Telegram Web
ነገ ቅዳሜ ጋድ ነው ይጾማል

እንዴት ይጾማል...?

ነገ ጥር 10 ቀን የጥምቀት ጋድ ነው፡፡ አባቶቻችን እንዳይረሳ ጥምቀት ረቡዕ ወይም ዓርብ ሲውል ብቻ ሳይሆን ሁሌም በየዓመቱ  እንዲጾም ወስነዋል፡፡ ከሰባቱ አጽዋማት ገብቶ መቆጠሩም ለዚህ ነው፡፡

ቅዳሜ (ቀዳሚ ሰንበት) ባይሆን እስከ ምሽት አንድ ሰዓት ጾሙ ይቆይ ነበር፡፡ እናቶች በጥምቀተ ባሕሩ ተገኝተው "የጥምቀት እራት" እያሉ ታቦት አክባሪ ካህናትን መመገባቸው ለምን እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡

ግን ዘንድሮ ቅዳሜ ጋድ በመሆኑ እንደ ዐቢይ ጾም ቅዳሜ ከጥሉላት መባልት (ሥጋ፤ ቅቤ፤ ወተት...) እንከለከልባታለን.... (ስንክሳር ጥር 10)

መልካም በዓለ ጥምቀት ይሁንላችሁ።
👍5
የ2017 ዓ.ም የከተራና ጥምቀት በዓላትን ለምትዘግቡ ሚዲያዎች በሙሉ።
በበዓሉ በሁሉም ቋንቋ ቃለ መጠይቅ እንዲሰጡና መልዕክት እንዲያስተላልፉ ከታች ስም ዝርዝራቸው የተገለጸ ሊቃውንት የተመደቡ መሆኑን እየገለጽን; በጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ባልደረቦች ሁነቱን የሚያስተባብሩ መሆኑን እናስታውቃለን።
መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
Forwarded from Meseret Media
በጥምቀት በዓል መዳረሻ በርካታ ወጣቶች በአዲስ አበባ ከተማ እየታፈሱ መሆኑ ታወቀ

(መሠረት ሚድያ)- በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ስፍራዎች በተለይ በደማቁ የጥምቀት በአል ወቅት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቁ ወጣቶች እየታፈሱ መሆኑ ታውቋል።

መሠረት ሚድያ የደረሰው መረጃ እንደሚያሳያው እንደ ሽሮ ሜዳ፣ ፈረንሳይ፣ ካዛንችስ፣ ሳሪስ፣ አዋሬ ወዘተ ባሉ ስፍራዎች የሚገኙ ወጣቶች በብዛት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው።

ሽሮ ሜዳ አካባቢ ትናንት ማታ ከ30 በላይ ወጣቶችን የሽሮ ሜዳ ፖሊስ አፍሶ እንደወሰዳቸው የአይን እማኞች ተናግረዋል። ወጣቶቹ የቤተክርስቲያን ጥምቀት አስተባባሪዎች እና ምንጣፍ የሚሸከሙ ልጆች መሆናቸው ታውቋል።

በሌላ በኩል በዛሬው እለት ሳሪስ አዲስ ሰፈር እና ብሄረ ፅጌ አካባቢ ለጥምቀት በአል የተሰቀሉ ማስዋቢያዎችን ፖሊስ በሀይል ያነሳ ሲሆን ሰቅላችኋል የተባሉ አንዳንድ ወጣቶችም እንደታሰሩ ታውቋል።

ከዚህ በፊት በየመንገዱ የሚሰቀሉ እና የኦርቶዶክስ አርማ ያለበት ባንዲራ ጭምር በፖሊስ በበርካታ ስፍራዎች እንዲወርድ እየተደረገ መሆኑን ሰምተናል።

ማምሻውን ከፖሊስ ምላሽ ለማግኘት ያረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ፎቶ: ፋይል

መረጃን ከመሠረት!

@MeseretMedia
👍2
Forwarded from Ashebir abdo
+ + ያን ጊዜ #ኢየሱስ_በዮሐንስ ሊጠመቅ + + ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።

#ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል
አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር።

#ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤
እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው።
ያን ጊዜ ፈቀደለት።

ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤
እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ
እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤

እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦
#በእርሱ_ደስ_የሚለኝ_የምወደው_ልጄ_ይህ_ነው_አለ

( ማቴ 3 ፥ 13 -17 )

🙏🏽 እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ 🙏🏽

ሠዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት
👍2🕊1
-በሀዲያ ዞን የሚገኙት የጊንብቾ ከተማ ኦርቶዶክሳውያን ለከተራና ጥምቀት በዓል ማክበሪያ ቦታ አንሰጥም ስለተባሉ ጥቁር ለብሰው ተቃውሞ በመግለጽ በሐዘን እንዲያከብሩ ተገደዋል። የሀድያ ዞን ካድሬዎች በተሳሳተ ትርክት "ጨቋኝ ነበሩ" በሚል የተፈረጁ አካላትን በዚህ ዘመን መጨቆን ተራችን ነው የሚሉ ይመስላል። መፍትሔ ለመስጠት እጅግ ቀላል ነገር የሆነውን ሁሉ የሚያወሳስቡት ሆነ ብለው ነው። በሐሰት ትርክት በትንሽ በትልቁ የመጨቆን ተረኝነት ይውደም!

-እንኳን አደረሰን።
1
+ ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ +
(Posted upon request)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታቦታት ላይ የተጻፈው ምንድር ነው? ተብለው ቢጠየቁ መልስዎ ምን ይሆን? ‹ዐሥርቱ ትእዛዛት ተጽፈዋል› ካሉ መልስዎ ትክክል አይደለም፡፡ ትክክለኛውን መልስ ከመመልከታችን በፊት ጥቂት ነገሮች ስለ ታቦት እንመልከት፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ ታቦት አስፈላጊነት በሚሠጡ ማብራሪያዎች ላይ ሰፊውን ቦታ የሚይዘው ስለ ብሉይ ኪዳን ታቦት የሚናገሩ ጥቅሶችን በመጥቀስ በመሆኑ ምክንያት ስለ ታቦት የሚነሡ ጥያቄዎች እንዳያቋርጡ ያደረገ ይመስላል፡፡ ስለዚህ በዚህች አጭር ጽሑፍ ‹ነገርን ከሥሩ› የሚለውን አካሔድ ሳንከተል በቀጥታ ስለ ሐዲስ ኪዳን ታቦት ብቻ እንመለከታለን፡፡

ታቦት በሐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጌታችን በመጨረሻዋ ምሽት ሐሙስ ምሥጢረ ቁርባንን ባስተማረ ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱ በተሰበሰቡበት ‹‹እንጀራውን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ሠጣቸው እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ እንካችሁ ጠጡ ይህ ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው አለ›› (ማቴ. 26፡26) ጌታችን አስቀድሞ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ብሎ በትምህርት የመሠረተውን ምሥጢረ ቁርባን በተግባር ለሐዋርያቱ በዚህ መልኩ አስተማራቸው፡፡ (ዮሐ. 6፡56) ሐዋርያቱም ከጌታችን ዕርገት በኋላ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹እንጀራውን በመቁረስ ይተጉ ነበር›› (ሐዋ.2፡42) ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ ሠጥቻችኋለሁ›› በማለት ሥጋ ወደሙን እንዴት መቀበል እንደሚገባና ‹ሳይገባው የሚቀበል የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ›› እንዳለበት በማስተማር የቁርባንን ሥርዓት ደነገገ፡፡ (1ቆሮ. 11፡23-30)

ልብ እንበል የክርስቶስ ሥጋና ደም መሠጠቱን የሚያምን አንድ ክርስቲያን ይህ የከበረ ሥጋና ደም እንደ ተራ ማዕድ በየቦታው ፣ በየጠረጴዛው ሊቀርብ ይችላል ብሎ ለማሰብ እጅግ ይከብደዋል፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ስደትዋ እስካበቃበት ዘመን ድረስ በሒደት እየተሻሻለ በመጣ የቤተ መቅደስ ሥርዓት የሐዲስ ኪዳኑን መሥዋዕት በክብር ለመሠዋትና ለምእመናን ለማቀበል በቅታለች፡፡ የበግና የፍየል ደም ይሠዋ በነበረበት የኦሪት ዘመን እንኳን ለብቻው ትልቅ መሠዊያ ተዘጋጅቶ ፣ መሠዊያው ተቀድሶ ሰው በማይገባበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉት አሮንና ልጆቹም የተለየ ልብስ ለብሰው የበጉን ደም በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ቀርነ ምሥዋዕ (የመሠዊያ ቀንድ) ላይ እየቀቡ ሥርዓቱን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ለበግና ለፍየል መሥዋዕት ይህ ሁሉ ክብር ከተሠጠ እንደ በግ ስለ ሁላችን ኃጢአት ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው የእግዚአብሔር በግ ፣ እንደ ሊቀ ካህናትነቱ እጁን በመስቀል ላይ ዘርግቶ የተሠዋውና ሥጋና ደሙን እንካችሁ ብሉ ብሎ የሠጠን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት መሠዊያ ምንኛ የከበረ ይሆን?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥጋ ወደሙ ‹መሠዊያ› የምትለው ታቦት በቅርጽም ፣ በአገልግሎትም ፣ በክብርም በኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ ከሠጠው ታቦት ጋር አንድ አይደለም፡፡ የቀደመው ታቦት በአራት ካህናት የሚያዝ በውስጡ ጽላት የሚቀመጥበት ሲሆን የአሁኑ ታቦት ግን የጽላት ቅርጽ ያለው ጽሌ (ሰሌዳ) ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሐዲስ ኪዳኑን ታቦት በሦስት ስያሜ ትጠራዋለች - የቃልኪዳኑ ታቦት ፣ ጽላት እና መሠዊያ ብላ፡፡ የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስላደረገው ስለ ቀድሞ ቃልኪዳን ሳይሆን ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ተብሎ ስለተሠጠው እና ‹‹ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› ብሎ ጌታችን ስለ ሠጠን አዲሱ ኪዳን ነው፡፡ (ማቴ. 26፡26-30) የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው በሥጋ ወደሙ ስለተሠጠን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ታቦት መባሉ ደግሞ እግዚአብሔር በረድኤት የሚያድርበት ፣ በሥጋ ወደሙ ደግሞ በአካል የሚገለጥበት ዙፋን ስለሆነ ነው፡፡

ጽላት (ሰሌዳ) የሚባለው ዐሠርቱ ትእዛዛት ተጽፈውበት አይደለም፡፡ የሕግ ሁሉ ፈጻሚ የሆነው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የከበረ ስሙ በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን /ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ/ ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ/)

አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡

ሌሎች ደግሞ "በበዛችሁም ጊዜ በምድርም ላይ በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን፦ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት፡ ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም፤ ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም:" የሚለውን ጥቅስ ለአሁኑ ታቦት አለማስፈለግ ሊጠቅሱ ይሞክራሉ:: (ኤር 3:16) ይህ ቃል ግን እስራኤል የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው የሚጠሩት የኦሪቱ ታቦት ለእነርሱ አገልግሎት መሥጠት እንዳቆመና እግዚአብሔርም ከሕዝቡ ጋር አዲስ ቃል ኪዳን እንደሚገባ የሚያስረዳ ነው:: አሁን የምገለገልበት ታቦት የቀደመው ቃልኪዳን ታቦት ሳይሆን "ይህ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው" ብሎ በደሙ አዲስ ኪዳን የሠጠበትን ሥጋውንና ደሙን የምንቀበልበት የአዲስ ኪዳን ታቦት ነው:: አዎ እስራኤል የቀደመውን ታቦት አይሹትም ዐሠርቱ ትእዛዛት ያለበት የቃልኪዳን ታቦትም ከእንግዲህ ወዲህ አይደረግም:: እኛ ያለን አዲስ ኪዳን በስሙ የተጠራበት የክርስቶስ ቃልኪዳን ነው::

የኦሪቱን ያልመሰለው አሁን ያለነው ሐዲስ ኪዳን ላይ ስለሆነና የታቦቱ አገልግሎት የተለየ ስለሆነ ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦ ት ከቀድሞው አንድ ታቦት ተለይቶ በቁጥር የበዛውም ለብዙዎች መድረስ ያለበት የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚፈተትበት መሠዊያ ስለሆነ ነው፡፡ መድኃኒት ቤት የሚበዛው መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሲበዙም አይደል? ታቦት የበዛው በታቦቱ የሚሠዋው መሥዋዕት ለብዙዎች ስለ ኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰውና ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻው ያለሱ ሕይወት የላችሁም የተባልነው ሥጋና ደሙ ለኃጢአት በሽተኞች ስለሚያስፈልገን ነው::

