🔴ብታምኑም ባታምኑም ይሄ ፈረንሳይ ነው🔴
የግብፅ ኦርቶዶክስ እጅግ የተሳካ ኦርትዶክሳዊ የወንጌል አገልግሎት በፈረንሳይ እያካሄደች ነው ። #ወደ_17_ሺህ የሚጠጉ ፈረንሳዊያን ባለፈው ዓመት በጥምቀት ወደ አማናዊቱ ቤተክርስቲያን መጨመራቸው ይታወቃል ።
➨ድንግል ማርያም በፈረንሳይ በተዋህዶ ልጇች ከበረች♥️
➨የፓሪስ እና የሰሜን ፈረንሳይ ሀገረ ስብከት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በቅድስት ድንግል ማርያም ካቴድራል እና በሊቀ መላእክት ሩፋኤል (የሀገረ ስብከቱ መንበር) ድራቪ። የእየሩሳሌም እና የቅርቡ ምስራቅ መንበር ሜትሮፖሊታን ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮስ ከጸጋው ጳጳስ ማ ጋር ተሳትፈዋል።
©ayu prince fb

❤3
ከመ ትንሣኤ ወልዳ👏
ስለ እመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት ከመ ትንሣኤ ወልዳ የተባለውን ይዘው ብዙዎች ብዙ ሐሳብ ይሰጣሉ በተለይም ሱባዔው በ14 አልቆ በ16 ከማክበራችን ጋር ተያይዞ በተቀበረች በ3ኛው ቀን እንደተነሣች የሚያስቡ አሉ በዚህም ዙሪያ በተቀበረች በ3ኛው ቀን ተነሣች የሚል ሐሳብ የያዙ መጻሕፍቶች አሉ አብዛኞች ሊቃውንትና መተርጉማን ግን የሚናገሩትና የሚያስተምሩት በ14 ሐዋርያት ሥጋዋን ተቀብለው በክብር ከቀበሯት በኋላ ዕለቱኑ ቶማስ በደመና ሲመለስ እመቤታችን በይባቤ መላእክት ስታርግ አገኛት መች? በ14 ይህንንም ቶማስ ተመልሶ ለሐዋርያት ካሳያቸው በኋላ እነርሱም ቶማስ ያየውን ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ ሱባዔ ገቡ
በ14 ሁለት ሱባዔ ቢጨርሱም እመቤታችን የተገለጸችላቸው ግን በ16 ስለሆነ በዓለ ዕርገቷን ልክ እንደ ሐዋርያት በ16 እናከብራለን እንጂ የተነሣችውና ያረገችው በ14 ነው ብለዋል
ትንሣኤዋ ከመ ትንሣኤ ወልዳ መባሉ ግን
1ኛ የተፈጸመበት ቀን ዕለተ ሰንበት በመሆኑ ዕለቱ እንደ ጌታ ትንሣኤ አማናዊው ትንሣኤ በተፈጸመበትና ትንሣኤ ዘጉባኤ የሚፈጸምበት ዕለትን ሳይለቅ በዕለተ ሰንበት በመሆኑ
እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21 ቀን ዕለተ እሑድ እንደነበር ታሪኳ ይናገራል ቀኑ ሲቆጠር ደግሞ ነሐሴ 14 በዕለተ ሰንበት ሲውል ነሐሴ 16 ቀን ግን ማክሰኞ ይሆናል ስለዚህም የተነሣችው በተቀበረች በሦስተኛው ቀን በ16 ቀን ነው ካልን ከመ ትንሣኤ ወልዳ የሚለውን በዕለተ ሰንበት መነሣቷን ይቀይረዋል
2ኛ የክብርና ብርሃናዊ ትንሣኤ መሆኑ እንደነ አልዓዛር ዳግም ምት ያለበት ሳይሆን በትንሣኤ ዘጉባኤ እንደምንነሣው ያለ ክርስቶስ በትንሣኤው የሰጠን የክብር ትንሣኤን በመነሣቷ
3ኛ እንደ ልጇ ትንሣኤ ዕርገት የሚከተለውና ወደ መንግሥተ ሰማያት ማረግ ያለበት ትንሣኤ በመሆኑና ወደ መንግሥተ ሰማያት ያረገችበት በመሆኑ ከመ ትንሣኤ ወልዳ አለ እንጂ ትንሣኤና ዕርገቷ ልክ ጌታ በተቀበረ በ3ኛው ቀን እንደተነሣ ያለ አይደለም ያ ቢሆንማ ጥንተ ትንሣኤዋ እሑድን ትቶ ማክሰኞ ይሆን ነበር
ዕርገቷም አርባ ቀን በጠበቀ ነበር ብለው መተርጉማን አብራርተው ተናግረዋል።
በተለይ በጥሩ ስንክሳር ላይ ከቀበሯት በኋላ ሦስት ቀን በዚያ ቆዩ የሚለውን ይዘው በሦስተኛው ቀን ነው የተነሣችው ትንሣኤዋና ዕርገቷ የሆነው በ16 ነው የሚሉም አሉ ነገር ግን በዚያ ሦስት ቀን ቆዩ አለ እንጂ የእርሷን ዕርገት በዚያ ቀን ነው አላለም ቶማስ ወደ እነርሱ እስኪመጣ አላወቁም ነበር
ያም ሆነ ይህ ቀኑ ሳያጣላን እኛም ትንሣኤዋና ዕርገቷ ለሐዋርያት ሁሉ በተገለጠበትና ጌታ እርሷን ያገናኛቸው እርሱም የተገለጠላቸው በ16 መሆኑ እኛም በ16 እንድናከብር ፈቃዱ ቢሆን ነው ብለን በፍጹም እምነትና በታላቅ ሐሴት ነሐሴ 16 ልክ እንደ ሐዋርያት በዓለ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን እናከብራለን
የእመቤታችን ረድኤት በረከቷ ይደርብን ጸጋዋ ይከልለን👏
እንኳን አደረሳችሁ❤
©መጋቤ ሐዲስ ዘለዓለም ሐሳቤ እንደጻፉት