Telegram Web
መልካም ዜና!

የኔታ ይባቤ ከእስር ተፈተዋል እግዚአብሔር ይመስገን

የባህር ዳር ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል ለአባታችን
12
#ሕንጸተ_ቤተ ክርስቲያን ዘእግዝእትነ ማርያም።
🍂የቤተ ክርስቲያን መታነጽ በእመቤታችን ስም #ሰኔ_21

🍂 #ጌታችን በዐረገ በስምንተኛው ዓመት ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ገብተው በክርስቶስ ስም አሳምነው ብዙ አሕዛብን ካጠመቁ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሊሠሩላቸው ወደዱ፡፡

በዚህ ጊዜ ርእሰ ሐዋርያት እያለ እኛ መሥራት አይገባንም ብለው በሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት ላኩበት፡፡ እርሱም ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር መጥቶ ከቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ በርናባስ ጋር በኢየሩሳሌም ተገናኙ፡፡

🍂 በዚያም በአንድነት ሱባዔ ይዘው ከቆዩ በኋላ ጌታችን የሞቱትን አስነሥቶ፣ ያሉትንም ጠርቶ ቅዱሳን ሐዋርያትን #በፊልጵስዩስ አገር ሰብስቦ ‹‹በእናቴ በድንግል ማርያም ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚሠራዉን የአብያተ ክርስቲያናት ሥራ ላሳያችሁ፤ ሥርዓቱንም ላስተምራችሁ ሰብስቤአችኋለሁ›› ብሎ ወደ ምሥራቅ ይዟቸው ወጣ፡፡

#በዚያም_ሥፍራ የነበሩትን ሦስት ድንጋዮችንም የተራራቁትን አቀራርቦ፣ ጥቃቅኑን ታላላቅ አድርጎ ቁመቱን በ፳፬፤ ወርዱን በ፲፪ ክንድ ለክቶ ለቅዱሳን ሐዋርያት ሰጣቸው፡፡

🍂 ከዚህ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ሰም እሳት ሲያገኘው እንዲለመልም፣ ድንጋዩ በእጃቸው ላይ እየተሳበላቸው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ሠርተው ፈጽመዉታል፡፡

#ሕንጻ_ቤተ_ክርስቲያኑ የተሠራዉም ጌታችን በዐረገ በ፲፱ኛው ፤ እመቤታችን በዐረገች በ፬ኛው ዓመት ሰኔ ፳ ቀን ሲኾን፣ በ፳፩ኛው ቀን (በማግሥቱ) ኅብስት ሰማያዊ፣ ጽዋዕ ሰማያዊ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ወረደ፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችን ጋር ከሰማየ ሰማያት መጥቶ እመቤታችንን ታቦት፤ ሐዋርያትን ልዑካን አድርጎ፣ እርሱ ሠራዒ ካህን ኾኖ ቀድሶ ካቈረባቸው በኋላ “ከዛሬ ጀምሮ እናንተም እንደዚህ አድርጉ “ ብሎ አዝዟቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡

( መጽሐፈ ስንክስራ የሰኔ 20 ፣ መጽሐፈ ግስ ወሰዋሰው)

ንጽሕት በድንግልና ፣
ሥርጉት በቅድስና
እመቤታችን ወላዲተ አምላክ
ከመከራ ስጋ
ከመከራ ነፍስ
ትሰውረን
🙏43
ዘ-ጋርዲያን በትግራይ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ሴቶች ላይ ዘግናኝ ወሲባዊ ጥቃት መፈፀማቸውን የሚገልጽ ሰፊ የምርመራ ሪፖርት አቀረበ‼️
በጦርነቱ ወቅት በትግራይ ከሚገኙ ጠቅላላ ሴቶች 10% የሚጠጉት ሴቶች ለጾታዊ ጥቃት መጋለጣቸውን ጥናቶችን ጠቅሶ ዘጋርዲያን አስነብቧል። ከነዚህ ውስጥ 70% በቡድን የመደፈር የደረሰባቸው ናቸው ብሏል።

እንደ ዘ ጋርዲያን ጥናት ሪፖርት የኤርትራ ወታደሮች አለም አቀፍ የጦርነት ህግ ከሚፈቅደው ውጭ የትግራይ ሴቶችን ዳግም መውለድ እንዳይችሉ በማሰብ በማህጸናቸው ውስጥ ባዕድ ቁሶችን መቅበራቸውን ከተጠቂዎች ማረጋገጥ ተችሏል።
ዘጋርዲያን አንዲት የፅናት ነው የምትባል ተጠቂ አናግሮ ነበር። በትግራይ ጦርነት ወቅት በኤርትራ ስድስት ወታደሮች ተደፍራ እራሷን ስታ ነበር። ፅናት ከመደፈሯም በላይ ኢ-ተፈጥሮአዊ ግፍ እንደተፈፀመባት በገለልተኛ ሀኪሞች መረጃ ተረጋግጧል።

ይህም በኤርትራ ወታደሮች በማህፀኗ የብረት ቁርጥራጭ፣ የማስታወሻ ወረቀት፣ ብሎኖች ብቻ የትግራይ ሴቶች ማህፀን ፍሬ እንዳያፈራ የሚያደርጉ ቁሳቁሶች በሴትነት ገላዋ በኩል  ወደ ማህፀኗ እንዲገባ ተደርጓል።

ይህ በፅናት ላይ ብቻ ሳይሆን በሺዎች በሚቆጠሩ የትግራይ ሴቶች ላይ የተፈፀመ አረመኔያዊ የወሲብ ጥቃት መሆኑን ሪፖርቱ ይገልፃል።
ሙሉውን ዘገባ ከስር ባለው ሊንክ ገብተው ያንብቡ👇👇
https://www.theguardian.com/global-development/2025/jun/30/sexual-violence-tigray-women-abuse-gang-rape-ethiopia-eritrea?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR7b4oO0CVacVI1Hbh9iOu9QeHvFp_HTwzNtyNu6qUh4N_sMfSM7tpDuQdD-aA_aem_D8a0JLsPn6xgr8lOej5LLA
===============
አዩ ዘሀበሻ
😢92
የሰላማ አባባሎች

+እኛ ኢትዮጵያውያን የጀግንነታችን ምልክት ሃይማኖታችን ነው፡፡

+ አሁን እናንተ ይህ የነገረ መለኮት ትምህርት እንዴት ይዋጥላችኋል ገና እኮ የምትበሉትንና የምትጠጡትን፣ የሚጠቅማችሁንና የሚጎዳችሁን ለይታችሁ የማታውቁ ሕፃናት ናችሁ፡፡ ምክንያቱም ማርና ወተት ከቤታችሁ አውጥታችሁ ሸጣችሁ አረቄ ገዝታችሁ የምትጠጡ ሰዎች ይህ የነገረ መለኮት ምግብነት ጠቀሜታማ እንዴት ይረዳችኋል፡፡


+ የሰው ልጅ ጽድቅ አስፓልት ሆኖለት ከሚመላለስበት ይልቅ እርሱ የኃጢአት አስፓልት ሆኖ አጋንንት እንዲመላለስበት ይመረጣል፡፡

+ ሰማይ የሚያክል እንጀራ ቢሰጥህ ቀና ብለህ የሰማዩን ከዋክብት ተመልከት፡፡

+ የሰው መውደቅ አምላክን እስከሞት አደረሰው

+ ገዳም መንፈሳዊ ሐኪም ቤትና መንፈሳዊ የጤና መኮንኖች መፍለቂያና ማሠልጠኛ ነው፡፡

+ የምናስተምረው ለአዋቂዎች ነው፡፡ አላዋቂና ሲሚንቶ የጠጣ መሬት አንድ ነው፣ ውኃ አይቋጥርም፣ ሁልጊዜ ደረቅ ነው፤ ለዚህ ምን ይሁን ተብሎ ያጠጡታል፡፡

+ አላስፈላጊ ኢትዮጵያዊነት በልብ መሸጥ ነው፡፡ ራስንም መለወጥ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ሕግ ውጭ የሆነ አሠራር ደግሞ _መጨረሻው የኋሊት መውደቅ ነው፡፡

+ ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚመጣ ሥልጣን ሁሉ የውርደት ሥልጣን ነው፡፡
72
Forwarded from Kesis Getnet Aytenew
ዐዲስ ፍልፈል አጥማቂ

ሰውየው ያልተማረ ጨዋ ነው። ክህነትም የለውም። የተማመነባት ጥንቆላውን ነው። አይዞህ የሚሉት የደብር ዐለቆችም አይጠፉም። መሣሪያው ገንዘብ ነዋ።

ይህ ሰው ጥንቆላውን የጀመረው በቸሪቱ ከተማ በሕገወጥ አጥማቂያን መፍለቂያ በዐዲስ አበባ ነው። የጀመረበት አጥቢያም በአያት ጣፎ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ነው። ቆሻሻ እንዳገኘ ዝንብ ግርርር የሚለው ወገናችን ይኸው ገና ከአሁኑ መከተል ጀምሯል። በተለይም እነ ወለተ ቡሩኮች ናቸው። ዝም ብሎ ሳያመዛዝኑ መከተልን ያውቁበታል።

እንዲህ ያሉ አጭበርባሪዎች የበዙት ሕዝቡ ተአምር ፈላጊ ዐመጸኛ ትውልድ ስለሆነ ነው። አትራፊ ቢዝነስ ስለሆነ ክህነት አልባው ጨዋ ሁሉ ጀመረው። ደግሞ ለማጭበርበር እንዲመቻቸው። "የንስሐና የቄደር ጥምቀት፣ የፈውስ አገልግሎት ጥሪ" ይሉልሃል። ሕዝቤም በቀጠሮ ሊፈወስ ጀርደድ ይላል።

ሰው እንዴት ክህነት በሌለው ጨዋ ምእመን ይጠመቃል? ቤተ ክህነቱም ሞቶ ቃብር ላይ ስለሆነ እንደዚህ ባለ ጉዳይ አይተነፍስም። አንዳንዶችም የጥቅም ተጋሪዎች ናቸውና አፋቸውም አዕምሯቸውም እስረኛ ነው። ሌቦች ናቸው።
2
+ ‘አቤል አቤል ስለምን ታሳድደኛለህ?’ +

ዘንድሮ ሐምሌ አምስትን የምንፈስከው በላምና በጊደር ፣ በበግ በፍየል ደም አይደለም፡፡ የዘንድሮ መግደፊያ በዕለቱ የሰማዕትነት ደሙን ባፈሰሰው በታላቁ ሐዋርያ በብርሃነ ዓለም በቅዱስ ጳውሎስ በራሱ ነው፡፡ በዚህ ዓመት ሐምሌ አምስትን የሐዋርያውን ዜና ሕይወት በልተንና ጠጥተን በንባብ ገበታ እንፈስካለን፡፡

ሐምሌ አምስት ገስግሰን ደማስቆ ላይ እንገናኛለን፡፡ ዲያቆን አቤል ካሣሁን ‘በዚህ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ፥ [በጳውሎስ ፍቅር] እያሰረ [በሃሳብ] ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ [የሚሆን ‘ቅዱስ ጳውሎስ’ የተሰኘ መጽሐፍን ይጽፍ ዘንድ] ከእርሱ [ከቅዱስ ጳውሎስ] ለመነ’ ተሳክቶለትም የቅዱስ ጳውሎስ የሕይወቱ ብርሃን በብዕሩ ላይ አንጸባረቀ፡፡

በመጽሐፉ እንደሚል የአቤል ደም እንደጮኸበት በሚነገረው በደማስቆ መንገድ የአቤል ብዕር ድምፁን ከፍ አድርጎ እየጮኸ ነው ፤ በእርግጥም በደማስቆ መንገድ ላይ ታላቅ ወንድሙን ቃየንን የሚከስስ ሳይሆን ታላቅ አባቱን ጳውሎስን የሚያወድስ የአቤል ብዕር ይጮኻል፡፡ መቼም ለሦስት ዓመታት ሙሉ በንባብ አሰሳ ጳውሎስን ሲፈልግ የነበረውን አቤል ቅዱስ ጳውሎስ ቢያገኘው ‘አቤል አቤል ስለምታሳድደኛለህ?’ የሚለው ይመስለኛል፡፡ በእርግጥም የጳውሎስ መገኛው ደማስቆ እንደሆነች የአቤል ደማስቆ ቅዱስ ጳውሎስ ሆኖለታል፡፡

