Telegram Web
ኑሮ ዳገት ሆኖ ቢከብደኝም መኖሬን ማንም ስላልሰጠኝ መኖሬን አላቆምም። ህይወት ተራራ ሆና ለመውጣት ብትከብደኝም ከፊቴ ካስቀመጥኩት ግቤ ከመድረስ ግን የሚያግተኝ አንዳች ነገር የለም። ያጣሁት፣ የተቀማሁት፣የተነጠኩት፣ሁሉ በፈጠረኝ የተከለከሉ ለኔ የማይበጁ በመሆናቸው ነው። የምኖርበት ምክኒያት ስላለኝ ነገዬን እሰራለው። ነገዬን ናፍቃለው ህልሜ ሩቅ ነው ካሰብኩበት ለመድረስ በማደርገው ጉዞ ደክሞኝ አርፋለው እንጂ አልቆምም። የምኖርበት ምክኒያት አለኝ የምናፍቀው ሂዎት ብርሀን የፈነጠቀ ተስፋን የሰነቀ ነውና በሂዎቴ ካጣሁት ያለኝና የሚኖረኝ ይልቃል።

አበበ ተሾመ
(የዱርዬው ማስታወሻ)

@abepoet
@abepoet
@abepoet
መቼ እንደሆነ  ለኔም ግልጽ አልነበረም የፈለኩትን ሆኜ እንደቀረብኩሽ እኔ የሆንኩትን እንድትለምጂው ያስገደድኩሽን ቀናቶች አንቺ በየዋህነት ብትዘነጊያቸውም  እኔ ልረሳቸው አልችልም፡፡ ግን ሁል ጊዜ ሰው እንደሚያስበው ነገሮች ቀንተው አያቁምና የአንቺ ትዕግስት ነው ብዬ እኔ በደመደምኩት በጊዜ ሒደት እንደቀረፁኝ አመንኩ፡፡ ግልጽ ለመሆን ውስጤ ሲያስብ አንቺን አንድም ቀን ቀርቦሽ  ለምዶሽ  ወዶሽ ሊያውቅ ይችላል ብሎ መገመት በጣም አስቸጋሪ ነው ፡፡ ጥሩነቶችሽ እኔን ካወቅሽ ቡሀላ የመጡ ቢሆኑ ኖሮ  እኔ መሄድ ያሰብኩ ቀን ልትዘነጊያቸው እንደምትችይ በጣም ግልጽ የሆነ የአንቺ አውነታ ነበር ፡፡ግን አልሆነም ሳለውቅሽ እኔ የምፈልገው ጥሩነትሽ አንቺ ውስጥ ነበር በመኖር ቆይታሽ ያስቀመጥሻቸው ያንቺ ነገሮች ለኔ ጎልተው የታዩት በጊዜ ሒደት ባወራንባቸው አንድ ሁለት ተብለው በማይቆጠሩት ቀናቶች ውስጥ ነው፡፡ ያንቺ ከኔ መለየት አለመፈለግ እኔን እስከምታስቢው የህይወት ጎዶና አብሮሽ ሊዘልቅ እንዲችል ማድረግ ይሳነው ይሆናል፡፡ ከመኖር የመትፈልጊው ያልተቋረጠ ነገን ያልነጠለ ትላንትን ያልዘነጋ ዛሬን በተስፋ የሰነቀ ሊሆን ግድ ነውና፡፡ ለውጥ ፈልጌ ከእኔም ከአንቺም ሳይሆን እኔም አንቺም መሆን ከምንሻው አብሮ የመሆን ምኞት ውስጥ  የፀነሳል ብልም አድካሚ ቢሆንብኝ ምኞት አይጨበጥ ብዬ አስቤ እኔ ያንቺ ምኞት ለመሆን ጣርኩኝ እንደጨበጥሽኝም ይሰማሽ ብዬ አካሌን በ ንግግሬን ለገስኩሽ ለመዘንጋት ሞክረሽ ይሆን ለመዳሰስ የሚሆን ካለኝ የህይወት ዓላማ  በተግባር ያልተቃኘ  በቃላት እምነትን የተሸከመ ብዙ የሚነበብም ነገር ሰጠሁኝ ቸልተኝነትሽ ቢያዘነብልብኝ መኞትስ ይኖራታል ባይሆን ባትረዳው እሷ የኔ ምኞት እንደሆነች በመፈለግ ገፅታ ለመግለጥ መሞከሬ እኔን ላለማየት የፈልግሽ እስኪመስል ሸሸሽኝ በቃ የእውነት ልነግርሽ የፈለኩት እያየሁሽ እኔን አንቺ ውስጥ እንዳገኘሁት እንዲሰማሽ ከመፈለግ ብዛት ነበር እሱም አይሆንም ብትይ ልታወሪኝ ፈልገሻል ብዬ ባሰብኩበት ቅጽበት ስሜቴን ሊገልጹልኝ ባልቻሉ ደካማ ቃላት ደጋግሜ ነገርኩሽ ለማድመጥ በትፈጥኚም ለመወሰን በመዘግየትሽ የማወራሽ እኔን ለማለየት ከመምረጥ ውጪ ሌላ ምርጫ እንደሌለሽ ስሜትሽን በደበቁ ላንቺ ጠንካራ በተባሉ እውነታዎችሽ  ነገራችንን ደመደምሺልኝ፡፡ ማወቅ ያለብሽ ነገር ላትመጪ ሄደሻል ብዬ መደምደም አልፈልግም ግን ማስበው ልትቀሪም እንደምትችይ ነው፡፡ እኔ ፍቅር እንዳለ ለማስተማር አቅሙ ቢኖረኝ ስለ ፍቅር የመሰከሩትን ስለ ፍቅር የሞቱትን ስለ ፍቅር የሚሰቃዩትን አይደለም ፍቅር ራሱ ፍቅር ነው ብሎ የሰበከውን ለመመልከት እንድትሞክሪ አደረግ ነበር  ግን ምን አልባት ሰባኪዋ አንቺ  ሆነሽ በፍቅር መድረክ ላይ መጽዋትን እየሰበክሽ የመኖር እሳቤሽ ግልጥ መሆኑን እኔ ያልተረዳሁ ቀን ከሆነ ብቻ፡፡

(28/9/15  ሰኞ  1:44 pm  taxi ውስጥ)
( Dm.....)

ፀሀፊ
ደምሰው ሀይለማርያም ( የዱርዬው ማስታወሻ)
@abepoet
@abepoet
@abepoet
Channel photo updated
Channel photo updated
Forwarded from በትረ ሙሴ
ተለቀቀ አዲሱ የ ዮርዳኖስ ሰጠ ሙዚቃ ዮርድዬ እንክዋን ደስ አለሽ
Forwarded from በትረ ሙሴ
ተለቀቀ አዲሱ የ ዮርዳኖስ ሰጠ ሙዚቃ  ዮርድዬ እንክዋን ደስ አለሽ
ገጣሚ መሆኔን ጠንቅቆ እያወቀው
አፍቃሪ አደረገኝ እግዜር ቅኔ ሲያምረው::

#ገጣሚ. አበበ ተሾመ
#የዱርዬው ማስታወሻ
ሚስቴ ዛር አለባት ቡና ትወዳለች
አልጋ ላይ ቁጭ ብላ ና ቁላ ትላለች::

አበበ ተሾመ (Ra's Ab)
የዱርዬው ማስታወሻ
/የኔ ወይ የማነሽ?/
    የኔ ባላትና ባረጋት የግሌ
  የራሴ የምላት በሆነች አካሌ፤
  ብትሆነኝ ከጎኔ አጋሬ ሆናልኝ
ቢደርስ ልመናዬ ፀሎቴ ሰምሮልኝ፤
    ነበረ ምኞቴ አብረን ብንዛመድ
ጠብቀን ብንታሰር በማይላላ ገመድ፤
  መሻቴን ተረድቶ ጭንቀቴን ቢሰማኝ
ከሁሉ አስቀድሞ ለኔ አንቺን ቢሰጠኝ፤   ሌላ ምን እሻለው ምን ያስፈልገኛል
በብቻ ያጡት ነገር ባብሮነት ይገኛል፤
ግን እደዛ ባይሆን አንቺ የኔ ካልሆንሽ
ጊዜው እረፍዶብኝ ለኔ ያላት ሳትሸሽ፤
    እውነቱን አውቄው ለኔም እንዲቀለኝ    ፋታአልሰጥም ያለኝ ልቤ እንዲቆርጥልኝ፤
እባክሽ ቆንጂቷ ተንፍሺ እስቲ ልስማሽ
ሁለት ነው ምርጫው የኔ ወይ የማነሽ?!
                           

አበበ ተሾመ
የዱርዬው ማስታወሻ

ገጣሚ. መሳይ-ግርማ
መች ነው ይሄ ቀን? ሰው ከተዋደደደና ከተፋቀረ ለምንድን ነው ተማምኖ የማይረሳውን ጊዜ የማያሳልፈው? ጊዜ ቆሞ አይጠብቅ ዛሬ ነገ እያልን ለምን ክፍተት እንፈጥራለን? በተፈጠረው ክፍተት ሌላ ሰው ገብቶ የምንወደውን የራሱ ቢያደርግብንስ? መች ነው ግን ይሄ የሚሆነው???

በዚ ሳምንት ምንም እንዳትሰራ ሁሉንም ቀን ለኔ ስጠኝ ብለሽ ቀን አብረሺኝ ውለሽ ሌሊት አብረሺኝ አድረሽ ጠዋት በክንዶቼ ታቅፈሽ የምንነቃበት ቀን መች ነው? የብቸኝነት ጊዜ አልፎ በአብሮነት ተሳስበን ያለናፍቆት የምንኖርበት ቀንስ መች ነው?


Ra's Ab

አበበ ተሾመ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰው ያልገነባውን እንዴት ያፈርሳል? ማፍረስና ሳር መትከል ዘመቻው በዚሁ ከቀጠለ ከተማዋ የጆባ መፅሐፍ መምሰሏ እውን ይሆናል። የቆሸሸ የሚፈርስ ታሪክ የለም።
Channel photo updated
Channel photo updated
Channel photo updated
ሳቄን ናልኝ ብዬ ሳቄ ሳለ ደርቆ፣
ስጠብቀው አዳር ከሌላ ቤት ሄዶ፣
ሙድ ሲይዝ ሰማሁት ሳቅ በኔ ተሳልቆ፣
ሲያዝን አየሁት ሳቅ በኔ ተሳቆ


ገጣሚ አበበ ተሾመ
.me/tztbt
.me/tztbt
2025/04/06 17:58:24
Back to Top
HTML Embed Code: