የእውነት ክርስቲያን ነህ?
፦አንድ እግዚአብሔር ያለው ኦርቶዶክሳዊ ነህ? ኤፌ.፬፥፭
፦አንድ እናት አንድ አባት ያለው ጥሙቅ ነህ? ማር.፲፮፥፲፮
፦አንድ ሙሽራ ያላት አንዲት ሙሽሪት ነህ? ማቴ.፳፪፥፩-፯
፦አንድ መምህር ያላት አንዲት ደቀመዝሙር ነህ? ማቴ.፳፰፥፲፱
፦አንድ መሥዋዕት ያላት አንድ ተቀባይ ነህ?፤ ዕብ.፩፥፩፣ዮሐ፮፥፶፮
፦አንድ ክህነት ያላት አንድት ተባራኪ ነህ? ማቴ.፲፮፥፲፰
፦አንድ ራስ ያላት ህዋስ ነህ? ቆላ.፩፥፲፰
፦ከማይጠፋ ዘር የተወለድህ ልዩ አካል ነህ?፤ ዮሐ.፫፥፬
፦አንድ ዐላማ ያላት ተስፈኛ ነህ?፤ (ግዕዝ ርትዕት) ማቴ.፲፫፥፮
፦ግእዛን ያላቸው ፍጥረታት እና የፈጣሪ ግንኙነት ኅብረት ባለቤት ነህ?
፦አንድ ቀዛፊ ብዙ ተሳፋሪ ባያላት መርከብ ውስጥ ነህ?ዘፍ.፮፥፲፭
፦አንድ የክርስቶስን መስቀል የተሸከምህ ክርስቶሳዊ ነህ? ማቴ.፲፮፥፳፬
፦ሐዋርያዊት፣ቅድስት፣አንዲት፣ኲላዊት በሆነች ቤተ ክርስቲያን ሥር ነህ? ማቴ.፲፰፥፲፯
.....ይሄንን ሁሉ ከሆንህ በጣም ጥሩ።
ክርስቲያን ከሆንህ እያደረግህ ያለኸው ምንድን ነው?
እየመከርህ ያለኸው ከማን ጋር ነው?
በቤተ ክርስቲናን ላይ እየሆነ ያለውን እንዴት ታየዋለህ?
ክርስቲዮኖቹ ሁሉ አካሌ ናቸው ብለህ ታስባለህ?
ትንሣኤ ሙታንን የማምን ርቱዕ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ብለህ ታስባለህ?
የምኖርበት ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ነው ብለህ ታምናለህ?
የምታምነውና የምትኖረው አንድ ነው? አፍህና ልብህ የተስማሙ ናቸው?
የእውነት የክርስቶስን መስቀል የተሸከመ ክርስቲያን ነህ?
በመንደር፣በቋንቋ፣በጎሳ፣በሥሁት ፖለቲካ፣በአስመሳይነት፣በግብዝነት፣በስግብግብነት ውስጥ የለህበትም?
አንድ ክርስቶሳዊ ወንድምህን ስታይ ክርስቶስ ይታሰብሀል?
የቤተ ክርስቲያን መዋረድ፣መሳደድ፣በመንደርተኞች ምክንያት መለያየት፣የቀኖናው መጣስ፣የምእመናን መከራ ያስጨንቅሀል?
የእውነት ክርስቲያን ነህ?
የኔታ ገብረመድኅን እንየው

❤5🙏3
ዜና ሹመት
ብፀዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለተለያዩ የሥራ ኀላፊዎች ሹመቶችን ሰጡ።
( ሰኔ 09 2017 ዓ.ም)
በዛሬው ዕለት ብፀዕ አቡነ ሳዊሮስ
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለመምሪያ ኀላፊዎች ዝውውር እና ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኀላፊዎች ሹመቶችን ሰጥተዋል።
በዚህም መሠረት፦
፩ኛ. መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ ከጠቅላይ ቤተክህነት ቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ ወደ ጠ/ቤ/ክህነት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ፤
፪ኛ. መ/ር ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ ከጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር መምሪያ ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት ድርጅት EOTC TV ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
፫ኛ. ሊ/መ ሐረገወይን ጫኔ ከሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር መምሪያ፤
፬ ዶ/ር አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ ከጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ወደ ጠ/ቤ/ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ፤
፭ኛ. መ/ር ምትኩ ከንቲባ ከጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌል መምሪያ ተዘዋዋሪ ሰባኪነት ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት የቅርሳቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ፤
፮ኛ. ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሳ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን ሥርጭት ድርጅት ወደ ቅ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ተዛውረው እንዲሠሩ ተመድበዋል።
በሌላ በኩል ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ጨምሮ የተወሰኑ አዳዲስ ዋና ክፍሎችን በመምረጥ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ፊርማ እንዲመደቡ አድርገዋል።
በዚህም መሠረት፦
፩ኛ. መ/ም አባ ገ/መድኅን ንጉሤ ከም/ሸዋ ሀገረ ስብከት ወደ ከዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተዛውረው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው እንዲሠሩ ተመድበዋል።
፪ኛ. መ/አእላፍ ማሙዬ ሸዋፈራው ከጠቅላይ ቤተክህነት ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ምክትል ኀላፊ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ፤
፫ኛ. መምህር አስናቀ ሸዋዬ ከጠቅላይ ቤተክህነት ቁጥጥር መምሪያ ተቆጣጣሪነት ወደ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከ ሂሳብ እና በጀት ዋና ኃላፊ፤
፬ኛ. ሊ/ኅሩያን ባዩ ተዘራ ከአዲስ ከተማ ቂርቆስ ልደታ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት የሰንበት ትምህር ቤቶች ክፍል ኀላፊ ወደ የሀ/ስብከቱ የሰው ኀይል አስተዳደር ዋና ክፍል ኀላፊ፤
፭ኛ. መ/ሰላም ጽጌ ከበረ ከጠቅላይ ቤተክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ምክትል ኀላፊ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የማኅበራት ማደራጃ ዋና ክፍል ኀላፊ፤
፮ኛ. ሊቀ ሥልጣናት አባ ጥዑመ ልሳን ኪዳነ ማርያም ከመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪነት ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማት ዋና ክፍል ኀላፊ፤
፯ኛ. መ/ስብሐት ዐቢይ ዘለቀ ከቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተዛውረው የሀገረ ስብከቱ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ልዩ ጸሐፊ ሆነው እንዲሠሩ ተመድበዋል።
መረጃው፡-የኢ/ኦ/ተ/ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኘነት መምሪያ ነው፡፡

❤3
Forwarded from ዮሐንስ ጌታቸው
+++#የባሕራን_ደብዳቤ#+++
በሰኔ 12 ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ከሚከበርበት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ የባሕራንን ደብዳቤ የሚመለከት ነው። ባሕራን መመጽወትና መዘከር ጽኑዕ አገልግሎቱ ከኾነ አባት የተወለደ ነው። እናቱም በዚያ መልካም ግብር ተጸምዳ ትኖር የነበረች ናት። አባትና እናት በአስተሳሰባቸው አንድ ኾነው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሲሠሩ ፡ ጎረቤታቸው ያለው ክፉ ባለ ጸጋ የመልካምነት ክንፉን በቅምጥልነት ሕይወቱ ስላጣው፡ በአስተሳሰብ ልዕልና ከመገኘት ይልቅ መሬታዊ በኾነ ክፋት ቆሳስሏል። የቅዱስ ሚካኤልን መክበር በፍጹም አካሉ፣ በፍጹም ነፍሱና በፍጹም ልቡናው ተጸይፏል። ይህ ሰው ከቤቱ ደጅ ያለውን የመልካምነት ትምህርት ቤት (የባሕራንን ቤተሰብ ሕይወት) ለመማር ባለመፈለግ ደንቁሯል! ይህ በእጅጉ አሳዛኝ የኾነ ሕይወት ነው። የተሰጠውን ሀብት አለመጠቀሙ! ያሳዝናል፤ ያስቆጫልም! ምናልባትም የእኛ ምሳሌ ኾኖ እርሱ ራሱ በአኗኗሩ እንዳይገስጸን እንመርምር!
ባሕራን ስሙን የወረሰው ከተገኘበት ባሕር የተነሣ ነው። ከባሕር ተገኝቶ የተገኘባትን ባሕር በስሙ ተሸክሟት ኖረ። ተወዳጅች ሆይ የተገኘንባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ተሸክመናት ይኾን? ወይስ አኹንም በላዩአ ተንሳፈን እየተጓዝን። ማለትም ተኝተንባት! ንስሓ ላይ ተኝተን፤ ቅድስና ላይ ተኝተን፤ ምጽዋዕት ላይ ተኝተን፤ ክብረ መላእክት ላይ ተኝተን፤ ፈቃደ እግዚአብሔርና ሕገ እግዚአብሔር ላይ ተኝተን የምንጓዘው እስከ መቼ?! ባሕራንን ባሕራን ብሎ የሰየመው የበጎች ጠባቂ እረኛ የነበረው አሳዳጊው ነው። ክርስቲያኖች የኾነውን እኛንም ክርስቲያን ያሰኘን ስለ እኛ የቅድስት ድንግል ማርያምን ፍጹም ሥጋና ነፍስ ነሥቶ በተዋሕዶ ሰው የኾነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ከእርሱ ፈቃድ መውጣት ክርስትናን ማጣት መኾኑን ልብ ይሏል።
ከዕለታት አንድ ቀን ባሕራን የጨካኙ ጎረቤታቸውን ሀብት ንብረት የሚወርስ መኾኑ በእግዚአብሔር መልአክ ተነገረ። ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ የባሕራን አባት ሞተ። ባሕራንም የባለ ጸጋውን ሀብት የሚረከብ መኾኑን ባለጸጋው እንዲያውቅ እግዚአብሔር ፈቀደ። ሀብቱ የተሰጠው እንዲጠቀምበት ነበራ! በእጃችን ያለው ገንዘብ እንደ እውነቱ ከኾነ እኛ ጋር ያስቀመጠው የእግዚአብሔር ነው። የተሰጠንን ቍሳዊ ሀብት በፍትሐዊነትና እግዚአብሔር በሚፈቅደው መንገድ ካልተጠቀምን የሚወሰድብን መኾኑን ልብ እንበል! አስተውሉ!እኛ ራሳችን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መኾናችን ከገባን ሀብት ንብረታችንማ እንዴት የእርሱ አይኾን! አብርሃምን ባለ ጸጋ ያደረገው በተሰጠው ነገር ኹሉ በቅንነት እግዚአብሔርን ማገልገሉ መኾኑን አንድም ከባለ ጸጋው ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምቶ መኖሩ መኾኑን ልብ ይሏል። ባለ ጸጋው ከባሕራን እናት ልጇን የሚንከባከብ መስሎ ተረከበው፤ ወደ ባሕርም በሳጥን አድርጎ አስወረወረው። ከዚያን ባሕራንን ባሕራን ባለው በግ ጠባቂ ባሕራን ባሕር ዳር ላይ ተገኘ። ባሕራንም ተባለ!
ከ20 ዓመት በኋላ ባለጸጋው መንገድ ሲሄድ ባሕራን ካለበት ድንገት ደረሰ። ከአሳዳጊው ታሪኩን ሲሰማ ቀድሞ ያስጣለው መኾኑን ተረዳ፤ የሞት ደብዳቤ አስይዞ ባሕራንን ላከው። የራሱን የሞት ደብዳቤ ይዞ የሚጓዘው ባሕራን ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ወደ ሕይወት ደብዳቤ ገለበጠለት። ብዙዎቻችን ባለማወቃችን ምክንያት የሞት ደብዳቤ ይዘን ወደ ሲዖል እንፈጥናለን። በጭካኔ፣ በጥላቻ፣ ባልተገባ ትችት፣ በሐሜት፣ በሌሎች ሰዎች ውድቀት በመደሰትና በመሳሰሉት የሞት ደብዳቤ ወደ ጥፋት እንፈጥናለን። የዕለት ዕለት የሕይወት መርሐችን ወደ ሞት የሚወስድ እንጂ ወደ ሕይወት የሚያደርስ አይመስልም። ምክንያቱም ዕለት ዕለት እንደ ምግብ ኃጢአትን እየደጋገምን እንፈጽማለንና። እንግዲህ መልአኩ የልቡናችንን ሐሳብ በምልጃው ባያቀናልን ኖሮ እየገሠገሠን ያለነው ወደ ዘረኝነት ሞት፣ ወደ ድንቁርናና ስንፍና ሞት፣ ወደ ቅናትና ትዕቢት ሞት መኾኑን ልብ እንበል!
ቅዱስ ሚካኤል በኃጢአታችን ምክንያት ወደ ተስፋ መቍረጥ የምንጓዘውን ከመንገድ ያግኘን። ከሞት አፋፍ በምልጃው ይታደገን። ወደ ሕይወት የምንገባበትን መልካም ሥራ በሰውነታችን ውስጥ ያለምልምልን። እንግዲህ ያ የባሕራንን ደብዳቤ የሚቀለበስልን በምንሠራው ሥራ አማካኝነት መኾኑን እንረዳ፤ ወደ ጽድቅ እንሩጥ፤ ከጥላቻ ሰውነታችንን እናላቅቅ! ጣዕሙ እጅግ ደስ የሚያሰኘውን የፍቅር ደብዳቤ ከልቡናችን መዝገብ አጽፈን፤ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንገሥግስ። በሕይወታችን ሊገጥሙን የሚችሉትን መሰናክሎች እኛ ባናያቸውም እንኳን መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ይለውጥልናል። ሕይወታችንን በለመለመ የውኃ መስክ አጠገብ የበቀለች ተክል አድርጎ ያሳምረዋል። እንግዲህ የባሕራን ደብዳቤ መነሻዋ ጥፋት መድረሻዋ ግን ሕይወት ኾኗል። አምላካችን እግዚአብሔርም በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ምልጃ የኃጢአት ደብዳቤያችንን ሰርዞ የጽድቅ ያድርግልን አሜን!

❤5
Forwarded from Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
የአፈና ዜና…
"…አቶ ዳንኤል ክብረት ቂም የያዘባቸው፣ በጦማሩ ሲጠቅሳቸው የከረመው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሰሜን ሜጫ ወረዳ ቤተ ክህነት ድል በትግል ቀበሌ የምትገኘው የፈለገ ብርሃን ናዳ ቅድስት ማርያም እና የክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም
አበምኔት የሆኑትን ታላቁ አራት ዓይናው የአራቱ ጉባኤ መምህር፥ የፍትሐ ነገሥቱ፣ የአቡሻኸሩ ሊቅና የቅኔው ጌታ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ ዛሬ ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ ወደ ገዳሙ ባቀኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለጥያቄ እንፈልግዎታለን ተብለው በወታደር አጀብ መወሰዳቸው ተነግሯል።
"…የአይን ምስክሮቹ እንደነገሩኝ ከሆነ መጀመሪያ ለአንዳንድ ጥያቄ እንፈልግዎታለን ብለው ወደ ቢኮሎ ዓባይ ወሰዷቸው። በዚያም አርበኛ ዘመነ ካሤን ካለበት ፈልገው ካላመጡት አንለቅዎትም በማለት በዚያ አዋሉአቸው፣ በመቀጠልም ከቢኮሎ ዓባይ አዙረው ወደ ዱር ቤቴ ወሰዷቸው፣ በዚያም መንፈሳዊ ልጅዎ ነውና አርበኛ ዘመነ ካሤን ይውለዱ ሲሏዋቸው ዋሉ ከዚያ ሲመሽ አሁን ምሽት ላይ ወደ ባህርዳር አምጥተው ባህርዳር በመከላከያ ካምፕ መኮድ ውስጥ እንዳሰሯቸው ተሰምቷል።
"…አቶ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም አስር ጊዜ የኔታ ይባቤ የኔታ ይባቤ እያለ የሚከሳቸው፣ የደቡብ ጎንደሮቹ አፍቃሬ ብአዴኖቹ እነ አያሌው መንበርም በተደጋጋሚ የሚዝቱባቸው አራት ዓይናው ሊቅ የኔታ ይባቤ በስተመጨረሻ በኦሮሙማው አገዛዝ እጅ ወድቀዋል። ቀጥሎ ምን ይሆናል? አብረን እናያለን። የክሱ መነሻም 7ተኛው ንጉሥ የአሕመድ ልጅ ሳይሞት አርበኛ ዘመነ ካሤን ለንግሥና ቀብተዋል የሚል ነው። ከዚህ ቀደም እስክንድር ነጋ ይነግሣል ተብሎ ደብረ ኤልያስ መውደሙ የሚታወስ ነው።
• ሻሎም…! ሰላም…!

❤1
አባታችን ሊቀ ብርሃናት የኔታ ይባቤ በላይ ለምን ታሠሩ?
የቅኔ፣የ፹፩ መጻሕፍት፣የአቡሻኽር፣የጥበባት መምህሩ፣
የናዳ ገዳም አበ ምኔት (አስተዳዳሪ)
ለበርካታ ዓመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ወንበር ዘርግተው ደቀ መዛሙርት አብዝተው ሲያስተምሩ የኖሩ እያስተማሩ ያሉ ናቸው።
እንደ አባትነታቸው ትጉኅ አበ ምኔት ናቸው መቆፈሪያ ይዘው ዕርፍ አርቀው ሞፈር ጠርቀው አርሰው ቀፍረው ትሩፋት ሠርተው ገዳም ገድመው የኖሩ የሚኖሩ አባት ናቸው።
እንደ ሰባኪ ዙረው የሚያስተምሩ እያስተማሩ ያሉ ሐዋርያ ናቸው።
የኔታ ይባቤ አይደለም መታሠር በወርቅ ወንበር ተቀምጠው ያስተምሩን የሚባሉ ረቂቅ ሊቅ፣ምጡቅ ባለ አእምሮ ናቸው።
ለየኔታ ይባቤ በላይ የማይሆን ፍትህ ምን አይነት ነው?
መምህራችንን አባታችንን ፍቱልን።
እኔም የየኔታ ይባቤ በላይ ልጅ ነኝ።
እሥራታቸው እሥራቴ፣መከራቸው መከራየ ነው።
አድባር የሆኑትን ትልቅ ሰው ማሠር ትልቅ ስህተት ነው።
ለሀገር ባበረከቱት፣የወንጌል፣የሰላም፣የልማት፣የቅኔ፣የሀገር በቀል ዕውቀት፣የአቡሻህር፣የአርአያነት አስተዋጽኦ ሽልማታቸው እሥራት እና እንግልት ሊሆን አይገባም።
ሊቁ አባታችንን ሲሸለሙ እንጂ ሲታሠሩ መስማት ትልቅ ዕዳ ነው።
ከገዳማቸው ሂዶ በየኔታ ይባቤ ተመክሮ ያልተጽናና፣ተገሥፆ ያልተረጋጋ፣ከመስቀላቸው ተባርኮ ከጸበሉ ተጠምቆ ዕረፍተ ህሊና ያላገኘ ሰው የለም ማለት ይቻላል።
የኔታ ያለ ውግንና የሁሉም መምህር፣የሁሉም አባት፣የሁሉም ዘር ቀለም ሳይለዩ አስተማሪ፣የሁሉም ፊት ደረት ሳይለዩ ገሥፆ መካሪ ናቸው።
እንዲህ ያሉትን የኔታችንን አባታችንን በክብር ወደ ገዳማቸውና ወደ ማስተማሪያ ወንበራቸው መልሱልን።
"ቢያድጥ ቢያድጥ ወደላይ ያድጣል?"
©የኔታ ገብረመድኅን እንየው

Forwarded from እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo Media
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኦርቶዶክሳውያን መከራ በየቦያው ነው ያለው ይህ የሶርያ ኦርቶዶክሳዊያን ናቸው ትናንት የተጨፈጨፉት
😢9❤1
Forwarded from ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ( Ethio Beteseb Media)
✏አሳዛኝ ዜና
👉በሸገር ሀገረ ስብከት ዓለም ገና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ቄስ ዮሐንስ ግርማ በዛሬው ዕለት ለቅዳሴ አገጋግሎት በሎሊት ወደ ቤተክርስቲያን እየሄዱ ባሉበት ወቅት ቤተክርስቲያኑ በር መግብያ ደጃፍ ላይ በጩቤ ማንነታቸው ባልታወቀ ተወግተው መገደላቸውን የመረጃ ምንጮች አድርሰውናል ፦
♣የአባታችንን ነፍስ ፈጣሪ ከቅዱሳኑ ጋር ይደምርልን ፣ ለቤተሰቡም መጽናናትን ያድልልን ፣
👉በዚህ አሰቃቂ ግድያ ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦችን ወይም ቡድኖች ፣ መንግሥት እንዲመረምር ፣ በሸገር ሀገረስብከት ስር እንዲህ ዐይነት ግድያቸው ቀጣይነት ሊኖራቸው እንደሚችል የመረጃ ምንጮቻችን አድርሰውናል ፣
👉 ምክንያቱም የሀገረስብከቱ ደገፊና ተቃዋሚ በሚል ቡድን እንደተለየ ፣ ብልሹ በሆነው የሀገረስብከት አሰራር ይህንን የሚቃወም ፣ ከቦታ ይነሳል ፣ ከስልጣን ይሻራል ፣ አልያም በቡድን ተቦዳድኖ በዚህ መልክ መጠፋፋቱ እንዳይነግስ ፣
👉በሀገረስብከቱ ላይ መልካም አስተደደር እንዲሰፍን ሲኖዶሱ ይችላሉ ፣የለውልጥ አባት ናቸው ብሎ የሾማቸውን አባ ሳዊሮስን በድጋሚ በሸገር ሀገረ ስብከት ምን እየሰሩ እንዳለ መጠየቅ አለበት እንላለን ፣ ቤተክርስቲያን አስተዳደር በቲፎዞ መምራት አይቻልም ።
👉ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም ድምፅ
ቤተሰብ ይሁኑ ፦ https://www.tgoop.com/ethiobeteseb

❤2
Forwarded from Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
የግድያ እና የአፈና ዜና…!
"…በፎቶው ላይ የሚታዩት ቄስ ዮሐንስ ግርማ የተባሉና በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ሀገረ ስብከት በሸገር ሀገረ ስብከት የዓለም ገና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ካህን ባለፈው ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ለአገልግሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ላይ ሳሉ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ደጃፍ ላይ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ በተባሉ ኃይሎች በጩቤ ተወጋግተው መገደላቸውን ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ዘግቧል።
"…በዚያው በሸገር ሲቲ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በሚያስተዳድሩት ሀገረ ስብከት የቦሌ አራብሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም የስብከተ ወንጌል ሓላፊ እና የአንድ ልጅ አባት የሆኑት መምህር ብርሃነ መስቀል የካቲት 16/2017 ዓም ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ ምንም ዓይነት መለዮ ባልለበሱና የፖሊስ ፓትሮል በያዙ በቁጥር ስምንት በሚሆኑ አፋኞች ታፍነው የደረሱበት ከጠፋ እነሆ አምስት ወር እንደሆናቸው ተነግሯል።
"…በተያያዘ ዜና በዛሬው ዕለት ከሥራ ቦታው የታፈነው መምህር ደረጀ ነጋሽ (ዘወይንዬ) ከዜናው መበተን በኋላ በስተመጨረሻ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ በሚገኘው የእስረኞች ማቆያ ውስጥ እንደሚገኝ የመረጃ ምንቼ አድርሰውኛል። የእስሩም ምክንያት መምህሩ በጤና ባለሙያዎቹ የደሞዝ ጥያቄ ዙሪያ በሠራው ቪድዮ ምክንያት በጠቅላይ ሚንስትሩ በአቢይ አሕመድ ቀጥተኛ ትእዛዝ ምክንያት ለምርመራ መወሰዱ ነው የፖሊስ ምንጮቼ የገለጹልኝ።
"… የሰኔ የደም ግብርም ያለእንከን እየተፈጸመ ነው። ከኦሮሚያና ከሸገር ሲቲም ካህናት መነኮሳትም እየጸዱ ነው። አቡነ ሳዊሮስ እና አቡነ ዲዮስቆሮስም ሥራቸውን አገዛዙን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እየፈጸሙ ይመስላል። የኔታ ይባቤም እስከአሁን ድረስ አልተፈቱም። እዚያው ባሕርዳር መኮድ ጨለማ ቤት እንደታሰሩ ነው።
• ማነህ ባለ ሳምንት…?

በሶሪያ የተጨፈጨፉት 22 የአንጾኪያ ኦርቶዶክስ ሰማዕታት ቀብር ተፈጸመ
በሶሪያ ቅዳሴ ላይ እያሉ የተጨፈጨፉት የ22 የአንጾኪያ ኦርቶዶክስ ሰማዕታት የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጽሟል። የእዚህን ዓለም ፈተና በድል አጠናቀቁ።
ይህ አሳዛኝ ክስተት ለአንጾኪያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሰማዕትነት ጉዞ የሚያጸና ነው