Telegram Web
ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
ዲያቆኑን ማባበልም ጀመረ "የአንተን ሃሳብ የሚያራምዱ ሰዎችን ከልቤ አከብራለሁ:: እውነት እውነት እላችሁዋለሁ የሚለውን ይዘው ይህ እውነተኛ ሥጋው ነው የሚሉት ከልብ አከብራለሁ" አለ:: አክባሪ ይሥጥልን ግን እኛ ይሄን ጥቅስ እንደማስረጃ አላነሣንም:: ዲያቆኑ እዚያው ቆሞ "ለተራ እንጀራ ሰው እንዴት ይሞታል?" ብሎ የጠየቀውን ፍጥጥ ያለ ጥያቄ ትቶ ከዚህ በፊት ሌሎች ሰዎች ያነሡትን weak argument…
ፓስተሩ ለኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ Debate መልስ ሠጠ የተባለበትን ቪድዮ ልካችሁልኝ አየሁት:: አሁንም ትራንሰብስታንሺዬሽን እያለ ነው:: የቡሄ ዕለት ያበደ ሰው ሁሌ ሆ ሲል ይኖራል ይባላል:: Transubstantiation አናምንም እኛ በMystical change እንጂ በchange of substance አናምንም እየተባለ አሁንም ያንኑ ይደጋግማል:: ቪድዮውን እንዳታዩት ብሎ ጀምሮ ክርክሩን ደህና አድርገው እንዳልተወጡት አመነ:: ከዚያ በቁርባን ማመን አለማመን matter አያደርግም ብሎ አረፈው:: እንደዚያ ከሆነ ሙግት የገጠምከው ለውጥ ለማያመጣ ጉዳይ ነው ወይ:: ኢትዮጵያን ሲያነሣ አልሰማሁትም:: we got people starving to death today የምትለዋ ምናልባት ማሸማቀቂያ አሽሙር ከሆነች አላውቅም::
✍️Stuart and Cliff ከምሕረት መልአኩ ጋር በ MIT ካምፓስ ያደረጉት ክርክር በዐለም ከናኘ በኋላ Cliff ያንን ውይይት በአግብቡ የተቆጣጠሩት አንዳልነበር ሒሱን ወስዷል፡፡ በሌላ አነጋገር በዝረራ መሸነፋቸውን አምኗል፡፡

በመልሱ ግን ያልነበሩ፣ ያልተባሉና እውነትነት የሌላቸው ነርቨስ የሚያደርጉ መልሶችን ሰጥቷል፡፡ ክሊፍ ጉዳዩን ወይ ሊጠመዝዘው ወይም ደግሞ አሁንም ድረስ የተሸነፉበትን ምሥጢር አላገኘውም፡፡ ‘ሰዎች የክርስቶስን አምላክነት ሳያምኑ፣ መሞቱን፣ መሰቀሉን፣ ከሙታን መነሣቱን ሳያምኑ፣ አጠገባቸው ያለውን ሰው ሳይወዱ ክርስቶስን ወድጃለሁ ቢሉ ሐሰተኞች እንጂ ክርስቲያኖች አይደሉም፣ የሐሰት ሐዋርያት እንጂ የክርስቶስ ሐዋርያት አይደሉም’ የሚል ዐሳብ አንሥቷል፡፡ አስቂኝ መከራከሪያ ነው፡፡ እርሱ ያለውን ሁሉ የማያምን ነገር ግን ክርስቲያን ነኝ የሚል በዐለም ላይ የለም፡፡ እንዲያ ብለው የማያምኑትንማ ቤተ ክርስቲያን በየጊዜው እያበጠረች ስትለያቸው ኖራለች፡፡ አርዮስ የተለየው እኮ የወልድን አምላክነት ባለማመኑ ነው፡፡ አቡሊናርዮስና ንስጥሮስ የተለዩት እኮ ክርስቶስ ሰው የሆነ አምላክ መሆኑ ችግር ውስጥ የሚከቱ ፍልስፍናዎችን በማምጣታቸው ነው፡፡
ክሊፍ የዘረዘራቸውን ነገሮች የማያምን ነገር ግን ደፍሮ ክርስቲያን ነኝ የሚል ሰው የለም፡፡ በዘረዘራቸው ነገሮች አይደለም ኦርቶዶክስን ካቶሊክንም ሊከሳት አይችልም፡፡ በሌላ በኩል ሰውን ከእምነት አልባነት እርሱ ወደሚያምነው ማምጣት እንጂ እርሱ ያለበት ጎደሎ ክርስትና ይሁን የተሟላ አምነት የሚገደው አይመስልም፡፡

ሌላው የገረመኝ ምሕረት በተደጋጋሚ ኦሮዶክሳዊነቱንና በ Transubstantiation እንደማያምን ነግሮት አሁንም የመለሰው በዚያ ዐውድ ነው፡፡ ንጽጽሩን በካቶሊክና በZwinglian (Eucharist as symbolic) አድርጎ ነው የተመለከተው፡፡ ኦርቶዶክሳዊው ምንልከታና ምሕረት ያተኮረበት አማናዊ የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው የሚል ሲሆን እነሱ በሚሉት 'ምሳሌና የሞቱ መታሰቢያ ነው የሚለው ላይ አተኩሮ መመለስ ነበረበት፡፡ ይኸንንም ብዙም ትኩረት መሳብ የሌለበት አስመስሎ ነው ያቀረበው፡፡ ክርስትና ሰዎችን ወደ Fullness of truth ማምጣት እንጂ አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ፣ ወይም አለባብሰህ የምታርሰው እርሻ አይደለም፡፡

የሚገርመው የሳምንታት ያህል ጊዜ ኖሯቸውም ጉዳዩን ሳያብላላው ነው ለመመለስ የሞከረው፡፡ በዚያ ላይ ጉዳዩ ቫይራል መሆኑ ‘ምነው ያኔ እግራችንን በቆረጠው ኖሮ’ የሚል ስሜት የተሰማቸው መሆኑን ነው ከመልሱ የሚነበብበት፡፡

በጠቅላላው ዘንድሮ ሜንጤ አናቷ አየተቀጠቀጠ ያለበት ዐመት ነው፡፡ ሀገር ቤትም በጣም እየተቀጠቀጠች ነው፤ አሁን ደግሞ በውጭም በምሕረት የተነሣ በውጭም እየተመታች ነው፡፡ ሜንጤ ቲኦሎጂ ካጠና እና የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ ጠንቅቆ ከሚያውቅ ሰው ፊት ቆማ ለመከራከር የሚያስችል እውነትም ይሁን ማስረጃ የላትም፡፡ በጭራሽ፡፡ ሜንጤ ማድረግ ያለባት አሕዛብ ወይም ኢአማኑ ወደሆኑት ዘንድ ሄዳ ሰዎችን ወደ ግማሽ እውነት ማምጣት ላይ ታተኩር፡፡ ከዚያ ወደ ተሟላው እምነት ማምጣቱን ለእኛ ትተወው፡፡

እግዚአብብሔር በምሕረት ላይ አድሮ አስደናቂ ሥራ ሠርቷል፡፡ በውጩ ዐለም ክስተቱን ብዙዎች እየተነቃቁበት መሆኑን አይቻለሁ፡፡ ካቶሊኮችም ወደ ክርክሩ መጥተው ተመልክቻለሁ፡፡ ምሕረት በነበረው ክርክር ላይ ‘ኦቶሪቲ ያለው ማን ነው?’ የሚል ጥያቄ ከስቱዋርት ቀርቦለት ‘ቤተ ክርስቲያን ናት’ የሚል መልስ ሰጥቶ ነበር፡፡ ትክክል ነው፡፡ ባይሆን ካቶሊኮች ‘ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ስላሉ የትኛዋ ቤተ ክርስቲያን ናት የክርስቶስ ተወካይ ወይም ቪካር?’ የሚል ጥያቄ ጠይቀው ‘ክርስቶስ ሥልጣኑን የሰጠው ለጴጥሮስ ሲሆን የጴጥሮስን ሊቀ ሐዋርያት ከጥንት እስከ አሁን የጠበቅነው እኛ ስለሆንን ሥልጣን ያላት ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ናት!’ የሚል ግማሽ እውነት ሲያራግቡ አይቻለሁ፡፡ ያው የእነ ክሊፍ እናትና አባት ስለሆኑ አይፈረድባቸውም፡፡ ከካቶሊክ ጽንፈኝነት ነው ሜንጤ የተባለ የባሰበት ጽንፈኛ የተወለደው፡፡ ይኸ ወደ ሌላ ስለሚወስድ ሌላ ቀን እናነሣዋለን፡፡

በመጨረሻም ምሕረት በክርክራቸው ጊዜ ስቱዋርትን ‘በ1ኛውና በሁለተኛው መቶ ዐመታት ከነበሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥጋወ ደሙ አማናዊ አይደለም የሚል አንድ እንኳን ጥቀስልኝ’ ብሎ የነበረ ቢሆንም ስቱዋርት ታሪካዊቷን ቤተ ክርስቲያናት ስለማያውቃት መመለስ አልቻለም ነበር፡፡ ምሕረት ቅዱስ ጳውሎስን፣ አግናጥዮስን፣ ሄነሪዎስን፣ ዮስጢኖስ ሰማዕትን ጠርቷቸዋል፡፡ የቅዱስ ጳውሎስን 1ኛ ቆሮ. 11:30 ደግሞ ጠቅሶ ተከራክሮበታል፡፡

ሌሎቹን በስም ጠቀሳቸው አንጂ ያሉትን ስላላነሣ፣ እነዚህ አባቶች በዘመኑ ስለቁርባን አማናዊነት ከተናገሩት ውስጥ ከታች ለአብነት አስቀምጫለሁ፡፡

-“Consider how contrary to the mind of God are the hetrodox. They do not admit that the Eucharist is the flesh of our savior, Jesus Christ” St. Ignatius of Antioch 90 AD.

-“For not as common bread and common drink do we receive these. We have been taught that the food which is blessed is the flesh and blood of Jesus, who was made flesh.” St. Justine Martyr 155 AD.

-If the Lord were from other than the Father, how could He rightly take bread, which is of the same creation as our own, and confess it to be His body and affirm that the mixture in the cup is His blood?” St. Irenaeus 189 AD.

-The flesh feeds [in the Eucharist] on the body and blood of Christ, that the soul likewise may be filled with God” Tertullian 280 AD.

👉 ዶ/ር አረጋ አባተ
👍21
በዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዙሪያ የተሠራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ ገዳማውያኑ ተናገሩ !

ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]

''የዋልድባ አብረንታትን ገዳም በሰላም መደፍረስ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት እንደ ደረሰበት የገዳሙ አባቶች ገለጹ!'' በሚል መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም መረጃ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

ከዚህም ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት ሚያዝያ 03 2017 ዓ.ም ከገዳሙ ተወክለው የመጡ መነኮሳት ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገዳሙ በማያውቃቸው አባቶች አማካይነት የተሠራጨው ዘገባ ከገዳሙ ዕውቅና ውጪ መሆኑን በመግለጽ ድርጊቱ ማኅበረ መነኮሳቱን እንዳሳዘነ ተናግረዋል።

ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክም ቅሬታ ማቅረባቸውን የገለጹት የገዳሙ ተወካዮች የሆኑት አባ ገ/ሥላሴ፣ መ/ር ዓምደ ሥላሴ እና አባ ገ/ማርያም ወ/ጊዮርጊስ ቅዱስነታቸው ከዚህ በፊት ለተሠራጨው መረጃም ዕውቅና እንደሌላቸው ነግረውናል ብለዋል።

በተለይም በአሁኑ ሰዓት አንድነት ገዳሙ በእግዚአብሔር እርዳታ በጾምና በጸሎት በሚተጉ ማኅበረ መነኮሳት ተጠብቆ እንደሚገኝ እና ሰላም መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም ከዚህ በፊት የተሠራውን የሐሰት ዘገባ ተከትሎ ገዳሙ የማያውቃቸው ሕገ ወጥ አካላት ነገ ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የገቢ ማሰባሰቢያ ሊያካሂዱ በመሆኑ ሕገ ወጥ ተግባሩ እንዲቆም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመሆኑም በዚህ በጾም ሰዓት ሱባኤ አቋርጠው ወደዚህ ለመምጣት እንዳስገደዳቸው የተናገሩት ገዳማውያኑ ምእመናንም የገቢ ማሰባሰቢያ በሚል የተጠሩበት ቦታ ላይ እንዳይገኙ ገልጸዋል።

የተከሠተው ጉዳይ በገዳሙ ላይ የመጣ ፈተና ስለሆነ በተቻለ ዓቅም ሕገ ወጥ ተግባሩ በአስቸኳይ መቆም እንዳለበት አሳስበዋል።

©ማኅበረ ቅዱሳን
👍21
የሰሙነ ህማማት ሰኞ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

◦ የሰሙነ ህማማት ሰኞ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡

◦ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.፲፩፥፲፩) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ "ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ" ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ-እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡

◦በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ድኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡

◦በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡

አንጽሆተ ቤተመቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦

◦ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተመቅደስ ሄደ፤ ቤተመቅደስ፣ቤተጸሎት፣ ቤተመሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ፦ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው ፤ ገርፎም አስወጣቸው ፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡

◦ በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና ፭ሺ ከ፭መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት

❤️ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን ❤️

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን
3👍3
በሰሙነ ህማማት ወቅት የምንሰማቸው እንግዳ ቃላትና ትርጉማቸው

በግብረ ሕማማት ውስጥ በግዕዝም ሆነ በኋላ በአማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የእብራይስጥ፣ የቅብጥና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ። የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፦

#ኪራላይሶን፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ
< ኪርዬ ኤሌይሶን> ነው። #ኪሪያ ማለት እግዝእትነ / እመቤታችን" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ / ጌታ ሆይ / አቤቱ" ማለት ነዉ፡፡ "ኤሌይሶን" ማለት ደግሞ "ማረን / ይቅር በለን" ማለት ነዉ ፡፡ ትርጉሙም "አቤቱ ማረን" ማለት ነዉ፡፡ "ኪራላይሶን" የምንለዉ በተለምዶ ነዉ፡፡ ይኸዉም "ኪርዬ" ከሚለዉ "ዬ" ኤሌይሶን" ከሚለዉ ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸዉ በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረዉ ነዉ፡፡

#ናይናን፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሐረነ፤ማረን" ማለት ነው።
#እብኖዲ ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "አምላክ" ማለት ነው። "እብኖዲ ናይናን" ሲልም " አምላክ ሆይ ማረን" ማለቱ ነው።
#ታኦስ ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ጌታ፣አምላክ" ማለት ነው።
#ማስያስ ፦ የእብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሲህ" ማለት ነው።
#ትስቡጣ ፦ "ዴስፓታ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም "ደግ ገዥ" ማለት ነው።
#አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግስትከ- አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ" ማለት ነው።
#አምነስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ " ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግስትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነው።
#አምነስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ " ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግስትከ -የሁሉ በላይ የሆንክ ሆይ በመንግስትህ አስበን " ማለት ነው።
6👍1
ከበሮ፣ጸናጽል፣መቋሚያና ከ፲ በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች ሥራ ተመዝግቦ ከሚያዚያ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አእምሯዊ ንብረት መሆኑ ተረጋግጧል።

ከዚህ ቀደምም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ በአእምሯዊ ንብረት ዐቢይ ኮሚቴ አማካኝነት በርካታ የቤተክርስቲያን ንብረቶች ተመዝግበው እውቅና ማግኘታቸውን የመምሪያው ኃላፊ መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ ገልጸዋል።
👍43🕊2👏1
"የመስቀል በዓል የጣዖት በዓል ነው” ያለውን ግለሰብ ፍርድ ቤት በነጻ ዋስ ማሰናበቱ ተገለጸ !
ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም [ተሚማ/ አዲስ አበባ]
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ አቶ መርክነህ መጃ የተባለ ግለሰብ ሰኞ መስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም በግል የፌስቡክ ገጻቸው ላይ “የመስቀል በዓል እንግዲያውስ እስከተነሳ ድረስ እንነጋግርበት” በማለት የመስቀል በዓልን ከጣዖት አምልኮ ጋራ አገናኝተው የጥላቻ ንግግር በመጻፋቸው ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የወላይታ ሀገረ ስብከት ክስ መስርቶ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መብት ለማስከበር ግለሰቡን በሕግ ጥላ ሥር እንዲቆይ በማድረግ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
ግለሰቡም በዋስትና ተለቅቆ በውጭ ሆኖ ክሱን ሲከታተል የቆየ ሲሆን በመጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም የወረዳው ፍ/ቤት በዋለው ችሎት ተከሳሹን በነጻ ማሰናበቱን በመግለጹ ሀገረ ስብከቱ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርበን ሳለ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መብት አልተከበረም ሉዓላዊነቷም ተደፍሯል በማለት ይግባኝ ማለቱን የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም ቦክቻ ኤንጋ ለተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል አሳውቀዋል፡፡
ክቡር ሥራ አስኪያጁ አክለውም ።፤ ግለሰቡ “የመስቀል በዓል በብዙ አቅጣጫ ከጣኦት አምልኮ ጋር አያይዘው የሚጠቀሙ ግለሰቦች ስላሉ ለቤተ ክርስቲያን አደገኛ ስለሆነ ፤ በዚህ በዓል እግዚአብሔር አይደለም የሚከበረው” ያሉ እና “ገና ከመነሻው የጣኦት አምልኮ የተካተተበት ነው” በማለት በታሪክም በጽሑፍም ያለውን ማስረጃ የሌለ አድርገው ቅድስት ቤተክርስቲያን የማታስተምረውን እንደምታስተምር ፣ የማትቀበለውን እንደምትቀበል አድርገው የጥላቻ እና የተሳሳተ ንግግር በማኅበራዊ ገጻቸው ያስተላለፉ ሲሆን ይሄንንም በምሳሌ ብለው ሲያስረዱ “እንደሚሉት ንግሥት እሌኒ መስቀሉን በእሳት ጭስ ተመርታ ካገኘች በኋላ የምስጋና ጭስ ላስገኛት አካል አቅርባለች በማለት ለጭሱ የሚያመልኩም አሉና፡፡” በማለት ከእውነት የራቀ የተሳሳተ መረዳታቸውን በአደባባይ አስተላልፈው ሳለ የወረዳው ፍ/ቤት በነጻ በመልቀቁ ቅሬታዋን ቅድስት ቤተክርስቲያን የገለጸች ሲሆን መንግሥት በልዩ ትኩረት ሊከታተለው እንደሚገባ እያስገነዘብን በቀጣይ ፍትሕ እንደምናገኝ በልበ ሙሉነት እየተማመንን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ የተጠየቀ መሆኑን እንገልጻለን በማለት አያይዘውም የጎጮ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይዞታም ከዚሁ ወረዳ በይግባኝ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ ውሳኔ ማግኘቱ ይታወሳል ብለዋል።
የመስቀል ክብረ በዓልን ዩኔስኮ [Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ] በማለት በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን 2006 ዓ.ም በኢንታንጀብል [መንፈሳዊ] ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ በአዘርባጃኗ ባኩ ከተማ ባደረገበት ጊዜ መመዝገቡን ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
👍3
ረቡዕ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰብስበው ጌታችንን ኢየሱስን እንዴት እንደሚይዙትና እንደሚያስገድሉት ምክር የጀመሩበት ዕለት ነው፡፡ ነገር ግን የፋሲካ በዓል ቀርቦ ስለነበር ሁከት እንዳይፈጠር እንዴት መያዝ እንዳለበት ሲጨነቁ ከጌታችን ደቀ መዛሙርት መካከል ይሁዳ ከምክራቸው በመቀላቀሉ ጥያቄአቸውን አቀለለላቸው፡፡ (ማቴ. 27፥3-5፣ሉቃ. 22፥1-2፣ማር.14፥1-2) እንዲሁም እንዲሞት የወሰኑበት ዕለት ነው፡፡ (ማቴ. 26፥3-5)

ምንጭ:- ማኅበረ ቅዱሳን ድኅረ ገጽ
1👍1
💔በህማማቱ ከወደ ናይጄሪያ አሳዛኝ ዜና ፡በትናንትናው እለት በፕላቶ ግዛት በጂሃዲስቶች 51 ክርስቲያኖች ሰማዕትነትን ተቀበለዋል ከዚህ በታች ስማቸው ተዘርዝሯል። በጣም የሚያሳዝነው ዝርዝሩ ከሶስት እስከ አስር አመት የሆኑ 13 ልጆችን ያካትታል።
1. ሙሳ ዳኮ፣ 64 ዓመቱ
2. ዳንኤል አዳምስ፣ 27 ዓመቱ
3. አብዲያ ኡስማን፣ 31 አመቱ
4. ዚናስ ጄምስ፣ 22 ዓመቱ
5. ሰኞ ሰረቀ፣ 37 ዓመቷ
6. ዮሃና ኩሳ፣ 43 ዓመቱ
7. ጃኔት ዳንጁማ፣ 29 ዓመቷ
8. እሑድ ዳኮ, 49 ar
9. ሮበን አዳሙ፣ 94 ዓመቱ
10. ዶጋራ አዳሙ፣ 69 ዓመቱ
11. ቡሉስ ሙሴ፣ 26 ዓመቱ
12. እስጢፋኖስ ጆን፣ 28 ዓመቱ
13. መንቸ እስጢፋኖስ፣ 7 ዓመቱ
14. ነማ እስጢፋኖስ፣ 4 ዓመቱ
15. ማርያም እስጢፋኖስ፣ 24 ዓመቷ
16. ዊኪ ጆን፣ 30 ዓመቷ
17. ኢያሱ ጆን ባጉ፣ 46 ዓመቱ
18. ማርጋሬት ሞሪስ፣ 6 ዓመቷ
19. ደበኔ ሞሪስ፣ 4 ዓመቱ
20. ሰኞ ሽያጭ, 52 ar
21. ሳላማ አጋህ፣ 15 ዓመቷ
22. ላራራ አጋህ፣ 4 ዓመቷ
23. ታላቱ ማንጉዋ፣ 42 ዓመቱ
24. ግሬስ ዴቪድ፣ 45 ዓመቷ
25. Lovina ሰኞ, 19 ዓመቷ
26. Agah ሰኞ, 4 ና
27. ኑኃሚን ሰኞ, 37 ar
28. ኖኤል ዴቪድ፣ 13 ዓመቱ
29. ጁሙሚ እስጢፋኖስ፣ 10 ዓመቱ
30. ሰኞ Keyi, 37 ar
31. ጄሪ ሙሴ፣ 7 ዓመቱ
32. ጄምስ ሙሴ፣ 10 ዓመቱ
33. ያዕቆብ ሙሴ፣ 3 ዓመቱ
34. ዳንጁማ ጋዶ፣ 38 ዓመቱ
35. ዓርብ ሙሴ, 14 ar
36. ጣላቱ ሙሴ፣ 47 ዓመቷ
37. አኩስ ሙሴ፣ 46 ዓመቱ
38. አሲ ጄሪ፣ 58 ዓመቱ
39. ቴሌ ዘአ፣ 29 ዓመቱ
40. ብሬ ሸቱ ናንዙዋ፣ 61 ዓመቱ
41. ናንዙዋ ኢቭ፣ 5 ዓመቷ
42. ካጃ ዳንኤል፣ 42 ዓመቷ
43. ኤሊሻ አንቶኒ፣ 37 ዓመቷ
44. አና አንቶኒ, 67 ዓመቷ
45. ዳንላሚ ራንዱም (ሙላ)፣ 49 ዓመቱ
46. አዶ ዳንጁማ፣ 17 ዓመቱ
47. ሳራ ኩላ፣ 16 ዓመቷ
48. ኢሻያ ሙሴ፣ 10 ዓመቱ
49. ሁዋን ሙሴ፣ 5 ዓመቱ
50. እሑድ ማንጓ, 25 ና
51. ሙሴ ባላ፣ 43 ዓመቱ
መረጃው ከናይጂሪያ ኦርቶዶክስ ካህን የተገኝ ነው
https://www.facebook.com/100092641014007/posts/585926121172083/?app=fbl

Ayu Prince
👍1💔1
ይሁዳን አገኘሁት!

ይሁዳን ስናነሣ በተቀደሰ መንገድ አገልግሎታቸውን ፈጽመው ያረፉ ቅዱሳን ሰዎች መኖራቸውንም መርሳት የለብንም።

አንዳንድ ሰዎች ሌላ ይሁዳ ያለ ስለማይመስላቸው መልዕክት የጻፈልንን ሐዋርያ ጌታን ከሸጠው ይሁዳ ጋር ሲያምታቱ ይሰማሉ።
“የተረገመ ነበር አንድ ምዕራፍ ያላት መልዕክት ጽፎ ቀረ” ብለው ፈገግ የሚያደርጉን አንዳንድ ሰባኪዎችም ሳናይ ሳንሰማ አልቀረንም።

ለማንኛውም እኔ ለዛሬ ልጽፍላችሁ ወደ ምፈልገው መልዕክት ልመለስና ይሁዳን የት እንዳገኘሁት ልንገራችሁ።

ተመሳስሎብህ እንዳይሆን ካላችሁኝ የለም ራሱ ይሁዳ ነው ብየ በእርግጠኝነት እነግራችኋለሁ። ከሁለት ሺህ ዓመት በኋላ የት አገኘኸው? የሚል ጥያቄ ከልባችሁ ሲወጣ ይታየኛል።

እኔንም ያስገረመኝ እሱ ነበር ግን እናንተም ብትገረሙ ነው የሚሻላችሁ ይሁዳ ዛሬም አለ።
ኃጢአት ከብዶት ወደ ክርስቶስ የመጣው ይሁዳ “እናንት ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ” ማቴ. 11፥28 የሚለውን ጥሪ ሰምቶ የመጣ ቃለ እግዚአብሔር ገብቶት በራሱ ተነሳሽነት የተመለሰ ሰው ነው።

አምላከ መምህራን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ጴጥሮስና እንደ ዮሐንስ ባለበት ቦታ ሂዶ ጠርቶ አላመጣውም፤ ራሱ ከኃጢአት ለመሸሽ የመጣ ሰው ነው።

በጽድቁ ስፍራ ኃጢአት ያገኘኛል ብሎ መች አሰበና እንዲሁ መጥቶ በጌታ ፊት ሰገደ ኃጢአቱ ተተወችለት።

ከመጣ በኋላ የተለወጠችው መንገዱ ይሁዳ ቀድሞ ያሰባትና የጠበቃት አልነበረችም። ይሁዳ ከኃጢአት ከመፈታት በቀር ሌላ ምኞት አልነበረውም። ግን እንዳሰበው መቀጠል አልቻለም። ከኃጢአት ሸሽቶ የመጣው ይሁዳን ኃጢአት በዚህም ስፍራ ጠበቀችው። ለካ ወደ መንፈሳዊ ስፍራ ገብቶ መቆም ብቻ ሳይሆን ልብን መንፈሳዊ ማድረግ ግዴታ ነው።

ካህኑ ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት “ኦ እኁየ ሀሉ በዝንቱ መካን እንዘ ትሔሊ ኃጣውኢከ፤ ወንድሜ ሆይ በዚህ ቦታ ኃጢአትህን እያሰብህ ኑር” ብሎ የሚያውጀው በመንፈሳዊ ቦታ መቆማችን ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ነገር በማሰብ ጸንተን አለመኖራችን በመንፈሳዊ ቦታ ሥጋዊ ሥራ ሊያሠራን ስለሚችል ነው።

ዛሬም ዓለማዊነት ሰልችቷቸው፣ መንፈስ ቅዱስ ከዕለታት በአንዱ ቀን በልባቸው አድሮ ዕለተ ሞታቸውን አሳስቧቸው ከታሰሩበት ልማድ ሊፈቱ የሚመጡ ብዙዎች ናቸው።

መብላት መጠጣት፣ ማግባት መፍታት፣ መስረቅ መቀማት፣ ጉቦ መብላት ፍርድ ማድላት፣ መተኛት መነሣት ሆኖባቸው ሕይወት ግራ የምታጋባ ሆናባቸው ደግመው ላይመለሱ ምለው ከዓለም የተመለሱ ሰዎች ዛሬ ንስሐ ገብተው ቢያገኛቸው “ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኗል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቷል” ሉቃ. 15፥24 ብሎ ክርስቶስ የተቀበላቸው ናቸው።
ጠልተዋት የመጧት ኃጢአት መልሳ በሌላ መንገድ ወረሰቻቸው። ያንጊዜ ከሰሩት ይልቅ የከፋ በደልን ወደ መሥራት ተሸጋግረዋል።

ይሁዳ ከጸሐፍት እና ከፈሪሳውያን አንዱ ስንኳ ያልደፈረውን ኃጢአት እንደሠራ እነዚህም በዓለም ሳሉ ከሠሩት ይልቅ ወደ መቅደሱ ከመጡ በኋላ የሠሩት ኃጢአት ይበልጣል።

ከጸሐፍት ከፈሪሳውያን መካከል ክርስቶስን ለመግደል እንጅ ለመሸጥ ያሰበ አልነበረም ይሁዳ ግን ሊሸጠው እየመከረ ነው ማቴ. 26፥15።
ይሁዳ ዓለማዊ ሳለ ያልታወቀች ኃጢአቱን ሊናዘዝ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀረበ፤ መንፈሳዊ ከሆነ በኋላ ግን የተገለጠች ኃጢአቱን በማስመሰል ሊሰውር ፈለገ።
በልቡ ያሰባትን ኃጢአት ገልጾ መናገሩ ተመልሶ እንዲተዋትና ወደ መዳን እንዲመጣ ነበር እሱ ግን አላደረገውም እንዲያውም ከወንድሞቹ ጋር አብሮ “እኔ እሆንን?” ማለት ጀመረ ማቴ. 26፥25 ድሮ ዓለማዊ ሳሉ ሰዎችን ሲዋሹ ይደነግጡ የነበሩት ሰዎች ዛሬ ፈጣሪአቸውን መዋሸትን እንደ ቀላል ነገር ቆጥረዋታል።

ከመቅደስ ወጥተን በገሀነም እንዳንጣል እግዚአብሔር የሰጠንን ዕድል ካለመጠቀም በላይ ይሁዳነት አለ? በዓለም ከሠራነው በላይ ኃጢአትን አብዝተን በመንፈሳዊነት ሰበብ ከመሥራት የሚበልጥ ይሁዳነትስ የት ይገኛል? መጠጥ ቤት ገብቶ ማመንዘር ምናልባትም ወደ ዝሙት የሚገፋፋ መብልና መጠጥ ስላለ ሊሆን ይችላል፤ ቤተ መቅደስ ገብቶ ማመንዘር ግን በምን ሊተረጎም ይችላል? መጠጥ ቤት ያሉ ሰዎች ፈልገውት የመጡ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ቤተ መቅደስ ያሉት ግን ሴቶችም ሆነ ወንዶች ይህንን አስበው የመጡ አይደሉም።
ታዲያ መንፈሳዊ አገልግሎትን ጥግ አድርጎ ነውር መሥራት ይሁዳነት አይደለም?

ይሁዳ በሌላም ቦታ ዘወር ዘወር ብትሉ ታገኙታላችሁ። በክርስቶስ ጉባኤ ብዙ ዕዳ ያለባት ሴት ቀርባ እግሩን ይዛ እያለቀሰች ይቅርታ ጠየቀች፤ ክርስቶስም ብዙ ኃጢአቷን ተወላት። ይሁዳ እንደ አገልጋይነቱ ብዙ ኃጢአቷ በተተወላት ሴት ደስ ሊሰኝ ሲገባው ይዛው የመጣችው ሽቶ ተሽጦ ለድሆች ባለመሰጠቱ ማንጎራጎር ጀመረ።

ወደ ቤተ መቅደስ መጥተው ንስሓ የሚገቡ ነፍሳትን ሳይሆን የሚያመጡትን ሳንቲም የሚጠባበቁ ሰዎችን ባየሁ ጊዜ ይሁዳን በዘመናችን ባለችው ቤተ መቅደስ መኖሩን አረጋግጣለሁ። “ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ የአምላኬንስ ፊት መቼ አያለሁ?” መዝ. 42፥2 እያሉ በናፍቆት የመጡ ምዕመናንን ማሰናከል እግዚአብሔርን እንዴት እንደሚያሳዝነው ብናስብ እኮ እንዴት ያስፈራል መሰላችሁ!

ለገንዘብ ማስቀመጫዎቻችን የምንጠነቀቀውን ያክል ለምዕመናን ነፍሳት አለመጨነቃችንን ሳስብ ከዚህ በላይ ይሁዳነት አለ? ብየ ከራሴ ጋር እሟገታለሁ።

አንድ የገንዘብ ሳጥን {ሙዳየ ምጽዋት} ቢጠፋ በዕለቱ ይታወቃል አንድ ምዕመን ቢጠፋ ግን በዓመቱም ላናውቀው እንችላለን። ገንዘብ ተቀባዩን በብዙ ሰነድ አስፈርመን ብዙ ማንነቱን የሚገልጡ ሰነዶች ተቀብለን እንቀጥረዋለን፤ በምዕመናን ላይ የምንሾመውን ካህንስ ካላችሁኝ የትምህርት ችሎታው አያስጨንቀን፣ የምዕመናን አባት አብነት መሆን ይችላል ወይ ብለን አንጠይቅ፣ በእጁ ስላሉ ምዕመናን መረጃ አይጠየቅ እንዲሁ ይዟቸው ወይም ይዘውት ይኖራል።

አንዳንድ ምዕመናን እኮ ለአባቶቻቸው አባት ሆነው እየኖሩ ነው እኛ ይህ ሁሉ አያስጨንቀንም። ከቤታቸው እኩል ለንስሐ አባቶቻቸው ዕዳ የወደቀባቸው ምዕመናን ብዙ ሆነው እንመለከታለን።

በክርስቶስ ያሳመንናቸው የፈረሰ ቤታችንን እንዲሠሩልን ነው? የተጣመመ ኑሯችንን እንዲያቃኑልን ነው? ለዚያውም አንዳች ቃለ እግዚአብሔር ያልነገርናቸው በክርስቶስና በገብርኤል መካከል ያለውን ልዩነት እንኳን ያላስተማርናቸው የዋሆችን ክርስቶስን በማወቅ ነው እንጅ የኛን ቤት በመሥራት ገነት ይገቡ ይመስል ገንዘባቸውን እንጅ ልባቸውን ያልሰበሰብናቸው ብዙ ናቸው።

አንዳንድ ምዕመናንም የሰበካ ጉባኤ አባል ሆነው ሲመረጡ ልማት የሚመስላቸው ሕንጻ መሥራት ግቢ ማጽዳት ነው እንጅ ምን ያክል ምዕመን ሠርክ ጉባኤ ይከታተላል፣ ስንት ሰው ልጆቹን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ያስተምራል፣ ከተመዘገበው ምዕመን ስንቱ ይቆርባል ብለው አያስቡም።

ዕቅዱን ሁሉ በየቤተ ክርስቲያኑ እየዞራችሁ ብትመረምሩ ስንት ገቢ እናስገባለን፣ ስንት ወጪ እናወጣለን አይነት ነው እንጅ ድኅነተ ምዕመናንን ታሳቢ ያደረገ ዕቅድ ብዙም አታገኙም። ፈርታችሁ ካልሆነ እናንተም ይሁዳን አግኝታችሁት ታውቃላችሁ።
👍3
በአጥቢያችሁ በዓመት ለምን ያኽል ጊዜ ታቦት ይወጣል? ስንት ድርብ ታቦት አለ? ለክርስቶስ ተብሎ የመጣውን ሽቶ ሽጦ መክበር የሚፈልጉ ሰዎች ክርስቶስን የሚያገለግሉት የሽቶው ብር ተሽጦ ገቢ እስከተደረገ ድረስ ብቻ ነው። ካልሆነ ጉባኤው ክርስቶስን መስማቱን ትቶ “ይህ ገንዘብ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይገባ ነበር” በሚል የእንጉርጉሮ ቃል እንዲሞላ ለማድረግ ፈጣኖች ናቸው።

ከላይ ስትመለከቱት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ካላቸው ፍቅር የተነሣ የሚመስል ውስጡ ግን የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር የተፈጠረ አጀንዳ መቅረጽ የሚችሉ ይሁዳዎች በእኛ ዘንድ ብዙ አሉ።

የተነሡት አለቆች፣ ጳጳሳት እና ሌሎችም አገልጋዮች ሁሉም ሥራ አበላሽተው ቤተ ክርስቲያንን በድለው ይመስላችኋል? ምናልባትም የሴቲቱን ዕንባ እንጅ የያዘችውን የአልባስጥሮስ ሽቶ ስለማይመለከቱ በከረጢት ያዦች ዘንድ ነገራቸው ስላልተወደደ ይሆናል ዮሐ. 12፥6።

ይሁዳ ይኼውላችሁ ከሚፈሰው እንባችን ይልቅ የሚፈሰው ሽቶ የሚያስቆጨው ከዳኑ ነፍሳት ይልቅ ከነሱ የሚያገኘውን ጥቅም የሚያስቀድም ሰው ካገኛችሁ ይሁዳ እሱ ነው።

ይሁዳ በሌላም ቦታ አለላችሁ። ይሁዳ ክርስቶስን ሸጠ፤ ጸጋውን ሽጦ መኖር የሚፈልግ ስንት ይሁዳ አለ መሰላችሁ? መጽሐፍ እንደነገረን ክርስቶስ ጸጋ ሆኖ ተሰጥቶናል ዮሐ. 1፥18 ይህንን ጸጋ ምዕመናንን ከመጥቀም በቀር ለሌላ ጥቅም ማዋል ይሁዳነት ነው።

ለሚያስተምር መምህር የሚገባውን ዋጋ መክፈል ምዕመናን የታዘዙት ትዕዛዝ ነው። ሐዋርያው እንደነገረን በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል የለምና።

ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላም አይገኝም። መምህራንም መንፈሳዊውን ዘርተው ሥጋዊውን እንዲበሉ ተፈቅዶላቸዋል። ነገር ግን ከአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት የተለየ መቀበል ከይሁዳ በቀር ማንም የማያደርገው ነውረኛ ገንዘብ dirty money ነው።

ቤተ ክርስቲያን በየቀኑ “ለይሁዳ ወልዱ ወውሉደ ውሉዱ ይደምሰስ” እያለች ብትረግመውም ይሁዳ ግን ዛሬም አለ። የሄው በእኔ ውስጥ፣ በእናንተም አጠገብ ይሁዳን አገኘሁት።

እስኪ የእናንተን ሀሳብ ልስማ? ይሁዳ አለ ወይስ ሞቷል?

©️ስምዐኮነ መልአከ
👍2
ሰሙነ ሕማማት
  ዕለተ ሐሙስ

"…እንበለ ደዌ ወሕማም፤ እንበለ ፃማ ወድካም፤ ዓመ ከመ ዮም፤ ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍሥሐ ወበሰላም…

፩፥ የምሥጢር ቀን

"…ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፦ እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው። ማቴ 26፥ 26-28
                  
፪፥ ሕጽበተ እግር/

"…ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ። ዮሐ 13፥ 4-5

፫፥ ምሴተ ሐሙስ/ሐሙስ ምሽት/ጸሎተ ሐሙስ

"…በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደምትባል ስፍራ መጣ ደቀ መዛሙርቱንም፦ ወዲያ ሄጄ ስጸልይ ሳለ በዚህ ተቀመጡ አላቸው። …ወደ ደቀ መዛሙርቱም መጣ፤ ተኝተውም አገኛቸውና ጴጥሮስን፦ እንዲሁም ከእኔ ጋር አንዲት ሰዓት እንኳ ልትተጉ አልቻላችሁምን? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው። ማቴ 26፥ 36-41
👍31
2025/08/28 18:33:05
Back to Top
HTML Embed Code: