ኹለት ጉዳዮች...
1ኛ፦
ነገረ ማርያም፥ እንኳን የአዳምን መርገም የተፈጥሮን ሕግ የሻረ ነው።
አሮጌው ክርክር በቤታችን እንደ አዲስ ባይነሣ ጥሩ ነበር።
ለማንኛውም፥
አምጦ መውለድ የመርገም ውጤት ነበር።
“ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ።” እንዲል
ዘፍጥረት 3፥16።
ጌታችን ክርስቶስ ይኽን ቀዳማዊ(አበሳ ዘጥንት) መርገምንና ኀጢኣትን ከደመሰሰልንም በኋላ፥በሰማንያ ቀን ተጠምቀው ከእግዚአብሔር ለተወለዱ እናቶችም በምጥ መውለድ አልቀረም።
እንግዲህ ሴቶች በምጥ ስለወለዱ፥ የወደቀ ሥጋ ስለያዙ ነው እንላለን?? አንልም።
እንዲኽ የምንል ከኾነማ የክርስቶስ ቤዛነት ከመርገም ከፍሎ ያስቀረው አለ ያሰኝብናል።
ነገረ ማርያም፥ የተፈጥሮን ሕግ እንኳ የሻረ መኾኑ፥ ሰይጣን እንኳ ያወቀው ፀሓይ የሞቀው ዕውነት ነው።
ለዚኽም ምስክራችን ብዙ ነው።አንዱን ብንጠራ እንዲኽ ይለናል።
"ወሊድ ዘእንበለ መወልዲት ወዘእንበለ ሕማም፤
ያለ አዋላጅ ያለ ሕመም መውለድ"። እያለ ይደነቃል ኤራቅሊስ።
ጌታችን ክርስቶስ ከመሰቀሉ አስቀድሞ የውድቀት ውጤት የኾነው ምጥ በወሊድ ጊዜ ካላገኛት
የመርገም ምልክት የነበረ መስቀልን የድል ምልክት አድርጎት የኀጢኣት ውጤት የነበረ ሞትን በሞቱ ክቡር አድርጎት ሳለ፥ የእመቤታችን ሞት እንዴት የውድቀት ምልክት ይኾናል?አይኾንም።
ሲጠቃለል
ነገረ ማርያም፥ እንኳን የአዳምን መርገም የተፈጥሮን ሕግ የሻረ ነውና ዕፁብ ብለን ማለፍ ይሻለናል።
2ኛ፦
በማኅበራዊ ሚዲያ ብዙ ወጣት ከሚሰማቸው አንዱ ወንድማችን፥ አገልግሎቱን ለጊዜው እንዳቆመ ሰማኹ። እኔ ግን እላለኹ። አገልግሎቱን ከምታቆም አቋምኽን አስተካክል። ምን ማለት ነው? ዕይታኽ ከውስጥ ወደ ውጭ ይኹን።
እና ደግሞ በአብነት ትምህርት ወይም በነገረ መለኮት ትምህርት ቤት የሚነሱ አከራካሪ ጉዳዮችን በማኅበራዊ ሚዲያ አታንሣ።
የጥብርያዶስ ቀለም ለዮርዳኖስ አይኾንም። ቦታው አይደለምና።
ወንድማችን ላይ ጥርጣሬ ያለን ሰዎች፦
ከመቶ ዘጠና ያመጣውን ተፈታኝ ከትምህርት ማባረር አግባብ አይደለም። ሙሉ በሙሉ ፈተናውን እንዲያልፍ ከተፈለገ እንዲያነብብ ያነበበውን በውስጣዊ ዐይን እንዲረዳ ማድረግ ነው ትርፍ። ማባረር ኪሳራ ነው።
ውስጣዊ ዐይን የምለው ምኑን መሰላችኹ?
ኹሉም የሊቃውንት መጻሕፍት ትርጓሜዎች ናቸው። ለምሳሌ የቄርሎስ የዮሐንስ... መጻሕፍት ሃይማኖተ አበውን ጨምሮ ራሳቸው ሊቃውንቱ ሲጽፏቸው በትርጓሜ መልክ ነው።
የእኛ ሊቃውንት ደግሞ ትርጓሜውን ተረጎሙት። ዐውድ እንዳንስት በሀገርኛ ምሳሌ አብራሩት። የሊቃውንት መጻሕፍት የትርጓሜ ትርጓሜ ናቸው። ውስጣዊ ዐይን ያልኩት ይኽ ነው።
Edited
"የወደቀ ሥጋ ማለት ሞት የሚስማማው ማለት ነው" የሚል መልስ እያየኹ ነው፡፡ መልካም፡፡
አዳም ከመውደቁ በፊት ሞት የሚስማማው እንጂ የማይስማማው አልነበረምኮ፡፡ ስለኾነም "የወደቀ ሥጋ" ማለትና ሞት የሚስማማው ማለት፥ እንዴት አንድ እንደሚኾን ለሚነግረኝ ሰው እርማቴ ፈጣን ነው፡፡
መጭው ዐቢይ ጾም የፍቅር ጾም ይኹንልን።
✍ሊቀ ሊቃውንት ስሙር

👍4❤3
ቀሲስ መብራቱ ኪሮስ(ዶ/ር) ስለ አኬ ምን አሉ?
+ አክሊልን እንደ አጵሎስ
ወንድማችን አክሊል የአበውን መጻሕፍት በትጋት በማንበብ ራሱን አስተምሮ አስደናቂ የዕቅብተ እምነት ሥራ እንደሠራና በዚህም ለብዙዎች ወደ ኦርቶዶክሳዊት (ርትዕት/ የቀናች) እምነት መመለስ ምክንያት እንደሆነ ይታወቃል፡፡
በቅርቡ ግን ወጣቱ Apologist አክሊል በሚያነሣቸው የነገረ መለኮት እሳቤዎች (theologoumena = ዶግማዊ ውሳኔ ያለተሰጠባቸው አመለካከቶች) ላይ ብዙዎች ጥያቄ ሲያቀርቡና አንዳንዶችም አክሊልን ሲከስሱ ታዝቤአለሁ፡፡ የዚህ ታዳጊ ወጣት አገልግሎት ያስታወሰኝ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 18 ውስጥ የምናገኘውን የእስክንድርያ ተወላጁን አጵሎስን ነው፡፡ ጸሐፊው ሉቃስ እንዲህ ከትቦታል፦
የሐዋ ሥራ 18፡ 24 “በወገኑም የእስክንድርያ ሰው የሆነ፣ ነገር አዋቂ የነበረ አጵሎስ የሚሉት አንድ አይሁዳዊ ሰው ወደ ኤፌሶን ወረደ፤ እርሱም በመጻሕፍት እውቀት የበረታ ነበር።
25 እርሱ የጌታን መንገድ የተማረ ነበር፥ የዮሐንስንም ጥምቀት ብቻ አውቆ በመንፈስ ሲቃጠል ስለ ኢየሱስ ይናገርና በትክክል ያስተምር ነበር።
26 እርሱም በምኵራብ ገልጦ ይናገር ጀመር። ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜ፥ ወስደው የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት።"
አጵሎስ በመጻሕፍት እውቀት የበረታ እንደነበር፣ ወንድማችን አክሊልም የአበውን መጻሕፍት በትጋት በማንበብና የሚያውቀውን በማካፈል ብርቱ ነው፡፡ አጵሎስ በመንፈስ እየተቃጠለ (እንግሊዝኛው "with burning enthusiasm" ይላል) ስለ ኢየሱስ ይናገርና በትክክል ያስተምር እንደነበር፣ አክሊልም ከኦርቶዶክሳውያን አባቶች የተማረውን በትክክል ያስተምር ነበር፡፡
ልዩነቱ ያለው አጵሎስንና አክሊልን ባረሙ (ባቀኑ) ሰዎቸ ላይ ነው፡፡ ባልና ሚስቱ ጵርስቅላና አቂላ የአጵሎስን ቅንዐት (zeal) ተመልክተው፣ አንዳንድ እርማት የሚያስፈልጋቸው ነገሮች እንዳሉ ባስተዋሉ ጊዜ ወደ ቤታቸው ወስደው "የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት" እንጂ አልከሰሱትም፤ አላወገዙትም፡፡
እኛም ለወንድማችን አክሊል ልናደርግ የሚገባው ይህንኑ ነው፡፡ በተሻለ መልኩ በጥበብ ሊቀርቡ የሚገባቸው አስተምህሮዎች ካሉ አክሊልን በፍቅር እናቅናው እንጂ፣ አናውግዘው፡፡ አንዳንድ ጽንፈኞች ስም እያጠፉ በማስደንበር ከኦርቶዶክሳዊት በረት ያስኮበለሏቸው በጎች ብዙዎች ናቸውና ያለፈው ጥፋት ይበቃል!
✍️ቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ እንደጻፉት
`
`````````+ አክሊልን እንደ አጵሎስ

❤7👍4👎1
“ሰው በሰው ሲታረም እግዚአብሔርን ደስ ይለዋል” /የእግዚአብሔር መልአክ ለአንድ ቅዱስ የተናገረው/።
እንዴት እንተራረም? ትክክለኛው መንገድስ የትኛው ነው?
የሰሞኑ የመፈራረጅ ጠርዝ ያስገርማል። ሆኖም “እግዚአብሔርን ለሚወድዱት እንደ ሀሳቡ ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን” እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ ይህም ለእውነተኞቹ አማኞች ለበጎ እንደሚሆን አምናለሁ። ቢያንስ አንድ መሠረታዊ ጥቅም ያለው ይመስለኛል። በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለነው ምእመናን ያለንበት የዕውቀት፣ የእምነት፣ የአመላክከት፣ የምግባር እና የመሳሰለው ልዩነት ማለትም ከየት እስከየት እንደሆንንን በአስተውሎት ለተመለከተ ምን ዓይነት ጸሎት፣ ምን ምን ዓይነት ትምህርቶች፣ እንዴት ባለ አኳሃን ማቅረብ እንደሚገባ ለመረዳት ፍንጭ ይሰጣል ብዬ አስባለሁ። ይህም ቢሆን የተቻለን በቅንነት ለማቅረብ እንጂ ለሁሉም መልስ ሰጥቶ ሁሉን አሳምኖ እና አስማምቶ መሔድ ይቻላል ለማለት አይደለም። ያንን ጌታም እየተቻለው አላደረገውም። ያለባለቤቶቹ ፈቃድ ምንም ለውጥ ሊመጣ አይችልምና። ጌታም የመጣበትን ዓለሙን የማዳን ሥራ በፍጹም ትሕትና ፈጸመ እንጂ ሌሎችን የበተለይም በተቃውሞ እና በጥርጣሬ የነበሩትን ለማሳመን ምንም ነገር አላደረገም። በአምላክነቱ ኃይል ሁሉን ማደረግ ቢችልም በማንም ላይ አስገድዶ ያደረገው ነገር የለም።
በአንድ ሽምግልና ወቅት የሰማሁት አባባል ለዚህ ሰሞንም የሚሠራ ይመስለኛል። አንዱ ተናጋሪ እንዲ አለ ፦ “እታረቃለሁ ያለ ንጉሥ በገበሬ ይታረቃል፤ አልታረቅም ያለ ገበሬ በንጉሥ አይታረቅም”። እውነትም ነው። ንጉሡ የታረቀው በልቡ ገርነት እንጂ በአስታራቂው ትልቅነት አይደለም። ገበሬውም ያልታረቀው ሽማግሌ አጥቶ አይደለም፤ ልቡ እልከኛ ሆኖ እንጂ። አሁንም ካለነው ብዙዎቻቸን አልታረቅም ያለውን ገበሬ እንመስላለን። ከራሳችን ፍላጎት ጋር ያልገጠመውን ሁሉ የምንጠራጠር በሆነ ታሪክና ምሳሌ ወይም በጥቅስ አስደግፈን የምናደርገው ሙግት አስገራሚ ነው። አንዳንዶቻችችን ለሃይማኖት መቅናትን አስቀድመን ስለወንድም ፍቅር ያለን ነገር ምንም ቦታ የሌለው ይሆናል። አንዳንዶቻችን ደግሞ ለወንድም ፍቅር ብለን ሃይማኖታዊ ጉዳዩ ሁሉ ሁለተኛ ይሆኑብናል። አንዳንዶቻችን የሌሎችን የሃይማኖት ጥራት በእኛ እውቀት ልክ ብቻ እንመዝንና ደረጃ ልናወጣላቸው እንሞክራለን። ሌሎቻቸን ደግሞ ራሱን ሃይማኖቱን በእኛው ዕውቀት፣ ንባብ እና መረዳት ልክ እንመዝነዋለን። አንዳንዶቻችንም ፈራጅ እና ወሳኝ ሁነን ተሰይመናል። አንዳንዶቻችን ደግሞ የሆኑ ሰዎች እንዳይጎዱ ብለን ከመጠን በላይ እንጨነቃለን። በርግጥ በአንዱ ጭንቀት ሌላው ሊድን ይቅርና በጭንቀት ራስንም ማዳን አይቻልም። ለሰው ማሰብ ተገቢ ቢሆንም እርሱም መንገድና ሁኔታ አለው። ሆኖም እነዚህ ሁሉ ፈተናዎች በአግባቡ ከተቀበልናቸው ጥቅም እንጂ ጉዳት የላቸውም።
ነቀፌታ የበዛባቸው ሰዎችም ቢሆኑ እኔ በግሌ ኦርቶዶክሳዊ እስከሆኑ ድረስ ይጎዳሉ የሚል እምነት የለኝም። ይህ የሚሆነውም በሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ነው። አንደኛው ሰዎች ወደ ሌላ ሰው የሚልኳቸው ነቀፌታዎች፣ ትችቶች፣ ስድቦች፣ ሐሜቶች ፣ ፍረጃዎች እና ጥላቻዎች ሁሉ ያን ሰው የሚጎዱት ራሱ ሲቀበላቸው ብቻ ነው። ይህም ማለት ለራሱ የተለየ ቦታ ይሰጥ ከነበረ፣ ነቀፌታ ትችት አይገባኝም የሚል ውስጣዊ እምነት ካለው፣ የሚሰጠው አገልግሎት የተለየ ዋጋ እና ክብር ይገባዋል ብሎ በውስጡ የሚያስብ በተለይም ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ትልቅ አስተዋጽዖ አለኝ ብሎ በውስጡ የሚያምን ከሆነ ጉዳቶቹ የሚመነጩት ከዚህ የተሳሳተ አስተሳሰቡ ስለሚሆን ነው። ተቺዎች፤ ሰዳቢ ነቃፊዎች ሆነ ብለው ጉዳት ለማድረስ የሚመጡትም ሆነ ባለማወቅ በቅንነት ቢያድረጉም በድርጊታቸው መጠን መጠየቃቸው አይቀርም። “ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል” /ማቴ 12 ፤ 36/ ተብሎ ተጽፏልና። የተነቀፈው የተሰደበው ሰው ግን እግዚአብሔር ባወቀ ትችቶቹ ነቀፌታዎች ይጠቅሙታል እንጂ አይጎዱትም። እንዲያውም ራስን ለማየት ፣ ለራስ የምንሰጠውን ያልተገባ ቦታ እንድናስተካክል የሚያደርጉ ቁንጥጫዎች ስለሚሆኑ ይጠቅማሉ እንጂ ሊጎዱት አይችሉም። በተለይ ጻድቅ ታጋሽ ልባል ብሎ ሳይሆን በውስጡ ይገባኛል ብሎ ከልቡ የሚቀበላቸው ሰው ካለ ዋጋ ማግኛው ያ ጊዜ ይሆናል። ከመጠን በላይ ሆነው ሰውየውን ሊጎዱት አይችሉም ወይ የሚል ጥያቄም ልናነሳ እንችላለን። አንድ ገዳማዊ አባት ግን ማንም ሰው ከአቅሙ በላይ ሊፈተን በፍጹም አይችልም ይላል። ከአቅማችን በላይ የሆነ ፈተና ወደ እኛ እንዲመጣም እግዚአብሔር አይፈቅድም። እንኳን እግዚአብሔር ሸክላ ሠሪ እንኳን ሸክላውን ምን ያህል ሰዓት በእሳት ውስጥ ማቆየት እንዳለበት ያውቃል። ስለዚህ እግዚአብሔርም ሊያጠነክሩን፣ ሊጠቅሙን የሚችሉትን ያህል ይፈቅዳል እንጂ ሊያጠፉን ሊሰብሩን የሚችሉትን በፍጹም አይፈቅድምና ፈተና ይጎዳኛል አትበሉ ይላል ገዳማዊው አባት። ስለዚህ ለሰዎች ፍቅር ማሳየት እና ማበርታት ተገቢ ቢሆንም ወዳጅነትቻንና አግርነታችን ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ድንበሩን ያልዘለለ፣ ቴፎዞአዊ ጠባይ የሌለው ፣ ሰዎችን ካላስተዋሉት ችግራቸው በሚያላቅቅ መልኩ ሊሆን ይገባዋል ሰዎቹን እግዚአብሔር ከችግሮቻቸው ሊያወጣበት ያመጣውን ሁሉ እንደ ችግር ቆጥረን የላይ ፈሪ እና የታች ፈሪ በሚል መንገድ እንዳናደርገው የአበው ምክሮች ያስገነዝቡናል።
ከዚሁ ጋር አንድ መሠራታዊ ችግራችንም ጠቆም አድርጌ ባልፍ ጥሩ ይመስለኛል። እንኳን እኛ ደካሞቹ እንቅርና ብዙ ሰዎች የማይረዱት አድሎ ወይም ወደ አንዱ የማዘንበል ውስጣዊ ድክመት ይታይብናል። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የቅዱስ ጴጥሮስ ሕይወት ነው። ቅዱስ ጴጥሮስ በትውልዱ አይሁዳዊ መሆኑን አንረሳውም። ጌታቻን መጀመሪያ ከመረጣቸው ሐዋርያት መካከል መሆኑንም አንስተውም። ታዲያ ቅዱስ ጴጥሮስ የቅንነቱን ያህል ችኩልነት፣ የእውነተኝነቱን ያህል የማያውቃት አድሎ እንደነበረችበት ቅዱስ መጽሐፍ ላይ ከተመዘገቡት ታሪኮች መረዳት ይቻላል። ጌታ ሮማዊውን ቆርኖሌዎስ እንዲያጠምቅ ለቅዱስ ጴጥሮስ ያስረዳው በራዕይ ነበር /ሐዋ 10 ያንብቡ)።
ይህ ከመሆኑ በፊት ቅዱስ ጴጥሮስ ብዙ ነገሮች ተደረገውለት ነበር። ሐዋርያ ሆኖ ተመርጦ፣ ተምሮ ተሹሟል። በጌታ ስቅለት ዕለት ጌታውን ደጋግሞ አላውቀውም ብሎ ቢክደም ንስሐ በገባ ጊዜ ይቅርታ ተደርጎለታል። ያም ብቻ ሳይሆን በኋላ አንተ እኮ ጌታህን ክደህ ነበር እየተባለ እንዳይነቀፍ ጴጥሮስ ሆይ ትወደኛለህን እያለ እየጠየቀ ቤተ ክርስቲያንን በአደራ ሰጥቶታል። ሊቀ ሐዋርያትም አድርጎታል። ይህም ለእርሱ የተደረገለት ልዩ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ለተመለሰ ሰው ልንሰጠው የሚገባን አመኔታ እና ከበሬታ ሁሉ የሚያመላክት ነበር። ከዚያ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ወርዶለታል። ሰባ ሁለት ቋንቋዎችን አናግሮታል። በዚያው ዕለት ስብከቱ ሦስት ሺህ ሰዎችን በቅጽበት አሳምኖለታል። በሌላ ቀን ስብከቱም በአንድ ጊዜ አምስት ሺህ ሰዎችን አስምኖለታል። በቤተ መቅደስ ተቀምጦ ይለምን የነበረውን ሽባ ፈውሶታል። በልዳ ሞታ የነበረች ዶርቃ የተባለችን ከሞት አስነስቷል። በዚህ ሁሉ ብቃት እና ኃይል ላይ እያለ ጌታም ዓለምን ሁሉ አስተምሩ የሚለውንም ትዕዛዝ ተቀብሎ እያለ ግን በውስጡ ለአሕዛብ ያለው አመለካከት ገና ስለነበረ ቆርኔሌዎስን አላጠምቅም እንዳይል ጌታ በማይበሉት እንስሳት አምሳል እያወረደ እና ተነስተህ አርደህ ብላ ይለዋል። ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ ርኩስ እና የሚያጸይፍ ነገር

👍1
በአፌ ገብቶ አያውቅም እያለ ይከራከራል። በመጨረሻም ስለ ራእዩ ሲጨነቅ ከቆርነሌዎስ የተላኩት ሰዎች መጠተው ተጣሩ። እንደ ገና መንፈስ ቅዱስ እኔ የላኳቸው ሰዎች ስለሆኑ አብረህ ሒድ ሲል አዘዘው። ወደ ቂሳርያም ተጓዘ። በዚይም ሲደርስ የተጠራበትን ጠይቆ ከተረዳ በኋላ እንዲህ አለ፦ “አይሁዳዊ ሰው ከሌላ ወገን ጋር ይተባበር ወይም ይቃረብ ዘንድ እንዳልተፈቀደ እናንተ ታውቃላችሁ፤ ለእኔ ግን እግዚአብሔር ማንንም ሰው ርኵስና የሚያስጸይፍ ነው እንዳልል አሳየኝ” /ሐዋ 10 ፤28/ ትንሽ ቆይቶም ደግሞ ፤ “እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ” /ሐዋ 10 ፡ 35/ አለ። ይህ ሁሉ የተደረገው ቅዱስ ጴጥሮስን በውስጡ ተደብቃ ከምትኖር አድሎ ለማለቀቅ እና አሕዛብንም ለማዳን ነበር።
ሆኖም ይኼው ቅዱስ ጴጥሮስ እሥራኤልን ለቅቀው ወደ ሶርያ ከገቡ በኋላ አይሁድ በሚኖሩበት ጊዜ እነርሱን በመፍራት አሕዛብ ጋር ተቀምጦ ለመብላት እንኳ አይደፍርም ነበር። ቅዱስ ጳውሎስ ፊት ለፊት ተቃወምሁት፤ ሊፈረደበት ይገባ ነበርና / ገላ 2፡11/ ሲል ታሪኩን ይነግረናልና ።ይህ ያደረገው ደግሞ ከላይ የተመዘገበው ታሪክ ከተፈጸመ እና ማንንም ሰው እንዳልጸየፍ እግዚአብሔር አሳየኝ ብሎ ከመስከረ በኋላ መሆኑን ስናስብ ሰውነት ምን ያህል ድካምነት እንዳለበት አስበን እንገረማለን። ከዚህ የምንረዳው በውስጣችን ያለች አድሎ ምን ያህል ከባድ መሆኗን ለቅድስና የበቁትን የተመረጡትን ሳይቀር ምን ያህል እንደምትፈትንም ጭምር ነው። በእነርሱ ዘንድ እንኳ እንዲህ ያለ ነገር ጨርሶ ካልጠፋ በእኛ ዘንድማ ምን ያህል ይሰለጥን ይሆን? የብዙዎቻችን አስተያየቶች ከዚህች አድሎ ነጻ የምትሆን አይመስለኝም። ይህን መተረክ ያስፈለገውም ወደ ሌሎቹ አጥብቀን በምርመራ መንፈስ ከምናይ ወደ ራሳችን ብናይ የበለጠ እንጠቀማለን ለማለት ነው። ለማንኛውም መንፈሳቸው፣ አጠቃላይ ሰብእናቸው ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ በተለያየ ምክንያት የማያስተውሏቸው ኑፋቂዎች እና ስሕተቶች ሲያጋጥሙ አበው ለማረም ከሔዱባቸው ታሪኮች ሁለቱን ላቅርብና ነገሬን ልቋጭ።
ስሕተት፣ ኑፋ/ቄ ፣ እርማት፣ እና አራሚዎች
በመጻሕፍት ካነበብኳቸውና አባ ዳንኤል ዘገዳመ አስቄጥስ ከመዘገባቸው ታሪኮች ውስጥ አንዱ የሚከተለው ነው። ቅዱስ ቄርሎስ በእስክንድርያ መንበር ፓትርያርክ በነበረበት ዘመን በብቃቱ የሚታወቅ አንድ ቅዱስ ገዳማዊ አባት ነበር። የዚህ አባት ዋናው ብቃቱ ደግሞ ሰዎች በሆነ ነገር ሲቸገሩ እና ለእርሱ ሲነግሩት ሱባኤ ይገባላቸውና ከእግዚአብሔር የተገለጸለትን ይዞ ምክር በመስጠት የብዙ መናኞችን እና አማኞችን ችግር ይፈታ ነበር። ሆኖም አንድ ቀን ባለማወቅ እና የራሱንም መረዳት በመደገፍ አንድ አዲስ ትምህርት ለገዳሙ መነኮሳት መናገር ጀመረ።
ይኸውም መልከጼዴቅ ወልደ እግዚአብሔር ነው የሚል ነው። ከእመቤታችን ተወልዶ ኢየሱስ ተብሎ የመጣው ቀድሞ ለአብርሃም የተገለጸለት የሳሌሙ ንጉሥ መልከጼዴቅ ነው እያለ ወደ መነኮሳቱ እየዞረ መናገር አበዛ። ይህን ኑፋቄ መናገር የጀመረው ያ በቅድስና ሕይወቱ እና በብቃቱ የታወቀው አባት ነው። ክፉን ያርቅና በእኛ ዘመን እንዲህ የሚል ትምህርት አንድ አባት ይዞ ቢመጣ ምን እንደረጋለን? ምንስ እንለዋለን? ድርጊቱንስ እንዴት እንመለከተዋለን? እስኪ ራሳችንን እንመልከትበት ።
የገዳማቱ አባቶች በትምህርቱ ታወኩ። የሚያደርጉትም ቸገራቸው። ሁኔታው ለፓትርያርኩ ለቅዱስ ቄርሎስ ደረሰ። እርሱም ሲሰማ አዘነ፣ ተጨነቀም። በኋላ ግን አንድ ነገር አስታወሰ። ይህ አባት እንዲህ ያለ ሁከተ ኅሊናም ሆነ ሌላ መንፈሳዊ ችግር ለገጠማቸው ሁሉ በጥብቅ በእግዚአብሔር ፈቃድ እና በተገለጠው ብቻ እንዲመሩ ሱባኤ ገብቶ የተገለጠለትን በመናገር እና በመምከር የታወቀ ነበር። ለርሱ ፈተና ጊሼ የሚሆን ሰው ግን በወቅቱ አልነበረም። ስለዚህ ቅዱስ ቄርሎስ ይህን አባት አስጠራው። ይህ አባት ሲመጣም ቅዱስ ቄርሎስ እንዲህ አለው። አባቴ ሆይ እኔ በሁለት ሀሳቦች ተጨነቅሁኝ። አንዱ አእምሮዬ መልከጼዴቅ ወልደ እግዚአብሔር ነው ይለኛል። ሌላው አእምሮዬ ደግሞ አይ መልከጼዴቅ ሰው ነው እንጂ ወልደ እግዚአብሔር አይደለም ይለኛል። እባክህን ሱባኤ ገብተህ የትኛው ትክክል እንደሆነ ከእግዚአብሔር የተገለጸልህን ንገረኝ አለው። ያ አባትም ችግሩ የራሱ መሆኑን ረስቶ ለአባ ቄርሎስ ሦስት ቀን ስጠኝ አለው። ከሦስት ቀን በኋላ በገዳሙ እየዞረ መልከጼዴቅ ሰው ነው። ከአባቶች አንዱ እንጂ ወልደ እግዚአብሔር አይደለም እያለ መናገር ጀመረ። መነኮሳቱም በምን አወቅህ ሲሉት ጌታ ከአዳም እስከ አብርሃም ያሉትን አባቶች አምጥቶ ሲያሳየኝ አንዱ መልከጼዴቅ ነበር። ስለዚህ እርሱ ከአባቶች አንዱ እንጂ ወልደ እግዚአብሔር አይደለም እያለ ያጠፋውን አረመ። ቅዱስ ቄርሎስም ነገሩ ሲሰማ እግዚአብሔርን አመሰገነ። ችግሩንም እጂግ መንፈሳዊ በሆነ መንገድ ፈታው።
በዚህ ታሪክ ውስጥ ብዙ ቁምነገሮችን መውሰድ የምንችል ይመስለኛል። በመጀመሪያ እነማን ሊስቱ እንደሚችሉም መረዳት እንችላለን። እግዚአብሔር ካልጠበቀን በቀር በተምሪያለሁ፣ አንብቤያለሁ ፣ አውቃለሁ ባዮች ይቅርና እንደዚህ አባት የበቁትም ሳይቀሩ የመሳት ሁኔታ ይገጥማቸዋል። እንኳንስ ነገሮችን በትንሽዬ ዕውቀት የምናየው የእኛ ትውልድ ይቅርና በቅድስና ያላቸው ሳይቀር ለስሕተት እንደሚጋለጡ በቂ ምስክር ይመስለኛል። ይህ አባት በሁለንተናው ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ነበር። ይህም ሆኖ ሕሊናው የራሱን መረዳት መከተል ስትጀምር ደግሞ ስሐተት ወዲያው ስታጠምደው እንመለከታለን። ይህ እንግዲህ የተጻፈው ለሰው የታወቀ ስሕተት ስለሆነ እንጂ ለሰው ያልታወቀማ ብዙ ስሕተት ሊኖረን እንደሚችል ለመረዳት የሚያስቸግር አይመስለኝም። ሁለተኛው ነገር ኦርቶዶክሳዊያን የሆኑ ሰዎች ትልቅ ስሕተት እንኳ ቢሳሳቱ እንዴ መፍታት እንዳለብንም ከዚህ ታሪክ መረዳት እንችላለን። በርግጥ መፍቻ መንገዱ እንዲህ ዓየነት ብቻ ነው ማለም አይደለም። ወደ ሌላ ታሪክ ላምራና ሌላ መንገድም እንመልከት ።
አሁንም በአበው ሕይወት ውስጥ እንዳነበብኩት ታሪክ የተፈጸመው በመጀመሪያው ምዕተ ዓመተ ክርስትና ነው። ለብቃት የደረሰ አንድ ካህን ነበር። ይህ ካህን ረዳት ካህንም ዲያቆንም ስላልነበረው ብዙ ጊዜ ብቻውን እየቀደሰ አማኞችን ያቆርብ ነበር። በዚህም ምክንያት በቅዳሴ ጊዜ ሁልጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ በመሰዊያው አጠገብ ቆሞ ይታየውና ያጸናው ነበር። አንድ ቀን ግን አንድ ዐዋቂ ዲያቆን ሊጠይቀው ሲመጣ ቅዳሴ እንዲረዳው ይዞት ገባ። ያ ዘመን እንዳሁኑ የቅዳሴ መጻሕፍት በመጽሐፍ ተጽፈው ስላልነበሩ በትውፊት የተቀበሉትን መሠረታዊ ነገር ይዘው በቃላቸው እየጸለዩ እየቀደሱ ነበርና የሚያቆርቡት ይህም አባት በዚያው መንገድ ቅዳሴውን ወደ መቀደስ ገባ። ቅዳሴው መካከል ላይ እያሉ ያ እንግዳ ዲያቆን በቅዳሴው ላይ ከምትጸለያቸው ጸሎቶች መካከል አሳፋሪ የሆኑ የኑፋ/ቄ ቃላትን ተጠቅመሃል አለው። ያ አባትም ደንገጥ ብሎ በቅዳሴ ጊዜ ሁሉ የማይለወን መልአክ ዘውር ብሎ ይህ ዲያቆን የሚናገረኝ እውነት ነውን ሲል ጠየቀው። መልአኩም አዎን ሲል መለሰለት ። በዚህ ጊዜ ያ ካህን ታዲያ እስከዛሬ ለምን አልነገረከኝም ሲል መልአኩን መልሶ ጠየቀው። መልአኩም ሰዎች ስሕተታቸውን ከሰው ተምረው ሲያስተካክሉ እግዚአብሔር ስለሚደሰት ለዚህ ብዬ ነው ዝም ብዬ የጠብቅሁት አለው ይላል ታሪኩ።

ከዚህም ብዙ ቁምነሮችን የምናገኝ ይመስለኛል። ይኸኛው እንደ ቅዱስ ቄርሎስ ሳይጠነቀቅ እዚያው ፊት ለፊት ካህኑን ገጥሞታል። መልአኩ ደግሞ ምን ያህል ጊዜ እንደታገሰው እና እንደጠበቀ እናስተውል። መልአኩ እንዳለው ሰዎች ከስሐተታቸው በሌሎች ሰዎች ሲታረሙ ማየት እግዚአብሔርንም መላእክትንም የሚያስደስት መሆኑ አስገራሚ ነው። ያም በመሆኑ ደግሞ እግዚአብሔር ለመጀመሪያው አባት ቅዱስ ቄርሎስን ለዚህ ካህን ደግሞ አዋቂ ዲያቆን አዘጋጀ። ስሕተት ደግሞ የማትገባበት ጊዜ እና ቦታም እንደሌለ የምትምረውም የሰው ዓይነት እንደሌለ ከታሪኮቹ መረዳት ይቻላል። ከዚህ ታሪክ ሌሎች ብዙ ነጥቦችንም መውሰድ እንችላለን። እንደላይኛው ሁሉ መልአክ ተገልጾለት የሚነጋገር አባት ሳይቀር ሊስት የኑፋ/ቄ ቃላትንም ሊጠቀም መቻሉ እንደተጠበቀ ሆኖ ነገረ ግን ሰውየው ውስጡ እምነቱና ሀሳቡ ኑፋቄና ተንኮል ከሌለው እግዚአብሔርም ይታገሰዋል። ቀኑንም ጠብቆ የሚያርመውንና የሚያስተምረውን ሰው ይልክለታል። ከሁሉም በላይ ደግሞ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኘው በሌላ ሰው ስንስተካከል ነው። ለዚህ አባት የተላከለትም ከእርሱ በላይ የበቃ አባት ሳይሆን ከእርሱ በሥልጣነ ክህነትም የሚያንስ ዲያቆን ነው። ዲያቆኑን ተጠራጥሮ አልቀበለም ሲል ደግሞ መልአኩ ተገልጾ ማረጋገጫ የሰጠው ከእኛ ያንሳሉ ብለን ከምናስባቸው ሰዎችም ቢሆን ሰምተን እንድንታረምና እንድንሰተካከል ጭምር ነው።
በሰው መታረምን በተመለከተ ደግሞ ሌላ ታሪክ ልጨምር። ቃለ እግዚአብሔርን ከምጠያየቃቸው እና ከምጫወታቸው አንዱ የሆነው መምህር በረከት አዝመራው ካነበበው የትርጓሜ መጽሐፍ የነገረኝ ነው። ሙሴ ደብረ ሲና ወጥቶ ሲመለስ እሥራኤል ጣዖት አቁመው ሲሰግዱ አግኝቷቸው እነዚያን ጣዖት የሚያመልኩትን እንዲገደሉ አዝዞ በወገኖቻቸው ተገድለዋል። እርሱ እንደነገረኝ መተርጉማኑ አንድ ጥያቄ አንሥተው ይመልሳሉ። እግዚአብሔር እነዚያን ጣዖት አምላኪዎች እንደ ፈርዖን ለምን ራሱ አላጥፋቸውም ወይም ለምን ራሱ አልቀሰፋቸውም? በሙሴ ትዕዛዝ በራሳቸው ወገኖች እንዲገደሉ ለምን አደረገ የሚል ጥያቄ ያነሡና ይመልሳሉ።
እግዚአብሔር ራሱ ሳያጠፋቸው በራሳቸው ወገኖች እንዲገደሉ ያደረገው ስለሁለት ምክንያት ነው። የመጀመሪያው እሥራኤል ታሪካቸው እግዚአብሔርን ክዶ ጣዖት ማምለክ ብቻ ሳይሆን ጣዖት አምላኪዎችንም የማጥፍት ታሪክ እንዳላቸው እንድናውቅ ነው። ሁለተኛም ከላይ እንዳልነው የሰው ስሐተት በሰው ሲታረም እግዚአብሔር ደስ ስለሚለው ነው የሚል ነው። ከላይ ባየነው ታሪክ መልአኩም ያለው ይህንኑ ነው።
ከዚህም ጋር በሁለቱም አባቶች ታሪክ ላይ አንድ ሌላ መሠራታዊ ትምህርት እናገኛለን። ይኸውም ሰዎች በሚሳሳቱ ጊዜ በሁለንተናቸው ኦርቶዶክሳዊ ሆነው የሆነ ኑፋቄያዊ ቃላት እና ሀሳብ ባገኘንባቸው ጊዜ መማማሩ እንዳለ ሆኖ ልናደርገው የሚገባን ጥንቃቄ ፣ ከበሬታ ፣ ልናሳያቸው የሚገባው ፍቅር ተገልጾልናል። ያን አባት ያረመው ያ ዲያቆን በእኛ ዘመን ቢሆን ኖሮ እንኳን በዚያ አባት በመልአኩም ሊናደድ የሚችል ይመስለኛል። ለምን ሳይቀስፈው ብሎም መልአኩንም የሀሳቡ ተባባሪ አድርጎ ሊቆጥረው ይችላል። (ይህን የምለው ስለእኛ ሕሊና መሆኑ ሳይረሳ) ምክንያቱም የእኛ ዘመን አንዱ ትልቁ ድክመታችን የመጨረሻ ፍርድ ሁሉ ሰጭዎች መሆናችን ነውና።
ማጠቃለያ
እንዲህ ያሉ ነገሮች ለምን ተነሡ? ምን ሲል እንዲህ ተባለ? ለምን እነእገሌ እንዲህ ይላሉ? ... ለምን ዝም ይባላል? የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ማቆም ይኖርብናል። በየትኛውም ዘመን በየትኛውም መዓርግ ባለ መንፈሳዊ ሰውም ላይ ብዙ የምናውቃቸውም የማናውቃቸውም ስሐተቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ መረዳት ተገቢ ነው። እባብ ያዬ በልጥ በረዬ የሚባልላቸው መሆንም የለብንም። እንዲያውም እንዲህ ዓይነት ታሪኮች ሁልጊዜም ማስተማሪዎች በመሆን አንዱ የእግዚአብሔር የመግቦት መገለጫዎች፣ የየዘመኑን ሰው ማንቂያዎች፣ ወዳጆቹንም መጠበቂያዎች (በተለይ ከትዕቢትና ኩነኔ ከሚያመጣ ጥፋት) ናቸው። ዋናው የሚያስፈልገን ነገር ከሁሉም ነገር እግዚአብሔር ሊያስተምረን የፈለገው፣ እኛ ውስጥ ሊያርመው የፈለገው ነገር ምንድን ነው የሚለው ጥያቄ መሆን አለበት ። ካስተዋልን ሁላችንም የየራሳችንን ስሐተቶች የማየት እና የመታረም ዕድል እናገኝበታለን።
ማር ይስሐቅ መላእክትን ለማየት ከበቃ ሰው ይልቅ የራሱን ስሕተት ለማየት የበቃ ሰው የበለጠ ብቃት ደረጃ ላይ ደርሷል ይላል። ቅዱሱ አባት መላእክትን የሚያይ የውጭ ዐይኑ የተከፈተለት ነው፣ የራሱን ስሕተት የሚያይ ግን የውስጥ ዓይኑ የተከፈተለት ነውና እርሱ የበለጠ በቅቷል እንዳለ ወደ ሰው ስሕተት ከማየት ይልቅ ወደራሳችን ስሐተት ማየት ኦርቶዶክሳዊም መንፈሳዊም መንገድ መሆኑን እናስተውል። በዚህ ጽሑፍ ላነሣቸው ያልፈልኳቸው ብዙ ድክመቶች እንዳሉብን ይሰማኛል። ለሁላችንም የሚጠቅመን ግን የራሳችን ስሐተት ማየት እንጂ የሌሎቹ ላይ ማፍጠጥ እና ከፍ ዝቅ አድርጎ መናገርም ሆነ መጻፍ አይደለምና አጥብቀን እንታረም። ይልቁንም ያለነው በዐቢይ ጾም ዋዜማ ላይ ስለሆነ በቀሩን ቀናት ይቅርታ ተጠያይቀን ከቡድነኝነት፣ ከተሳሳቱ ግምቶች እና ግምታዊ ንግግሮች፣ ከፍረጃ እና ከአጸፋዊ ፍረጃ፣ በማናውቀው እና በማይገባን ነገር ከመነጋገር ወጥተን ወደ መንፈሳዊ ድንኳናችን እንሰብሰብ። ያን ጊዜ ስሕተቶቻቸን ይታዩናል። ለሰዎችም ፍቅር ሐዘኔታ የተመላ የማስተካከያ መንገድ ይገለጽልናል። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ስለኦርቶዶክሳዊ ነገር ዕውቀት ትንሽዬ ማስታወሻ ለጾም ቅበላችን እጨምራለሁ፤ መልካም ጾም ያድርግልን። ልዑል እግዚአብሔር ከሚታወቅም ከማይታወቅም ስሐተት ሁላችንንም በቸርነቱ ይጠብቀን፤ አሜን።
✍️ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ እንደጻፈው

❤5
Forwarded from Tsegaye Kiflu
የምሥራች በውጭ ሀገራት ለምትኖሩ ሁሉ:-
መሰረታዊ የአብነት ትምህርት ለራሳችሁም ሆነ ለልጆቻችሁ መማርና እና ማስተማር ለምትፈልጉ ሁሉ ሙሉ በሙሉ በቨርችዋል (zoom or google meet) የሚሰጥ ትምህርት ተጀመርዋል።
ትምህርቱን ልዩ የሚያደርገው ደሞ አንድ ለአንድ የሚሰጥ የአብነት ትምህርት በመሆኑ ተማሪው በሚፈልገው ቀንና ሰዐት የሚሰጥ መሆኑ ነው።
ልጆቻችሁን ዲያቆናት ለማድረግ አመቺ በሆነ ሁኔታ የተዘጋጀላችሁን ይህን እድል ይጠቀሙበት።
“ካህናት ሁኑ፣ ጸልዩ፣ ቀድሱ”
ፍላጎት ያላችሁ በውስጥ መልዕክት አስቀምጡልኝ
@girum6123 @kid121921

👍2❤1
የጾመ ኢየሱስ ሱባዔ (ዐቢይ ጾምን) አስመልክቶ የቅዱስ ፓትርያርኩ መልዕክት::
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤
#Ethiopia| በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ ፤
የዲያብሎስን የፈተና ወጥመዶች በጣጥሶ በድል አድራጊነት የተገለጠው ጌታችን ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት የጾመ ኢየሱስ ሱባዔ አደረሰን አደረሳችሁ!
“አኮ በኅብስት ክመ ዘየሓዩ ሰብእ አላ በኵሉ ቃል ዘይወፅእ እምኣፉሁ ለእግዚአብሔር፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም” (ማቴ.፬÷፬)
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ ሳይውል ሳያድር ወዲያውነ ወደ በረኻ በመሄድ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ፡፡
በአርባዎቹ ቀናት ሁሉ በቀንም ሆነ በሌሊት ምንም አልበላም ነበር፣ ካርባ ቀንም በኋላ ተራበ፤ በመብል ስውን ከእግዚአብሔር ጋር ማጣላት ልማዱ የሆነ ዲያብሎስም መራቡን ኣይቶ ለምን ትራባለህ?
እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ ይሁነ ብለህ እዘዝና ብላ፧ የእግዚአብሔር ልጅ አይደለህምን? ይህንን ማድረግ ኣያቅትህም ብሎ በመብል ምክንያት የሱ ታዛዥ እንዲሆን ፈተነው::
በዚህ ጊዜ የጌታችን መልስ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም” የሚል ነበረ፤
ጌታችን በዚህ አባባሉ የዲያብሎስን ክፉ ሐሳብ የሚንድ እንጂ የእሱ ታዛዥ አለመሆነን ኣሳየ፣ ዲያብሎስ በዚህ ሳያበቃ በትዕቢት በፍቅረ ንዋይና በባዕድ አምልኮ ሊጥለው ደጋግሞ ሙከራ አደረገ፣ ግን አልተሳካለትም፤
በመጨረሻም ጌታ “ሑር እምድኅሬየ ሰይጣን፣ ሰይጣን ከኋላዬ ወግድ" ብሎ እኩይ ተግባሩን ውድቅ ኣድርጎበታል፣ እሱም ተስፋ ቆርጦና በጌታችን መንፈሳዊ ልዕልና ተሸንፎ ሂዶአል::
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
ከጌታችን ጾም የምንወስደው ብዙ ትምህርት አለ፣ ከሁሉ በፊት ሰው በሕይወት መኖርየሚችለው በእንጀራ ብቻ ኣይደለም ብሎናል፣ ይህ ኣባባል በሕይወት ለመኖር እንጀራ አያስፈልግም ማለት ኣይደለም ፧
ሕይወትን ማኖር የሚቻለው በእንጀራ ብቻ እንደ ሆነ አድርገን እንዳናስብ ግን ቃሉ ያስተምራል ይህም በዓለማችን በየዕለቱ የምናውቀው ሓቅ ነው፤ ብዙ ሰዎች እንጀራን ሳያጡ በየዕለቱ ሕይወትን ያጣሉ፤ ምክንያቱም በሕይወት ለመኖር የእግዚአብሔር ቃልም እንጂ እንጀራ ብቻው በቂ አይደለምና ነው::
ዓለማት ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ሁነ ተብለው በቃሉ እንደተፈጠሩ፣ በቃሉም ጸንተው እንደሚኖሩ ኋላም በቃሉ እንደሚያልፉ ሁሉ የስው ሕይወትም በዚህ ቃል ይወሰናል፤
እንጀራ ኖረም አልኖረ ቃሉ በቃ ካለ ያበቃል፣ ኑር ካለ ደግሞ እንጀራ ባይኖርም ይኖራል፤ ስለዚህ በሕይወታችን ወሳኝ ሥልጣን ያለው የእግዚአብሔር ቃል እንጂ፣ እንጀራ ብቻ አለመሆነ ጌታችን በዚህ አስተምሮናል::
ከዚህም ሌላ የዲያብሎስን ፈተናዎች እንዴት በድል ማለፍ እንደምንችል ጌታችን በተግባርኣሳይቶናል፣ ጌታችን ዲያብሎስን ያሸነበፈበት ስልት በመንፈስ ልዕልና እንጂ በዱላም፣ በካባድ መሳሪያም ኣይደለም፣ አለመሆነንም የድርጊቱ ሂደት በግልጽ ያመለክታል፤ እንግዲያውስ እኛም ዲያብሎስን የምናሸንፈው በዚህ የመንፈስ ልዕልና ነው ማለት ነው::
ይህም ማለት በእግዚአብሔር የተከለከሉትን ግብረ ኃጣውእ እንድንፈጽም ዲያብሎስ ኅሊናችንን ሲገፋፋው፣ ያን ጊዜ ዲያብሎስ ሊፈትነን እየከጀለ እንደሆነ መንቃት ያስፈልገናል::
ጌታችን እንዳሳየንም ለክፉው ግብረ ኃጢኣት የእሺታ መልስ ሳይሆን የእንቢታ ግብረ መልስ መስጠት ይገባናል ማለት ነው፤ ይህንን ኣቅዋም የሕይወታችን ቀዋሚ መርሕ ካደረግን፣ ዲያብሎስ እየተሸነፈ፣ እኛም እያሸነፍን እንኖራለን፣ ይህንን ስንለማመድ ሓሳባችን ወይም መንፈሳችን ከዲያብሎስ በላይ የላቀና የተራቀቀ ይሆናል !
ዲያብሎስ ረቂቅ ነው፤ የሚጣላንም ረቂቁን አእምሮኣችን በመጠቀም ነው: እኛም እሱን መዋጋትና ማሸነፍ የምንችለው ረቂቁ ኣእምሮኣችን ከሱ የላቀና የረቀቀ ኣድርገን በመጠቀም መሆኑን መገንዘብ ይገባል ይህን ካደረግን እሱ በኛ ላይ አቅም ኣይኖረውም::
• የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
ጾመ ኢየሱስ እያልን በየዓመቱ የምንጾመው የታላቱ ጾማችን ዓላማ ዲያብሎስን ለማሸነፍ ነው፤ የዲያብሎስ ማሸነፊያ ስልት የመልካም ጎሊና ልዕልና ነው!
ሰውነታችን በመብልና በመጠጥ ሊደነድን መልካም ኅሊና በውስጣችን ዓቅም ያጥረዋል፣ መልካም ኅሊና ሲያጥረን ዲያብሎስ ዘው ብሎ ይገባና ወደ ክፉ ኅሊና፣ ከዚያም ወደ ግብረ ኃጢኣት ይወስደናል፣ በዚህ ጊዜ እኛ ተሸናፊዎች እሱ ኣሸናፊ ይሆናል፣
በአንጻሩ ደግሞ ስውነታችን ከመብልና ከመጠጥ ሊለይ መልካም ኅሊና፤ ቍጥብነት፣ ማስተዋልና ማመዛዘን በውስጣችን ትልቅ ጉልበት ያገኛሉ :
እነሱ ጕለበቱ ማለት ዲያብሎስ መግቢያ አጣ ማለት ነው፤ እሱ ካልገባ ግብረ ኃጢኣት አንፈጽምም፣ በዚህ ጊዜ ዲያብሎስ ተሸናፊ እኛ ኣሽናፊዎች እንሆናለን፤ ስለሆነም ጾምን የምንጾመው በዚህ ስልት ዲያብሎስንና ግብረ ኃጢአትን ለማሸነፍ ነው::
ከዚህ አኳያ ዲያብሎስን ለማሸነፍ መጾም ግድ ስለሆነ ጌታችን በከፈተልንና ባሳየን መንገድ እንጾማለን፣ እንግዲህ በወርኃ ጾም ከመልካም ኅሊና የሚመነጭ መልካም ስራ ማከናወን ግድ ይለናል።
ምክንያቱም ጾምን የምንጾመው መልካም ኅሊና ኖሮን ለእግዚአብሔር ለመታዘዝና ለመገዛት፤ ከዚያም ከቃሉ በተነገረን መሠረት የተራቡትን ልንመግብ፣ የተራቈቱትን ልናለብስ፣ የተጣሉትን ልናስታርት፣ ፍትሕ ያጡትን ፍትሕ እንዲያገኙ ልናደርግ፣ ለንኡሳን የሕብረተ ሰብ ክፍሎች የተለየ ትኵረት ልንሰጥ፣ እኩልና ፍትሓዊ የሀብት ክፍፍል በሰው ልጆች መካከል ልናረጋግጥ፣ ሰብኣዊ ክብር እንዳይነካ ጦርነት፤ ጥላቻ፤ አደገኛ የቃላት ውርወራና መነቃቀፍ እንዲቀርልናደርግ ነው!
በዚህ መንፈስ ጾሙን ከጾምን ጾማችን ግቡን መትቶአል፤ ዲያብሎስም ተሸንፎአል ማለት ነው፤ ስለሆነም በዚህ መንፈስ ጾሙን ልንጾም ይገባል፡።
በመጨረሻም-
ወርኅ ጾሙን የተራበውን በመመገብ የተራቈተውን በማልበስ በኃላፊነት ያለን የኅብረተሰብ መሪዎችም ፍትሕንና እኩልነትን በማስፈንና ከነገሮች ሁሉ በፊት ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ በመስጠት ጾሙን እንድናሳልፍ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን::
መልካም ወርኀ ጾም ያድርግልን።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አሜን!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም
===***===

👍2🙏2
በነገረ ሃይማኖት ከውስጥ ወደ ውጭ ማየት አለብን ስንል፥
--
1.ራሱን የቻለ ሲኖዶስ አለን፣ ከሥሉስ ቅዱስ በታች በሥሩ ነን፣
2.የኢኦተቤክ የተቀበለችውን ይዛ በማቆየት ((preservation) ግሩም ሪከርድ እንዳላት እናምናለን፣
3.የቅዳሴ ቋንቋችን (liturgical language) የሆነው ልሳነ ግእዝ (እነዚያ Ethiopic የሚሉት) የጥንታውያን መዛግብትን ቅጂ በመያዝ በዓለም ክርስትና ላይ የተከበረ ቦታ አለው፣
4.በሃይማኖት ቀውሶች ያለመበገርና ክርስትናው ወደ አናሳነት እንዳይቀየር በመጋደል በአፍም፣ በመጽሐፍም፣ በሰይፍም ተመክሮ አለን፣
5.ጳጳስ ማስመጣት ማለት እምነት ማስመጣት እንዳልሆነ ማሳያዎች አሉ:- ጳጳሳቱን አስገድዶ ለማስገረዝ እስከ መሞከርና ቀዳሚት ሰንበትን እንዲያከብሩ እስከማስገደድ፣ የጳጳሳቱን እምነታቸውን ከመመርመር እስከ ማሻር፥ ብሔራውያን ጉባኤያትን ያለግብፅ ጳጳስ በራስ ሊቃውንት እልባት መስጠት፣ ለሚጠይቁን የሃይማኖት መግለጫዎችን የማዘጋጀት የተመዘገበ ታሪክ አለን።
--
ስለዚህ ከውስጥ ወደ ውጭ እናያለን ብንል ትምክሕት ሳይሆን ባመኑት መቆም ፣ በተፈተነ መሠረት መጽናት ነው።
✍️በአማን ነጸረ

👏2
ከኤፌሶን ጉባኤ (431) ታዳሚዎች አንዱ የነበረው ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘእንቆራ - Theodotus of Ancyra (d. before 446)- እመቤታችን እንዲህ ያመሰግናል። የቅዱስ ያሬድ ወይም የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መጻሕፍትን እንደማንበብ ነው፦
"Innocent virgin, spotless, without defect, untouched, unstained, holy in body and in soul, like a lily-flower sprung among thorns, unschooled in the wickedness of Eve, unclouded by womanly vanity... Even before the Nativity, she was consecrated to the Creator .... Holy apprentice, guest in the Temple, disciple of the law, anointed by the Holy Spirit, clothed with divine grace as with a cloak, divinely wise in your mind; united to God in your heart. ... Praiseworthy in your speech, even more praiseworthy in your action .... Good in the eyes of men, better in the sight of God."
***
(Theodotus of Ancyra, Homily 6, II)
🔁"ንጽህት ድንግል ፣ መርገም የሌለባት ፣ እድፈት ያላገኛት በሥጋም በነፍስም ቅድስት የምትሆን ፣ በእሾህ መካከል የወጣች አበባ ፣በሔዋን ክፋት ያልተጎበኘች ፣ በሴት ከንቱነት ያልተሸነፈች ከመጸነሷ በፊት ገና( በማኅጸን ሳለች) ለእግዚአብሔር የተለየች ነች።"
"እድፈት ያላገኛት በሔዋን ክፋት ያልተጎበኘች በእሾሕ መካከል የበቀለች" የሚሉት ገለጻዎች ድቀት የሌለበትን ሥጋን መያዟን የሚያሳዩ ናቸው።
"a lily-flower spring among the thorns" - 'ጽጌ ዘሠረጸት በማዕከለ አስዋክ' ... ህምምም .. ወይ ግሩም 🤔 .. እግዚአብሔር ይስጥልኝ ወንድማችን ቤኪ።
✍️ዲ/ን በረከት አዝመራው

❤4⚡1👍1
ስለሌሎች ስንናገር
ስለኦርቶዶክሳዊ ነገረ ዕውቀት የገባሁትን ቃል አልረሳሁትም። ነገር ግን ይህች ብትቀደም ወደድኩ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ወደ ግሪክ በሔዱበት ወቅት የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የእኛ ፓትርያርክ ቀድሰው አማኞቻቸውን ያቆርቡበት ዘንድ አንድ ቤተ ክርስቲያን በውሰት ይሰጣሉ። የታሰበው አገልግሎት የተፈጸመበትን ይህን ቤተ መቅደስ ግን ግሪኮች ከዚያ በኋላ አልተጠቀሙበትም። እንደተዘጋ ትተውት ቀሩ እንጂ። ይህን ያደረጉበት ምክንያት ደግሞ ኦሪንታል ኦርቶዶክሶች አውጣኪያውያን ናቸው፤ ስለዚህ እነርሱ አርክሰውታል ብለው በማመን ነው። ይህን የሰማሁት የዛሬ 16 ዓመት ወደ ግሪክ ለአገልግሎት ብቅ ባልኩበት ወቅት እዚያው ግሪክ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ነበር።
ግሪኮች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ምሥራቅ ኦርቶዶክሶች ስለኦሬንታል ኦርቶዶክሶች የነበራቸው አመለካከት ወይም እምነት ይህ ነበር። ይህ የሆነበት ምክንያትም በ448 ዓ.ም. በአውሳብዮስ ከሳሽነት በፍላብያኖስ ዘቁስጥንጠንያ መሪነት ወደ 40 የሚጠጉ ሊቃነ ጳጳሳት ተሰብስበው ነበር። ክስሱ አውጣኬን ባሕርየ መለኮት ባሕርየ ሥጋን ዋጠው መጠጠው ስለዚህ አንድ ንጥል ባሕርይ (Monophysite) ነው ብሎ አስተምሯል የሚል ነበር። በርግጥ ቀጥታ የተጠየቃቸው ጥያቄዎች ሌሎች ነበሩ። በጉባኤው ላይም አውጣኬ በአካል አልተገኘም ነበር። ላቲኖች እንደሚሉት ከሆነ ያልተገኘው የገዳም አበምኔት እንደመሆኑ መጠን በዓቴን ለቅቄ አልወጣም በማለቱ ነበር። በዚህም ምክንያት ይህን ታምናለህ አታምንም እየተባለ የተጠየቀው በመልእክተኞች ሲሆን መልእክተኞቹም ዮሐንስ የሚባል ቄስ እንድርያስ እና አትናቴዎስ የሚባሉ ዲያቆናት እንደነበሩ መዝግበዋል። እነርሱን ወደዚህ ድምዳሜ የወሰዳቸው ግን ጌታ ሰው ከሆነ በኋላ ሁለት ባሕርይ መሆኑን ታምናለህ? ተብሎ ሲጠይቅ እኔ እንዲህ አልልም ቅድመ ተዋሕዶ እንጂ ደኅረ ተዋሕዶ እንደ ቄርሎስ አንድ ባሕርይ እላለሁ እንጂ ሁለት አልልም በማለቱ እነርሱ ሁለት አልልም አንድ እንጂ ካለ አንደኛው ባሕርይ ጠፍቷል ማለቱ ነው የሚል ትርጉም ራሳቸው ሰልሰጡ ነበር። በዚህም ላይ የጌታ ሰውነት እንደ እኛ አይደለም ብሏል ብለው ዲያቆናቱ የሰጡትን ምስክርነት ይዘው ነበር ያወገዙት፤ እንዳነበብኩት።
አውጣኬ ደግሞ እኔ እንደዚህ ብዬ አላስተማርኩም፤ ያወገዙኝ ያለአግባብ ነው ብሎ ለንጉሡ ቴዎዶስዮስ ካልዓይ ክስ አቀረበ። ንጉሡም የእስክንድርያው ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ ባለበት እንዲታይለት እርሱን በማወገዝ ግንባር ቀደም የነበሩት እና ልዮን፣ ፍላብያኖስ እና ሊሎች አራት ያልህ ደግሞ በዳኝነት በዚህኛው ጉባኤ እንዳይሰየሙ አዘዘለት ። ቅዱስ ዲዮስቆሮስም ሊቃነ ጳጳስት እና ሊቃውንት ተሰብስበው የአውጣኬ ክስሱ እንዲሰማ እና የርሱም መልስ እንዲደመጥ በ449 ዓ.ም. ጉባኤ ጠራ። በጉባኤውም ወደ 127 ጳጳሳትና ሊቃውንት ተገኙ። አውጣኬን እንዲወገዝ ያስተባበሩት እነ አውሳብዮስ ፣ ፍላብያኖስ ግን ቢጠሩም ሳይገኙ ቀሩ። ጉባኤው ግን ተካሔደ። አውጣኬም ተጠየቀ። እርሱም እነርሱ ያወገዙኝ እኔን ብሏል የሚሉትን አላልኩም፤ እኔ አንድ ባሕርይ ነው ብዬ አምናለሁ። እምነቴ ቄርሎስ እንዳስተማረው እንጂ እነርሱ እንደሚሉት አይደለም ብሎ ቃሉን ሰጠ። በዚህ ምክንያት ይህ በቅዱስ ዲዮስቆሮስ የሚመራው ጉባኤ አውጣኬን ከግዝቱ ፈታው።
በዚህ ጊዜ ቀድመው ያወገዙት ሰዎች ዲዮስቆሮስ አውጣኬን ከግዝቱ የፈታው ራሱ ዲዮስቆሮስ እንደ እርሱ ቢያምን ነው ብለው ማስወራት ጀመሩ። እንዲያውም ልዮን ይህን ጉባኤ የሚጠራው ጉባኤ ፈያት እያለ እንደነበር ጽሑፍ ማንበቤን አስታውሳለሁ። አስወርተውም አልቀሩ የ451ዱ ጉባኤ ኬልቄዶን እንዲጠራ እና ሀሳቡ እንኳ በአግባቡ ሳይደመጥ ዲዮስቆሮስ እንዲወገዝ ተደረገ። በዚህ ምክንያት እስከቅርብ ጊዜያት አንዳንዶቹም እስካሁን ድረስ ኦሬንታሎቹን አውጣኬያውያን እንደሆንን ያምናሉ። የሚያስገርምም የሚያሳዝንም ነገር ነው።
አንዳንዶች ሀሳባቸውን በታወቀ መንገድ መቀየር እና ማስተካከል የጀመሩት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ (አሁን ዩኒቨርሲቲ) የመጀመሪያው ዲን የነበሩት ሕንዳዊው V.C. Samuel የተባሉት ሊቅ ለሦስተኛ ዲግሪ መመረቂያ ጥናታቸው መጽሐፍ ሆኖ ከታተመ በኋላ ነበር። የኒህ አባት መጽሐፍ “the Council of Chalcedon Re-Examined” – ‘ጉባኤ ኬልቄዶን እንደገና ሲመረመር’ በሚል ርእስ በሠሩት ጥናት ላይ ይህን ንጥል አንድ ብቻ ባሕርይ /monophysite/ የሚለውን እንኳን ዲዮስቆሮስ ሊቀበለው ይቅርና አውጣኬም ስለማለቱ ማረጋገጫ አላቀረባቸሁም። እርሱ ያላለውን ብሏል ብላችሁ አወገዛችሁት እንጂ እርሱ እንዲህ ነው የማምነው ብሎ ልክ አርዮስ፣ ንስጥሮስ፣ መቅዶንዮስ እንዳደረጉት አልተከራከረም ፤ ሀሳቡንም አላስረዳም። እርሱ እናንተ የምትከስሱበትን ለማለቱ ማስረጃ የላችሁም። አላልኩም ፤ እኔ የማምነው እንደ ቄርሎስ ነው ስለማለቱ ግን ማስረጃ አለ። ኦሪነታሎች አንድ ባሕርይ የሚለውን የምንጠቀመውም በተዋሕዶ እንጂ እናንተ እንደምትሉን ሞኖፊሳይት አይደለንም፤ አይመለከተንም፤ ይህን ለማረጋገጥ ከፈለጋችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስሟን ብቻ ብትመለከቱ ይበቃችኋል። ተዋሕዶ የሚለውን የስሟ መጠሪያ አድርጋዋለችና የሚለውን ሀሳብ በሰፊ ጥናት ካሳዩ በኋላ ብዙ ሊቃውንቶቻቸው ስለኦሬንታሎች ያላቸውን የተሳሳተ አመለካከት አስተካክለዋል።
በቅርብ ጊዜ ደግሞ የእኛው ቀሲስ ዶክተር መብራቱ ኪሮስ የማስተርስ ጥናቱን በዚህ ዙሪያ በመሥራት የኦሬንታሎቹ እምነት ምሥራቆቹ እንደሚሉን እንዳልሆነ ጥሩ አድርጎ አስረድቷል። የቀሲስ ዶክተር መብራቱ ትኩረቱ ታሪኩ ላይ ሳይሆን ቀጥታ ነገረ እምነታችን ወይም ዶክትሪኑ ላይ ነው። የቀሲስን ጥናት የፈለገ “Miaphysite Chrystology: An Ethiopian Perspective” በሚል ረእስ አፈላልጎ ማግኘት እና ማንበብ ይቻላል። እነዚህን ሁለቱን እንደምሳሌ አነሣሁ እንጂ ሌሎችም ይኖራሉ።
ይህም ሆኖ ብዙዎች ገዳማውያኑ እና ዓለም አቀፍ ጥናቶችን ለማወቅ ወይም እኛን ኦሬንታሎችን ቀርበው እምነታችንን በትክክል ያልተርዱት ግን እስካሁን ድረስ እኛን የሚያዩን አውጣኬያውያን አድርገው ነው። እንዲያውም አንድ ወንድም እንደ ነገረኝ በአቶስ ተራራ (Mount Athos) የኖሩት እና አሁንም ያሉት በኃይለኛ ምናኔ እና ብቃት የሚመሰገኑት የግሪክ ኦርቶዶክስ አባቶች እስካሁን ድረስ ኦሬንታሎችን አጥፋ የሚል ጸሎት ሁሉ አላቸው ብሎ ነግሮኛል። እኔም ራሴ ባለፈው ዐሥር ዓመት ውስጥ አሜሪካን ሀገር ያለ አንድ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መካነ ድር ላይ የአውጣኬን እምነት የያዙ ቤተ ክርስቲያኖች አሁንም አሉ፤ ለምሳሌ የኮፕቲክ እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብሎ ጽፎ አንብቤ እንዴት በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች በቀላሉ መረጃ በሚያገኙበት እንዲህ ትጽፋለህ ብዬ ጽፌለት ጽሑፉን የጻፈው ቄስ ይቅርታ ጠይቆ አስተካክሏል።

👍3
እነዚህ አጋጣሚዎች ለእኔ እጅግ አስተማሪዎች ነበሩ። እውነት ለመናገር ስለሌሎች ከመናገር በፊት እነዚያ አካላት የሚሉትን በትክክል ማወቅ በእጂጉ አስፈላጊ መሆኑንና ስለተለያዩ ብቻ እያነሡ መለጠፍ፣ እንደ ልብ መናገር በጣም አደገኛ መሆኑን የተማርሁት ይህን ከመሰሉ ስለእኛ ከተነገሩ እጂግ የተሳሳቱ ትምህርቶች ፣ ጽሑፎች እና አመለካከቶች ነው። ከዚያም ወዲህ ትላልቅ የሚባሉት የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ሊቃውንት ጽሑፎች ውስጥ ሳይቀር ይህን የመሰለውን ስለእኛ ያላቸውን የተሳሳተ እምነታቸውን ሳይ በእጂጉ አዝናለሁ፤ በዚያ ምክንያትም የሥራዎቻቸውን ደኅና ነገር ሁሉ በዚያው ዓይን እያየሁ እንድጠራጠራቸው እሆናለሁ።
ይህን ሁኔታ በሌሎችም አይቻለሁ። በተለይ በእስልምናው ሐዲዝ ላይ እኛን መነኮሳቶቻቸውንና ሊቃውንቶቻቸውን ያመልካሉ ብለው የጻፉት ሁልጊዜ ሲያስቀኝ እና ሲያስገርመኝ ይኖራል። እንዲህ ያለው ችግር በርግጥ በእኛም ዘንድ አለ። በተለይ ካቶሊኮች እመቤታችንን ኃይል አርያማዊት ናት ይላሉ የሚለው አሳፋሪ ነገር እስካሁንም የሚናገሩት ሞኞች አሉ። በነገራችን ላይ ለእመቤታችን ወላጆች በተለይም ለቅድስት ሀና ብዙ ቤተ ክርስቲያን በመሰየም የካቶሊኮችን ያህል የሚኖር አይመስለኝም። ተመልከቱ እንግዲህ ይህ ሁሉ ባለበት ነው እመቤታችንን ኃይል አርያማዊት ናት ይላሉ የሚል የስሚ ስሚ ወሬን በአደባባይ ሳይቀር በድፍረት እንናገር የነበረው።
ዋናው የፈለግሁት ነገር ሌሎች እኛ ያልሆንነውን ብለዋል ሲሉ እኛን የሚሰማንን ያህል ወይም ከዚያም በላይ የናም የግምት ንግግር ሌሎቹንም ልክ እንደእኛ እንዲሰማቸው ያደርጋል። በግሌ ስለሌሎች በድፍረት መናገር ምን ያህል ስሐተት እንደሆነ እና እኔን የእነርሱ ደጋግሞ እንደሚያሳዝነኝ እነርሱንም የእኛ እንዲህ ሊያደርጋቸው እንደሚችል እና ስለማንኛውም አካል ስለምንናገረው ነገር በእጂጉ መጠንቀቅ እንዳለብኝ የተማርኩት ከእነዚህ አጋጣሚዎች ነበር።
የሚያሳዝነው ግን አሁንም እየሆነ ያለው እንደዚያው መሆኑ ነው። አሁንም ሰዎች ራሳቸው ስለሚያምኑት ነገር ከሰዎቹ በላይ ሆነው እንዲህ ነው የሚያምኑት እያሉ መናግር እጂግ በጣም አደገኛ ስሕተት ነው። የተጠራጠረ ሰው ማድረግ ያለበት መጠየቅ ነው። ከዚያ ራሳቸው የተጠየቁት አካላት እምነታቸውን አስተሳሰባቸውን አረዳዳቸውን በግልጽ ያስረዱ። እዚይ ላይ ምን ለማለት እንደፈለጉ ደጋግሞ እየጠየቁ ማጣራት እና በትክክል መረዳት መቅደም አለበት ። ካለበለዚያ ዲዮስቆሮስ አውጣኪያዊ ነው ብለው እስካሁን በስሕተት እንደሚያምኑት እና ስለማናምነው ነገር ከእኛ በላይ ሆነው እንዲህ ነው የምታምኑት እንደሚሉን አንዳንድ ምሥራቃውያን ከመሆን የዘለለ ጠቀሜታ የለውም።
✍️ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ

👍5
Forwarded from መነ ይብልዎ
👌4❤3👍3
ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ዕውቀትን በተመለከተ
አንድ ወንድም ከቲክታክ ውይይት ሰማሁት ብሎ የጠየቅኝ ጆሮጅዬን ጭው ነው ያደረገኝ። አንዳንድ ተወያዮች እድገት ያመጡ እና ከፍ ያለ ዕውቀት ላይ የደረሱ እየመሰላቸው ነው መሰል በአብና በወልድ መካከል ገብተው ሁሉ አስተያየት እየሰጡ መሆኑን (የጠየቀኝ ሰው ያለኝን ቃለ በቃል መድገም አልፈለግሁም) ከጥያቄው ተረድቻለሁ። ኪሩቤል ቀና ብለው ወደማያዩት ዙፋን፣ ሱራፌል በሁለት ክንፎቻቸው እግራቸውን በሁለት ክንፎቻቸው ፊታቸውን ሸፍነው ሁለት ክንፎቻቸውን ደግሞ ዘርግተው ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው ከማመስገን ውጭ ወደ ማይደፍሯት ዙፋን ወይም ገናንነት መግባት የሚፈልግ ሕሊና በፍጥነት በንስሐ መመለስ አለበት ብዬ አምናለሁ።
አንድ ወንድም አንድ ጊዜ እንዲህ ያለ ነገር ገጥሞት ነበር። ከጓደኛው ጋር ወደ ጎንደር በሔዱበት ወቅት ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራን ሰላም ለማለት በገቡበት ጥያቄ አነሣ። ምሥራቅ ኦርቶዶክሶች በአንድ አካል ሁለት ባሕርይ የሚሉት ባሕርየ ትስብእት ከባሕርየ መለኮት ጋር ከተዋሐደ ፣ ወልድ ደጎሞ በባሕርይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ስለሆነ እንዴት ሊይድርገው ነው ይላሉ ብሎ ይጠይቃል፤ እንደማስታውሰው ነው። ሊቀ ሊቃውንትም እርሱ ከበደኝ አላለ እናንተን ምን አስጨነቃችሁ ብለው መለሱለት ብሎ የነገረኝን ባስታወስኩ ቁጥር እደነቃለሁ። (በአጻጻፍ የሳትኩት ካለ ሓላፊነቱ የእኔ ነው)። መልሱ ሁልጊዜ ያስደስተኛል። ምክንያቱም በሥላሴ አንድነት ውስጥ ገብታ ቦታ ለማካፈል የምትደፍር ኅሊና እንዴት ያለች ደፋር እና አላዋቂ ናት በእውነት ። ሙሴ እንኳ ወደ ዕፀ ጳጦስ ለመጠጋት ጫማውን እንዲያውልቅ ታዝዞ ነበር። የቀረበውም በረዓድ እና በመንቀጥቀጥ ነበር። ምሳሌው ለተመረጠው ለሙሴ እንኳ እንዲያ የሚያስፈራ ከሆነ አማናዊው የተዋሕዶ ምሥጢርም ይልቁን ምን ያህል ትሕትና እና ጥንቃቄ ይፈልግ ይሆን?
የተገለጠና እና በትክክል የምናውቀው እንኳ ቢሆን እንዲህ ያለው ይዘት በፍጹም ለማኅበራዊ ሚዲያ የሚሆን አይደለም። እውነቱን ለመናገር “የተቀደሰውን ለውሾች አት ስጡን” ለምን አንጠብቀውም የሚለውን እጠይቅና የተቀደሰውን ስለማናውቀው ይሆናል በሚል መልስ እንደገና እቆማለሁ። በርግጥም የምናውቀው አይመስለኝም። ይህ ሁሉ እንግዲህ ኦርቶዶክሳዊውን ነገረ ዕውቀት በመጠቆም ለማሳሰብ እንደ መግቢያ ያነሣሁት ነው።
ሴባስቲያን ብሮክ የሚባለው የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የኦሬንታል በተለይም የሶርያ ኦርቶዶክስ አባቶችን ጽሑፎች በተመለከተ ብዙ ካጠና በኋላ ሀሳቦቹን ካጋራባቸው መጻሕፍት አንዱ ሰሞኑን በሕሊና በለጠ ብርህት ዓይን ተብሎ የተተረጎመውን The luminous Eye የተባለ መጸሐፍ ጽፏል። ብሮክ በዚህ መጽሐፉ ካነሳቸው መሠረታዊ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የምሥራቃውያን (ኦሬንታል) አባቶች ትምህርታቸውን እንደ ምዕራቡ በነገረ ጉዳይ የተደራጀ (Systematic) ለምን አላዳረጉትም የሚለው ይገኝበታል። (ይህን ስጽፍ መጽሐፉን እያየሁ ስላልሆነ በትክክል ባልገልጸውም አሁን) እርሱ የሚለው የኦሬንታል ሊቃውንት የምዕራብ ሊቃውንት ያደረጉትን ማድረግ ስለማይችሉ ወይም አቅም ስለሌላቸው ሳይሆን ስለኦርቶዶክስ ነገረ ዕውቀት ባላቸው መረዳት ምክንያት ነው። ለምሳሌ የምዕራብ ሊቃውንት አንድን ጉዳይ ብያኔ (definition) ሰጥተው ይጽፋሉ። ለምሥራቃውያን ደግሞ ብያኔ ችግር ያመጣል።
ምክንያቱም መበየን ማለት ለነገሮች ድንበር መሥራት፣ መከለል፣ መለየት፣ መወሰን ማለት ነው። ነገረ ሃይማኖት ደግሞ ለሰው ልጅ አእምሮ በሚመጥን ከእግዚአብሔር የተገለጠ መለኮታዊ ሀሳብ ነው። ያን መልኮታዊ ሀሳብ ደግሞ ጥልቀቱን መወሰን እና ለዚያም ድንበር ማበጀት አይቻልም። የሰው ቋንቋም ለሰው ማስረዳት ቢችልም ነገረ አምላክን ወስኖ መያዝ ግን አይችልም። ስለዚህ እግዚአብሔር በገለጠልን መጠን እናብራራዋለን (እንተረጉመዋለን) እንጂ ልንወስነው ወይም በብያኔ ልንዘጋው አንችልም የሚል እምነት ወይም አረዳድ ስላላቸው ብያኔ እና ብያኔያዊ አካሔድ አይጠቀሙም የሚል ማብራሪያ ይሰጣል። ይህን ሀሳብ በየንታ እሸቱ ርጢን መጽሐፍ መቅድም ላይ ለመጠቆም ሙከራ አድርጊያለሁና ያንንም ማየት ይቻላል።ይህን እውነታ ከእኛም ሆነ ከሌሎች የኦሬንታል አብያተ ክርስቲያን ትውፊት መረዳት ይቻላል።
ኦሬንታሎቹን ብቻ ሳይሆን እኔ እስካየሁት ድረስ ምሥራቅ ኦርቶዶክሶችን ከምዕራቡ (ከካቶሊክም ከሮቴስታንትም) ከሚለዩን መሠረታዊ ነገሮች አንዱ ይህን የሚመለከት ነው።
ሌላውና መሠረታዊው የኦርቶቶዶክስ ነገረ ዕውቀት የሚያጠነጥነው ደግሞ መገለጥ ላይ ነው። መገለጥ በሁሉም ክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ቢሆንም በሮማ ካቶሊክ በተለይም ደግሞ ከቶማስ አኲናስ መምጣት በኋላ (በእምነት መግለጫዋ ላይም እንዳለው) የሰው አእምሮ ወይም የመረዳት ችሎታ (reason) ብቻውን እግዚአብሔርን በርግጠኝነት ለማወቅ በአጠቃላይ ሃይማኖትን ለማወቅ በቂ ነው ብለው ያምናሉ። (ይህን ሀሳብ Thinking Orthodox እና የመሳሰሉትን መጻሕፍት አንብቦ የበለጠ መረዳት ይቻላል።)
በሁለቱም ኦርቶዶክሶች ግን ይህ ሀሳብ ተቀባይነት የለውም። እንደዚህ ከሆነ ሃይማኖት ከሳይንስ የሚለይበት መሠረታዊ ነገር ይጠፋል ወይም ያንሣል። ይህን ጉዳይ አሁንም በስፋት መግባት ባልፈልግም ኦርቶዶክሳዊው ነገረ ዕውቀት ከዚህ በጅጉ የራቀ እና የተለየ መንገድ ያለው ነው። ምንም እንኳ ሲስተማቲክ ቲዖሎጂ በእኛም ተቋማት እየተሰጠ እና በዚሁ መንገድ መጻሕፍት እየተጻፉና እየተዘጋጁ ቢሆንም መሠርታዊ ጥንቃቄ እና ኦርቶዶክሳዊውን ድነበር መጠበቅ ግን በብዙ የምሥራቅ ሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ብቻ ሳይሆን የተለመደም ጭምር ነው።
በኦርቶዶክሳዊያን ዘንድ ደግሞ በሰው አእምሮ አድሮ የሚናገረው ራሱ እግዚአብሔር ነው። ይህም በጥልቅ መግቦቱ ለሰው ልጆች በመግለጥ የሚያሳየው ነው። ሰዎች በቅጥነተ ኅሊና ማለትም አእምሮአቸውን በማራቀቅ ብቻ ሊደርሱበት የሚቻላቸውም አይደለም። ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ምእመናን “እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤” /1ኛ ቆሮ 3 ፤ 1 – 2/ የሚላቸው በክርስትና ለመንፈሳዊ ሕይወት ሕጻናት ስለሆኑ እንጂ ለእውቀት ለፍልስፍና እና ለአመክንዮ ሕጻናት ሆነው አልነበረም ባዮች ናቸው። ስለዚህ በመንፈሳዊ ሕይወት በተጋድሎ ውስጥ በምትገኝ የማትቋረጥ መገለጥ የሚሰጥ እንጂ የሰው አእምሮ የማሰብ ችሎታ ብቻውን ይደርስበት ዘንድ አይቻልም ብለው ያምናሉ። በተለይም ደግሞ መጀመሪያ ቅዱስ ወግሪስ እንደተናገረው የሚታመነው “እውነተኛ የነገረ ሃይማኖት ዐዋቂ የሚጸልይ ሰው ነው” የሚለው አባባል የሰው የሃይማኖት ዕውቀት የመረዳት ችሎታ ላይ እንዳያርፍ መጠበቂያ አጥራቸው ነው።
የኦርቶዶክሳዊ ነገረ ዕውቀት ሦስተኛው መሠረታዊ መለያ ደግሞ ሃይማኖታዊ ዕውቀት በመሠርቱ ለሰዎች ድኅነት ቅድሚያ የሰጠ (Pastoral) መሆኑ ነው። ይህም ማለት ጉዳዮች የሚብራሩት የሚተረጎሙት የሚሰበኩት የሰውን ድኅነት ቅድሚያ ሰጥተው እንጂ ለዕውቀት እና ለርቃቄ ተብለው አይደለም። ከዚህ የተነሣ ለድኅነት ከሚጠቅመው ውጭ እንኳን እንዳሁኑ ማንም ሊያየው በሚችል ሚዲያ ይቅርና ለኦርቶዶክሳዊያን ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን የጉባኤ ቀለም ለመናገር እና ለማራቀቅ የሚደክም የለም፣ ሲያጋጥምም አይመሰገንም። ምክንያቱም ለድኅነታቸው

👍2
ሳይሆን ለመመስገን፣ ለምደነቅ ወይም ለመከበር ተብሎ ስለሚሆን እና እነዚህም ጠባያት ደግሞ የሥጋ ጠባዮች ስለሆኑ እነዚህ መግቢያ አድርጎ ሰይጣን እንዳያስተውም ስለሚፈራ ነው።
ሁልጊዜም ቢሆን በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ችግሮች የሚፈጠሩት ቲኦሎጂን ወይም ነገረ እምነትን ለአማኞች ድኅነት ቅድሚያ ሰጥቶ ማስተማር ቀርቶ የራስን ፍላጎት ለማርካት በሚደረግ አላስፈልጊ ዕውቀት መሰል ክርክር ውስጥ ነው። ይህ ጉዳይ ከዚህም አልፎ ክርክር በማያስነሡ ጉዳዮች እንኳን የሚነሣው የተለየ ነገር ተናግሮ ማስደነቅና መከበርንም ሆነ ሌላ ነገር ሲፈለግ የሚያጋጥም ስለሆነ ነው።
እንዲያውም ከዚህም አልፎ አሁንም ብዙ ገዳማዊያን ሊቃውንት አንድ መሠረታዊ ሥጋታቸውን ደጋግመው ሲያነሡ አይቻለሁ። ይህም አሁን አሁን ኦርቶዶክሳዊያን ክርስትናን ወደ ዕውቀትነት እያወረዱት ነው የሚል ሥጋት ነው። ይህ ሥጋታቸው ደግሞ ተራ ሥጋት አይደለም። በአሁኑ ጊዜ በርከት ያሉ ኦርቶዶክሳዊያን ክርስትናን ያጠኑታል፣ ለማወቅ ይጥሩለታል፣ ይወድዱታል፤ በዚያም ደስተኞች ይሆናሉ። ከዚህም የተነሣ ወደ እውነተኛው የመዳን ዕውቅት ሳይሸጋገሩ ልክ እንደ አካዳሚክ ዕውቀት በጥናት ላይ ብቻ ተመሥርተው ይቀራሉ። ይህ ባሕል እየሆነና እየተለመደ ስለሔደ ክርስቲያናዊው እውነተኛው ሕይወታዊውን ዕውቀት አካዳሚያዊ ዕውቀት እየተካው ስለሆነ ክርስትና አደጋ ላይ ነው ያለው ይላሉ። ይህን የሚሉበት ምክንያት ክርስቲያናዊ ዕውቀት ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት በማድረግ ከመነገር በላይ ወደ ሆነው ወደ ሚኖረው ዕውቀት ካልተሸጋገረ አካዳሚያዊ ዕውቀት ይሆናል። ከዚህም የተነሣ እንደማንኛውም አካዳሚያዊ ነገር በሰው አእምሮ መረዳት (reasoning) ላይ ይወሰንና ስፉሕ አእምሮ ያላቸው ሰዎች ሲመጡ ያንን የሚያሻሽሉት የሚያስፋፉት፣ ጠባብ አእምሮ ያላቸው ሲይዙት ደግሞ እንደዚያው የሚያጠብቡት ይሆንና በመጨረሻም በሒደት የመበረዝ ፣ የመለወጥ ፣ የመጥፋት አደጋ ይገጥመዋል የሚል ተጨባጭ ሥጋት አላቸው።
የእኛ ዘመን ተሟጋች ትውልድ ደግሞ አብዛኛው መጀመሪያ የተማረው ዘመናዊውን ወይም ምዕራባዊውን ትምህርት ነው። ይህን አስቀድሞ መማር በራሱ ችግር አይደለም፤ ( ሊሆንም አይችልም። እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቅዱስ ባስልዮስ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮ ዘእንዚናዙ እና ሊሎችም ጭምር መጀመሪያ የተማሩት የዓለሙን ፍልስፍና ነውና። የእኛ ትውልድ ግን ከመጠን በላይ ሲስተማቲክ በሆነው አካዳሚክስ ውስጥ ከማለፉ የተነሣ ነገሮችን ሳያውቀው በዚያ መጠን የመበየን፣ ጨርሶ የማወቅ እና አቋም መያዝ ድረስ መድረሱ ችግሩ ብቅ እያለ መሆኑን ያመለክታል ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም ክርስትናን ከትምህርት ከሚገኝ መጠነኛ ዕውቀት በሕይወት ወደሚደረስበት የመረዳት ዕውቀት ካልተሸጋገረ ችግር መግጠሙ አይቀሬ ነው። በሰሚዕ የሚገኝ ዕውቀት እና እምነት መግቢያ በር እንጂ መድረሻ አዳራሽ ወይም ቤት አይደለምና።
ይህ ጉዳይ ራሱን የቻለ ብዙ እንድንማማር የሚያደርግ ስለሆነ ጊዜውና ችሎታው ያላችሁ ሁሉ በዚህ ጉዳይ ሰፋ ያለ ዕውቀት ብታካፍሉን ብዙዎቻቸን መንገዳችንን ለማቃናት ብዙ ይጠቅመናል፤ ጉዳዮችን በአካዳሚ መንገድ እና ዓይን ከማየት፣ አለፍ ሲልም እንደ ፖለቲካ አቋምን ከመለካካት ሊያተርፉን ይችላሉ፤ ሲሆን ሲሆን ደግሞ ወደ መንፈሳዊው ዓለም እንድንገባ እና መንገዳችንን ወደዚያ እንድናደርግ ሊረዱን ይችላሉ ብዬ አስባለሁ።
ከሰሞኑ ውይይቶች በተለይ አስተያየት መስጫ ላይ የማያቸው ጥያቄዎች እና መልሶች ብዙዎቹ ትውልዱ ወደዚህ አካዳሚያዊ የነገረ መለኮት ዕውቀት ሳያውቀውም ቢሆን እያደላ መሆኑን የሚጠቁሙ ይመስለኛል። በእኔ መረዳት ኦርቶዶክሳዊ የነገረ ዕውቀት አቀራረብ ቀርቶ ምዕራባዊ የምነለውንና የራሱ ሥነ ሥርዓት ያለውንም ያንን እንኳ የማያሟሉ፣ የነገሮቹን መቅድማቸውን እንኳ በውል ሳናገኘው አንኳር ጉዳዩ ላይ ገብተን እንደዚያ ያለ አስተያየቶች መወራወራችን በእጂጉ ያስፈራል። ሕያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው በእጂጉ ያስፈራል። እኔን እስከገባኝ ደርሰ ከፍተኛ ድፍረት የተሞላው የአላዋቂ ክርክር ወስጥ መሆናችንን በታላቅ ትሕትና (ነገሩ እንኳ ሳስበው ድፍረትም ጭምር ነው) መጠቆም እፈልጋለሁ።
በማኅበራዊ ሚዲያ ልናደርጋቸው የሚገቡንን ውይይቶች እና ትምህርቶች በተመለከተ እኔ ከጠቆምኳቸው እና ከሌሎቹም መሠረታዊ ትውፊቶቻችን አንጻር በማየት በውስጥ መወያየት እና አቀራረቦችን ማስተካከል ይቻላል፤ ይገባለም ብዬ አምናለሁ። አበቃሁ። መልካም ጾም ይሁንልን።