የዛሬው እለት ሁለቱ የክርስትና ከዋክብት፣ ሐዋርያቱ፣ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ የሚታሰቡበት እለት ነው፡፡
ሁለቱም ከዋክብት ሰማዕትነትን የተቀበሉት በሮም ከተማ ነበር፡፡ ዘመኑም በ64 ዓም አካባቢ ነው፡፡ ያ ዘመን የሮም ሥልጣኔ በዐለም ገናና የነበረበት ዘመን ነበር፡፡
ሁለቱ የክርስትና ከዋክብት ሰማዕትነትን እንዲቀበሉ ያደረጋቸው ኔሮን ቄሣር የተባለ ጥጋበኛ ንጉሥ ነበር፡፡ ምክንያት ያደረገባቸው ደግሞ ከፊሉ የሮም ከተማ በዚያው ዓመት በከባድ እሳት በመቃጠሉ ነበር፡፡ ከተማውን ያቃጠለው ራሱ ኔሮን ቄሣር ነው የሚሉ አሉ፡፡ በሌላ በኩል 'የድሆች መኖሪያ የነበረና የተጨናነቀ ሰፈር ስለነበረ በድንገት በተነሣ እሳት ወደመ' የሚሉም አሉ፡፡
ኔሮን ቄሣር ጠባዩ የዘመኑን አምባገነን ፖለቲከኞችን ይመስላል፡፡ ራሱ አቃጠለውም ቢሉ በተነሣ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ተቃጠለም ቢባል ኔሮን ተጠያቂ ያደረገው በጊዜው ይሳደዱ የነበሩትን የክርስቶስ ተከታዮችን፣ ክርስቲያኖችን ነበር፡፡ ይኸንን መሰለ አመክንዮ እና ድሆችን የኃጢአት ተሸካሚ፣ የመከራ ገፈት ቀማሽ ማድረግ ኔሮናውያን ለዓመታት ሲተገብሩት የሚኖሩት ፖለቲካዊ ስልት መሆኑ ያስገርማል፡፡ አሁንም ድረስ በኔሮናውያን ሲተገበር የምናየው ይኸው ስልት ነው፡፡
ኔሮናውያን 'ከተማውን ያቀጠሉት ክርስቲያኖች ናቸው፣ መሪዎቹ ደግሞ ጴጥሮስና ጳውሎስ ናቸው፣ ለአማልእክቶቻችንም መስገድን ይቃወማሉ፣ ለሮም ትውፊትም ተገዥዎች አይደሉም፣ የአምላካችንን ሥጋም እንበላለን ይላሉ፣ ስለዚህ ማሰቀያት፣ መግድ*ል፣ እና መ*ፍጨፍ አለብን' ብለው ክርስቲያኖችን በአንፊ ቲያትር ውስጥ ሳይቀር ለአናብስት ሰጧቸው፡፡ ቆዳቸውን ከእንጨት ጋር በማጣበቅ በሚስማር በመምታት ሁሉ ያሰቃዩቸው ነበር፡፡
ነገር ግን ያ ሁሉ መከራ ክርስቲያኖችን ሊያጠፉቸው አልቻለም፡፡ የነገሥታቱ ክፋትና አረመኔነት ክርስቲያኖችን የበለጠ አጠናከራቸው፡፡ ሰማዕታት ብርታት፣ ኃይል እየሆኗቸው፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ መከራውን እንዳይሰቀቁት በማድረግ ምድራዊ መከራን ሁሉ እንዲያሸንፉ አስቻሏቸው፡፡ ይኸም ኔሮናውያንን አላስተማራቸውም፡፡
እንዲያውም 'መሪዎቻቸውን በመግ*ል ተከታዮቻቸውን መበተል ይቻላል' በማለት ሁለቱን ከዋክበት ለሞት አበቋቸው፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስን በራሱ ምርጫ 'እንደ ጌታየና አምላኬ እየሱስ ክርስቶስ ልሰቀል አይገባኝም፣ ይልቁንም ቁልቁል ስቀሉኝ' ባለው መሠረት የቁልቁሊት ሰቅለው ገድለውታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስን ግን የሮም ዜግነት ስለነበረው ለዜጎቻቸው የተገባውን የሮማውያንን ቅጣት በመወሰን በሰይፍ ቀልተው ገድለውታል፡፡
ነገር ግን ኔሮንና ደጋፊዎቹ እንደጠበቁት የሁለቱ ከዋክብት መገደል ክርስትናን አላቆመውም፡፡ የሚያስገርመው ቅዱስ ጳውሎስንና ቅዱስ ጴጥሮስንም ከኢየሩሳሌም ወደ ሮም አምጥቷቸው የነበረው 'ክርስትናን ለመቅበር መሪያቸውን ክርስቶስን መስቀልና አዋርዶ መግደል' በሚል ሮማዊ ፈሊጥ የተደረገው ግፍ፣ አምላካቸው ሞትን ድል አድርጎ ትንሣኤን በማብሠሩና የምሥራቹም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይነገር ዘንድ ይገባው ስለነበረ ነው፡፡ የጠሉት ክርስትና ሮም ድረስ መጥቶ የራሳቸውን ወገኖች ሳይቀር ወረሳቸው ማለት ነው፡፡
ንጹሑን በግዕ በግፍ መግደላቸው ለውጥ አለማምጣጡን በኢየሩሳሌም ከተማ ያዩ ቄሣራውያን፣ ክርስትናን ለማጥፋት ቅዱስ ጳውሎስንና ተከታዮቹን ሰብስበው በሮም ከተማ ማስርና ማሰቃየት አልነበረባቸውም፡፡ መከራ ለክርስትና ታላቅ ዘር ነው፡፡ ሐዋርያት በሸንጎ መቅረብን ከደስታ ይቆጥሩት ነበርና መከራ ክርስትናን ሊያስቆመው እንደማይችል ማወቅ ነበረባቸው፡፡ አልሆነም፡፡ ኔሮናውያን ስሕተታቸውን ደጋገሙት፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በቄሣራውያን መታሰርን በደስታ ተቀበለው፣ የቄሣርን ቤተሰብም ሳይቀር ሰበከ፣ አሳመነ፤ ከቄሣርም ቤተሰብ ጭምር ክርስትናን ተቀበሉ፡፡ ቅዱሳንም ሆኑ፡፡ አይገርምም?
ቅዱስ ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ በላከው አስደናቂ መልእክቱ ይኸንን ደስታውን ለሚወዳቸው የፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ 4 ቁጥር 22 ላይ 'ቅዱሳንም ሁሉ፣ ይልቁንም ከቄሳር ቤተሰብ የሆኑ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል' በማለት ይነግረናል፡፡
ሊያሰቃዩት ያሰሩትንም ሰዎች ሳይቀር አሳምኖ ክርስቲያን አድርጎ በሌላ ቦታ ላሉ ክርስቲያን ወገኖቻቸው ሰላምታን የሚያቀርቡ አድርጓቸዋል፡፡ ከዋክብትነት ይኸ ነው፡፡ የክርስትና ትምህርት ይኸ ነው፡፡
ኔሮንና ቄሣራውያን ግን በክርስትና መሸነፈቸው ሲያናድዳቸው ክርስትናን ሊያጠፋው የማይቻለውን ይበልጥ የሚለመልምበትን መከራ ያበዙበታል፡፡ በሥጋዊ ሐሳብና በብስጭት ተነሣስተው መምህራንን በመግደል፣ መሪዎችን በማሰር ሊያጠፉት ይሞክራሉ፡፡
አልሆነም፣ በመጨረሻው ሮምም፣ ቄሳርም አበቃላቸው፣ ክርስትና ግን በሰማዕታት ደም ላይ የበለጠ እየጠነከረች፣ እየለመለመች ቀጠለች፡፡ 'ቤተ ክርስቲያንን የሲዖል ደጆች አይችሏትም' ያለው ራሱ አምላካቸን ነውና እስከ ዐለፍ ፍጻሜ ድረስ የሚሆነው እንዲያ ነው፡፡ ክርስትናን አላውያን ነገሥታት፣ ጨካኞች ቁማር በመቆመር ሊያስቆሙት፣ ተንኮል በመሸረብ ሊያጠፉት አይቻላቸውም፡፡
የእነዚህ ከዋክብት ሕይወትና ቅድስና የሚያስተምረን ይህንን ታላቅ እውነት ነው፡፡ ከዋክብቱን የቤተ ክርስቲያን ዐምዳ ወድዳ ያስባላቸው ይኸ ድንቅ አገልግሎታቸው ነው፡፡ ይኸንን ታሪካቸውን፣ ሰማዕታትነታቸውን በየጊዜው እንዘክረዋለን፣ የክርስትና ኑሮ ምሳሌም እናደርገዋለን፡፡ በዓመት አንድ ጊዜ ደግሞ በሰፊው በዐል ይደረግለታል፡፡
ሰማዕታቱ ታሳድዳቸው ለነበረችው ሮም ጌጧ ሆነውላታል፣ ከተማዋንም ክርስቲያኖች ከኔሮናውያን እጅ ወርሰዋታል፡፡ ያስተማሩት፣ የሞቱለት የክርስትና እውነትም ዐለምን አጥለቅልቋል፡፡ ስማቸውም በበጉ ደም ለዘላለም ተጽፎ ይኖራል፡፡
የሰማዕታቱ በረከት አይለየን!
መልካም በዓል፡፡
©ዶ/ር አረጋ አባተ

❤6❤🔥1
ሐምሌ 7 ተወልዶ ሐምሌ 7 ያረፈው
በአብርሃም ቤት እንግዶች ክብር ተመሥጠን ልደቱንና ዕረፍቱን ሳንዘክር እንዳንቀር የምንሰጋለት የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ሊቅና የድንቅ መጻሕፍት ደራሲ እጅግ ትሑት ድንቅ ባለ ቅኔ የሥነ ጽሑፍ ከፍታ ማሳያ የዜማ ሊቅ የምናኔ መገለጫ
በረከቱ ይድረሰንና ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ አለ
“ከልቦቻችን በማይነቀሉ የፍቅሩ ችንካሮች ተቸነከርን:: ያዝነው አንለቀውም እርሱም አቀፈን አልተወንም:: ወደ እርሱ በሃይማኖት አቀረበን:: ከእርሱም ወደ ቀኝ ወደ ግራ አንሸሽም:: እንደ ቀለበት በልባችን እንደ ማኅተም በክንዳችን አኖርነው:: እንደ ዕንቁ በልባችን ሳጥን አስቀመጥነው:: እንደ ወርቅ በሕሊናችን መዝገብ አኖርነው::
እንደ ግምጃ ለበስነው:: እንደ ሐር ግምጃ ተጎናጸፍነው:: እንደ ወታደር ሰይፍ ታጠቅነው:: ለጦር ዕቃ እንደተዘጋጀ የድል ጋሻ ተደገፍነው:: ተከዜና ግዮን በኢሎል ወር እንደሚሞሉ ፍቅሩ በልባችን መልቶአል:: እንደ መከር ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ እንደ ክረምት ጊዜም የጤግሮስ ወንዝ ስንዴ ሲያሹት እንደሚሆን እንደ ኤፍራጥስ ወንዝ ልባችንን በወንጌል ፈሳሽነት አረሰረሰው:: መርከባችንንም በሃይማኖት ወንዝ አስዋኘው" መጽሐፈ ምሥጢር 24:20
©ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

❤10
!!!✍️📢ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ያፈረሰ ጳጳስ አያስፈልገኝም ብሎ ከእንዲህ ዓይነቱ ሰው ቡራኬን፣ ቁርባንን ባለመቀበል ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅና ማስጠበቅ ይቻላል✍️📢.....!!!፡፡
++++++++++++++++++++
ሊቁ ቴዎዶስዮስ
ሊቁ ቴዎዶስዮስ የእስክንድርያ ፴፫ኛ ሊቀ ጳጳስ ነው፡፡ ክፉ ሰዎች ከንጉሥ ጋር መክረው ከመንበሩ አሳደዱት፡፡ በእርሱ ምትክም ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ ፈርመው ከነበሩት አንዱ የነበረው የእስክንድርያው ሊቀ ዲያቆናት አቃቅያኖስን ሾሙት፡፡ ቴዎዶስዮስም ፫ ወር ግርማኖስ በሚባል ሀገር ኖረ፡፡ ንቡረ እድ ሳዊሮስ በሐዋርያት፣ በአትናቴዎስ፣ በዮሐንስ አፈ ወርቅ የደረሰውን እየነገረ ያበረታው ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ መሊግ ወደሚባል ሀገር ሄዶ ፪ ዓመት ኖረ፡፡
የእስክንድርያ ሰዎች እረኛቸውን ቴዎዶስዮስን ፈልገው በመኰንኑ ላይ ተነሡበት፡፡ እሱም ቴዎዶስዮስን አስመጥቶ አቃቅያኖስን አባረረው፡፡ ንጉሡ ዮስጣቲያኖስና ንግሥት ታዖድራ ይህንን ሰምተው መጀመሪያ የተሾመው በሹመቱ ይቀመጥ ብለው ጻፉ፡፡ ፶፰ ካህናት ጉቃኤ አድርገው አስቀድሞ የተሾመ ቴዎዶስዮስ ነው ብለው ጻፉ፡፡ አቃቅያኖስም ክፉ ሰዎች አሳስተውኝ ነው በማለት ሹመቱን ለቀቀ፡፡ ሕዝቡም ከግዘት እንዲፈታውና ያለ ክህነት እንዲኖር ለመኑት፡፡ እሱም እንደ ለመኑት አደረገ፡፡
ንጉሡ ቴዎዶስዮስ በሃይማኖት የሚመስለው መስሎት ለእስክንድርያ መኳንንት በሃይማኖት የሚመስለን ከሆነ የእስክንድርያ መኰንን ይሆናል ካልተስማማ ግን ከሹመቱ ይሻር ብሎ ጻፈ፡፡ ቴዎዶስዮስም ይህንን ሰምቶ "ሰይጣን በበርሀ ጌታችንን ብትሰግድልኝ የዓለም መንግሥታትንና ክብራቸውን ሁሉ እሰጥሀለሁ" አለው ብሎ ከእስክንድርያ ወጥቶ ሄደ፡፡ ወደ ላይኛውም ግብጽ ሄዶ ሕዝቡን እያስተማረ ኖረ፡፡
ንጉሡም ከአንተ ዘንድ ልባረክ፣ እንድትመክረኝም እሻለሁ ብሎ አታልሎ መልእክት ላከበት፡፡ እሱም ወደ ቁስጥንጥንያ በሄደ ጊዜ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሕዝቡ፣ ሠራዊቱ ሁሉ ተቀበሉት፡፡ ንጉሡ ሲከራከረው ቢሰነብትም ሊቁ ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሰ ስለረታው እሱን ወደ ላይኛው ግብጽ አሳዶ ጳውሎስ የሚባለውን ሰው ሾመው፡፡ ጳውሎስ ወደ እስክንድርያ ከተማ በመጣ ጊዜ ሕዝቡ አልተቀበለውም፡፡ ዓመት ሙሉ ሲኖር ከእርሱ ማንም ቁርባን አልተቀበለም፡፡ ንጉሡም እስኪታዘዙለት ድረስ አብያተ ክርስቲያናት እንዲዘጉ አዘዘ፡፡ ምእመናን ግን ከእስክንድያ በመውጣት ከቅዱስ ማርቆስ፣ ከቅዱስ ቆዝሞስ፣ ከቅዱስ ድምያኖስ ቤተ ክርስቲያን ይቆርቡ ነበር፡፡ የክርስትና ጥምቀትም ይጠመቁ ነበር፡፡ ንጉሡ ይህንን በሰማ ጊዜ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ አዘዘ፡፡ አባ ቴዎዶስዮስ ይህንን ሰምቶ ንጉሡ እንዳያስታቸውና በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ መልእክት ጽፎ ሰደደላቸው፡፡ መላ ዘመነ ሹመቱ ፴፪ ሲሆን ፬ ዓመት በመንበሩ፣ ፳፰ ዓመት በስደት አሳልፏል፡፡ ብዙ ድርሳናትን ደርሷል፡፡ ምእመናን በያዕቆብ ያዕቆባውያን እንዲባሉ በስሙ ቴዎዶስዮሳውያን ተብለው ተጠርተውበታል፡፡ ዕረፍቱ በሰኔ ፳፰ ነው፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር)
©ምሥራቀፀሐይ ጉባኤ ቤት

አሁን እንዲህ ያለ አባትና እንዲህ ያለ ሕዝብ ነው የሚያስፈልገው፡፡ መሪዎች ፈቃዳቸውን የሚፈጽሙበት ተቋምም ሆነ ግለሰብ ሊኖረን አይገባም፡፡ አባቶች እንዲህ ዓይነቱን ነውረኛ አስተሳሰብ ሊጋፈጡ ይገባል፡፡ አባቶች ይህንን ማድረግ ቢያቅታቸው ሕዝብ ለሐሰተኛ ጳጳሳትና መነኰሳት ባለመታዘዝ ቤተ ክርስቲያንን ማዳን ይቻላል፡፡ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ያፈረሰ ጳጳስ አያስፈልገኝም ብሎ ከእንዲህ ዓይነቱ ሰው ቡራኬን፣ ቁርባንን ባለመቀበል ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅና ማስጠበቅ ይቻላል፡፡
©ምሥራቀፀሐይ ጉባኤ ቤት
❤7
Forwarded from Kesis Getnet Aytenew
መጽሐፈ ድጓ .pdf
155.7 MB
የጸበል ማስታወቂያዎች ላይ
--
አዳዲስ ቅዱሳት መካናትን ለማስተዋወቅ ወይም ነባሮቹን ለማግነን ሲባል ከጸበል ጋር ተያይዞ የሚተላለፉ መልእክቶችና ምስክርነቶች ጥንቃቄ ይፈልጋሉ። በተለይ እንደ ስኳር፣ ካንሰር፣ ኩላሊት፣ ጉበት የመሳሰሉ ሕመሞች ላይ። ታማሚዎቹ ድንገተኛ ሕክምና ቢያስፈልግ እርዳታ የማያገኙበት ሩቅ ቦታ ጎትጉቶ ወስዶ ከሰውም ከእግዚአብሔርም ከራሳቸውም ሳይሆኑ በፀፀት ሲያልፉ ታዝበናል። በልኩና በሥርዓቱ ይሁን።
--
እናስተውል!
1.ሁሉንም ሕመም ከሰይጣን ጋራ አናያያዝ።
2.ሕመም የሥጋ ለባሽነታችን መገለጫም ነው።
3.ታሞ መዳንና አለመዳን የግድ ከእምነት ጋር አይያያዝም።
4.የሕክምና ክትትልን፣ በተለይም የውስጥ ደዌን ከጸበል ጋር አስማምቶ ማስኬድ ይቻላል።
5.ሕክምና ለሥጋ ድካማችን የተፈቀደ የፈውስ መንገድ ነው፣ ሥራውም ላከበሩት ክቡርና ቅዱስ የአገልግሎት መስክ ነው። ከእምነትና ጸበል አይቃረንም። እንደ ተቋም ቤተ ክርስቲያን ሆስፒታልም ክሊኒክም አላት፣ ገና ይኖራታል።
--
ለሕሙማን ፈውስ ይስጥልን።
#ማስታወሻ:- ጽሑፉ በምወደው ወንድም አሳዛኝ ፍጻሜ ምክንያት የቀረበ ነው።
©በአማን ነጸረ

❤15🙏5
ቤተ ክርስቲያን ሲዘጋባቸው አሁን ደግሞ 'ለቦታው ቅርብ ሆቴሎች' በማለት እንደ እነ አስራኤል ዳንሳ በየሆቴሉ በመቁጠሪያ ሊደበድቡ ነው መሰል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ስም አልጠቀሱም፡፡
ካናዳ ሰዎችን ማስለፍለፍ የሚቻልበት ሆቴል መኖሩ ያስገርማል፡፡
መልአከ አንከርት ግርማ ሰዎችን ከማንከራተት ውጭ ሙያና መንፈሳዊነት የሌለው ነጋዴ ነው፡፡ ዐይነ ጥላ ሄኖክ ደግሞ ሀብታም እሆን ባይ ተለማማጅ አጭቤ ነገር ናት፡፡ ዐይነጥላዋ ራሷን ለመሸጥ አጃቢ ያስፈልጋታል፡፡ ባይሆን ግርምሽ ልጁን ረስቶታል፡፡
ከአሁን በኋላ እነዚህን ከንቱዎች ተከትሎ ለሚነጉድ ከረፈፍ ብዙም መጨነቅ አያስፈልግም፡፡ ተነግሮት፣ ተምሮ፣ ሐሰተኞች ናቸው ተብሎ አልሰማም ብሎ፣ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ዱርየዎችን መርጦ የሚሄድ ሕዝብ ካለ ገልቱና የማይጠቅም ስለሆነ ይብሉት፣ ይበዝብዙት፡፡
መከላከል ያለብን ይኸንን ወንጀል በቤተ ክርስቲያን ስምና አቅራቢያ እንዳይፈጽሙት ነው፡፡ ቤተ ክህነቱም እንደነ ደቤ የሚይዝባቸው ነገር ያለ ከሆነ ይያዝባቸው፡፡ ያኔ ከነገሩ የሌለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡
እኒህን ከንቱዎች ከሰው ለመለየትና ጠንቋይነታቸውን ለማጋለጥ ጥረት ለደረጋችሁ ክብር ይገባችኋል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች እንዲህ ቀስ በቀስ መነቀላቸው አይቀርም፡፡
ይኸው ነው፡፡
©አረጋ አባተ (ዶ/ር)

❤3👌3👍2
Forwarded from ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)
ጠብቁ
አብይ በሐረር፣ በባሌ፣ በከሚሴ፣ ሸገር ሲቲ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ሻኪሶ ሐላባ፣ ጅግጅጋ . ..ሙስሊሙን እርስ በርሱ አልያም ክርስቲያንና ሙስሊሙን ለማጨፋጨፍ አቅዷል።

ጾመ ፍልሰታ
የጾም ትርጕም
‹‹ጾም›› ማለት ‹‹ጾመ – ተወ፤ ታቀበ፤ ታረመ፤›› ካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ቃል ሲኾን የቃሉ ትርጕም ደግሞ ምግብ መተው፣ መከልከልና መጠበቅ ማለት ነው ፡ ጾም ጥሉላትን፣ መባልዕትን ፈጽሞ መተው፣ ሰውነትን ከመብልና ከመጠጥ እንደዚሁም ከሌላውም ክፉ ነገር ዅሉ መጠበቅ፣ መግዛት፣ መቈጣጠር፣ በንስሐ ታጥቦ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መቅረብና እርሱንም ደጅ መጥናት ማለት ነው፡፡
የጾም ሥርዓቱና ጥቅሙ
‹‹መላው ሕዋሳታችን ካልጾሙ የምግብና መጠጥ ጾም ብቻ ዋጋ የለውም፡፡ መጽሐፉም የሚለው ‹ወደ አፍ የሚገባ ሰውን አያረክስም፤ ከአፍ የሚወጣ እንጂ› ነው፡፡ ስለዚህ ዐይን፣ ጆሮ፣ እግርና እጅ የመሳሰሉት የስሜት ሕዋሳታችን መጾም አለባቸው፡፡ ከምግብና መጠጥ ይልቅ የሚበልጡት እነዚህ ናቸው፡፡ ከምግብና መጠጥ የምንቆጠበው በራሱ ኃጢአት ስለ ኾነ ሳይኾን ምግብና መጠጥ ሥጋን አጥግቦ በገደል ስለሚጥል ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ስለሚጎትት ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት እንዲቋረጥ ይደረጋል፡፡ ስንጾምም ከሐሜት፣ ከአሉባልታ፣ ከዝሙትና በሐሰት ከመመስከር፣ ወዘተ. መቆጠብ አለብን››
‹‹የጾም መሠረቱ ሃይማኖት ነው፡፡ በሃይማኖት የተነሣ ለተወሰኑ ጊዜያት ከምግብና ከመጠጥ የምንከለከልበት ኹኔታ ይኖራል፡፡ ነገር ግን ጾም ይህ ብቻ አይደለም፤ ሁለት ዓይነት መስመር አለው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአጽዋማት ወቅት ከምግበ ሥጋና ከኃጢአት ትከለክላለች፡፡ ከኃጢአት ዅልጊዜም እንከላከላለን፡፡ ከምግብ የምንከለከለው ምግብ ኃጢአት ስለኾነ ሳይኾን ከሃይማኖት የተነሣ ነው፡፡ ምግብ በልተን ፈቃደ ሥጋችንን ከምናደልብ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ሥጋችንን ጎስመን ያለ ምግብና ያለ መጠጥ እግዚአብሔርን እያመሰገንን የምንኖርበትን ሰማያዊና ዘለዓለማዊ ሕይወት የምናስብብት መንገድ ነው።
የጾም ዓይነቶች
ጾም የግል እና የዐዋጅ (የሕግ) ጾም በመባል በሁለት ይከፈላል፡፡ የግል ጾም ደግሞ የንስሐና የፈቃድ ጾም ተብሎ በሁለት ይከፈላል፡፡ የዐዋጅ (የሕግ) አጽዋማት ሰባት ናቸው፡፡ እነዚህም ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም)፣ ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)፣ ጾመ ገሃድ፣ ጾመ ነነዌ፣ ጾመ ድኅነት (ረቡዕ እና ዓርብ) እና ጾመ ፍልሰታ ናቸው፡፡ የዚህ ጽሑፍ መነሻም ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነው ጾመ ፍልሰታ ነው፡፡ ምክንያቱም አሁን ወቅቱ የፍልሰታ ጾም ስለኾነ፡፡
የፍልሰታ ጾም
ጾመ ፍልሰታን ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምን እንደ ኾነ እንመለከታለን፡፡ የፍልሰታን ጾም ሕፃን አዋቂው ሳይቀር በልዩ ሥነ ሥርዓትና በደመቀ ኹኔታ ይጾማል፡፡ አብዛኞቹ ምእመናን የዕረፍት ጊዜ በመውሰድ በገዳማትና በየአብያተ ክርስቲያናት ሱባዔ በመግባት ከነሐሴ አንድ ጀምሮ እስከ አሥራ አምስት ቀን ድረስ ጾም፣ ጸሎት በማድረግ ይቆያሉ፡፡ ጾም ጸሎት ሲያደርጉ ደግሞ በድሎት ሳይኾን በየዋሻው፣ በየመቃብር ቤቱና አብያተ ክርስቲያናት ዙሪያ እንጨት ረብርበውና ሳር ጎዝጉዘው ጥሬ እየበሉ ነው፡፡
ፍልሰታ ምን ማለት ነው?
‹‹ፍልሰታ ማለት ‹ፈለሰ – ተሰደደ› ከሚለው ግሥ የወጣ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››
፡ ‹‹‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡ ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡
ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡ እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡
የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?
የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?‹‹ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐሥራት አገር በመኾኗ እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡ ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው፤›› በማለት ያብራራሉ፡፡
የእመቤታችን በከረከት በሁላችን ላይ ይደር 🙏

❤4🙏2
Forwarded from ነገረ ቤተ ክርስቲያን፦ በዲያቆን ዘማርያም (ዘማርያም ዘለቀ)
2.pdf
16.6 KB
የእመቤታችን ዕረፍታ ወፍልሠታ በቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
❤2
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጀልባ መገልበጥ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖችን አስመልክቶ የተሰማውን ኀዘን ገለጸ።
ነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ የኃዘን መግለጫ፤
“እግዚአብሔር አምላከ ሕያዋን ያነሥአክሙ በትንሣኤሁ
የሕያዋን አምላክ እግዚአብሔር በትንሣኤው ያስነሳችኋል"
(ማቴ 22፡31 ሮሜ6፡5፤ቅዱስ ያሬድ) ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር በአርአያውና በመልኩ የፈጠረው የሰው ልጅ እሾህና አሜከላ ወደምታበቅለው ምድር፣ ጥሮ ግሮ ወጥቶ ወርዶ ወደሚኖርበት ዓለም ከመጣ ጊዜ ጀምሮ መከራ ሥጋን ማስተናገድ መጀመሩ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈ፣ በተግባርም የምንኖረው እውነታ ነው፡፡
የሰው ልጅ አካለ መጠኑ አድጎ ራሱን ማወቅ ሲጀምር ሕይወቱን ለማቃናት የተሻለ ኑሮ ለመኖር፣ ነግዶ ለማትረፍ፣ ዘርቶ ለማጨድ፣ በሀገሩም ሆነ በሌላው ዓለም ሠርቶ ለማግኘት ብዙ ጥረቶችን ያደርጋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ለተፈጥሮአዊና ለሰው ሠራሽ አደጋ መጋለጡ በሕይወቱ የሚያጋጥመው አሳዛኙ ክስተት ነው፡፡
ጥሮ ግሮ ፣ ወጥቶ ወርዶ ባፈራው ሀብቱ እና ንብረቱ ብቻ ሳይሆን ዳግም የማይተካ ሕይወቱንም ጭምር ለሚያጣው የሰው ልጅ በሕይወተ ነፍሱ ያለው መጽናኛ “የሕያዋን አምላክ እግዚአብሔር በትንሣኤው ያስነሣችኋል" የሚለው ሕያው ቃል ነው፡፡
የምንኖርበት ዓለም በብዙ ሥጋቶችና አደጋዎች የታጠረ በመሆኑ ዘመድ ወገን በሌለበት በባዕድ ምድር ሥጋችን ቢጣልም፣ በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቅን፣ ነፍሳችንም ሕያው ከመሆኗ የተነሣ ጠፍታ የማትቀር መሆኑን ስናስብ እንጽናናለን፡፡ ልንጽናናም ይገባናል፡፡
በቅርቡ ከሀገር ወጥተው በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ ወገኖቻችን የጀልባ መገልበጥ አደጋ ደርሶባቸው ሕይወታቸው በማለፉ ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰማው ኃዘን ጥልቅ መሆኑን እየገለጸ፣ በአደጋው ምክንያት ለሞቱት ኢትዮጵውያን ወገኖቻችን እግዚአብሔር ዕረፍተ ነፍስን እንዲሰጣቸው ፣ለቤተስቦቻቸውና ለወዳጆቻቸውም ሁሉ መጽናናቱን እንዲያድላቸው ይጸልያል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በክረምቱ ወራት በሁሉም አቅጣጫ በአንድ በኩል በመሬት መንሸራተትና በድንገተኛ ጎርፍ ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የዝናብ እጥረትን በመሰሉ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋ ችግር እየገጠማቸው ለሚገኙ ወገኖቻችን ፣ ሁሉም የሰው ልጆች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ/ም

❤3