ሥላሴ በዕለተ ቀናቸው ሦስት የነገረ ድኅነት ማግኛ የመሠረት ድንጋዮችን ጣሉ።
በዛሬዋ ዕለት የተጣሉ 3 የመሠረት ድንጋዮችም
❖ ፅንሰተ ማርያም
ሚ ቡርክት ወቅድስት ይእቲ ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ" እንዳለ ደራሲው በዛራዋ ዕለት የድኅነት መሠረት የሆነችዋ እናታችን ድንግል ማርያም የተፀነሰችበት ዕለት ነውና የነገረ ድኅነት ሕንፃው የመሠረት ድንጋዩ ተቀመጠ።
❖ ፅንሰተ ቤተ ክርስቲያን (በዚህችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራታለሁ) ቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያትን ወክሎ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ በመመለሱ ይህንን ነገረ ሃይማኖት የምትመሰከር ቤተ ክርስቲያን በዚህ አስተምህሮት የጸናች ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይዋ በቂሳርያ ተመሠረተ።
❖ፅንሰተ ክህነት(የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻ ቁልፍ እሰጥሃለሁ በማለት ጌታችን መድኃኒታችን ቅዱስ ጴጥሮስ አስቀድሞ ለመለሰው መልስ የክህነት ሽልማት በሐዋርያት በኩል ለቤተ ክርስቲያን ተሰጠ።
እንኳን አደረሳችሁ

የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
❤8
ይሄን በኢትዮጵያ ያለ ክርስቲያን ማወቅ ያለበት መረጃ ነው!
♥️➨ዓለም አያቀውም የተባለው #የእመቤታችን_እርገት_ብሔራዊ_በዓል ሆኖ የሚከበርባቸው አገሮች
➨ኦስትሪያ፣
➨ቤልጂየም፣
➨ክሮኤሺያ፣
➨ፈረንሳይ፣
➨ጣሊያን እና
➨ፖላን
➨ስሎቫኒያ
➨ፖርቱጋል
➨ስፔን
➨ቤሩት
©ayu prince fb

🙏5❤1
ምስክርነት !
(በእወቀተ ስዩም)
የግእዝ ፊደላትን ረቂቅ የቀረጹልን የአክሱም ሊቃውንት ናቸው፤ ምናልባት ከክርስቶስ ልደት በፊት ሳይሆን አይቀርም፤ ይሁን እንጂ፤ ፊደሎችን አራብታ ፤ ቅጥያ አበጅታ ትልልቅ ሀሳብ መግለጽ እንዲችል አድርጋ ያደራጀችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ቤተክርስትያን ናት፤ እንዲህ ቅሽር ያለ፤ የዘነጠ፤ ፊደል ስላወረሰችኝ አመሰግናታለሁ፤
ስእል መሳል፥ ድርሰት መጻፍ፤ ቅኔ መቀኘት ፤ ዜማ ማዜም፤ ዘመን መቀመር፤ ታሪክ መመዝገብ እኒህ ሁሉ የቤተክስያን ወርሶች ናቸው፤
ሰውን ሰው ያደረገው ታሪክ አይደለም እንዴ ?! ገበሬን ከበሬ የሚለየው ትውስታ ነው፤ በዚህ ረገድ ካየነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የታሪክ መዝግብ ብቻ አይደለችም፤ ህያው ሙዝየም ናት ፤ ሙዝየም የቀደምቶቻችን የእጅ እና የአእምሮ ውጤቶች የሚገኙበት ቤት ነው፤ አንድ ሺህ አመታት ያስቆጠረ ጽናጽል ብሪትሽ ሙዝየም ውስጥ ልታገኝ ትችላለህ፤ ይሁን እንጂ ጽናጽሉ እንዴት እንደሚሰራ ሙዝየሙ አይነግርህም፤ እንዲህ ያለው እውቀት ሙዝየም በመጎብኘት ወይም መጻህፍትን በማየት አይገኝም፤ ይህንን የምታውቀው ባጥቢያህ ወደ ሚገኝ ደብር ጎራ ስትል ነው፤ ቤተክርስትያን ውስጥ ነባር ቅርሶች ብቻ ሳይሆኑ ነባር ተሰጥኦዎች ካንዱ ትውልድ ወደ አንዱ ትውልድ ይሸጋገራሉ፤
ምእራቡ አለም እውቀት የማከማቸት ባህል አለው፤ ግን አንዳንዴ የእውቀት ፍለጋው ክፍተት ያጋጥመዋል፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ቤተክርስትያን እንዲህ ዓይነቱን ክፍተት Missing link በመሙላት የአገር ኩራት ምልክት ሆና ቆይታለች፤ የመጽሀፈ ሄኖክን ታሪክ የሚያውቁ የማወራው ይገባቸዋል፤
ከግሪክ ስልጣኔ መክሰም በሁዋላ አብዛኛው የምእራብ ዓለም ቅድስና የሚለውን ጸጋ የሚያቀዳጀው ለወንዶች ነው፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ግን ለሴት ቅድስታት እና ሰማእታት እውቅና ሰጥታለች፤ ገድል እና ድርሳንም ትጽፍላቸዋለች፤ በቅድስና ትርጓሜው ላይ ላንስማማ ልንከራከር እንችላለን፤ ያም ሆኖ፤ ሴትን " አሳሳች" እና " የሀጥያት ሰበብ" ብቻ አድርጎ ከሚያቀርበው ትውፊት የተለየ ትውፊት ማቅረብ ስልጣኔ ነው፤
በአገራችን ፤ በኩራት ለጎብኝዎች ከምናቀርባቸው ድንቆች መካከል ግንባርቀደሞቹ የላሊበላ አብያተክርስትያናት ናቸው፤ ሮሀ ላይ ከተከመሩት ግዙፍ አለቶች መሀል እንዲህ አይነት ውብ ህንጻ አስፈለፍላለሁ ብሎ ለማሰብ በመለኮታዊ ተአምር ማመን የሚጠይቅ ይመስለኛል፤
ያለ ግብዝነት የምናወራ ከሆነ፥ ራሴን እንደ ዓለማዊ እና እንደመርማሪ ነው የማየው፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የማመንን ብቻ ሳይሆን የመጠየቅን የመመራመርን ጸጋ አውርሳናለች፤ ከእለታት አንድ ቀን ብራና ላይ የተጻፈ የጥንት የዘፍጥረትን ትርጉዋሜ ሳነብ፥ ስለ ሳጥናኤል አመጽ የሚወሳ ሐተታ አገኘሁ ፤ ሳጥናኤል በፈጣሪ ላይ ማመጹን ተከትሎ የተወሰኑት መላእከት ከሳጥናኤል ጋራ ወገኑ፤ የተወሰኑት በእምነታቸው ጸኑ ፤ የተወሰኑት ደግሞ ፈዘዙ፤
ሊቁ ፥ የፈዘዙትን መላእክት በማስመልከት የጻፈው ሀሳብ አሰላሳይነትን (Freethinking )የሚያበረታታ ደንቅ ሀይለቃል ስለሆነ እንደሚከተለው እጠቅሰዋለሁ፤
“ በሰጣቸው አእምሮ ባይመረምሩበት እዳ ሆነባቸው፤ ዛሬም ሰው በተሰጠው አእምሮ ባይመረምርበት እዳ ይሆንበታል”

❤3
'የሙታን መንፈስ ሳቢዎች'
ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በዐለመ ነፍስ ያሉ ቅዱሳንን ስታከብር፥ አንዳንዶች
ኦርቶዶክሳውያንኮ የሞቱ ቅዱሳንን ስለሚያከብሩ" የሙታን መንፈስ ሳቢዎች ናቸው" ይላሉ።
ያረፉ ቅዱሳንን ማክበር የሙት መንፈስ መጥራት ከሆነማ በሐዲሱ ኪዳን የመጀመርያው 'ሙታን ጠሪ 'ራሱ ጌታችን ክርስቶስ ነው።
ከሞተ ሺ ስድስት መቶ ዐመት የሆነውን ሙሴን ጠርቶ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠለት እሱ ነውና። ከሙሴም በፊት 'የአብርሃም የይሥሐቅ የያዕቆብ አምላክ እኔ ነኝ' እያለ የሙታንን ስም ይጠራ ነበርና።
ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ደብረ ታቦር ናት። ከጌታዋና ከአምላኳ እንደተማረችው ሕያዋንና ሙታን የሆኑ ቅዱሳን ስማቸው በክብር ስለ ሚጠራባት።
©ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው

❤10🥰1