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ ‹‹የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡ ይህ ግን (የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት) የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት (ጌታችን) ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊያ) ነው፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው፡፡›› (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 109) ሌላው አስገራሚ ነገር አቡነ ጎርጎርዮስ በታቦት ሥርዓት ከግሪኮች አንዲሚስዮን ጋር እንደምንመሳሰል ጠቅሰው ሲጽፉ ግሪኮቹ ደግሞ ስለ አንዲሚስዮን ሲያብራሩ ከኢትዮጵያ ታቦት ጋር የሚመሳሰል ብለው መጻፋቸው ነው።
1
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ. 2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል፡፡ ሥጋ ወደሙን ‹‹ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያከብር አንጠብቅም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡

የታቦቱ ሌላ መጠሪያ የመሠዊያ ታቦት (ታቦተ ምሥዋዕ) የሚል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ መሠዊያ ‹‹መሠዊያ አለን በድንኳኒቱ የሚያገለግሉ ከእርሱ ሊበሉ መብት የላቸውም›› በማለት ስለ ሐዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ይነግረናል፡፡ (ዕብ. 13፡10) ይህ መሠዊያ በኦሪት ድንኳን የሚያገለግሉ የአሮን ልጆች ከእርሱ ሊበሉ መብት የሌላቸው ለእኛ ክርስቲያኖች ብቻ በመሠዊያው ያለውን ሥጋና ደም እንድንበላ የተሠጠን ታቦተ ምሥዋዕ (Christian Alter) ነው፡፡ እነርሱ ቤተ እስራኤላውያን ነቢዩ እንደተናገረው "ከእንግዲህ አይሹትም የቃልኪዳኑ ታቦት ብለውም አይጠሩትም" ለእኛ ለአዲስ ኪዳን ልጆች ግን የተሠጠን የሥጋ ወደሙ ቃልኪዳን ነውና ዘላለማዊ ነው::

የታቦትን የሐዲስ ኪዳን አገልግሎት ስንናገር የሚቃወሙ ሰዎች ከሚያነሡት ተደጋጋሚ ትችት ‹‹አንዱ ታቦት ያላት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት›› የሚል ነጥሎ የመምታት ጥረት ነው፡፡ በተለይም የግብፅ ቤተ ክርስቲያንን በመጥቀስ ‹‹ግብፆች ታቦት የላቸውም›› የሚል ንግግር ይዘወተራል፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛ መልስ ከምንሠጥ የራሳቸው የግብፃውያንን ምላሽ ብቻ ማስቀመጥ ይቀልለናል፡፡ ግብፃውያን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጋር አቻ የሆኑ ሁለት ንዋያተ ቅድሳት አሏት፡፡ አንደኛው የመሠዊያው ጽላት (ሰሌዳ) /Alter Board/ ሲሆን ሁለተኛው ታቦት /Ark/ ነው፡፡
ቄስ ታድሮስ ማላቲ የተባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅ ጸሐፊ ‹‹Church The House of God›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ስለ የመሠዊያው ሠሌዳ (Alter Board) አሠራር ሲናገሩ ‹‹ይህ የመሠዊያ ጽላት አንድ መስቀል ወይም ብዙ መስቀሎች ይሳሉበታል ፤ አልፋና ኦሜጋ ተብሎ ይጻፍበታል ፤ ከዚያም መዝ. 86፡1 ላይ ያለው መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ቃል ይጻፍበታል፡፡›› ይሉና ስለ አሠራሩ ሲናገሩ ‹‹የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መሠዊያው ስለሚሠራበት ቁስ የተደነገገ ሕግ የላትም ፤ እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ከእንጨት ብቻ ይሠራ ነበር፡፡ ከዕብነ በረድና ከድንጋይም ሊቀረጽ ይችላል፡፡›› ይህንን ካሉ በኋላም እግረ መንገዳቸውን ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ምሥዋዕ ሲናገሩ ‹‹ከእንጨት የሚሠራ ታቦተ ምሥዋዕ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሥጠቱን ቀጥሏል›› (Wooden Alters continue in use in the Ethiopian Church at the present time) ብለው ያጠቃልላሉ፡፡

ይህ ስለ መሠዊያ እንጂ ስለ ታቦት አይናገርም፡፡ ስለ ታቦት ደግሞ እኚሁ ጸሐፊና በቤተ ክርስቲያኒቱ ኦፊሴላዊ ድረ ገጾች ላይ የሚከተለው ተጽፎአል፡፡ ‹‹In the middle of the Alter, there is a wooden box, called in Coptic 'pi totc' which means 'a seat' or 'a throne', and is used as a Chalice-Stand. Usually it is cubicle in shape, about thirty centimetres high and twenty-five centimetres wide, the top is closed with high flaps. The beautiful carving is inlaid with ebony and ivory and is decorated with four small icons. It can be only the Lord in the last supper, St Mary, Archangel Michael, St. Mark and then the patron Saints.

It is called 'the Throne' for it represents the presence of the Crucified Lord. Its name also corresponds to the 'Ark of the Old Testament', for it contained the Tablets of Law written with the finger of God to declare God's covenant with man. The new Ark now contains the true Blood of Christ, as the New covenant, that fulfils the Law and the prophets.›› (‹‹ከመሠዊያው መካከል የሚቀመጥ የእንጨት ሳጥን ሲኖር ይህ በኮፕት ቲቶት ተብሎ የሚሠራ ሲሆን ትርጉሙም ‹መንበር› ወይም ዙፋን ማለት ነው፡፡ ጽዋው የሚቆመውም በዚህ ላይ ነው፡፡ ቅርጹ ክበባዊ ሲሆን 13/25 ሴንቲሜትር ነው፡፡ ከላይ በጨርቅ ይሸፈናል፡፡ በጥቁርና ነጭ ኽብረ ቀለማት ያጌጠ ሲሆን አራት ሥዕላት በዙሪያው ይደረጋሉ፡፡ ሥዕላቱ የጌታችን ጸሎተ ሐሙስ ሥዕል የእመቤታችን ፣ የቅዱስ ሚካኤልና የሚታሰበው ቅዱስ ሥዕላት ናቸው፡፡

‹ዙፋን› ተብሎ የሚጠራው የተሰቀለው ጌታ እንደሚያድርበት በማሰብ ነው፡፡ ይህ ስያሜም ‹ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት› ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ያ ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ቃልኪዳን የተጻፈባቸው የሕግ ጽላት ያሉበት ነበር፡፡ አሁን ያለው አዲሱ ታቦት ግን እውነተኛውን የክርስቶስ ደም የያዘ ሲሆን ክርስቶስም ሕግንና ነቢያትን ፈጽሞ አዲሱን ኪዳን የሠጠን ነው፡፡››) ይህ ማብራሪያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስለ እኛ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከሠጡት ማብራሪያ ጋር ምንም አይለያይም፡፡ ይህን እንደ ማሳያ ጠቀስን እንጂ ታቦቱ ዑደት ባለማድረጉ እና በሥርዓቱ ይለያያል እንጂ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሥጋ ወደሙ መሠዊያ ነው ብላ ከምታከብረው ታቦት ጋር በክብርና በአገልግሎት አቻ የሆኑ በቅብዐ ሜሮን የሚከብሩና በመንበር የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡

ባለንበት ዘመን በሥጋ ወደሙ እውነተኛነት ከማያምኑ ሰዎች ጋር ስለ መሠዊያው አስፈላጊነት በመከራከር ብዙ ጊዜ ሲባክን ይታያል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጻፈበትን ታቦት ‹ጣዖት› ነው የሚሉ ‹ክርስቲያኖች› እያየን እንደነቃለን፡፡ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከክ›› ተብሎ የተጻፈበት ‹ጣዖት› እንዴት ይኖራል? ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚል ጣዖት አለ? ወንጌል በላዩ ላይ የተቀመጠበት ፣ በቅብዐ ሜሮን የከበረ ፣ ሥጋ ወደሙ የሚፈተትበት ታቦት እንዴት ጣዖት ተብሎ ይጠራል? አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ በሥላሴ ስም የሚቀደስበትን ታቦት ባዕድ አምልኮ ለማለት መድፈር እንዴት ያስደነግጣል፡፡
👍1
አንዳንዶች ‹ታቦት ተሰርቆ ተሸጠ› የሚሉ ዜናዎችን በማራገብ ታቦቱ ኃይል የለውም ሊሉን ይሞክራሉ፡፡ እንኳን የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ቀርቶ ራሱ ክርስቶስ በሠላሳ ብር ተሸጦ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እየተተፋበት ፣ እየተደበደበ ተጎትቶ ተሰቅሎ የለምን? ክብር ይግባውና ኃይል የለውም ሊባል ይችላል? ‹‹ታቦቱን ገልጠን እናሳያለን›› ብለው እየፎከሩ ቤተ ክርስቲያንን ያዋረዱ የሚመስላቸው ፣ በታቦቱ እግዚአብሔርን የምታመልከውን ቤተ ክርስቲያን ታቦት ታመልካለች ብለው ያላለችውን በግድ ብላለች ብለው ድርቅ የሚሉ ሰዎች ስናይ ከማዘን ውጪ ምን እንላለን? ቤተ ክርስቲያን ታቦትን የምትሸፍነው ስለሚሠዋበት የጌታችን ሥጋና ደም ክብር እንጂ ቢገለጥ የምታፍርበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ ቢገለጥ የሚታየው የመድኃኔዓለም ክርስቶስና የቅዱሳኑ ስም ነው፡፡ ጌታዋ ዕርቃኑን በመሰቀሉ ያላፈረች ቤተ ክርስቲያን ስሙ በተጻፈበት ታቦት አታፍርም!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 10 2009 ዓ ም
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ::
6
“እንኳን ለጥምቀት ለቅዱስ ሚካኤል በዓል አደረሳችሁ!”

የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል በዓል

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥር ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፡፡ በዚች ቀን እስራኤል ወደ ተባለ ያዕቆብ እግዚአብሔር ልኮታልና ከወንድሙ ከኤሳውም ፈርቶ ሳለ አዳነው፡፡

ዮርዳኖስንም አሻግሮት ወደ እናቱ ወንድም ወደ ላባ ሔደ፡፡ እርሱም ሁለቱን ልጆቹን ልያንና ራኄልን አጋባው ከዚህም በኋላ ከብዙ ገንዘቡና ከልጆቹ ጋር መንገዱን እየጠረገና እያቀና በሰላም በጤና ወደ አገሩ መለሰው ወንድሙ ኤሳውም በፍቅር በሰላም ተቀበለው ስለዚህም የሊቀ መላእክት ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን፡፡

ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር ጥር 11 ቀን
🙏5👍1
የጎንደር ከተማ አስተዳደር የቤተክርስቲያኗን የ75 ዓመታት ጥያቄ መለሰ

#Ethiopia | በጎንደር ከተማ የሚገኘው ታሪካዊው የመንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የነበረበትን የይዞታ ጥያቄ በ75 ዓመቱ ከተማ አስተዳደሩ ምላሽ ሰጥቷል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የጸደቀውን ካርታም አስረክበዋል።

ከተመሠረተ 385 ዓመታት ያስቆጠረው እና አጼ ፋሲል እንዳሠሩት የሚነገርለት የጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በዙሪያው የቦታ ይገባኛል ጥያቄ ሲያነሳ ኖሯል። ጥያቄው ለ75 ዓመታት በርካታ ውጣ ውረድ ማሳለፉን የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ተናግረዋል።

በየዘመኑ ባለፉ መንግሥታት የቤተ ክርስቲያኗን ጥያቄዎች እና ችግሮች ለመቅረፍ በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል ያሉት ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ "የ75 ዓመታት ጥያቄ እና የቤተክርስቲያኗ የዘመናት ችግር ዛሬ ተፈትቷል" ብለዋል። የቤተ ክርስቲያኗን ጥያቄ ለመመለስ ጥረት ያደረጉ የቀድሞ አገልጋዮች እና ይህ እድል የገጠማቸው የወቅቱ መሪዎችን አመስግነዋል።

ለቤተ ክርስቲያኗ የተዘጋጀውን ካርታ ከከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተቀብለው ለቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪ ያስረከቡት የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱሱ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ችግሩ ዘመንን ያስቆጠረ እና ሲገፋ የመጣ እንደ ነበር አስታውሰዋል።
ካለፈው ችግር በመማር ምዕመኑ ቤተ ክርስቲያኗን እንዲጠብቅ፣ እንዲያለማ እና ከመሪዎቹ ጋር በቅርበት እንዲነጋገርም አሳስበዋል። በመነጋገር፣ በመወያየት እና በመመካከር የማይፈታ ችግር የለም ያሉት ብፁዕነታቸው በሂደቱ የተሳተፋትን ሁሉ በቤተ ክርስቲያኗ ስም አመስግነዋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው በከተማ አስተዳደሩ ላለፋት ጊዜያት ከአምልኮ ቦታ ጋር የተያያዙ እና እስካሁንም ድረስ ያልተፈቱ ጥያቄዎች አሉ ብለዋል። ችግሮቹን እየለዩ እና እየተነጋገሩ ፈጣን ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

የመንበረ መንግሥት መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ጥያቄ ለ75 ዓመታት ሲንከባለል የቆየ እና አሁን ካሉ መሪዎች እጅ የደረሰ ችግር ነው ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ችግሩን ለመፍታት መቻል መታደል ነው ብለዋል።

የቤተ ክርስቲያኗ ጥያቄ በስምምነት እንዲጠናቀቅ መሪዎች በቅርበት ለመነጋገር የወሰዱት ቁርጠኝነት አበረታች መኾኑንም ገልጸዋል። በቀጣይም መሰል ችግሮችን ለመፍታት እና ፍትሐዊ ምላሽ ለመስጠት እንደሚሠሩም ተናግረዋል ሲል የጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን ያወጣው መረጃ ይገልፃል።

✍️ጌጡ ተመስገን እንደዘገበው
👍2
ለረ/ፕ መ/ር ግርማ ባቱ የምስጋና መርሐ ግብር ተካሔደ
________
(ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ/ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም)

ረ/ፕ መ/ር ግርማ ባቱ በቅርቡ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ በመኾን መሾማቸው ይታወቃል። ይህን ተከትሎም በመምህርነት በሚያገለግሉበት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም የምስጋና መርሐ ግብር ተካሒዷል።

የምስጋና መርሐ ግብሩን ያካሔዱት የዩኒቨርሲቲው መምህራን ሲሆኑ ለረጅም ዘመናት በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ሓላፊነቶችና በመምህርነት ለባረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ታሳቢ ያደረገ እንደኾነ የመርሐ ግብሩ አዘጋጆች ገልጸዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የበላይ ሓላፊ ፕሬዚደንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ዩኒቨርሲቲያችን ለቤተክርስቲያናችን ታላላቅ ሓላፊነቶች የሚያዘጋጅ አንጋፋ ተቋም ለመኾኑ የመ/ር ግርማ ባቱ ሹመት ምሥክር ነው ብለዋል። ከዚህ በፊትም ዩኒቨርሲቲው ለቤተክርስቲያናችን ጳጳሳትንና ዐለም አቀፍ ምሁራንን ሲያበቃ የነበረ መኾኑን በአባታዊ መልእክታቸው የገለጹት ብፁዕነታቸው አሁንም ምስጉን መምህራንንና መንፈሳዊ መሪዎችን እያዘጋጀ የሚያቀርብ የጀርባ አጥንት የኾነ አንጋፋ ተቋም መኾኑን በመግለጽ ለመ/ር ግርማ በመምህርነታቸው ላይ ካህንም ናቸው በማለት የእጅ መስቀል ሰጥተዋቸዋል።

በምስጋና መርሐ ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዚደንት ፕ/ር አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ፣ የአስተዳድር ጉዳዮች ም/ፕሬዚደንት መልአከ ኃይል አባ ጽጌድንግል ፈንታሁን እና ለረጅም ዘመናት በመምህረነት ያገለገሉ ምሁራን መልእክት እና በጎ ምስክርነት ያስተላለፉ ሲሆን የትምህርት ክፍል ሓላፊዎችና መምህራን በዕንግድነት ተገኝተው ለመልካም አገልግሎታቸው ስጦታና ማስታወሻ ሰጥተዋቸዋል።

(የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት)

#tsegayekiflu
2025/09/05 21:22:25
Back to Top
HTML Embed Code: