tgoop.com/tser666/2601
Last Update:
👆 የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ ቁጥር 4 ክፍል 11 ንዑስ ክፍል 3
በዚህ ክፍል ትረካ የፊፋው ተወካይ ኢትዮጵያዊን ኳስ አፍቃሪዎችን ለማደንዘዝና ገንዘቡን ለመዝረፍ ያቀዱት እቅድ ተተርኮበታል።
👉 የኢትጵያ ህዝብ እግርኳስን ከመውደዱ አልፎ ወደማምለከ እስኪሸጋገርና በጥልቅ እንዲደነዝዝ በርከት ያሉ እቅዶች ነድፈዋል። በድንዛዜው ሀገሪቱ መከበቧን እንዳያስተውል ፣ የኢኮኖሚ ቀኝ ተገዢ እየሆነች እንደሆነ እንዳይረዳና እንዳይጠይቅ ለማረግ ታቅዷል።
ታዋቂ ታዋቂ ተጫዋቾችን ወደ ሀገሪቱ መላክ የእቅዳቸው ክፍል ሲሆን ዋናው የሴራ እቅዳቸው ግን ቁማር ነው።
በኳስ ቁማር ጥቂት አብልቶ ብዙ ለመብላት እቅድ ነድፈዋል። ለመላው አለም 1 ትሪሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ ደሞ 60 ቢሊዮን ዶላር ይህን እቅድ ለመተግበር መድበዋል። በዚህ መነሻ ገንዘብ ህዝቡን ጥቂት ጥቂት እያበሉ የቁማር ቋሚ ሱሰኛ ካረጉ በኋላ የህዝቡን ገንዘብ እየበዘበዙ ለመብላት አቅደዋል። በኢትዮጵያ የመደቡት 60 ቢሊዮን ዶላር ለማብላትና በአንፃሩ ወደ 600 ቢሊዮን ዶላር ከህዝቡ ለመብላት ነው ። ከሚገኘው የገንዘብ ትርፍ ባለፈ ግን ዋናው አላማ ህዝቡን በኳስና ቁማር ሱሰኛ አርጎ ማደንዘዝ ነው።
እግረመንገዱንም ህዝቡ የዲጂታል ስርዓቱን እንዲላመደው ቁማሩ በብዙ ያግዛል። የአለም ፋይናንስ ተቋም በኢትዮጵያ ለመተግበር የከበደውን በሞባይል ገንዘብ ልውውጥ በዚህ የቁማር ስልት ለማሳካት አቅደዋል።
#በሀገራችን ካለፉት 3 ዓመት ጀምሮ የተጀመሩትና በርካታ ታዳጊና ወጣቶችን ቋሚ ሱሰኛ እያረጉ ያሉት በየሰፈሩ የተበራከቱት የኳስ ቁማር ቤቶች የነዚሁ የሉሲፈሪያን እቅድ ክፍል ነው። ዛሬ ላይ በዚህ ሱስ ተይዘው የደነዘዙ ወጣቶች ቀላል አደሉም። ከጠዋት እስከ ማታ ሀሳባቸው ሁሉ ኳስ የሆነባቸው በርካታ ናቸው። ሀገር ፣ ሀይማኖት ፣ ቤተሰብ ፣ አላማን ወዘተ... ለማሰብ ጊዜ አጥተው በየቁማር ቤቱና በየስልኮቻቸው በኳስ ቁማር የተወጠሩ ኢትዮጵያን ተበራክተዋል። ከሱሱ ለመላቀቅ እስከ ፀበልና ሱባኤም የደረሱ አሉ።
#መፍትሔ: በሚቻለን ሁሉ የኳስ ቁማር አንጀምር። የጀመርን ግን ምን ያህል ጊዜና ገንዘባችንን እየበላን መሆኑን አውቀን ከሱሱ ለመውጣት እንቁረጥ። ይሄ ቁማር በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን በሉሲፈራያኑ ታቅዶና ተጠንቶ ገንዘብህን ለመብላትና ትውልዱን ለማደንዘዝ የተሴረ መሆኑን አውቀን በጊዜ ልንነቃ ይገባል።
በቀጣይ ክፍል በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያቀዱትን ሰፋ ያለ ሴራ እናቀርብላችኋለን።
#ሼር_በማረግ_ህዝባችንን_እናንቃ
BY የኢሉሚናቲ ገመናና ሚስጥር
Share with your friend now:
tgoop.com/tser666/2601