ወንድሜ ዲያቆን አቤል ካሣሁን ቅዱስ ጳውሎስ ላይ ንባብና ምርምር ማድረግ ከጀመረ ሦስት ዓመታትን ደፍኖአል፡፡ ጳውሎስ ተጠርቶ ሦስት ዓመት በሱባኤ እንደዘገየ አቤልም ጳውሎስን ጠርቶ ሦስት ዓመት ይማጸነው ዘንድ ግድ ሆነበት፡፡ የብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ፍቅር በሚያስቀና መጠን ያደረበት አቤል ስለ እርሱ ማንበብና መጻሕፍትን መመርመር ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ በዚህ ምክንያት ከቅዱሱ ሕይወት ጋር በጣም ከመተሳሰሩ የተነሣ ስለ ሐዋርያው ሲያወራ በቅርበት ስለሚያውቀው አብሮ አደጉ የሚያወራ እንዲመስል አድርጎታል፡፡ በሐዋርያው ዙሪያ እጅግ በጣም ደክሞ ያዘጋጀውን ይህንን ብጥር መጽሐፍ ቀደም ብሎ ቢያወጣው እንኳን በቂ የነበረ ቢሆንም በሥራው ካለመርካትና ለጉዳዩ ክብር ከመሥጠት አንጻር ከድኖ ሲያበስለውና እየከፈተ ሲያማስለው ቆይቶአል፡፡

በክርስትና የታሪክ ጥናት ውስጥ እግዚአብሔር ምርጥ ዕቃው አድርጎ ብዙ ድንቅ ሥራውን የገለጠበትን ቅዱስ ጳውሎስን ማወቅ እጅግ ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ በማንም ሊተካ የማይችል ጉልሕ ሚና የተጫወተና የቤተ ክርስቲያንን የአገልግሎት ፍኖተ ካርታ ያሰመረ ሐዋርያ ነው፡፡ ‘እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ’ ያለውን ይህንን ሐዋርያ ሕይወት ማወቅም ክርስቶስንም ጭምር ለማወቅ እጅግ አንገብጋቢ ነው፡፡

ይህንን መጽሐፍ ባነበብኩበት ወቅት በእርግጥ ቅዱስ ጳውሎስን በዚህ ልክ ሳላውቀው እንዴት ቆየሁ? ይኼንን ጥቅስ እንዴት በዚህ መንገድ አልተረዳሁትም? የሚያሰኙ እጅግ በርካታ አዳዲስ እውነታዎችን አግኝቼአለሁ:: ልብ የሚነኩና መንፈሳዊ ተመስጦ ውስጥ የሚከትቱ ሃሳቦችና የቃለ እግዚአብሔርን ጣዕም የሚያቀምሱ አገላለጾች እዚህ መጽሐፍ ላይ ዘንበዋል:: ሌላው ቀርቶ የመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ የተጻፈውን ልብ የሚያቀልጥ ታሪክና ምሥጢር ያነበበ ሰው በዋናው ባለ ታሪክማ ምን ሊባል ይሆን ብሎ ነፍሱ በሐሴትም በጉጉትም እንድትናጥ የሚያደርግ ነው:: መጽሐፉን በማንበቤ ያገኘሁት ተደሞና መደነቅ ሌላው ሰው አንብቦ ምንኛ ይደሰትበት ይሆን? ብዬ እንድቸኩል አድርጎኛል::

መጽሐፉ ለማዘጋጀት የተደከመበትን ያህል ለማንበብ የሚያደክም መጽሐፍ አይደለም፡፡ በሥነ ጽሑፋዊ ውበቱና በአቀራረብ ግልጽነቱ ፣ በያዛቸው ተጓዳኝ መረጃዎች ሀብታምነቱ ደግሞ እውነትም የአቤል መሥዋዕት ሊባል የሚችል ከቃየናዊ ግዴለሽነት የጸዳ ለርእሱ የሚመጥን ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡ ለጥቃቅን እውነታዎች ሳይቀር ተጨንቆ የጻፈበትን ጥልቀት አንባቢ አይቶ የሚፈርደው ሲሆን ለርእሰ ጉዳዩ የሰጠው አክብሮት ደግሞ ‘አቤልም ከንባቡ በኩራትና ከስቡ አቀረበ’ የሚያሰኝ መሥዋዕት በማቅረቡ ‘የራሱን የማይረባ መሥዋዕት አቅርቦ በሥሙር መሥዋዕትህ ከሚቀና ከቃየናዊ ዓይን ይሰውርህ ፤ ‘ወደ ሜዳ እንሒድ’ ባዮችን ይያዝልህ’ የሚያሰኝ ሥራ ነው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስን በአራት መቶ በላይ ገጾች የሚያስነብበን ይህ ድንቅ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስን ለሚያጠኑ ክርስቲያኖች ሁሉ ትልቅ ማጣቀሻ ፣ ‘ይሄ ነገር የሐዋርያት ሥራ ትርጓሜ ይሆን እንዴ?’ ሊባል በሚያሰኝ ደረጃ ግብረ ሐዋርያትን አራግፎ የተጠቀመ ፣ ለቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት ደግሞ ለአንዳንዶቹ ክፍሎች ትርጓሜ ለአንዳንዶቹ ደግሞ መቅድም መሆን የሚችል መጽሐፍ ነው፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ወዳጆች ለጸሐፊው የተጻፈለትን በአበው ትምህርት የተፈተለ መወድስ ለመመረቅ ተዘጋጁ:: ሌሎቻችሁም ይህንን ድንቅ መጽሐፍ አንብባችሁ ከታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ጋር ዳግም በፍቅር እንድትተዋወቁ እጋብዛለሁ፡፡ ‘ማንበብን ለሚወዱት እንደ ጳውሎስም ለተጠሩት ይህንን መጽሐፍ ማንበብ ለበጎ ነው’

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሰኔ 29 2017 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
8
ከአመታት በፊት ባርሴሎና የሚባለው የስፔን እግርኳስ ክለብ ሶስት የሚገርሙ እጥቂዎች ነበሩት።እነኚህ አጥቂዎች ሜሲ ኔይማር እና ሱዋሬዝ ይባላሉ።በዛን ወቅት የነበርነው የባርሳ ወይም የተቀናቃኙ ክለብ ደጋፊዎች ይሄ ክለብ ሶስቱ ተጫዋቾች ከሌሉ ጨርሶ የሚፈርስ ክለቡንም የሚደግፍ ሰው ፈፅሞ የሚጠፋ ይመስለን ነበር።ባርሴሎና የሚባለው ክለብ ሶስቱ ተጫዋቾች ከመፈጠራቸው በፊት እንደነበረ ሶስቱ ባይኖሩም መኖሩ እንደሚቀጥል ረስተነው ነበር።
የሚገርመው ነገር ሜሲ ኔይማር እና Suarez ክለቡን ከለቀቁት አመታት ተቆጥረዋል። ሶስቱም ተጫዋቾች ክለቡን ከለቀቁት በኋላ የድሮ ዝናቸው እንጂ የፈጠሩት አንድም አዲስ ታሪክ አንድም አዲስ ነገር የለም ።እንደውም ባርሳ እያሉ በገነቡት ስም ነው ሁሉ ቀጣሪ የሚያገኙት።
ባርሴሎና ግን በአዳዲስ እና ወጣት ተጫዋቾች አሁንም ከከፍታው ማማ ላይ ተቀምጦ አለ።

©Koan AD እንደጻፈው
👏8😁4👍32🔥1🌚1
2025/08/24 12:04:43
Back to Top
HTML Embed Code: