የእስልምና አስተማሪዎች የክርስትና እና የእስልምና ንጽጽር ትምህርት ማስተማር ከጀመሩ በጣም ቆይተዋል፡፡ ከ1980ቹ አካባቢ ጀምሮ በመጻሕፍት ኅትመት ከዚያም በቪድዮና በድምጽ ጭምር በአደባባይ ሰብከዋል፡፡
በዚህም ክርስትናን እስከቻሉት ድረስ አጥላልተዋል፡፡ በሃይማኖታችን ላይም የሐሰት ክምርም ከምረዋል፡፡ አንድ ነገር ያስመሰግናቸዋል፡፡ የንጽጽር ትምህርት መጀመራቸው!
ሆኖም ግን ንጽጽር ሲባል የራስን አስተምህሮ ጠንቅቆ ከማወቅ ጋር አነጻጽሮ ሐሰት ነው የሚሉትን የሌላውን አስተምህሮም በጥንቃቄ ማወቅ ይገባል፡፡ በእስላሞች ዘንድ ያለው ትልቁ ስህተት ክርስትናን በጭፍኑ ያጥላሉ እንጅ በእውነተኛ ማንነቱ አይሞግቱትም፡፡ አስተምህሮውንም አያውቁትም፡፡ ይህንን ለመረዳት የጻፏቸውን በርካታ መጻሕፍት ማንበብ በቂ ነው፡፡
ለምሳሌ፦ ኢየሱስ ሰው ነው ስለዚህ አምላክ አይደለም ለማለት የሰው ልጅ የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳሉ፡፡ በመጀመሪያ ቃል ነበረ . . . ቃልም እግዚአብሔር ነበረ . . . ያም ቃል ሥጋ ሆነ የሚለውን ግን ማየት አይፈልጉም ፡፡ ተራበ የሚለውን ቀንጭበው የሚራብ ከሆነ እንዴት አምላክ ይሆናል? ይሉናል፡፡ እኔ የሕይወት እንጀራ ነኝ የሚለውንና በ5 እንጀራ በ2 ዓሣ 5000 ሺህ ሕዝብ፣ በ7 እንጀራ በ1 ዓሣ 4 ሺህ ሕዝብ መመገቡን፣ እንዲሁም 12 ቅርጫት ትርፍ መነሣቱን መናጋር ግን አይፈልጉም፡፡ ይህንን የመሰለው በጣም ብዙ ነው፡፡
የሆነው ሆኖ ምንም በሐሰት ቢሆንም እንኳ በመጻሕፍት፣ በሚድያ የንጽጽር ትምህርት ለማስተማር የሄዱበት ርቀት ለእኛ ብዙ ነገሮችን ማያና ማንቂያ ነው፡፡
በጣም የሚገርመው ነገር የንጽጽር ትምህርት የሚያስተምሩበት ተቋም እስከ መገንባት መድረሳቸው ነው፡፡ ይህንንም ወሒድ ዕቅበተ እሥላም ከሚለው የእስልምናና ክርስትና ንጽጽር ጽሑፎችን ፖስት ከሚያደርግ የቴሌግራም ግሩፕ ነው ያገኘሁት፡፡
በእኛ ቤትም በጣም ብዙ መጽሐፎች ተጽፈዋል፡፡ ከተጻፉት መጽሐፎች ግማሾች መልስ ሲሆኑ ሌሎች ግን የእስልምናን ስህተት የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ይኸ ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው፡፡
በርግጥ እነሱ በእኛ በኩል የተጻፉትን ሰብስበው ነው የሚያቃጥሏቸው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ያሳተመውን ሐመረ ተዋሕዶ (2000 ዓ.ም መሰለኝ የታተመ) ሰብስበው ነው ያቃጠሉት፡፡ ቢሆንም ክብሩ ይስፋ! ያልተቃጠሉ መጻሕፍት ነፍ ናቸው፡ ሐመረ ተዋሕዶም በሕትመት ባይኖር እንኳ በላይበራሪዎችና በፒድኤፍ ይገኛል፡፡
በእኛ በኩል የቀረው ሥራ የንጽጽር ትምህርት የሚያስተምር ተቋም መገንባት ነው፡፡ ይህንን ደግሞ አሁን ያለው ወጣት ያደርገዋል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እፎይ ወንድማችን ይህንን ሲል ሰምቸዋለሁ፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ሰው ከዚህ ወንድማችን ጎን በመሰለፍ ሊደርስበት ከሚችል ማንኛውም ጥቃት መታደግ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ ወንድማችን ላይ የአ.አ ፖሊስ የእስር ማዘዣ አውጥቶበታል ሲባልም እየሰማን ነው፡፡ ምክንያቱም የእኛ አባቶች ዝም ስላሉ፡፡ ዝም ካሉ ጥፋተኛ ነው ብለው ተስማምተዋል ያሰኛልና፡፡
ገዳ*ይና አራ*ጆች ግን አሁንም ሊገድሉት እየፈለጉት ነው፡፡ እንኳን እሱን እኔም እፎይ ነኝ የሚለውን ሁሉ ለመግደል በመቋመጥ ላይ ናቸው፡፡ ሐረመያ ዩኒቨርስቲ ላይ እኔም እፎይ ነኝ ያለውን አንድ ክርስቲያን ከፎቅ ሊወረውሩት ሲሉ ያዳኑት የዩኒቨርስቲው ሠራተኞች ናቸው፡፡ ለጊዜው በዩኒቨርስቲው አመራሮች ተይዞ ይገኛል፡፡ መንግሥት እፎይን ዝም ስላለው ይህንን ልጅ የሚያደርጉበት አጥተዋል፡፡ ሲለቁት ግን እንገድለዋለን ነው ሲሉ የሰማኋቸው፡፡ የእኛ ቤት ግን ምንም እንዳልተፈጠረ፣ በሀገር ውስጥም እንደሌለ ለጥ እንዳለ ነው፡፡
በመጨረሻም የሰላም ምኒስተር የሚባለው ግን መንግሥታዊ ተቋም ነው? ወይስ ሃይማኖታዊ ተቋም? የንጽጽር ትምህርት የሚፈቅድበት አግባብስ እንዴት ነው? ሕገ መንግሥታዊ ነው ወይስ ምን ዓይነት ሕጋዊ ዕውቅና ነው? የእስልምና አስተማሪዎች እስካሁን ላጠፉት ጥፋትስ ተጠያቂ መሆን ይችላል? በራሱ በእምነቱ ተቋም ብቻ ያልተመሠረተውስ ለምን ይሆን? እየመለሳችሁልኝ!
© ሰለሞን ላመስግን

👍5
"ፈውስ መንፈሳዊ ሚዲያ ተጠልፏል"
ሰላም ለእናንተ ይሁን የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ አንድነት ገዳም የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ት/ቤት የፈውስ መንፈሳዊ ሚዲያ ተከታታዮች፤ ከቀን ፲፩-፯-፳፲፯ ሐሙስ ጀምሮ "ፈውስ መንፈሳዊ ሚዲያ -youtube " በሌሎች ሰዎች ስለተጠለፈ እኛ መግለጫ እስክንሰጥ ድረስ በሚዲያው የሚተላለፉ መልእክቶች ቢኖሩ የጉባኤ ቤቱ አለመሆናቸውን አውቃችሁ እንድትጠነቀቁ በጉባኤ ቤቱ ስም እንገልጻለን።
አምላከ ጉባኤ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅ።

👍4😢4
መምህር ኃይለ ማርያም ዘቦሩ ሜዳ እንደጻፉት ነው።
ስንት ጊዜ ብዙ ብለው ዛሬ ለጠየቁት ጥያቄ ከመጽሓፋቸው "እፎይ" መልስ ሰጠ፣ 'ውዱ' ተሰደበ አሉ።
#አባቱን_የጠላ_የሰው_አባት_ይሰድባል
ይህ በሀገራችን የተለመደ የአበው ብሂል ነው። ውነትም ዘሎ የሰው አባት የሰደበ ሰው አባቱን ለስድብ አጋልጦ መስጠቱ ሳይታለም የተፈታ ነው።
ሰሞኑን በክርስትናና በስልምና ጎራ ተሰልፈው ተዋሥኦ ሲያደርጉ በነበሩ ወንድሞችና እኅቶች ምክንያት የመግለጫ ጋጋተዎችን ሰምቻለሁ። ተዋሥኦ ወደ ጸብ እንዳይቀየር መሥራት መልካም ቢሆንም መግለጫዎቹ ግን ያተኮሩት (የሃይማት ተቅዋማት ኅብረትና የስልምናው ምክር ቤት ያወጡት) ችግሩን ወደ መፍታት ሳይሆን ክርስቲያን ወንድሞች እንዳጠፉ እንደ ገፉ። ስልምና እንደ ተገፋ አድርገው ነው።
ለዚህ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሆነው እፎይ የተባለው ወንድም ነው።
#ይህ_ወንድማችን በስብከት መልክ ቀርጾ የለቀቀው፤ ወይም በአውደ ምሕረት ያስተማረው ነገር የለም። በማኅበራዊ ሚዲያ ለክርክር ተሰልፈው ያቀረባቸው ጥያቄዎች ናቸው። መልሱ ቀላል ነው የቻለ ሃይማኖታዊ መልስ መስጠት። ወይም ሐሳቡን መቃወም ካልሆነም ክርክሩን ማቆም ነው። ከተከራከሩ በኋላ ግን በሕጉም ያለ ሕጉም ማስፈራራትና የመግለጫ ጋጋታ በጎ አይደለም።
#ማንም_የማንንም ሃይማኖት መሞገት እንጂ ማንቋሸሽ አይችልም ግን ሚዛናዊነት ያስፈልጋል።
መግለጫ የሚወጣው ለስልምና ብቻ ነውንዴ?
እስከ ዛሬ ክርስትና ሲነቀፍ ማን መግለጫ ሰጠ።
የሚዲያውንን የነአቡ ሀይደርን የዘወትር ነቀፋ እንተወውና በመጽሐፍ መልክ ብቻ በክርስትና ላይ የተደረገውን ድፍረት እንመልከት።
1.መጽሐፍ ቅዱስ ስለመሐመድ ምን ይላል? አሕመድ ዲዳት፤ 1989
2. ስለኢየሱስ እውነተኛ መረጃ፤ ዶ/ር ማንህ ሐምማድ አልጆሐኒ
3. ኢየሱስ እውን ፈጣሪ ነውን? አሕመድ ዲዳት፤ 1988።
4. እስልምና እና ክርስትና፤ መሐመድ አሊ አልሑሊ።
5. ክርስቶስ በኢስላም፤ አሕመድ ዲዳት፤ 1999።
6. የሴቶች መብትና እኩልነት በኢስላምና በክርስቲያን እምነት (አቀራረቅ) አሕመዲን ጀበል 2001።
7. መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነውን? 2003።
8. ለአብነት ያህል 1መቶ ስሕተቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ በዛኪር ናይክ(ትርጉም፦ አሕመድ ዐሊ) 2003።
9. የመጽሐፍ ቅዱስ ምሥጢር በሙስሊም መነጽር፤ ቀመር ሑሴን።
10. ክርስቶስ ማን ነው? 303 ወሳኝ ጥያቄዎች።፤ አሕመዲን ጀበል፤ 2001።
እነዚህና የመሳሰሉት መጻሕፍት ክርስትና ላይ አነጣጥረው ሲጻፉ።
ማን መግለጫ አወጣ?
ማን ተከሰሰ?
ማን የሞት አዋጅ ታወጀበት?
ቤተ ክርስቲያን የመጽሐፉን በመጽፍ
የአፍን በአፍ፤ ስትመልስ ኖረች እንጂ እንደዚህ ያለ ጋጋታና አዋጅ አላወጣችም። ታዲያ ዛሬ ምን ተገኘ?
ወደው ፈቅደው ሚዲያ ከፍተው እነከራከር ብለው ቀርበው እንደ ሕጻን ጨዋታ መተፋፈር መልካም አይለም። ሃይማኖቱ እንዲከበርለት የሚፈልግ የሰው ሃይማኖት አይነቅፍም። ከላይ የተዘረዘረው መጽሐፍ የተጻፈውኮ ክርስትናን ለማወደስ አይደለም ለማዋረድ እንጂ። ታዲያ ምንሁኑ ነው አሁን?
መፍትሔ
1. ተዋሥኦ/ክርክር አንፈልግም የሚል አካል በግልጽ ተናግሮ መተው።
2. ከመስመር የወጣ ነገር ካለ ሁሉም በየቤቱ መምከር። እንደ ጠቢብ ወላጅ(ጠቢብ ወላጅ ልጁ ከሌላ ልጅ ጋር ተጣልቶ ሲመጣ ቀድሞ ልጁን ይቀጣል ይገርፋል፤ ሞኝ ወላጅ ግን የራሱን ልጅ ትቶ የጎረቤት ልጅ ይሰድባል።)
3. ክርክሩ ከቀጠለ በአስተዋይ ሰው መጠን ተደማመጦ መከራከር። ከዚህ የወጣው ለማንም አይጠቅምም።

❤2
🤔 ማንም ሰው ይነሣና የጉዞ አዘጋጅ ይሆናል!
🤔ማንም ሰው ተነሥቶ ይደራጅና ማኅበር ነኝ ይላል!
🤔ማንም ሰው ተነሥቶ የሆነ ቤተ ክርስቲያን አጋዥና አሠሪ ነኝ የዚህ ገዳም ተጠሪና አስጎብኝ ነኝ ይላል!
እነዚያ ግለሰቦችም ስለ ፈለጉት ገዳም በራሳቸው መንገድ የራሳቸውን ነገር ያስገባሉ!
🤔 ስለ ገዳሙ የተጠና ሙሉ መረጃ ሳይዙ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮን ያልተከተለ ታሪክ መተረክና ጠበልና እምነት የቤተ ክርስቲያኗ መደበኛ የፈውስ መንገዶች እያሉ አዲስ ነገር ለመፍጠር ብለው እንደ ቂቤና እንደዚህ ሾላ ፍሬ በመሳሰሉት ፈውስ ይገኛል የሚል አላማ ይዘው ይነሣሉ
መዓር በዓይን ላይ ማድረግ ብለው ከቤተ ክርስቲያን የማታዘውን ሥራ የሚሠሩ ሰዎች እኔም አንድ ቦታ አይቼ በጣም አዝኛለሁ በዚህም ብዙ እናቶች ሲቸገሩ አይቻለሁ
ቦታው ላይ ካሉ ሰዎች ጋር የጥቅም ሽርክና ይፈጥሩና ቦታውን እናሳድገዋለን እናንተ ዝም በሉ ይላሉ እሺ ይባላል
ሀገረ ስብከቱም ደኅና ፐርሰንት ስለሚያስገቡ ባላየ ያልፋቸዋል
እንዲህ የሚያደርጉ አካላት ትክክለኛ የቤተ ክርስቲያን ልጅ መሆናቸውንና ሃይማኖታቸውን የሚገልጽ መረጃ እንኳን አያቀርቡም
የሚያገኙትን የገቢ ምንጭና ወጭና ገቢያቸውን የሚቆጣጠር አካል እንኳን የለም
አሁን ደግሞ ጨራሽ ሁለት ወንድማማቾች ተነሥተው የጉዞ ማኅበር ብለው እንደፈለገ ቢንቀሳቀሱ እንኳን የማኅበራት ሕብረት የሚለው ምዝገባ ውስጥ ይገቡና ቤተ ክርሰሰቲያኗ እውቅና ሰጥታናለች ታዋቂዎች ነን ብለው ለንግዳቸው ሌላ መተማመኛ አግኚተዋል
እና እንዲህ እየተሆነ ሕዝበ ክርስቲያኑ የነጋዴዎች መጫወቻ ገዳማቱም የነጋዴዎች መፈንጫ ሆነው መታየታቸው ምንም አይደንቅም
ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የት አለ?
የማኅበራት ሕብረቱ ሕግ የት አለ የቁጥጥር ሥራውስ ምን ላይ ነው?
የእየ ሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎችስ ሥራ ምንድን ነው?
ኦርቶዶክሳውያን ሚዲያዎችና የሚዲያ ባለሙያዎችስ ምን እያደረግን ነው?
አንድ ገዳም ሲተዋወቅና ወደ ቦታው ጉዞ ሲደረግ የሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት ከንግድ ጋር ያልተሳሰረና ሕዝበ ክርስቲያኑን የሚጠቅም መሆኑ በደንብ መጠናት አለበት ገዳም እያስተዋወቁ የነጋዴ ሕይወት መቀየሪያ መሆን የለበትም።
የአጠማመቅ አይነት የወደፊት ባሌን አየሁት፣ ጊዮርጊስ ፎቶ አነሣኝ ወዘተ የሚል ቅዠት እየተሰማ ነው!
ስንዴ የመስፈር ፕሮግራም፣ ነጠላ የማንጠፍ ሥነ ሥርዓት፣ ስመ ክርስትና የመጻፍ ወዘተ እየተባለ በምን ምክንያት የምዕመናንን ገንዘብ እናግኝ የሚል የንግድ ስልት መቆም አለበት!

Forwarded from ሀና
ሰላም ለእናንተ ይሁን የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ አንድነት ገዳም የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ት/ቤት የፈውስ መንፈሳዊ ሚዲያ ተከታታዮች፤ "ፈውስ መንፈሳዊ ሚዲያ -youtube " በሌሎች ሰዎች ተጠልፎ የነበረ ቢሆንም በእግዚአብሔር ቸርነት በእመቤታችን ተራዳኢነት በቅዱስ ቂርቆስ አጋዥነት በአባቶቻችን ጸሎት በእናንተም ጸሎት እንዲሁም በወንድሞቻችን ረዳትነት ወደ ጉባኤ ቤታችን የተመለሰ መሆኑን ልንናሳውቃችሁ እንወዳለን።
አምላከ ጉባኤ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅ።
https://youtube.com/@fewus_menfesawi_aba_gebrekidan?si=yoiBv0sUl7cZ6oXL

❤3
የሆነች ልጅ አለች መንገድ ላይ መስቀል ያደረጉ እህቶችን እያስቆመች ሂጃብ ታለብሳለች
የእኛ እህቶችም እሺ ብለው ለዚህ መጃጃል ትብብር ያደርጋሉ
መቼም ክርስትናው ላይ በዚያም በዚህም የሚደረገው ዘመቻ ቀላል አይደለም ከዚያ ያንን ፎቶ ሁሉም ሙስሊሞች ይቀባበሉታል በዚህ አለባበስሽ ያምራል ወላሂ ሙስሊሙ ሁኚ ምናምን አድናቆት ይጎርፋል
እስኪ አንዷን ሙስሊም ሴት አስቁመሽ ይህ መስቀል ያምራል ልሰርልሽ በያት መልሷ ምን እንደሚሆን ለአንቺ ልተወው
እህቴ ቤተ ክርስቲያን ያልጠፈነገችሽ ለነፃነትሽና ለጤናሽም ብላ ነው እንጂ በአግባቡ እንዳትለብሺ የከለከለሽ ነገር የለም
©መምህር ዘላለም ሐሳቤ

👍18❤6
ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች ታገደ።
#FastMereja I ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች በካውንስሉ በምዝገባ ቁጥር 03111 የተመዘገበች የሃይማኖት ተቋም መሆኗ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ ቤተክርስቲያኒቱ የካውንስሉ አባል ስትሆን ልታከናውናቸው ከሚገቡ መመሪያዎችና ደንቦች መካከል አንዱ የካውንስሉ አባላት ስነ ምግባር መመሪያ ሲሆን በስነ ምግባር መመሪያው አንቀጽ 9.3 ላይ የስነ ምግባር ግድፈቶች ተብለው በዝርዝር የተገለጹትን ተግባራት በቤተክርስቲያኒቱ መሪ መፈጸሙን አረጋግጠናል።
በመሆኑም ጉዳዩ በካውንስሉ ሥነ መለኮት ኮሚሽን እና የሕግ ኮሚሽን ታይቶ በሚመለከታቸው አካላት የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ የቤተክርስቲያኒቱ ፈቃድ ታግዶ የሚቆይ ሲሆን ሁሉም የካውንስሉ አስተዳደራዊ መዋቅሮችና የሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት ይህንንና ከዚህ በኋላ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን እንድታስፈጽሙ በግልባጭ ተመዝግቦላችኋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል

👍3❤2
ወደ ግሪክ አቴንስ የተጓዘው የቅዱስ ሲኖዶስ ልዑካን ቡድን ለበርካታ ዓመታት የቆየውን አለመግባባት በሰላምና በእርቅ መቋጨቱን ገለጸ።
++++++++++++++++++++++++++++++
(#EOTCTV መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተመርጦ ወደ ግሪክ አቴንስ ያቀናው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ልዑካን ቡድን ለበርካታ ዓመታት የቆየውን አለመግባባት በሰላምና በእርቅ በመፍታት የቤተ ክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነትን ወደ ቀደመ ቦታው እንዲመለስ ማድረጉን ገልጿል።
የቅዱስ ሲኖዶሱ ልዑካን ቡድን ባለፉት ቀናት በግሪክ አቴንስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ በተናጠልና በጋራ በርካታ ውይይቶችን ማድረጉን ገልጾ ይህ ሰላም እና አንድነት እውን እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደረጉትን ከካህናት፣ ምዕመናንና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ላበረከቱት የተቀደሰ ተግባር በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ምስጋናውን አቅርቧል።
በዚሁ የእርቅ፣የሰላምና ስምምነት ሂደት ላይ በግሪክ መንግሥት በኩል በተለይ የሃይማኖት ሚኒስትር መሥሪያ ቤት ለሂደቱ መሳካት ላደረገውና ወደፊትም ከቤተክርስቲያኗ ጋር አብሮ ለመስራት እንሁም በማንኛውም መስክ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱን የገለጹት የልዑካን ቡድኑ አባላት በውይይቱ ወቅትም በአካል ተገናኝተው መሳተፋቸውን በማድነቅ ምስጋናቸውን ገልጸዋል ።
የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/

👍7