Telegram Web
#እናመሰግናለን🙏
#የብፁዓን_አባቶች_አስተምህሮ_በተመለከተ
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም የመጨረሻ የጉባኤ ውሎ
አስመልክቶ የብፁዓን አባቶች አስተምሮ በተመለከተ ቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት የሊቃውንት ጉባኤ በሦስት ብፁዓን አባቶች ማለትም በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ጳጳስ ; በብፁዕ አቡነ በርናባስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ሊቀ ጳጳስ በተላለፉ ትምህርቶች ላይ ያቀረበውን የስህተት ትምህርት የሚያሳይ አስተያየት እና የውሳኔ ሐሳብ ቀርቧል። ምልዓተ ጉባኤውም የሦስቱን አባቶች አስተያየት አዳምጦ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል ።
በሦስቱ ብፁዓን አባቶች ማለትም በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ጳጳስ ; በብፁዕ አቡነ በርናባስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ጳጳስ ጥፋታቸውን አምነው በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት ቀርበው ይቅርታ በመጠየቅ ;በሊቃውንት ጉባኤ የቀረበው እውነተኛ የቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ የሚያምኑ እና የሚያስተምሩ መሆኑን በመግለጽ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ ጠይቀዋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ይቅርታቸውን በመቀበል ያስተላለፉትን የስህተት ትምህርት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (#EOTCTV) ቀርበው በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት የሰጡትን የእምነት ክህደት ቃል አስተምህሯቸውን አርመውና አስተካክለው እንዲያስተላልፉ መመሪያ ሰጥቷል።
ወደፊትም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና መምህራን የሃይማኖት ትምህርት ሳይሸራረፍ ለትውልድ ለማስተላለፍ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና በአከራካሪ ጉዳዮች በግለሰብ ደረጃ ምላሽ እንዳይሰጥ ጉባዔው ወስኗል ።

© የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት
❤‍🔥4👍31😁1
#የቅዱስ_ሲኖዶስ_ምልዓተ_ጉባኤ_ልዩ_አጀንዳ

ቅዱስ ሲኖዶስ በዚሁ ዕለት የተመለከተው የተለየ አጀንዳ፤ ለረጅም ዘመን ቤተክርስቲያንን ያገለገሉ ብፁዓን አባቶችን የተመለከተ ነው፡፡ በዚህም ላይ ውይይት አድርጎ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት በኤጲስ ቆጶስነት ተሹመውና በየአህጉረ ሰብከቱ ተመድበው ለረጅም ዘመን ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መዋቅርና ትውፊት ጠብቀው፣ የሚያስፈልገውን መሥዋዕትነት ሁሉ ከፍለው፣ ለቤተ ክርስቲያን ልዕልና' ለሐዋርያዊ ተልዕኮ መስፋፋትና ለእናት ቤተክርስቲያን ተቋማዊ እድገት የዕድሜ ልክ አገልግሎት የሰጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፡-
ብፁዕ አቡነ ታዴዎስ የካሪቢያንና የላቲን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ዮናስ የአፋር ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ስምዖን የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ
ሌሎችም አረጋውያን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
በምልዓተ ጉባኤው ዕውቅነና እንዲሰጣቸው ሆኖ የሚሰጠው ዕውቅና የሚታይና የሚታወስ እንዲሆን፤ አፈጻጸሙም ደግሞ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ሳይዘገይ እንዲፈጸም በማለት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡

በቋሚ ሲኖዶስ ስለሚያገለግሉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቋሚ ሲኖዶስ የሚያገለግሉ አባቶችንም መርጧል፡፡ በዚህም መሠረት፡-
ከግንቦት 2017 እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ላለው የሥራ ጊዜ
1. ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል — የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊና የከፋ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ
2. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ—የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት የበላይ ኃላፊ እና የምሥራት አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ
3. ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ — የጉራጌ ሀገረ ስብኡት ሊቀጳጳስ
4. ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ— የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ናቸው፡፡
ከነሐሴ 1 ቀን 2017 እስአ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ላለው የሥራ ጊዜ
1. ብፁዕ አቡነ ያሬድ— የሰበካ ጉባዔ ማደራጃ መምሪያ እና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
2. ብፁዕ አቡነ በርናባስ— የዋግሕምራ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
3. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ— የኢጣሊያና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
4. ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ— የምሥራቅ ጉራጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ
የቋሚ ሲኖዶስ አባላት ሆነው እንዲሠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

መ/ር ጌታቸው በቀለ
👍2
#ቅዱስ_ሲኖዶስ
"ያልተገባና መሠረት የሌለው መግለጫ የሚያሰራጩ አካላት እንዲታረሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ለአንዴየና ለመጨረሻ ጊዜ በጥብቅ ያሳስባል"

የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ አካሂዷል፡፡
የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና እድገት፣ ለሀገር ሰላምና መረጋጋት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋትና ለመንፈሳዊ ልዕልና ልዩ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ መስጠት፣ምትክ ለሌለው የሰው ልጅ ሕይወት ባለአደራ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ሰላም ያለማቋረጥ መጸለይ፣ ጸሎተ ምሕላ ማወጅ፣ የሰላምና የአንድነት ጥሪ ማስተላለፉ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሰላምና ለአንድነት ልዩ ትኩረት ሰጥተው ሁሉን አቀፍ ሥራ የሚሠሩ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን “የሀገራዊ ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ኮሚቴ” በማድረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
ኮሚቴውም ዘላቂ ሰላምንና አንድነትን ለማስፈን፣ የዜጎችን ሕይወት እየነጠቀ ያለው ግጭት እንዲቆም ጥረት እንዲያደርግ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ባካተተ መልኩ በየደረጃው የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና፣ ውይይቶችንና የጥናት መድረኮችን እንዲያዘጋጅ፤ አፈጻጸሙንም በየሦስት ወሩ ለቋሚ ሲኖዶስ ሪፖርት እንዲያደርግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
2. ለሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የትርጓሜ መጻሕፍትና የሴሚናሪ ደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት ዲግሪ እንዲሆን በተወሰነው መሠረት በመማር ላይ ያሉትና በቀድሞው ሥርዓተ ትምህርት ተምረው በመመረቅ ቤተ ክርስቲያናችንን በማገልገል ላይ የሚገኙት ምሩቃን ተጓዳኝ ትምህርቱን ተምረው ዲግሪያቸውን ማግኘት እንዲችሉ የቀረበው ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ እንዲደረግ፣በኮሌጁ የተጀመረው ሁለገብ ሕንፃም በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ መሠረት እንዲጠናቀቅ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3. በገዳማት አስተዳደር መምሪያ አስፈጻሚነት የተደረገው የአንድነት ገዳማት ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ በየዓመቱ እንዲካሄድና የአቋም መግለጫው ላይ የቀረቡት ሐሳቦች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በኩል እየታዩ በቅደም ተከተል እንዲፈጸሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስልፏል፡፡
4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገራችን እድገትና ሥልጣኔ ፈር ቀዳጅ በመሆን ያበረከተችው አስተዋጽኦ በታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ጉልህነት ያለው ሲሆን፣ አሁንም እየተሠራ ባለው የኮሪደር ልማት መርሐ ግብር ላይ ኃላፊነቷን እየተወጣች ትገኛለች፡፡
ይኽን ቋሚ ታሪክ ያልዘነጋው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ ለግንባታ በሚያመች ሁኔታ አሰባስቦ በመስጠት ለፈረሱ ቤቶች ካሣ በመክፈል፣ በጽርሐ ምኒልክ ሕንጻ ምትክ በነባሩ ቦታ ላይ B+G+4+ቴራስ በመንግሥት በጀት መልሶ እንዲገነባ በማድረጋቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

በይዞታዎቻችንም ላይ ደረጃውን የጠበቀ ግንባታ ለማካሄድ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተሰይሞ ገቢ የማሰባሰብ ሥራው በሕጋዊ መንገድ እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
በመሆኑም በፈረሱት ቤቶች ምትክ የተረከብናቸውን ክፍት ቦታዎች በአጭር ጊዜ ማልማት ግዴታ ስለሆነ በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እንደ አባቶቻችሁ የታሪክ ባለቤቶች ትሆኑ ዘንድ ልማቱን በገንዘብና በእውቀት እንድታግዙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
5. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የተፈጠረውን የአስተዳደር ችግር አስመልክቶ በብፁዓን አባቶች የሚመራው አጣሪ ልዑክ ባቀረበው ሪፖርት መሠረት ውይይት በማድረግና የሥራ ኃላፊዎቹን በማንሣት ቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡
ወደፊትም በየደረጃው ያለውን ችግር ማስተካከል ይቻል ዘንድ ችግሩን እያጠና የሚያቀርብ ኮሚቴ እንዲቋቋም ምልአተ ጉባኤው ወስኗል፡፡

6. ዝክረ ኒቅያ በሚል መሪ ቃል ከመላው ሀገራችን በተወከሉ የምስክር ጉባኤ ቤቶች መምህራን በተካሄደው ጉባኤና የጥናት ውይይት የቀረበው ምክረ ሐሳብ እጅግ የሚጠቅም የሊቃውንት ድምጽ በመሆኑ፣በነገረ ማርያም፣ በነገረ ክርስቶስና በሌሎችም አስተምህሮዎች ዙሪያ የተሰጡት ሐሳቦች የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜን መሠረት በማድረግ ተብራርቶና ተስተካክሎ፣ የጎደለው ሞልቶ፣ የጠመመው ተቃንቶ በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በመጽሐፍ መልክ እንዲታተም፣በሚዲያ ሊተላለፍ የሚገባው አስተምህሮ ደግሞ በሊቃውንት ጉባኤ ብቻ እንዲተላለፍ፣
የሊቃውንት ጉባኤውም በተሟላ የሰው ኃይልና በጀት ተጠናክሮ እንዲደራጅ፣ሀገር አቀፍ ጉባኤው በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲደረግና የጉባኤው መዋቅር በየአህጉረ ስብከቱ እንዲጠናከር ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

7. የመናገሻ አምባ ማርያምና የጋራው ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም ጥንታዊ የሆነ ሰፊ ታሪክ ያለው በመሆኑ ሁለቱ ገዳማት በአንድ አበምኔት በአንድነት ገዳም ሥርዓት በጋራ እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

8. በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት መነኰሳትን ከመላክ ጀምሮ፣በአስተዳደራዊና ቀኖናዊ አሠራር ክፍተት ምክንያት የተከሰቱ ችግሮችን በማረምና ሊቀ ጳጳሱን በማዛወር ማእከላዊ መዋቅር እንዲጠበቅ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን፣ነባሩ መተዳደሪያ ደንብ ተሻሽሎ እንዲቀርብ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ሰይሟል፤

9. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ልቡና፣በሕገ ኦሪትና በሕገ ወንጌል ያገኘቻቸው ዶግማዊ፣ ቀኖናዊና ትውፊታዊ ሀብቶቿ የሕግ ጥበቃና ከለላ አግኝተው ሃይማኖታዊ፣ታሪካዊና ሁለንተናዊ ይዘታቸውን ሳይለቁ ተከብረውና ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
10. የ2018 ዓ.ም የመደበኛ እና የካፒታል ዓመታዊ በጀት ብር 5,407,415,607.25/አምስት ቢሊየን አራት መቶ ሰባት ሚሊዮን አራት መቶ ዐሥራ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰባት ብር ከሃያ አምስት ሣንቲም/እንዲሆንና የበጀት አርዕስቱ ተጠብቆ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

11. በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ሕንጻ በተመለከተ የተፈጠረው የአሠራር ግድፈት እንዲታረም፣ዩኒቨርስቲው ከባንክ ጋር የገባው የብድር ውል እንዲቋረጥና የተጀመረውን ሕንፃ በራሱ አቅም እንዲገነባ ሆኖ፤ የቤተ ክርስቲያናችንን አንጡራ ሀብት ማለትም ሕንጻዎችን፣መሬቶችንና ሌሎች ቋሚ ንብረቶችን በማስያዝ የሚደረጉ ብድሮች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ የሚያደርግ መመሪያ ለሁሉም አህጉረ ስብከት እንዲተላለፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3👍2
12. የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅትን አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት መሠረት የሥራ ክፍተቱን በማረም በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች እንደየጥፋታቸው እንዲጠየቁና እንዲታረሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
13. የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምርጫን አስመልክቶ በሥራ ላይ የነበሩት ብፁዓን አባቶች የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ በመሆኑ ለቀጣይ ሦስት ዓመታት የሚሠሩ ብፁዓን አባቶችን ለመምረጥ ዕጩዎችን የሚያቀርቡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመሰየም ምልዓተ ጉባኤው ተገቢውን ምርጫ አከናውኗል፡፡
በዚሁም መሠረት ፡-
*. ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ በደቡባዊ ዞን ማይጨው፣ የደቡባዊ ምሥራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን መርጦ ሰይሟል

*. ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪጅነት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣የሸገር ከተማ እና የምስካዬ ኀዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስን መርጦ ሰይሟል፡፡
* ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የሀድያና ስልጤ አህጉረ ሰብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
* ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ መርጦ ሰይሟል፡፡
* ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ
* ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የሜኖሶታና የኮሎራዶ አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ መድቧል፡፡

14. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ሰብከት ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካልፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሚዲያ ያስተላለፏቸው ትምህርቶች ስሕተትና ነቀፋ ያለባቸው መሆናቸውን አምነው ቅዱስ ሲኖዶስንና መላውን ሕዝበ ክርስቲያን ይቅርታ በመጠየቅ ሊቃውንት ጉባኤ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማጣቅስ ያቀረበውን አስተምህሮ የተማሩት የሚያምኑትና የሚያስተምሩት መሆኑን በመግለጻቸው ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስቱን አባቶች ይቅርታ ተቀብሎ ወደፊት እንዲህ ዐይነት የስሕተት ትምህርት ውስጥ እንዳይገኙና ነቀፋ ያለበትን ትምህርታቸውን በማረምና በማስተካከል ርቱዕ የሆነውን የቤተ ክርስቲያናችንን አስተምህሮ መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን ሥርጭት ድርጅት በመቅረብ ትምህርት እንዲሰጡ በማለት ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
15. በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ በግልና በቡድን ተደራጅተው ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመክፈት ከሃይማኖት ሥነ ምግባር በወጣ መልኩ የቤተ ክርስቲያናችንን ልዕልና የቅዱስ ሲኖዶስን ክብር የሚጋፋ ፣የአባቶችንና የአገልጋዮችን ተልእኮ የሚያደናቀፍ ያልተገባና መሠረት የሌለው መግለጫ የሚያሰራጩ አካላት እንዲታረሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ለአንዴየና ለመጨረሻ ጊዜ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

በመጨረሻም በሀገራችን በአንዳንድ ቦታዎች የሚታየው ግጭትና መፈናቀል ተወግዶ፣የሰው ልጅ የመኖርና የመዘዋወር መብት ተከብሮ፣ ሰብዓዊ ክብሩ ተጠብቆ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በጋራ እንዲኖር፤ አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡

ግጭት፣ ጥላቻና ደም መፋሰስ፣ አካል ከማጉደልና ንብረት ከማጥፋት በቀር የሚያመጡት ክብርና ዘላቂ ሰላም ስለሌለ ልጆቻችን ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እንድትፈቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ደጋግሞ ጥሪውን በማቅረብ በመላው ዓለም ጦርነት ባለባቸው ሀገራት ሁሉ ሰላምና ዕርቅ እንዲሰፍን በመጸለይ ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ዓመታዊ ጉባኤውን በጸሎት አጠናቋል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
©የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

"በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”
ሐዋርያት ፳፥፳፰

🔵የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ስለ አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን።
1👍1
Forwarded from B-POEMS
መጥተህ እይ አለው

በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1:47 ላይ ፊሊጶስ ጌታችንን ካገኘው በኃላ ወደ ናትናኤል በመሄድ እንዲህ አለው "መጥተህ እይ"
ይህ ቀላል የሚመስል ነገር ግን ጥልቅ የሆነ ንግግር ነው። በስጋዊ ዐይናችን ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ዐይናችን ጌታችንን እንድናየው የሚጋብዝ መንፈሳዊ ጥሪ። ነገርግን ስንቶቻችን ነን ይህንን ጥሪ በእውነት እና በእርግጠኝነት ልንለው የምንችል?

ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ለመጥራት ፈጣን ነን ፤ ግን እኛስ አይተነዋል? ፊሊጶስ "መጥተህ እይ" ማለት ይችላል ምክንያቱም ክርስቶስን ቀድሞ አይቶት ስለነበር። ነገርግን ዛሬ ብዙዎች ይህንን ቃል ለመናገር ይቸገራሉ ምክንያቱም እውነተኛ ሆነው የሚያስተምሩትን እየኖሩት አይደለምና። ለምን ይሆን እኛ ሳናውቀው፣ በእውነት ሳናገኘው ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ለመጥራት እንደዚህ የምንጓጓው? እውቅና እና ገንዘብ ስለሚያስገኝ ይሆን? ባሁኑ ጊዜ ስለ ጌታችን መስበክ እውቅና እና ገንዘብ ያስገኝልን ይሆናል ነገርግን ከክርስቶስ ጋር ያለን እውነተኛ ግንኙነት እንዲኖረን እውነተኛ መሆንን፣ ትህትና ፣ ራስን መካድ ይጠይቃል ። ትኩረታችን መሆን ያለበት  ውጫዊው ላይ ሳይሆን ክርስቶስን በማየት የሚመጣው ውስጣዊ የማንነት ለውጣችን ላይ እንጂ።
ጌታ በወንጌል እንዳለ "አንተ ዕውር ፈሪሳዊ ውጪው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ"ማቴ 23:26

አስቀድሞ ማየት ከዛ ሌሎችን መጥታችሁ እዩ ብሎ መጋበዝ። እኛ ያላየነውን ነገር ሌሎችን መጥታችሁ እዩ ብለን መጥራት አንችልምና። ልክ ፊሊጶስ ክርስቶስን አይቶ ናትናኤልን እንደጠራው ሁሉ እኛም ሰዎችን ከመጥራታችን በፊት ከክርስቶስ ጋር ተባብረን መስራት ይኖርብናል። ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ በሚለው ትዕዛዝ ቅድሚያ ራስን መውደድ እንደሚገባን ሁሉ እንዲሁም መጥታችሁ እዩ ከማለታችን በፊት እኛ ራሳችን ቀድመን ማየት ይኖርብናል።

ናትናኤል በመጀመሪያ ስለ ክርስቶስ ሲሰማ ከናዝሬት መልካም ሰው ይወጣልን? ብሎ ጠይቆ ነበር ብዙዎች ዛሬም ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እውነተኛ ክርስቶስ ፣ እግዚአብሔር ይገኛልን? ብለው ይጠይቃሉ።
ናትናኤል ከክርስቶስ ጋር ሲገናኝ ጥርጣሬው ወደ መናዘዝ ተለውጦ መምህር ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ ብሎ መሰከረ። ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ እውነተኛ ክርስቶስ ፣ እግዚአብሔር ይገኛልን ብለው የጠየቁትም መጥተው ካዩ በኃላ ክርስቶስ በእውነት በዚች ቤተክርስቲያን ይገኛል ብለው ይመሰክራሉ። ልበ ንጹሐን ብጹአን ናቸው እግዚአብሔርን ያዩታልና ወንጌል እንደሚል ልባችንን ንጹሕ አድርገን እግዚአብሔር በማየት ሌሎችንም መጥታችሁ እዩ እንበል።

"አንድ ሰው ሌሎችን ንጹሕ ሁኑ ብሎ ከመጥራቱ በፊት ራሱ መንጻት አለበት፤ ማስተማር እንዲችል መማር አለበት ፤ ለማብራት ብርሃን መሆን አለበት፤ ሌሎችን ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ ራሱ መቅረብ አለበት፤ ለመቀደስ መቀደስ አለበት።" ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ኦሬሽን 2 ክፍል 7

ብሩክ መለሰ
3
ይህንን ቻናል ተቀላቀሉት

መክብብ 12 : 1 የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ብንኖር በዚህ ቻናል ላይ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ ግጥሞች ፣ ወጎች ፣ የተለያዩ ጽሑፎች ይቀርባሉ። የቻናሉ ቤተሰብ በመሆን አጋርነቶን ያሳዩን
👍3
🎓 ፕሮፌሰር አባ ኃይለገብርኤል ግርማ፣ (PhD, Ed.D., Psy.D.!) 🎓 🎓 Congratulations to Abba Hailegebriel Girma, PhD, Ed.D., Psy.D.! 🎓

በብዙ የምንወዳቸውና ለብዙዎቻችን አርአያ የሚሆኑ አባታችን ፕሮፌሰር አባ ኃይለገብርኤል ግርማ ሶስተኛ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን – ፓሪስ ከሚገኘው የአውሮፓ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጂ (Psy.D.) አጠናቀዋል!

ይህ ትልቅ ምዕራፍ ለአካዳሚክ ልህቀት፣ ለመንፈሳዊ አመራር፣ እንዲሁም ቤተክርስቲያንንና ማኅበረሰባችንን ለማገልገል የሥነ ልቦና እና ነገረ መለኮታዊ ጥበብን ለማቀናጀት ላላቸው የማያወላውል ቁርጠኝነት ምስክር ነው።

📚 በትምህርት፣ በነገረ መለኮት እና አሁን ደግሞ በሥነ ልቦና የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው ፕሮፌሰር አባ ኃይለገብርኤል ብርቅዬ የሆነውን የትምህርት ፣ የክርስቲያናዊ እረኝነት፣ የምዕመናን አያያዝ እና የዲቨሎመንታል ጥናት ላይ ሠፊ ዝግጅት ያላቸውና እነዚህን ጉዳዮች አስተባብረው የያዙ ብቸኛ አባት ናቸው።

በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ፕሬዝዳንት በኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት እና ሥነ ልቦና ጥልቅ መረዳት ያላቸው ፕሮፌሰር በመሆናቸው ለዩኒቨርስቲያችን፣ ለቤተክርስቲያን እና በሀገራችን በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች እያበረከቱ የሚገኘው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው።

እንኳን ደስ አሎት አባቴ
15
ባሕር ዳር

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅነት መልስ በባሕር ዳር ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው:

ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሦስት ዓመታትን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ዘመናቸውን አጠናቀው ወደ ሀገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል።

በባሕር ዳር በሚገኘው ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም ምእመናኑ በታላቅ ደስታና ድምቀት ተቀብለዋቸዋል።

ይህን አስደሳች አቀባበል ለማድረግ

1. የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ
2. ከተለያዩ ገዳማትና አድባራት የተውጣጡ አስተዳዳሪዎች
3. ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን
4. የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን
5. እንዲሁም በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ተገኝተዋል።

ቀጣይ መርሐ ግብሮች በመንበረ ጵጵስናው
የብፁዕነታቸው አቀባበል ሥነ ሥርዓት በአየር ማረፊያው የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በባሕር ዳር በሚገኘው ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል መንበረ ጵጵስና ቀጥሏል። በዚያም የተለያዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብራት እየተከናወኑ ይገኛል::

📷ፈለገ ገነት ሚዲያ
10🙏1🤣1
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ ዘለዓለም ሥላሴ።
በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች፣ የጉባኤ ቤታችን ቤተሰቦች በሙሉ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን እንደምን ሰነበታችሁ? እኛ አምላከ አበው እግዚአብሔር ይመስገን ደኅና ነን።
የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች ገዳም የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት የምስክር ት/ቤት በእሳት እንደተቃጠለ በማኅበራዊ መገናኛ መረቦች እየተላለፈ እንደሆነ ብዙዎቻችሁ ተጨንቃችሁ ደውላችሁልናል።
በመሆኑም ከጉባኤ ቤቱ ሐሙስ ግንቦት ሰባት ቀን እሳት ከቤት ተነሥቶ ለደቀ መዛሙርቱ ተሠርቶ የነበረ ቆርቆሮ በቆርቆሮ ጊዚያዊ መጠለያና የግማሾቹ ደቀ መዛሙርት ልብስና መጻሕፍቶቻቸው ተቃጥለዋል። ነገር ግን በሰማዕቱ በቅዱስ ቂርቆስና በእመቤታችን ጸሎት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠብቆን ጉባኤ ቤታችንና መጻሕፍቶቻችን ደኅና ናቸው።
እኛም ደቀመዛሙርቱና ዋናው ጉባኤ ቤት፣ እንዲሁም ገዳማችን ደኅና ስለሆነ፣ ጊዜው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የተጀመረበት በመሆኑ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ተጨማሪ ርእሰ ጉዳይ ላለመጨመር ለሚዲያ ሳንገልጽ ቆይተናል።በመሆኑም አሁን ግን ስለወጣ ይህንን መግለጫ ለተጨነቃችሁ ወገኖቻችን ልንገልጽ ፍቅር ያገብረናል።
ለጉባኤ ቤቱ የሚያስፈልጉን ጉዳዮች ቢኖሩ እኛ በፈወስ መንፈሳዉ የጉባኤ ቤታችን ሚዲያ በምስል የምንገልጽ መሆናችንን እየገለጽን ፣ ለተጨነቃችሁልን፣ለጸለያችሁልን፣ላሰባችሁልን፣ለረዳችሁን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ የጉባኤ አምላክ በምሕረቱ ያስብልን።
አምላከ ጉባኤ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያናችንንና ሀገራችንን ይጠብቅ።
የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና እናቶች አንድነት ገዳም የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ቤተ ጉባኤ
ግንቦት፳፫-፳፻፲፯ ዓም
1
2025/08/25 10:19:01
Back to Top
HTML Embed Code: