Telegram Web
የአፈና ዜና…

"…አቶ ዳንኤል ክብረት ቂም የያዘባቸው፣ በጦማሩ ሲጠቅሳቸው የከረመው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሰሜን ሜጫ ወረዳ ቤተ ክህነት ድል በትግል ቀበሌ የምትገኘው የፈለገ ብርሃን ናዳ ቅድስት ማርያም እና የክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም
አበምኔት የሆኑትን ታላቁ አራት ዓይናው የአራቱ ጉባኤ መምህር፥ የፍትሐ ነገሥቱ፣ የአቡሻኸሩ ሊቅና የቅኔው ጌታ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ ዛሬ ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ ወደ ገዳሙ ባቀኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለጥያቄ እንፈልግዎታለን ተብለው በወታደር አጀብ መወሰዳቸው ተነግሯል።

"…የአይን ምስክሮቹ እንደነገሩኝ ከሆነ መጀመሪያ ለአንዳንድ ጥያቄ እንፈልግዎታለን ብለው ወደ ቢኮሎ ዓባይ ወሰዷቸው። በዚያም አርበኛ ዘመነ ካሤን ካለበት ፈልገው ካላመጡት አንለቅዎትም በማለት በዚያ አዋሉአቸው፣ በመቀጠልም ከቢኮሎ ዓባይ አዙረው ወደ ዱር ቤቴ ወሰዷቸው፣ በዚያም መንፈሳዊ ልጅዎ ነውና አርበኛ ዘመነ ካሤን ይውለዱ ሲሏዋቸው ዋሉ ከዚያ ሲመሽ አሁን ምሽት ላይ ወደ ባህርዳር አምጥተው ባህርዳር በመከላከያ ካምፕ መኮድ ውስጥ እንዳሰሯቸው ተሰምቷል።

"…አቶ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም አስር ጊዜ የኔታ ይባቤ የኔታ ይባቤ እያለ የሚከሳቸው፣ የደቡብ ጎንደሮቹ አፍቃሬ ብአዴኖቹ እነ አያሌው መንበርም በተደጋጋሚ የሚዝቱባቸው አራት ዓይናው ሊቅ የኔታ ይባቤ በስተመጨረሻ በኦሮሙማው አገዛዝ እጅ ወድቀዋል። ቀጥሎ ምን ይሆናል? አብረን እናያለን። የክሱ መነሻም 7ተኛው ንጉሥ የአሕመድ ልጅ ሳይሞት አርበኛ ዘመነ ካሤን ለንግሥና ቀብተዋል የሚል ነው። ከዚህ ቀደም እስክንድር ነጋ ይነግሣል ተብሎ ደብረ ኤልያስ መውደሙ የሚታወስ ነው።

• ሻሎም…! ሰላም…!
1
አባታችን ሊቀ ብርሃናት የኔታ ይባቤ በላይ ለምን ታሠሩ?
የቅኔ፣የ፹፩ መጻሕፍት፣የአቡሻኽር፣የጥበባት መምህሩ፣
የናዳ ገዳም አበ ምኔት (አስተዳዳሪ)

ለበርካታ ዓመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ወንበር ዘርግተው ደቀ መዛሙርት አብዝተው ሲያስተምሩ የኖሩ እያስተማሩ ያሉ ናቸው።

እንደ አባትነታቸው ትጉኅ አበ ምኔት ናቸው መቆፈሪያ ይዘው ዕርፍ አርቀው ሞፈር ጠርቀው አርሰው ቀፍረው ትሩፋት ሠርተው ገዳም ገድመው የኖሩ የሚኖሩ አባት ናቸው።

እንደ ሰባኪ ዙረው የሚያስተምሩ እያስተማሩ ያሉ ሐዋርያ ናቸው።
የኔታ ይባቤ አይደለም መታሠር በወርቅ ወንበር ተቀምጠው ያስተምሩን የሚባሉ ረቂቅ ሊቅ፣ምጡቅ ባለ አእምሮ ናቸው።

ለየኔታ ይባቤ በላይ የማይሆን ፍትህ ምን አይነት ነው?
መምህራችንን አባታችንን ፍቱልን።
እኔም የየኔታ ይባቤ በላይ ልጅ ነኝ።
እሥራታቸው እሥራቴ፣መከራቸው መከራየ ነው።
አድባር የሆኑትን ትልቅ ሰው ማሠር ትልቅ ስህተት ነው።

ለሀገር ባበረከቱት፣የወንጌል፣የሰላም፣የልማት፣የቅኔ፣የሀገር በቀል ዕውቀት፣የአቡሻህር፣የአርአያነት አስተዋጽኦ ሽልማታቸው እሥራት እና እንግልት ሊሆን አይገባም።
ሊቁ አባታችንን ሲሸለሙ እንጂ ሲታሠሩ መስማት ትልቅ ዕዳ ነው።

ከገዳማቸው ሂዶ በየኔታ ይባቤ ተመክሮ ያልተጽናና፣ተገሥፆ ያልተረጋጋ፣ከመስቀላቸው ተባርኮ ከጸበሉ ተጠምቆ ዕረፍተ ህሊና ያላገኘ ሰው የለም ማለት ይቻላል።

የኔታ ያለ ውግንና የሁሉም መምህር፣የሁሉም አባት፣የሁሉም ዘር ቀለም ሳይለዩ አስተማሪ፣የሁሉም ፊት ደረት ሳይለዩ ገሥፆ መካሪ ናቸው።

እንዲህ ያሉትን የኔታችንን አባታችንን በክብር ወደ ገዳማቸውና ወደ ማስተማሪያ ወንበራቸው መልሱልን።
"ቢያድጥ ቢያድጥ ወደላይ ያድጣል?"

©የኔታ ገብረመድኅን እንየው
3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኦርቶዶክሳውያን መከራ በየቦያው ነው ያለው ይህ የሶርያ ኦርቶዶክሳዊያን ናቸው ትናንት የተጨፈጨፉት
😢91
አሳዛኝ ዜና

👉በሸገር ሀገረ ስብከት ዓለም ገና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት  ቄስ ዮሐንስ ግርማ በዛሬው ዕለት ለቅዳሴ አገጋግሎት በሎሊት ወደ ቤተክርስቲያን እየሄዱ ባሉበት ወቅት  ቤተክርስቲያኑ በር  መግብያ ደጃፍ ላይ በጩቤ ማንነታቸው ባልታወቀ ተወግተው መገደላቸውን የመረጃ ምንጮች አድርሰውናል ፦

የአባታችንን ነፍስ ፈጣሪ ከቅዱሳኑ ጋር ይደምርልን ፣ ለቤተሰቡም መጽናናትን ያድልልን ፣

👉በዚህ አሰቃቂ ግድያ ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦችን ወይም ቡድኖች ፣ መንግሥት እንዲመረምር ፣ በሸገር ሀገረስብከት ስር እንዲህ ዐይነት ግድያቸው ቀጣይነት ሊኖራቸው እንደሚችል የመረጃ ምንጮቻችን አድርሰውናል ፣

👉 ምክንያቱም የሀገረስብከቱ ደገፊና ተቃዋሚ በሚል ቡድን እንደተለየ ፣ ብልሹ በሆነው የሀገረስብከት አሰራር ይህንን የሚቃወም ፣ ከቦታ ይነሳል ፣ ከስልጣን ይሻራል ፣ አልያም በቡድን ተቦዳድኖ በዚህ መልክ መጠፋፋቱ እንዳይነግስ ፣

👉በሀገረስብከቱ ላይ መልካም አስተደደር እንዲሰፍን ሲኖዶሱ ይችላሉ ፣የለውልጥ አባት ናቸው ብሎ የሾማቸውን አባ ሳዊሮስን  በድጋሚ በሸገር ሀገረ ስብከት ምን እየሰሩ እንዳለ መጠየቅ አለበት እንላለን ፣ ቤተክርስቲያን አስተዳደር  በቲፎዞ መምራት አይቻልም ።

👉ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የሁሉም ለሁሉም ድምፅ
ቤተሰብ ይሁኑ ፦ https://www.tgoop.com/ethiobeteseb
2
የግድያ እና የአፈና ዜና…!

"…በፎቶው ላይ የሚታዩት ቄስ ዮሐንስ ግርማ የተባሉና በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ሀገረ ስብከት በሸገር ሀገረ ስብከት የዓለም ገና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ካህን ባለፈው ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ለአገልግሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ላይ ሳሉ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ደጃፍ ላይ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ በተባሉ ኃይሎች በጩቤ ተወጋግተው መገደላቸውን ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ዘግቧል።

"…በዚያው በሸገር ሲቲ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በሚያስተዳድሩት ሀገረ ስብከት የቦሌ አራብሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም የስብከተ ወንጌል ሓላፊ እና የአንድ ልጅ አባት የሆኑት መምህር ብርሃነ መስቀል የካቲት 16/2017 ዓም ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ ምንም ዓይነት መለዮ ባልለበሱና የፖሊስ ፓትሮል በያዙ በቁጥር ስምንት በሚሆኑ አፋኞች ታፍነው የደረሱበት ከጠፋ እነሆ አምስት ወር እንደሆናቸው ተነግሯል።

"…በተያያዘ ዜና በዛሬው ዕለት ከሥራ ቦታው የታፈነው መምህር ደረጀ ነጋሽ (ዘወይንዬ) ከዜናው መበተን በኋላ በስተመጨረሻ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ በሚገኘው የእስረኞች ማቆያ ውስጥ እንደሚገኝ የመረጃ ምንቼ አድርሰውኛል። የእስሩም ምክንያት መምህሩ በጤና ባለሙያዎቹ የደሞዝ ጥያቄ ዙሪያ በሠራው ቪድዮ ምክንያት በጠቅላይ ሚንስትሩ በአቢይ አሕመድ ቀጥተኛ ትእዛዝ ምክንያት ለምርመራ መወሰዱ ነው የፖሊስ ምንጮቼ የገለጹልኝ።

"… የሰኔ የደም ግብርም ያለእንከን እየተፈጸመ ነው። ከኦሮሚያና ከሸገር ሲቲም ካህናት መነኮሳትም እየጸዱ ነው። አቡነ ሳዊሮስ እና አቡነ ዲዮስቆሮስም ሥራቸውን አገዛዙን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እየፈጸሙ ይመስላል። የኔታ ይባቤም እስከአሁን ድረስ አልተፈቱም። እዚያው ባሕርዳር መኮድ ጨለማ ቤት እንደታሰሩ ነው።

• ማነህ ባለ ሳምንት…?
3
በሶሪያ የተጨፈጨፉት 22 የአንጾኪያ ኦርቶዶክስ ሰማዕታት ቀብር ተፈጸመ
በሶሪያ ቅዳሴ ላይ እያሉ የተጨፈጨፉት የ22 የአንጾኪያ ኦርቶዶክስ ሰማዕታት የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጽሟል። የእዚህን ዓለም ፈተና በድል አጠናቀቁ።
ይህ አሳዛኝ ክስተት ለአንጾኪያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሰማዕትነት ጉዞ የሚያጸና ነው
3
የኔታ ሊቀ ብርሃናት ይባቤ በላይ በዛሬው ዕለት ተፈትተዋል። እርሳቸውን ለማስፈታት የተባበራችሁ ብፁዓን አበው ጳጳሳት (ሁለት ጳጳሳት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንደደከሙ መረጃው ስላለኝ ነው)፣ ሊቃውንት፣ ካህናት፣ ምእመናን እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜን ይስጥልን።

ሊቃውንት የሀገር ሀብቶች ናቸው። በተለይ እንደየኔታ ይባቤ ዓይነት ሁለገብ ሊቃውንት ደግሞ እንደ ዓይን ብሌን የሚጠበቁ ናቸው። አንዳንዶች ወደላይ አያዳልጣችሁ። ትልቅን ሰው መሳደብ ውርደቱ ለራሳችሁ ነው። ትልቅን ሰው ማክበር ይልመድብን።
14
2025/08/24 21:10:17
Back to Top
HTML Embed Code: