›› በማለት የቅድስት ቤተክርስቲያንን ክብር የሚመሰክረው፡፡ ዛሬም ምእመናን የልጅነት ጥምቀትን ስንጠመቅ ውኃውን ካህኑ ሲባርከው በዕለተ ዐርብ ከጌታችን ጎን ወደ ፈሰሰው ማየ ገቦነት (የጎን ውኃ) ይቀየራል፡፡

ከጌታችን ትንሳኤ በኋላ ለንጊኖስ ወደ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘንድ ሒዶ ስለ እውነት ስለ ሃይማኖትም ተማረ። ተጠምቆ ምድራዊ ወታደርነቱን ትቶ እየሰበከ ከኢየሩሳሌም ወደ ቀዸዶቅያ ወረደ። ለዘመናትም ጌታችን ክርስቶስን በሥርዓተ ወንጌል አገለገለ።
በመጨረሻም በጢባርዮስ ቄሣር ዘመን አይሁድ አሳደዱት አንገላቱት። የነርሱ ወገን ስለነበረም መከራ አጸኑበት። የጽድቅ አርበኛና የክርስቶስ ሐዋርያ ቅዱስ ለንጊኖስ ግን ጸና። በእምነቱ የጸናው ለንጊኖስ አይሁድ አንገቱን ሰይፈውት ለሰማዕትነት በቃ። ቅዱሱ በሕይወቱም በዕረፍቱም ተአምራትን ሠርቷል::

ጌታን በመስቀል ላይ ጎኑን በጦር የወጋው ሰው መጨረሻ ክርስቶስን ወንጌል ሰባኪ ብሎም ጎኑን ለወጋው ጌታ ሰማእትነትን እስከመቀበል ደረሰ። ቤተክርስቲያን ሊንጊኖስን ቅዱስ ብላ ሰይማዋለች። ሰማዕትነት የተቀበለበትን እለት በስንክሳሯ መስግባ ትዘክረዋል።

የጌታን ጎን የወጋ የኋለኛው ሰማዕት ቅዱስ ሊንጊኖስ።

👉 ማርያማዊት ሄኖክ
👍3
ክርስቶስ በእውነት ተነስቷል።
እንኳን ለበዓለ ትንሳኤው በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ። መልካም በዓል
7
ፊል ሙልራይን፤ የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች አሁን ቄስ

ለማንቸስተር ዩናይትድ፣ ኖርዊች ሲቲ፣ ካርዲፍ ሲቲ የተጫወተው ፊል ሙልራይን እግር ኳስን እርግፍ አድርጎ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ሆኗል።
👍2🙏2
አንድም በአላዋቂነትና ድንቁርና፣ አንድም ነገር አማረልኝ ብለው የማይገባ ማራቀቅ ውስጥ ሲገቡ ፣አንድም ትኩረት ለመሳብ ካላቸው የትኩረት ጥማት ፣ አንድም ሆነ ብለው ልባቸውን ከውጭ እግራቸውን ከቤተክርስቲያን አጸድ ያቆሙ በሁለት ቢላዋ የሚበሉ ሰዎች፣ አንድም ሰውን ለማስደሰት የሚናገሯቸው ንግግሮች በቤተክርስቲያን ዐውደ ምሕረት የሚነገሩ ግን ደግሞ በጣም አደገኛና አንዳንዴም ኑ*ፋ*ቄ ጭምር ናቸው።

የቅድስት ቤተክርስቲያን ትምህርት ያልሆኑ፣ ከአበው ወይም ከመጻሕፍት ያልተገኙ፣ ትውፊታዊ መሠረትም የሌላቸው "ትምህርቶች" በየዐውደ ምሕረቱ መነገር ከጀመሩ ከራርመዋል። ከሰሞኑ ከአባ ገብርኤል 'ትምህርት' በተጨማሪ እኔ የገጠመኝን እና አንድ ወንድም ገጥሞት ያጫወተኝን ሁለት ታሪኮች ላንሳ።

የመጀመሪያው እና ባለፈው በጸሎተ ሐሙስ አንድ የደብር አስተዳዳሪ የተናገሩት ነው ብሎ አንድ ወንድም የነገረኝ ነወ። በቅዳሴው ወቅት ምዕመናን ሥጋ ወደሙን እየተቀበሉ አስተዳዳሪው እያስተማሩ በመሐል እንዲህ አሉ አለኝ። "የዛሬው ሥጋ ወደም እስከዛሬ ከምንቀበለው ሁሉ የተለዬ ነው።" አሉ አለ። ይህ በጣም ስሕተት ያለበት ንግግር ነው።

ቤተክርስቲያን በየዕለቱ በቅዳሴው የምትሰዋው ቅዱስ ሥጋውና ደሙ ያኔ ጌታ ለሐዋርያት ካቀበላቸው የተለየ መስዋዕት አትሰዋም። ምናልባት ሊሉ የፈለጉት ሌላ ሊሆን ይችላል። የዕለቱን ታላቅነት ለማጉላትም ሊሆን ይችላል።ምንም ይሁን ግን ንግግሩ ስሕተት ነው።ወዳጄ እንደነገረኝ ይህንን ከተናገሩም በሗላ ምን ማለት እንደፈለጉ አላብራሩትም። ቤተክርስቲያን ግን እስከ ዓለም ፍጻሜ የምትሰዋው ያንኑ አንዱን የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው።ሕይወቷም እርሱ ነው።

ሁለተኛውና እኔ የገጠመኝ ደግሞ በአንድ ቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ ውስጥ አንድ መምህር እያስተማሩ ነው። የሚያስተምሩት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ይጠብቃት ዘንድ ስለተሰጣት ስለ አረጋዊው ዮሴፍ ነበር። እና እስካሁን ባልገባኝ ከእሳቸውም ፈጽሞ በማልጠብቀው አገላለጥ "ዮሴፍ የጌታ የእንጀራ አባቱ ነው" አሉ።ዳኅፀ ልሳን ነው እንዳልል ወዲያው አላስተባበሉም።እዚያ የነበረው ብዙ ሰው መሠረታዊ የሚባል የቤተክርስቲያን ትምህርት የተማረ ነበርና ሁሉም በንግግሩ ደነገጠ። ጎን ለጎን አጉረመረመ።በዚህ መሐል አንድ ደቀመዝሙር ተነስቶ በድፍረት "አሁን የተናገሩት ስሕተት ነው" አላቸው::ከዚያ በሗላ የሆነው እዚህ ላይ አስፈላጊ ስላልሆነ ይቆይ።ዋናው ነጥብ ግን መምህሩ የተናገሩት ፍጹም ስሕተት ነበር።

እናም

አንዳንድ መምህራን ሆይ የምትናገሩትን ጠንቅቁ። ቃል ለማራቀቅ፣ በመድረክ ሙቀት በመገፋፋት፣ወይም የሆኑ አካላትን ደስ ለማሰኘት፣ ከዝግጅት ማነስ ወይም በሌላ ምክንያት ኦርቶዶክሳዊ ላሕይና መሠረት የሌለው፣ ትውፊታዊ፣ መጽሐፋዊ ያልሆነ ወይም ከአበው ያልተገኘ ጉሥዐተ ልባችሁን በቤተክርስቲያን መድረክና ዐውደ ምሕረት አትናገሩ።

እኛም ምዕመናን ሆይ ሁሌም ከዐውደ ምሕረትና ከመድረክ የሚነገረው ሁሉ ጥርት ያለ የቤተክርስቲያን ትምህርት ላይሆን ይችላል። መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት እንማር። ቤተክርስቲያንን በሕይወትም በትምህርትም እንወቃት። ከዚያ ያፈነገጠ ነገር ስንሰማ እንጠይቅ።ቤተክርስቲያን የእኛም ናትና።

ጸልዩ በእንተ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት!

👉ዮሴፍ ፍስሐ እንደጻፈው
👍21
ብጹዕ አባታችን በገጻቸው እንደ አባ ጊዮርጊስ ባለ ምስጋና ቤዛዊተ ዓለም ማርያምን አመስግነዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ የ"አቡነ ገብርኤል"ን ምንፍቅና እንደሚመለከተው ተስፋ የሚሰጥ ነው።

ቡራኬዎ ትድረሰን።
ቤዛ አትባልም (ደግሞ ሌላ አጀንዳ)፦ አትረፍ እና አትትረፍ ያለው ሕዝብ አጀንዳው ብዙ ነው።

እርሷማ ቤዛችን ነች። ለቤዛነቷ ምንም ጥርጥር የለውም።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስንኳንስ ለእኛ ለሰው ልጆች ለቅዱሳን መላእክትም ቤዛቸው ናት እነርሱ አይተውት የማያውቁትን አምላክ በሥጋ ወልዳ ቤዥታቸዋለችና። ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም መባሏም በምክንያት እንጂ በልምድ እና የዳኅጸ ልሳን ጉዳይ አይደለም።

በዚህ ደረጃ ወርዶ ቤዛዊተ ኩሉ ዓለምን ቤዛችን አይደለችም ማለት ግን የጤንነት ነው? ደግሞ እኮ "አይዟችሁ አትደንግጡ" ይላሉ ደፍረው። እንዴት አንደንግጥ!!!!

👉ዲያቆን ዶ/ር የሺዋስ መኳንንት
👍31
...........   ቤዛ...........................

የቃሉ  ትርጓሜ    እና   የትርጓሜው ምሥጢራዊ ነገረ ድኀነታዊ    ይዘት    ሲተነተን      ?  ?

            የቃሉ    ትርጓሜ
ቤዛ ፦  ቤዘወ  አዳነ   ፤ ተቤዠ፤   ዋስ ጠበቃ  ኾነ፤ ተካ  ፤ለወጠ፤ አሳልፎ  ሰጠ እና  ይህንን   የመሳሰሉ ትርጓሜዎች    አሉት ። ስለዚህ   ከዚህ  ግስ ውስጥ  ቤዛ   የሚል  ጥሬ  ዘር   ይገኛል ።

☑️የቤዛ   ትርጓሜ   "      ዋጋ፤  ካሳ  ፤ ለውጥ፤ ጥላ፤ ምትክ ፤ ዐላፊ፤ ዋቢ፤ ዋስ፤ መድን፤ ተያዥ፤ ጫማ፤ጥላ፤ ጋሻ ተብሎ  በዚህ ኹሉ ይተረጎማል ። ቤዛ እነዚህን ኹሉ ያስተረጉማል።

☑️ ነገር  ግን  እነዚህ  ኹሉ  የቃሉ ትርጓሜዎች   ማዳን  ወይም ትድግና  ከሚለው ቃል የሚወጡ እና የሚርቁ   ፈጽመው የማይገናኙም  አይደሉም።    ቤዛ ማዳን ወይም መታደግ እና መድኀኒት የሚለው ትርጓሜው ቋሚ  ኹኖ ከላይ ያየናቸው  ትርጓሜዎች  ከአውዱ የወጡ ሳይሆኑ  ቤዘወ አዳነ ከሚለው ሥርወ ቃል  ባሕርያቸውን ሳይለውጡ  እርሱን መስለው ነገር ግን ልዩ ልዩ መጠሪያ ልዩ  ልዩ  መልክ  ልዩ  ልዩ  ውበት በመያዘ ቤዛን መስለው የተወለዱ  የተገኙ  የወጡ   ናቸው ።
ቤዛ ፦ ዋጋ" ቢባል በምድር በምናደርገው በጎ ምግባር ሰማያዊ ዋጋ እናገኛለን።    ይህ  ሰማያዊ  ዋጋ   ደግሞ   መንግሥተ ሰማያት  መግባት፤ በቀኝ  መቆም  ከሲኦል  መዳን እና የመሰሉት ናቸው ።ስለዚህ  በምድሩ ሥራችን ፈንታ  ዋጋችሁ  በሰማይ ነው ያለው ጌታ ዋጋችን በሰማይ ከከፈለን   ይሄ  መዳን   ነው  ።
☑️2ኛቤዛ  ካሳ ይባላል ፦   ይሄ  ቃልም  በዚህ  ዓለም  ለሚደርጉ ልዩ ልዩ  የካሳ  አይነቶች  የሚጠቀስ  ቢኾንም  ነገር ግን የክርስቶስ  የማዳን  ትልቁ ምሥጢር  የካሣ  ሥራ ነው። ራሱን  ካሳ  አድርጎ  ለራሱ አቅርቦ  ራሱን ለራሱ  ክሶ     ይህንን   ዓለም  አድኖታል   ።ይሄም የነገረ  ድኀነትን ምሥጢር የተሸከመ   ቃል መኾኑን ያስረዳናል   ።
☑️3ኛ  ምትክ   ወይም  ለውጥ   ይባላል። ይሄ ቃልም በዚህ ዓለም ስለሚፈጸም  ምትክነት ለውጥነት የሚያገለግል  ቢኾንም  ነገር  ግን  አዳም ሲሞት በአዳም ምትክነት መጥቶ በአዳም  ተገብቶ ዳግማይ አዳም ተብሎ የአዳምን መከራ ኹሉ መከራ አድርጎ በአዳም  ሊኾኑ የሚገባቸውን ህመሞች ኹሉ ታሞ   በአዳም  ቦታ ገብቶ  ስለተቀበላቸው መከራዎች ምትክነት  ይነገርለታል   ።  በአዳም ተተክቶ  የተቀበላቸው መከራዎች ደግሞ የዚህ  ዓለም  ክብር   ድኀነት   ሕይወት    ናቸው   ።
ስለዚህ  ይህም ቃል  ከነገረ   ድኀነት   ሀሳብ  የሚወጣ   አይደለም   ።

☑️ሌሎችም ቤዛ ብል" ጥላ ቢሉ"  ጥላ ከፀሐይ  ዋእይ  የሚያድን  ነው። ጫማ  ቢሉትም  ጫማ ከእሾህ  ከአሜከላ የሚከላከል  የሚያድን   ነው  ። ፈንታ ቢሉትም  ስለ አንዱ ፈንታ  ሌላኛው  የሚያደርገው በጎ  ነገር  ኹሉ  ነው ።አንዱ  ስለ ኹሉ  ሙቶ የለምን ?ይሄ  ሞቱስ  ድኅነት  ኹኖን  የለምን? እና ቤዛ ማዳን የሚለውን  ዋና  የቃል ትርጉም ሳይለቅ በልዩ ልዩ ተመሳሳይ ወይም በአውዱ ዙሪያ ያለ አውዳዊ ትርጉምን  የቋጠረ   ኀይለ   ቃል   ነው   ።
☑️የክርስቶስ  ቤዛነት  እና  የእመቤታችን  ቤዛነትን ግን እንደ ምሥጢር ከኾነ   ኹሉም የቃሉ  ትርጓሜዎች  ሊገልጡ የሚችሉ ናቸው ። የጥላ  ቤዛነትም  የጫማ  ቤዛነትም ኹሉም  የክርስቶስን ቤዛነት ገላጭ ናቸው።ጥላ እርሱ  በፀሐይ እየተቃጠለ  በበረድ በዝናብ እየተደበደበ  በውስጡ ያለውን ሰው ግን ከመከራ ያድናል። በሰውየው ላይ ሊያርፍ የሚችለውን ኹሉ የፀሐይ ዋእዩን   በረዶውን  ከእርሱ ላይ እያረፈ እንዲቀር  ያደርገዋል ። ክርስቶስም ያደረገው ይህንን  ነው። ጫማም  ለተጫማው ሰው ቤዛ ነው። ሰውየውን ሊወጋ የተዘጋጀን እሾህ ኹሉ አስቀድሞ እርሱ  እየተወጋ ሰውየውን ከመወጋት በእንቅፋት ከመመታት  ይታደገዋል።ክርስቶስም ያደረገው ይህንን  ነው ።    ስለዚህ የቃሉ  ትርጓሜዎች ነገረ ድኀነትን ወይም  የክርስቶስን  የቤዛነት የማዳን ሥራ በልዩ   ልዩ  አገላለጥ  ሊገልጡ   የሚችሉ እንደ ኾኑ ቆም ብለን   ብንመለከታቸው   መልካም     ነው።

☑️ቤዛ  ከዚህም በላይ የሚታይ ኀያል ቃል እንደኾነ ይረዳኛል። ነገር  ግን እንዳይሰፋብን ይህንን ሀሳብ በመግታት ። የክርስቶስ   ቤዛነትን እና የእመቤታችን ቤዛነት በአጭሩ እናነፃፅር ። ይህንን ስናነፃፅር ቀዳማዊ አዳም እና ዳግማዊ አዳም ፤ ቀዳሚት  ሄዋን እና ዳግሚት ሄዋን ታሳቢ መደረጋቸው   ግድ ነው ። "

የመጀመሪያው ሰው ወይም ቀዳማዊ አዳም የሞት መግቢያ በሩ  ነው ። ኹለተኛው ሰው ወይም ዳግማዊ አዳም ክርስቶስ  ደግሞ የሕይወት መግቢያ  በር    ነው ።

☑️☑️ክርስቶስ ዳግማይ  አዳም  ነው። << በአንድ ሰው በደል ምክንያት ኀጢአት ወደ ዓለም ገባች። ስለዚችም ኀጢአት ሞት ገባ ብሎ ሲነግረን  ፥በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ቤዛነት እንደተሰጠን ይናገራል።በአንዱ ሰው በደል ዓለም እንደ ተፈረደበት ይናገር እና በአንዱ ሰው ጽድቅ ሰው ኹሉ ወደ ጽድቅ እንደ መጣ ይመሰክራል። ሮሜ6፥ 18በአንዱ በኩልሞት  በሌላኛው በኩል ሕይወት ወደ ሰው መጥቷል። በመጀመሪያው ሰው የመጣው ሞት በኹለተኛው አዳም በኩል በኾነው ቤዛነት እንደጠፋልን ቅዱስ ጳውሎስ   ነገረን። አንድ ነገር ልብ" እንበል።  ቃሉ የተነገረው በወንዱ በአዳም በኩል ቢኾንም ታላቋ የሞት መግቢያ በር ግን  ሄዋን ናት። ሴቶችም አስተውሉ። ዲያብሎስ ያልጣለውን ታላቁን ፍጡር አዳምን ሲቲቷ ግን ገነደሰችው።ሰይጣንን አሸንፎት ነበር።ሄዋን ግን አንበረከከችው።ወንዶች ኾይ!!የሴት ኀይሏን ተመለክቱ።ሴቶች ኾይ !! ይህንን ክፋታችሁን መርምሩ። ሊቁ"
☑️መጽሐፍ ቅዱስ ለአዳም በሚናገረው በርካታ ሀሳብ ውስጥ ሄዋንንም  እንደያዘ የሚነጋር መሆኑን ልብ ይሏል።በመጀመሪያዋ ሴት ሞት ወደ ሰው ገብቷል፤ በመጀመሪያዋ ሴት በኩል ኀጢአት ወደ ሰዎች  ገብቷል ። በሄዋን ምክንያት የገነት በር ተዘግቷል፥ ልጅነት ታጥቷል፤ በሰው ላይ ሞት ነግሧል ።በአንጻሩ በዳግማዊት ሔዋን በኩል  ሕይወት መጥቷል። ሕይወት ለሰው ልጅ ተሰጥቷል።
      አስረጅ 
ቅ/ዮሐ   አፈ  ሃይ  ም   66"
አስቀድሞ ሄዋን ድንግል ነበረች።ነገር ግን ዲያብሎስ  አሳታት ። ሄዋን ከዲያብሎስ  ቃል ሰምታ የሞት ምክንያት የኾነ ቃየልን ወለደች። እመቤታችን ማርያምን ግን ገብርኤል አበሠራት ከገብርኤልም ቃልን ሰምታ ሕይወትን ወለደች"  ይል እና ቃላ ለሄዋን ከሠተ ዕፀ የሄዋን ቃል በለስን እንብላ ማለትን ገለጠ። ከእመቤታችን የተገኘው ቃል ግን መስቀልን ገለጠ ይላል። እንግዲህ ሄዋን ከዲያብሎስ ድምጽ ሰማች፤ በለስን በላች።ቃየልን ወለደች። እመቤታችንግን ከገብርኤል ድምፅ ሰማች ጌታን ወለደች። ልጇ መስቀልን ገለጠ።  አሁን እንመልከት። ሞትን ከአዳም  ጋራ በጠቀስነበት ቅጽበት ኹሉ ሕይወትን ከክርስቶስ ጋራ መጥቀስ ግድ ነው።በተያያዘም ሄዋንን  የሞታችን  ምክንያት አድርገን በተናገርነበት አንቀጽ ኹሉ ድንግል ማርያም የሕይወታችን ምክንያት መኾኗ መዘንጋት  የለበትም ። ክርስቶስ ዳግማይ  አዳም በተባለበት አንቀጽ ኹሉ ድንግል ማርያም ዳግሚት ሄዋን መኾኗ መባሏ መዘንጋት የለበትም ። በመጀመሪያዋ ሄዋን ውድቀት ፥በኹለተኛዋ ሄዋን በኩል ትንሳኤ፤ በመጀመሪያዋ ሄዋን በኩል ሞት ፥በኹለተኛዋ ሄዋን በኩል ሕይወት፤ በመጀመሪያዋ ሄዋን በኩል መርገም፥
👍4
በኹለተኛዋ ሄዋን በኩል በረከት፤ በመጀመሪያዋ ሄዋን በኩል ኀሳር፤ በኹለተኛዋ ሄዋን በኩል ክብር፤ በመጀመሪያዋ ሄዋን በኩል ከገነት መባረር ፤ በኹለተኛዋ ሄዋን ኦ ገነት ነባቢት በተባለችው በድንግል በኩል ወደ ገነት መመለስ ኹኖልናል። ቅ/ኤፍሬም ሶርያዊ  በሄዋን ምክንያት የገነት ደጅ ተዘጋ። በድንግል ማርያም ምክንያት የገነት  ደጅ ተከፈተ ይለናል።ቀጥሎም እፀ ሕይወትን እንበላ ዘንድ ዳገመኛ ከእፀ ሕይወት አደለን  ይላል። ይሄ ንፅፅር ምን ያሳናል ?በእመቤታችን ምክንያት የገነት በር ተከፈተ  ማለት የገነትን በር የከፈተቸው የሚላት"የክርስቶስን ደም ትቶ ወይም ነጥቆ ነው እንዴ ? አይደለም። ነገር ግን የገነትን በር የከፈተው የክርስቶስ ደም ደማዊት ሥጋዊት መንፈሳዊትም ከኾነችው ከእመቤታችን የተገኘ ስለኾነ ነው። ዓለም የዳነበት የክርስቶር ደም ከሰማይ የወረደ አይደለም።ሥጋ ከሰማይ አላወረደም። ኢያውረደ ሥጋ እምሰማያት እንዳለ አባ ጊዮ መጽ ምስ" >የዓለም መዳኛ የኾነው ቅዱስ ሥጋ ክቡር ደም  የተከፈለ ከዳግማዊት ሄዋን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ መድኀኒት ከመድኀኒቱ መገለጫ እና ከምክንያቱ ጋራ አያይዞ መጥቀስ ሥርዓቱ  ነው ። እመቤታችን መስቀልንም ኾነ እመቤታችንም  ቤዛ ፥መድኀኒት፤ የገነት መክፈቻ እያሉ ደራስያን ሊቃውንት ሲገልጧቸው በእነርሱ በኩል ስለተፈጸመው ነገር ነው ። ወይም በእነርሱ በኩል የተፈጸመውን የማዳን ሥራ ለእነርሱ እየሰጡ መናገር  ለተፈጸመው የማዳን ሥራ የድኀነቱ ማከናወኛ መንገድ ወይም በር ስለ ኾኑ ነው።መንገዱ እና በሩ ክርስቶስ መኾኑን አንዘነጋም ። ነገር ግን ክርስቶስ የድንግልን ማኀጸን እና መስቀልን ለዙፋንነት ተጠቅሟል። የንጉሥን መንግሥት ከነ ዙፋኑ መግለጥ ግድ ነው። ድንግል በእባብ ለተደበቀው ዲያብሎስ  በሥጋ ተሰውሮ መጥቶ ድል ይነሳው ዘንድ መሰወሪያ የኾነው የሥጋው መገኛ ኹናለች።መስቀልን በመስቀል ተሰቅሎ አምላኬ አምላኬ እያለ ሊውጠው የቀረበ ዲያብሎስን መቀጥቀጫ አድርግታል። በኹለቱም የማዳን ሥራ ሠርቶባቸዋል።

☑️ቤዛን  ምትክ"  ብንለው  በገነት ባጣነው  እፀ ሕይወት ምትክ መስቀል ኹኖልናል። ስለዚህ መስቀል ቤዛችን ነው ቢል ድኀነት ስለተፈጸመበት በእፀ ሕይወት ፈንታ ስላገኘነው  ነው  ነው። ዳግመኛም በእፀ በለስ ምክንያት ብንወድቅ በእፀ መስቀል አዳነን ለማለትም ነው ። እመቤታችን   የሄዋን ቤዛ  ስንላት
ምትኳም  መድኀኒቷም፥ ጥላዋም ፦ ጫማዋም  ለማለት  ነው። የሄዋን ማሰሪያ የተፈታባት እመቤታችን ናት ዮ አፈሃይ"።ማሰሪያው ደግሞ ገመድ ወይም ሰንሰለት አይደለም።ኀጢአት መርገም ፍዳ  ነው። ምክንያቱም የሄዋን መርገሟ  ፍዳዋ  በደሏ ከእመቤታችን ሲደርስ አቁሟል።የጠፋው ወይም የጠወለገው የጎሰቆለ የሄዋን ባሕርይ በእመቤታችን  ንጹሕ  ኹኖ ተገኝቷል። በዚህም የባሕርይዋ መመኪያ ኹናታለች። ዳግመኛ አማናዊ የሄዋን መድኀኒት ኢየሱስ ክርስቶስ  ከዚች እናት ተገኝቶላታል። ስለዚህ ሄዋን ባሕርይዋ ነጽቶ ክቡር ኹኖ የተገኘባትን የእመቤታችን ባሕርይ መመኪያ ቤዛ ብትለው ትችላለች። እንዲያውም እመቤታችን የድኀነቱ ሱታፌዋን እንመልከት።የአዳም ቤዛ  የኾነው የክርስቶስ መገኛ ናት። ክርስቶስ የዓለም ቤዛ  ነው ።  ም የመጀመሪያው አዳም የኹሉም አባት ነው።ኹለተኛው አዳም ክርስቶስም የኹሉ አባት ነው። የመጀመሪያዋ ሄዋን የኹሉ እናት ናት።ኹለተኛዋ ሄዋን ማርያምም  የኹሉ እናት ናት። የመጀመሪያዋ የዓለም ኹሉ ሞት ምክንያት ናት።ኹለተኛዋ ማርያምም የዓለም ኹሉ ድኀነት ሕይወት ምክንያት ናት። ምክንያቱም  ዲያብሎስ ዓለሙን ኹሉ ማለት ሰውን ኹሉ ድል ለማድረግ ኀጢአትን ወደ ዓለም ለማስገባት ሄዋንን በለስን ተጠቅሟል። ክርስቶስም ሕይወትን ወደ ዓለም ለማስገባት መስቀልን ሴቲቱ ድንግል ማርያምን ተጠቅሟል። መስቀልን። ወደ  ዓለም በገባው ኀጢአት ምክንያት ሄዋን የኹልጊዜ ተጠሪ እንደኾነች ኹሉ  ወደ ዓለም ለገባው ድኀነት፥ ሕይወት ደግሞ ድንግል ማርያም የምንጊዜም ተጠሪ ናት ።ስለዚህ ቤዛዊተ ኲሉ  ቢሏት፥ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ አንችን ለዓለም ቤዛ አንድም ድኀነት ውብ አድርጎ የፈጠረ ቢባል ትክክል ነው። ሄዋን ቀታሊተ ዓለም ከኾነች እመቤታችን ቤዛዊተ ዓለም ናት። ዓለምን ኹሉ የወከለች ማርያም የዓለሙ ቤዛ  መገኛ  በመኾኗ  እና የወደቀችው ሄዋን ምትኳ የመዳኗ ምክንያት የመድኀኒቷ ማከናወኛ እና የዓለም ድኀነት መሠረት የተጣለ በማኀጸነ ማርያም ነው እና የዓለም የድኀነት  መሠረት የተጣለባት በመኾኗ ቤዛ መባሉ ከልክም በላይ የልክ ልክ  ነው  ።

☑️ዳግመኛም እመቤታችን የማየ ገቦው፤ የደመ ገቦው መገኛ ናት። በማየ ገቦው ተጠምቀን እንድናለን።ማየ ገቦ ግን ከድንግል ከተገኘ ሥጋ የተገኘ ነው። ደመ ገቦውን ወይም ከጎኑ የፈሰሰ ደሙን ጠጥተን እንድናለን።
ደም የተገኘበት ክርስቶስ ግን በሥጋ የተገኘ ከድንግል ማርያም ነው። የጌታ ስደት የድኀነታችን አካል እና  ለቤዛነት የተፈጸመ ነው ።የሚሰደድ ሥጋ የተጋኘ ግን ከድንግል ነው።ማለት መለኮት ከእርሷ ባሕርይ ባለ መከፈሉ እንጅ የተሰደደው ሥግው ቃል መኾኑ ግልጥ ነው። የክርስቶስ ረኀብ የድኀነታችን አካል ለቤዛነት ለካሳ የተፈጸመ ነው። የሚራበው ሥጋ ግን የተገኘ ከእርሷ ነው። የክርስቶስ ስቅለቱ  ሞቱ  የዓለም ድኀነት ነው። የሚሰቀል ሥጋ የሚሞት ሥጋ የተገኘ ግን ከድንግል ማርያም ነው ።እመቤታችን የክርስቶስ የቤዛነት ሥራ ኹሉ ይመለከታታል። ቤዛነት የተፈጸመበት ሥጋ መገኛ ናት።ቤዛ ዓለም ክርስቶስ  ዓለምን ለማዳን መገቢያ በር መንገሻ ዙፋን መራመጃ መንገድ መገናኛ ድልድይ መውጫ መውረጃ መሰላል አድርጓታል። ኹኖም ቀራንዮ ላይ የተሰቀለችው  ፥የሞተችው  ፥ ወደ ሲኦል በአካለ ነፍስ ወርዳ ሲኦልን የበረበረችው እርሷ ናት አንልም። ነፍሳትን ከዲያብሎስ እጅ የማረከችው  ወደ ገነት ያስገባችው ቀጥታ እርሷ ናት አንልም።ብለንም አናውቅም።ይሄ ኹሉ የተፈጸመበት ጌታ ግን በእርሷ በኩል  በእርሷ እንደመጣ እናውቃለን።እርሷም የዚህ የማዳን ሥራ ከዚህ እና ከዚህ በጠለቀ በሚታይ ምሥጢር ተሳታፊ ናት።ስለዚህ ቤዛ ቤዛዊት  መድኀኒት   ትባላለች። እመቤታችን ኀጢአት አልባ ናት።ያለ ዮሴፍ ሰሎሜ ቢሰደዱ ስለ ኀጢአታቸወም ነው።እመቤታችን በዚህ ዓለም ያገኛት መከራ ኹሉ ስለምኗ ይኾን?ያለ ኀጢአቷ የአዳምን ስደት የተሰደደልጇን ተከትላ ወይም ከልጇ ጋራ መሰደዷም በአጠቃላይ በዚህ ዓለም የተቀበለችው መከራ የጌታን የቤዛነት ሥራ ይተካል።ይተካከላል አንልም እንጅ ለዓለም ግን ቤዛ ነው። ጌታ  ያለ ኀጢአቱ የተሰደደው ስደት ስለ ሰው ነው። የእናቱም ለእርሱ መክበሪያ ለሰዎች ደግሞ ቤዛ ማለት የድኀነቱ አካል ነው። ይሄ ሰፊ እይታ ያሻዋል..።  ጥላው  ጫማው  ጋሻው በመጽሐፍ ቅዱስ ቤዛ ተብሏል።እመቤታችንም ከጥላ ከጫማ ከጋሻ አታንስም። ጋሻ ከጦር ከሠይፍ በማዳኑ ቤዛ ተብሏል።እመቤታችንም በአማላጅነቷ በነገረ ድኀነት ባላት ሱታፌ ቤዛ ትባላለች። ጥያቄ  ??????
እስራኤልን ባሕር ከፍሎ ማን አሻገራቸው ?
👍2😁1
ሀ   ሙሴ ?
ለ  የሙሴ በትር ?
ሐ  መልአከ እግዚአብሔር ።?
መ   እራሱ እግዚአብሔር ?
2ኛ  ጎልያድን   ማን ገደለው ?
ሀ   ዳዊት ?
ለ   የዳዊት ወንጭፍ ?
ሐ    መልአኩ?
መ እግዚአብሔር ?    መጽሐፍ ቅዱስ ከኾነ ለኹሉም የሚሰጥበት አውድ መኖሩን አይዘንጉ ።
ስለኾነም የብጹዕነታቸውን ሀሳብ    "
ከመጀመሪያ  እስከመጨረሻ ባልሰማውም ቃሉን የተናገሩበት አወራወሩ እና የቃሉ ቄንጥ ግን የታሰበበት ይመስላል።ያሰበ ሰው ደግሞ ማብራራት አለበት።በተለይ አባት መጠንቀቅ አለበት። አባቶች ሲናገሩት እና ወጣቶች ሲናገሩት ይለያያል። እኔ ግን ትልልቅ አባቶች  ኩታራው ኹሉ ሲጭረው ሲሞነጭረው በሚውል ቃል ያውም ለውጥ ላያመጡ አድምተውም ላይናገሩ   ባይፍጨረጨሩ መልካም ነው ስላለሁ።ይህ  የትምህርት አሰጣጥ የምድያ ሰለባነት የሚታይበት የትምህርት ሀሰጣጥ ነው።ብጹዕነታቸው ሊቅ ሊኾኑ ይችላሉ። ነገር  ግን ኹሉንም ላብራራው ባይሉስ ? ኹላችንም በትምህርቱ ዓለም  ደክመንበታል። መልስ ለመስጠት ግን ለአንዳንድ ሰዎች ብንተውስ ?እኔም ብተው ?እንዲያው ዲ/ን ያረጋል  አጭጀው፥ወቅተው    የከመሩትን የፕሮቴስታንት ከንቱ ትምህርት እንደ ልደተ ቃል መጽሐፉን በመጋበዝ  ብንተውላቸውስ? ከኾነም በደምብ እያነበብን ብንናገር  በእጅጉ መልካም ነው። ለማንኛውም ወደ ፊት ትምህርታቸውን  እንስማ እና  በመጡበት እንመጣለን።

ለምሳሌ    ..።

👉መምህር ጽጌ አስተራየ
👍4
በግሌ አመሰግናለሁ አባቶቼ!

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የቅርብ ጊዜ ፈተናዎች ውስጥ አንዱ ሕጉን የሚያውቁና የሚያስተምሩ ሊቃውንት ዝምታ ይመስለኛል።

በተለይም ባለፉት ሁለት ዓመታት በነበረው የታሪክ ጥላሸታችን ውስጥ በቁጥር ካሉን አንጻር ጥቂት የሚባሉት ብቻ ተሟግተዋል። በመናገራቸው ብቻም በራሱ በቤተ ክህነቱ ሳይቀር አናውቃችሁም ተብለው ተገፍተውም ነበር።

ብዙሃኑ ግን ዝምታን መርጠው ነበር። በዚህም እንደምእመን ለምን ብለን ጠይቀናል። ከውጭ ጫና ሲበዛ በትር ሲጠነክር ብቻ ሳይሆን ከውስጥ እሾህ አሜካላ ሲበቅል መጥተው ካልተጋፈጡ ወጥተው ካልመሰከሩ ምኑን አስተማሩን? ቤተ ክርስቲያን የሰጠቻቸውን ስምና ክብርስ ለምናቸው ነው ብለን አምተናቸዋል።

ዛሬ ብፁዕነታቸው በተናገሩት ላይ እነዚህና ሌሎች የመጻሕፍት መመህራን ግር ብለው ቢመጡ እጅግ ደስ አለኝ።

አንድም ስለሃይማኖታቸው አንድም እንተ ስማለማርያም ብለው በስሟ ተማጽነው የተማሩባት ትምክህታቸው ናትና ቅናታቸውን ቀናሁበት።

አንድም ደግሞ ብዙ ጊዜ ጳጳሳቱን ተው ማለት ዶግማ መጣስ ለሚመስለው በእውቀትና በአክብሮት መመለስን አሁንም ስላሳዩን፣ ሃይማኖታችን ከማንም ከምንም የማናስበልጠውና የማንደራደርብት መሆኑን ስላሳዩን እንደአንዲት ምእመን እጅ እነሳለሁ።

በተለይም በቤተ ክህነቱ መዋቅር ሁኖ መታገልን ነውር ለሚያደርጉና በፍርሃት ለተቀፈደዱ ምሳሌ ትሆናላችሁ።

እናንተ ዝም ስትሉ ነው ምእመኑ እመልሳለሁ እያለ የሚያጠፋውና አትጥፉብን።

https://www.facebook.com/share/16N1EEQJGE/?mibextid=wwXIfr

https://www.facebook.com/share/15LeKA2YEj/?mibextid=wwXIfr

https://www.facebook.com/share/12JFpjVbji1/?mibextid=wwXIfr

https://www.facebook.com/share/1RDzsSWj7h/?mibextid=wwXIfr

https://www.facebook.com/share/18uH1wSMr3/?mibextid=wwXIfr

https://www.facebook.com/share/12CmMHqEhXz/?mibextid=wwXIfr

https://www.facebook.com/share/16UmRUdqfC/?mibextid=wwXIfr

👉ጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው እንደጻፈችው
👍2
በአባ ገብርኤል የስሕተት 'ስብከት' ላይ የቀረበ ሙሉ ትችት
************************************************************
አባ ገብርኤል ከውጭ ወደ ውስጥ ያስተጋቡትን ትችት አዘል፣ በስሕተት የተሞላውን ስብከታቸውን በተመለከተ ትናንት ማታ ከመምህር በረከት ጋር በነበረን የቲክቶክ መርሐ ግብር በሰፊው ዳስሰነዋል፡፡
በዚህ ጽሑፍ በጥልቀት የዳሰስንባቸውን ነጥቦችና ዋና ዋና ትችታቸውን በቲክቶክ ላይ በነበርው ውይይታችን ያነሣነው ቢሆንም ያንን ላልተከታተሉትም ጭምር ይሆን ዘንድ አሰናድቸዋለሁና ተጋበዙ፡፡
በነገራችን ላይ ለሊቀ ጳጳሱ የተሰጡ መልሶች ላይ እስከ አሁን ባደረኩት ዳሰሰ፣ ‘እመቤታችን ቤዛዊተ ዐለም አይደለችም’ ከሚለው ትችታቸው ውጭ ጠቅላላ ስብከታቸውን ተመልክተው በዚያ ስብከት በኩል ከውጭ ወደ ቤተ ክርስቲያን የተጮኹ የሌላ አካል ድምጾችን በተመለከተ ትችትና አስተያየት ሲሰጥ አላየሁም፡፡
ርብርቡንና የሁሉንም ጥረት ባደንቅም ሁሉም የተረባረበው አንድ ጉዳይ ላይ ብቻ መሆኑ ጉዳዩን ሙሉዕ እንዳይሆን አድርጎታል ባይ ነኝ፡፡ ለዚያ ነው ይኸንን ጽሑፍ ጨርሶ ማንበብ ጉዳዩን በጥልቀት ለመረዳትና የሊቀ ጳጳሱን መልእክት በጠቅላላው ለመረዳት ሊያግዝ ይችላል የምለው፡፡
ሙሉ ቪዲዮውን ተመልክቼ ስጨርስ አባ ገብርኤል ያቀረቧቸው ነቀፋዎች አንድ ቤተ ክርስቲያንን ‘ቤቴ፣ መጠጊያ፣ አካሌ’ ከሚል አባት ወይም መምህር ሳይሆን፣ ቤተ ክርስቲያንን፣ ‘ጠላት፣ ሌላ፣ ውጭ’ አድርገው ከሚያዩት፣ ተሐዲሶና ፕሮቴስታንት በተደጋጋሚ የሚጮኹትን ጩኸትና እነሱን ተክተው፣ መስለውና አህለው የጮኹት ነው የሚል መደምደሚያ ላይ ነው ያደረሰኝ፡፡
መግቢያ
*********
ስብከቱን የሰበኩት አባ ገብርኤል የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ፣ የሰበኩበት ቦታ ደግሞ ባለሃብቱ አቶ ጸጋየ ለስቅለት ባዘጋጀው የአዳራሽ መርሐ ግብር ላይ ነው፡፡ እኔ የተመለከትኩት ስብከት የ51 ደቂቃ ቪዲዮ ነው፡፡
የስብከታቸው ርእስም ‘የሰባ ግብዣ’ የሚል ሲሆን ቅዱሳት መጻሕፍቱን በግእዝ ጠቅሰው፣ በአማርኛ ተርጉመው፣ በቀጥታ ወደ ራሳቸው ትችት የሚያዘነብሉበትን አካሄድ የተከተሉበት ነው፡፡ ርእሳቸውን የመረጡበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ኢሳ 25፡ 6 ላይ ያለውን ወይገብር እግዚአብሔር በዝንቱ ደብር ለኲሉ ሕዝብ ከመ ይብልዑ መግዝአ ስቡሐ ወመሥዋዕተ ስሙረ፣ እነሆ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር የሠራዊት ጌታ በዚህ ታላቅ ተራራ የሰባ ግብዣን ያደርጋል፡፡ ያረጀ የከረመ፣ የቆየ የወይን ግብዣንም ያደርጋል፡፡ በወገኖች ላይ የተጣለውን መጋረጃ በአሕዛብ ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛም ያስወግዳል የሚለው ነው፡፡
ጠቅላላ አስተያየት
***************
ስብከቱ የተሰበከው ክርስቶስ በእለተ ዐርብ የከፈለውን የቤዛነት ሥራ ለማሳየትና የቀኒቱን ታላቅነት ለማጉላት ይመስላል፡፡ የመረጡትም ‘የሰባ ግብዣ’ የሚለው ርእስ አብ ለሰው ልጆች ያዘጋጀው፣ ያረጀ፣ የከረመ የወይን ጠጅ (ሊቀ ጳጳሱ ባይጠቅሱትም፣ ያረጀ፣ የከረመ የወይን ጠጅ የሚለው ብሉየ መዋዕልነቱን ለማሳየት ነው ኢሳይያስ ያንን የተጠቀመው) ሲሆን፣ ታላቅ ግብዣ የተባለበትም አንዴ ተበልቶ ለዘላለም የማያስርብ አስደናቂ ግብዠ በመሆኑ ነው፡፡
እዚህ ላይ ስለ ሰባኪው አስተያየት ብንሰጥ፣ ርእስ አመራረጣቸውም ይሁን፣ ለመረጡት ርእስ የሚጠቅሷቸው መጻሕፍት ጥንቅቅ ያሉ ናቸው፣ ግእዙንና አማርኛውንም በደንብ አድርገውና አቀናጅተው የሚጠቅሱ ብቻ ሳይሆኑ ንባባቱን የሚረዱበትና ለሰማዕያኑ የሚያቀርቡበት መንገድ ቀልብን የሚስብ ነው ማለት ይቻላል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ከስብከታቸው ለመታዘብ እንደሞከርኩት ሁለት ወጥ ችግሮች አሉባቸው፡፡ 1ኛ) የመጻሕፍቱን ንባባት አስቀድመው በግእዝ፣ ከዚያ በአማርኛ ያስከትሉና ቀጥታ የሚገቡት የራሳቸውን ትርጓሜና ብይን ወደ መስጠት ነው፡፡ ይኸ ከተለመደው፣ በተጠቀሰው ንባብ ላይ ከጥንት ጀምሮ ሊቃውንቱ እንዴት እንደተረጎሙትና እንዳመሰጠሩት ካስረዱ በኋላ ወደ ሕይወታችን መተርጎም የሚለው ስልት ያላገናዘብ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ 2ኛ) በሚያነሧቸው ርእሰ ጉዳዮች ሁሉ ንባባቱን ለሐሜትና ሌሎችን ለመዝለፊያነት ወይም ትውፊትን ለማጣጣያነት ይጠቀሙበታል፡፡ ይኸም በወንጌል ስም ወይም ወንጌል ለራስ ፍላጎት ማስገደድ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፣ ይኸ መንፈሳዊነት ሳይሆን ፖለቲከኝነት ነው የሚባለውም፡፡ አይደለም ወንጌል መድረክ ላይ ተቁሞ ሐሜት መቼም የትም ቦታ ቢሆንም ነውርም ሐጢአትም ነው፡፡ ይኸ ወደ ጎን የሚተኩሱት ወይም ከውጭ ሆነው ወደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊትና ሥርዓት ላይ የሚያደርጉት ተኩስ ጥሩ የነበረውን ትምህርታቸውን ፈጽሞ ገድሎባቸዋል፡፡
ዝርዝር ትችት
************
የእኔ ዝርዝር ትችት የሚያተኩረው ከጉዳዩና ከመረጡት ርእስ ጋር የማይገናኙ ወይም ባያካትትቷቸው ስብከታቸውን ሙሉዕ ከመሆን የማያግደዷቸውን፣ ነገር ግን በዐላማና የተደራጀ በሚመስል በልኩ ባስተላለፏቸው ስሕተቶች ላይ ነው፡፡ ሊቀ ጳጳሱ ቢያንስ አምስት አካባቢ የሚሆኑ ነጥቦች ላይ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትችት አቅርበዋል ወይም የተሐዲሶና የፕሮቴስታንትን ድምጸት አስተጋብተዋል ብየ ስለለየሁ ስሕተቱ ከዚያ ቢልቅም ከዚህ ቀጥሎ የማተኩረው በአምስቱ ስሕተቶቻቸው ላይ ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ለመከተል ይመቻችሁ ዘንድ የማደርገው ሊቀ ጳጳሱ የተናገሩትን በጥቅስ ውስጥ አስቀምምጥና፣ በማስቀጠል ትችቴን ወይም ጥያቄዎችን አስከትላለሁ፡፡
1) ከ13ኛው ደቂቃ ጀምሮ ስለ ኦሪት ያላቸው ትችትና ምልከታ ኦርቶዶክሳዊ አይደለም፡፡
እንዲህ ይላሉ፣
‘የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው፣ የኃጢአትም ኃይል ደግሞ ሕግ ናት ይላል፣ ኦሪት ይላታል፡፡ ኦሪት ገዳይ ነች፣ ጨካኝ ነች፣ ኦሪት ጥላ ናት፣ እግዚአብሔር ኦሪትን አሳልፏል፤ የኦሪቱ መሥዋዕት አልፏል፣ የኦሪት መሥዋዕት ወይም ሕገ ኦሪት ማለት የወላጅ ቤት ማለት ነው፡፡ እንደ እናት አባት ቤት የሚቆጠር፣ አንድ ሰው እናት አባቱ ቤት እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ነው የሚኖረው እንጂ እድሜ ልኩን ለእርሱ መኖሪያ ሊሆን አይችልም፡፡ በዚህ ዘመን 40፣ 50 60 ዐመታቸው ድረስ ተዘፍዝፈው የሚኖሩ አሉ፣’
ይኸ ምልከታ ኦርቶዶክሳዊ አይደለም፡፡ ኦሪት ጨካኝ አይደለችም፣ ኦሪት ሞግዚት ነበረች፣ እናት ወንጌል እስከምትመጣ ልጆችን በአሳዳጊነት የጠበቀች ናት ኦሪት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‘ኦሪት ኃጢአቴን አበዛችብኝ’ ያለው፣ ሕግ የሚያስቀጡትን ነገሮች ዘርዝራ፣ ቆጥራ ስለምታሳውቅ ነው፣ ያለሕግ ሲያደርገው የነበረውን ሕግ ስተመጣ ስለከለከለችው ‘ቆጠረችብኝ፣ አበዛችብኝ’ አለ እንጂ ኦሪትን በሞግዚትነቷማ አመስግኗታል፡፡ የተሰጣትን ሚና ተወጥታለች፣ ኦሪት ያልተሰጣትን ታሳካ ዘንድ አልተጠየቅችም፣ በሌላ በኩል መጽሐፋዊው መረዳት ልጆች የወላጆች ወራሾች ናቸው፣ 'በአባቴ ቤት መኖሪያ አዘጋጅላችኋለሁ' ያለው ለዚያ ነው፡፡ የአባታችን ወራሾች ነን፡፡ የሊቀ ጳጳሱ ንጽጽርና ምሳሌም በዚህ ረገድ ደካማ ነው፡፡ በዋናነት ግን ይኸ ምልከታ የተሐዲሶና የፕሮቴስታንታት ነው፡፡
ቀጥለውም ሌላ በጣም ጎደሎ ምሳሌ ይጠቀማሉ፣
2025/08/28 09:24:37
Back to Top
HTML Embed Code: