Telegram Web
ባሕር ዳር

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅነት መልስ በባሕር ዳር ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው:

ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሦስት ዓመታትን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ዘመናቸውን አጠናቀው ወደ ሀገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል።

በባሕር ዳር በሚገኘው ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም ምእመናኑ በታላቅ ደስታና ድምቀት ተቀብለዋቸዋል።

ይህን አስደሳች አቀባበል ለማድረግ

1. የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ
2. ከተለያዩ ገዳማትና አድባራት የተውጣጡ አስተዳዳሪዎች
3. ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን
4. የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን
5. እንዲሁም በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ተገኝተዋል።

ቀጣይ መርሐ ግብሮች በመንበረ ጵጵስናው
የብፁዕነታቸው አቀባበል ሥነ ሥርዓት በአየር ማረፊያው የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በባሕር ዳር በሚገኘው ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል መንበረ ጵጵስና ቀጥሏል። በዚያም የተለያዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብራት እየተከናወኑ ይገኛል::

📷ፈለገ ገነት ሚዲያ
10🙏1🤣1
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ ዘለዓለም ሥላሴ።
በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች፣ የጉባኤ ቤታችን ቤተሰቦች በሙሉ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን እንደምን ሰነበታችሁ? እኛ አምላከ አበው እግዚአብሔር ይመስገን ደኅና ነን።
የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች ገዳም የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት የምስክር ት/ቤት በእሳት እንደተቃጠለ በማኅበራዊ መገናኛ መረቦች እየተላለፈ እንደሆነ ብዙዎቻችሁ ተጨንቃችሁ ደውላችሁልናል።
በመሆኑም ከጉባኤ ቤቱ ሐሙስ ግንቦት ሰባት ቀን እሳት ከቤት ተነሥቶ ለደቀ መዛሙርቱ ተሠርቶ የነበረ ቆርቆሮ በቆርቆሮ ጊዚያዊ መጠለያና የግማሾቹ ደቀ መዛሙርት ልብስና መጻሕፍቶቻቸው ተቃጥለዋል። ነገር ግን በሰማዕቱ በቅዱስ ቂርቆስና በእመቤታችን ጸሎት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠብቆን ጉባኤ ቤታችንና መጻሕፍቶቻችን ደኅና ናቸው።
እኛም ደቀመዛሙርቱና ዋናው ጉባኤ ቤት፣ እንዲሁም ገዳማችን ደኅና ስለሆነ፣ ጊዜው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የተጀመረበት በመሆኑ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ተጨማሪ ርእሰ ጉዳይ ላለመጨመር ለሚዲያ ሳንገልጽ ቆይተናል።በመሆኑም አሁን ግን ስለወጣ ይህንን መግለጫ ለተጨነቃችሁ ወገኖቻችን ልንገልጽ ፍቅር ያገብረናል።
ለጉባኤ ቤቱ የሚያስፈልጉን ጉዳዮች ቢኖሩ እኛ በፈወስ መንፈሳዉ የጉባኤ ቤታችን ሚዲያ በምስል የምንገልጽ መሆናችንን እየገለጽን ፣ ለተጨነቃችሁልን፣ለጸለያችሁልን፣ላሰባችሁልን፣ለረዳችሁን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ የጉባኤ አምላክ በምሕረቱ ያስብልን።
አምላከ ጉባኤ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያናችንንና ሀገራችንን ይጠብቅ።
የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና እናቶች አንድነት ገዳም የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ቤተ ጉባኤ
ግንቦት፳፫-፳፻፲፯ ዓም
1
#ይሉኝታ
በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ይሉኝታና ኩርፊያ አይሠራም። ቅድሚያ የሚሰጠው እግዚአብሔራዊው እውነት ነው። ዮናስ "ሐሰተኛ ነቢይ" እባላለሁ ብሎ እግዚአብሔራዊውን እውነት ላለመናገር በመርከብ ተጭኖ ሲሄድ ለብዙ ሰዎች ንብረት ውድመት ምክንያት ሆኗል። ሰዎች የሌለህን ማንነት ነህ ብለው በይሉኝታ አጥረው ክፋታቸውን ሲሠሩ ዝም እንድትል ሊፈልጉ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ይሉኝታ አያስፈልግም። የፈለገ ክብር ቢኖርህ ስለቤተ ክርስቲያን ብለህ ክብርህን ትተህ እውነታውን መጋፈጥ አስፈላጊ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስን በጩኸታቸው ብዛት በደለኛ ነው ይሰቀል ቢሉም እርሱ ግን ንጹሐ ባሕርይ ነበር። ብዙዎች በሐሰት ስለጮሁ የሚቀየር ማንነት ሊኖረን አይገባም። በጥበብና በፍቅር እውነታውን ማስረዳት ከሁላችንም ይጠበቃል። አንዳንዶች ዘረኛ እንባላለን ብለው ሰግተው የተወለዱበት አካባቢ ብዙ መከራ ሲደርስበት ድምፅ አይሆኑም። በዚህ ጊዜ ግን እውነታውን ተናግሮ ዘረኛ መባል የተሻለ ነው። ሰው እውነትን በመናገሩ ማንኛውንም ዓይነት ስም ቢሰጠው ማፈርም መፍራትም አይገባውም። ቅድሚያ ለእውነት። የቤተክርስቲያንም የማንኛውም ሰውም ባለቤቱ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀው እውነታውን መናገር ነው። የእኛ ደስታ እውነትን በመናገር የሚገኝ ነው። ቅዱሳን ሰማዕታት እውነትን በመናገራቸው የተለያዩ መከራዎች ደርሶባቸዋል። ያ መከራ ግን የክብር ምንጭ ነው።

በእውነትና በውሸት መካከል ሌላ ሦስተኛ ነገር የለም። እውነትንና ውሸትን አቻችለን እንኑር አይባልም። እውነት ከውሸት በላይ ገዢ ሆና እንድትኖር መሥራት ከሁሉም ይጠበቃል።

©በትረማርያም አበባው
4🙏1
በአዳማ ከተማ የመስቀል አደባባይን መጠቀም አትችሉም።

-በ27/09/2017 ዓ.ም የአዳማ ከተማ ከንቲባ የደብር አስተዳዳሪዎችን፣ የሀገረ ስብከት ኃላፊዎችን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮችን ሰብስበው "ለሥራ ፈልገነዋል የመስቀል አደባባይን ከዚህ በኋላ መጠቀም አትችሉም። ሌላ እንሰጣችኋለን። ቀጣይ ዓመት ጀምራችሁ መጠቀም አትችሉም" ብለዋል። የደብር አስተዳዳሪዎችና የሀገረ ስብከት ኃላፊዎች መንግሥት ያለውን ተቀብለው ተስማምተው አመስግነው ከስብሰባ ወጥተዋል።

-መስቀል አደባባይ ከተማው ከተቆረቆረ ጀምሮ ካህናትና ምዕመናን ሲጠቀሙበት የነበረ ነው። ከንቲባው ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጋር ለረጅም ጊዜ አውርተናል ሲል ነበር። ለማንኛውም በ2018 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በተለመደው የመስቀል አደባባይ የመስቀል በዓል አይከበርም። በተለይ የከተማው ነዋሪዎች አካባቢውን የምታውቁ ስለ መስቀል አደባባዩ ነገር ንገሩን። ቦታ መቀየሩ ምን ያህል ተገቢና ምክንያታዊ ነው?

©ዮሴፍ ፍስሐ
5
የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ኔማንያ ማቲች የ4 ጨዋታ ቅጣት ተጣለበት። የፈረንሳዩ ሊዮን ተጫዋች ማቲች በፈረንሳይ ሊግ 1 የመጨረሻ ጨዋታ ላይ ማሊያው ላይ ያለውን የተመሳሳይ ፆታ ሎጎ በፕላስተር ሸፍኖ ወደ ሜዳ በመግባቱ ለቅጣት ተዳርጓል። ሰርቢያዊው ማቲች ሀይማኖቴ አይፈቅድም በሚል ፕላስተሩን ሎጎው ላይ ለጥፏል። ኔማኒያ ማቲች የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ ነው።

ሲዲ ስፖርት/cd sport
10❤‍🔥3👍1
የሐዋርያት ጾም(ጾመ ሐዋርያት)

ጾመ ሐዋርያት ከሰባቱ የአዋጅ አጿማት መካከል አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋርያት የእግዚአብሔርን ሥራ ወንጌልን መስበክ ከመጀመራቸው በፊት የሥራቸው መጀመሪያ ያደረጉት ጾምና ጸሎት ነበር። ከዚያ በኋላም ቅዱሳን አበው ቀኖና ሲሰሩ በቅዱስ ሲኖዶስ ከአጿማት አንዱ እንዲሆንና ክርስቲያኖች ሁሉ እንዲጾሙት ወስነዋል። (ሐዋ•፲፫፣፪-፫)13:2-3)
በመሆኑም ጾመ ሐዋርያት ሁሌ እንደ የዓመቱ መግቢያው የተለያየ ነው። ነገር ግን መፍቺያው ግን ሁልጊዜ ሐምሌ ፭(5) ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ እና ብርሃነ አለም ማኅቶተ ቤተከርስቲያን ቅዱስ ጳውሎስ በሚታሰቡበት ዕለት ይፈታል።

እንደ ሥርዓት ጾመ ሐዋርያት የሚጾመው እስከ ዘጠኝ ሰዓት ነው። ይህ ጾም በቀመረ ባሕረ ሐሳብ የአጽዋማት አወጣጥ ቀመር መሰረት ጾሙ ዝቅተኛ ቀን ከሰኔ ፳ (20)ገብቶ እስከ ሐምሌ ፬(4) የሚጾም ሲሆን በሐምሌ ፭(5) ቀን የሚፈታበት ቀን የጾሙ ብዛት ፲፭ (15)ቀን ብቻ ይሆናል ማለት ነው።
የጾሙ ከፍተኛ ቀን ግንቦት ፲፮(16) ገብቶ እስከ ሐምሌ ፬ የሚጾም ሲሆን በሐምሌ ፭(5) ቀን የሚፈታበት ቀን የጾሙ ብዛት ፵፱ (49)ቀን ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህም የጾመ
ሐዋርያት የቀን ብዛት ፲፭(15) ቀን እስከ ፵፱(49) ቀን ይሆናል ማለት ነው።

በዘንድሮው የባህረ ሃሳብ ዘመን ጾመ ሐዋርያት በሰኔ ፪(2) ይገባል የአርብ እና የረቡዕ ጾም ሰኔ ፬(4) ይጀምራል ጾመ ሐዋርያት ከሰኔ ፪(2) እስከ ሐምሌ4(፬) የሚጾም ሲሆን በሐምሌ ፭(5) ቀን ይፈታል በዚህም መሰረት በዚህ ዘመን የጾሙ ቀን ብዛት ፴፫(33) ነው።
እግዚአብሔር አምላክ በቸርነቱ በረከት ለምናገኝበት ለከበረው ጾመ ሐዋርያት በሠላም ያድርሰን ያድርሳቹሁ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
2
በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ምዕመናን በአካባቢው የቤተክርስቲያን አንድነት እና መዋቅር በከፍተኛ ደረጃ ለአደጋ መጋረጡን ለቅዱስ ሲኖዶስ በጻፉት ደብዳቤ ገለጹ !

ሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናንን ጉዳይ መነሻ በማድረግ ለቅዱስ ሲኖዶስ የቀረበ ጥሪ በሚል ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ምእመናን የቤተ ክርስቲያን አንድነት አደጋ ውስጥ መግባቱን ነው የገለጹት።

“የዩናይትድ ኪንግደም ምዕመናኑን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚኖረው የአገልግሎት ተሳትፎ አማካይነት አላስፈላጊ ጉዳዮችን ወደ ቤተ ክርስቲያን በማምጣት የምዕመኑን አንድነት ከማጠናከር ይልቅ ወደ መለያየት በማድረግ ምዕመናኑ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ልዩነት ቢኖረውም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልዩነቶችን በማንፀባረቅ ምዕመናኑን በዘር፣በፖለቲካና በተለያየ አስተሳሰብ እንዲለያይ ተደርጓል" ብለዋል ምእመናኑ።

በሀገረ ስብከቱ ውስጥ በልዩነቶችና ባለመግባባት ፤በማንችስተር፣ በሼፊልድ፣በሊድስ፤ በለንደን፤ በቅርቡ ጊዜ ደግሞ በስቶክ ኦን ትሬንት ከተማ በመለያየት የተለያዩ መንፈሳዊ ማህበራትና ደብራትን ሲያቋቁሙ ታይቷል ያሉት ምእመናኑ ሀገረ ስብከቱ በስያሜ ደረጃ ካልሆነ በቀር በተግባር ሙሉ በሙሉ አለመኖሩና ለዚህ ከፍተኛ ተጽዕኖ የፈጠረው በቅዱስ ሲኖዶስ ተሰይመው በዩናይትድ ኪንግደምና አየርላንድ ሀገረ ስብከት በሚል የበላይ ጠባቂ ሊቀጳጳስ ተመድቦ የነበረ ቢሆንም በሀገረ ስብከታችን የተመደቡት ሊቀጳጳስ በተመደቡበት መንበረ ጵጵስናቸው አለመኖር እና የምዕመናኑ ድምጽ የሚያዳምጥ አባት አለመኖሩ ግልጽ ማሳያ ነው ብለዋል።

ምዕመናኑ በሚኖርበት ከተማና በሚገለገልበት ደብር ላይ ሰላሙን ሊያደፈርስ ወይም ምዕመናን ወደመለያየት የሚያደርሱ ጉዳዮች ሲከሰት ምዕመናኑ በህብረት ችግሩን በመጋፈጥ የችግር ፈጣሪዎችን ለይቶ በማውጣት የራሱን ሰላም ሊያስጠብቅ ይገባል ነው ያሉት ምእመናኑ ፤ ምእመናኑ በተጨማሪም የቤተ ክርስቲያን ልዩነት በእጅጉ ገዝፎ በሚታይበት ሀገረ ስብከታችን ውስጥ እንደመገኘታችን የሀገረ ስብከታችን አለመጠናከርና ሀገረ ስብከታችን በአገልግሎቱ ህልው ባለመሆኑ እንደስያሜው ተገቢውን ተግባራት ባለማከናወኑ በኃላፊነት ላይ የተሰየሙት ግለሰቦች የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም ከማስቀድ ይልቅ ግለሰባዊና የሥልጣን ጥማታቸውን ብቻ ለመጠቀም ፍላጎት በማሳየታቸው በመላው ዩኬ ለሚገኝ ምዕመናን መለየያየት ግድ የሌሽ መሆን የቤተ ክርስቲያናችንን ችግር ወደ ባሰ አዘቅት ውስጥ እየጨመረ መሆኑ ለማወቅ አያዳግተንም ነው ያሉት።

የምእመናን ሕብረቱም ለቅዱስ ሲኖዶስ

1ኛ. እንደቀደሙት አባቶቻችን ለቤተ ክርስቲያን እና ለመንጋችሁ ስትሉ ከቤተ ክርስቲያን እና ከመንጋው የሚበልጥ ምንም ስለሌለ ጉዳዩን በጥልቅ መክራችሁ በሀገረ ስብከታችን መንጋውን የሚጠብቅና የሚባርክ በጸሎት የሚያስቡንን አባት
በመንበረ ጵጵስናቸው እንዲቀመጡልን በልጅነት መንፈስ እንማጸናለን።

2ኛ. በየደብራቱ ( በየከተማ) የተፈጠረው ልዩነት ተወግዶ ቤተ ክርስቲያንን ወደ አንድነት ሊያመጣ የሚችል ጥንቃቄ የተሞላበት የሀገረ ስብከት አስተዳደር ደካማ እንቅስቃሴዎችንና ብልሹ አሰራሩ መፍትሄ በመስጠት ውሳኔ እንድትወስኑ አደራ
እንላለን።

3ኛ በቅርብ ጊዜያት በብፁዕ እቡነ ያዕቆብ ሰብሳቢነት በዩኬና አየርላንድ የሚገኙትን አገልጋይ ካህናት ዲያቆናት በመጥራት በተደረገው የሀገረ ስብከታችን ብልሹ አሰራርን በተመለከተ በተደረገው ውይይት ላይ ሰፊ ማብራሪያ እና ጥናት ተካሂዶ ሀገረ ስብከቱን በጥሩ አስተዳደር ለመተካትና በሀገሪቱ ያለችውን የቤተ ክርስቲያና አስተዳደራዊ ክንዋኔዎች በሕገ ቤተ ክርስቲያን ለማስቀጠልና ምዕመናኑን ከልዩነትና ከመከፋፍል ለመታደግ በተያዘው የሥራ ክንዋኔ በተመለከተ የጥናት አድራጊ ኮሚቴ የተከተውን ተልዕኮ እንዲያስፈጽምና የሀገረ ስብከታችንን አስተዳደራዊ ክፍተት በማደስ ወደ አንድነት መንፈሳዊ ጉዞአችን እንድንቀጥልና ስርዐተ አምልኮአችን በአግባቡ ለመፈጸም ያስችለን ዘንድ የቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እና እርዳታ እንድናገኝ በማለት ጥያቄ ማቅረቡን ለተ.ሚ.ማ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል።
1
2025/08/27 19:52:50
Back to Top
HTML Embed Code: