Forwarded from ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
ሰይፍ በባይብል
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
47፥4 *"እነዚያንም የካዱትን በጦር ላይ ባገኛችሁ ጊዜ ጫንቃዎችን በኃይል ምቱ"*፡፡ فَإِذَا لَقِيتُمُ الَّذِينَ كَفَرُوا فَضَرْبَ الرِّقَابِ حَتَّىٰ
ሙሽሪኮች ምእመናንን በበድር ዘመቻ ላይ ሊዋጉ ሲመጡ አምላካችን አሏህ ለምእመናን፦ "እነዚያንም የካዱትን በጦር ላይ ባገኛችሁ ጊዜ ጫንቃዎችን በኃይል ምቱ" አላቸው፦

በዚህ በድር ዘመቻ ላይ አሏህ መላእክትን ልኳል፥ ለምእመናን ሦስት ሺህ መላእክትን ለዘመቻው እንዲረዱ አድርጓል። ቢታገሱ እና ቢጠነቀቁ ደግሞ በአምስት ሺህ መላእክት እንደሚረዳ ተናግሯል፥ ሦስት ሺህ እና አምስት ሺህ ተከታታዮች ሲኾኑ እረድቷቸዋል፦
3፥123 በበድርም እናንተ ጥቂቶች ኾናችሁ ሳለ አላህ በእርግጥ ረዳችሁ፡፡ አላህንም ታመሰግኑ ዘንድ ፍሩት፡፡ وَلَقَدْ نَصَرَكُمُ اللَّهُ بِبَدْرٍ وَأَنتُمْ أَذِلَّةٌ ۖ فَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
3፥124 ለምእምናን «ጌታችሁ በሦስት ሺህ መላእክት የተወረዱ ሲኾኑ ቢረዳችሁ አይበቃችሁምን?» በምትል ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ تَقُولُ لِلْمُؤْمِنِينَ أَلَن يَكْفِيَكُمْ أَن يُمِدَّكُمْ رَبُّكُم بِثَلَاثَةِ آلَافٍ مِّنَ الْمَلَائِكَةِ مُنزَلِينَ
3፥125 «አዎን ብትታገሱ እና ብትጠነቀቁ ከዚህም ፍጥነታቸው ጠላቶቻችሁ ቢመጡባችሁ ጌታችሁ ምልክት ባላቸው አምስት ሺህ መላእክት ይረዳችኋል፡፡» بَلَىٰ ۚ إِن تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا وَيَأْتُوكُم مِّن فَوْرِهِمْ هَـٰذَا يُمْدِدْكُمْ رَبُّكُم بِخَمْسَةِ آلَافٍ مِّنَ الْمَلَائِكَةِ مُسَوِّمِينَ
8፥9 ከጌታችሁ ርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ «እኔ በሺህ መላእክት ተከታታዮች ሲኾኑ እረዳችኋለሁ» ሲል ለናንተ የተቀበላችሁን አስታውሱ፡፡ إِذْ تَسْتَغِيثُونَ رَبَّكُمْ فَاسْتَجَابَ لَكُمْ أَنِّي مُمِدُّكُم بِأَلْفٍ مِّنَ الْمَلَائِكَةِ مُرْدِفِينَ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ሺህ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "አልፍ" أَلْف ሲሆን ሙጅመል ነው፥ በሙፈሰል ደግሞ "ሦስት" እና "አምስት" በሚለው የገባው ቃል "ኣላፍ" آلَاف ሲሆን መላእክቱ "ተከታታዮች" ሲሆኑ የሚለው በሦስት ሺህ እና በአምስት ሺህ ቁጥር መምጣታቸውን ያሳያል። በበድር ዘመቻ አምላካችን አሏህ ለእነዚህ መላእክት፦ "እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና እነዚያን ያመኑትን አጽናኑ! በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ፡፡ ከአንገቶችም በላይ ምቱ! ከእነርሱም የቅርንጫፎችን መለያልይ ሁሉ ምቱ" በማለት አዘዛቸው፦
8፥12 ጌታህ ወደ መላእክቱ «እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና እነዚያን ያመኑትን አጽናኑ! በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ፡፡ ከአንገቶችም በላይ ምቱ! ከእነርሱም የቅርንጫፎችን መለያልይ ሁሉ ምቱ!» ሲል ያወረደውን አስታውስ፡፡ إِذْ يُوحِي رَبُّكَ إِلَى الْمَلَائِكَةِ أَنِّي مَعَكُمْ فَثَبِّتُوا الَّذِينَ آمَنُوا ۚ سَأُلْقِي فِي قُلُوبِ الَّذِينَ كَفَرُوا الرُّعْبَ فَاضْرِبُوا فَوْقَ الْأَعْنَاقِ وَاضْرِبُوا مِنْهُمْ كُلَّ بَنَانٍ
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚሽነሪዎች ወቃሽና ነቃሽ ሆነው፦ "መላእክት እንዴት የሰው አንገት ይቀላሉ" በማለት ባዕዳና እንግዳ ያልሆነ እና ያረጀና ያፈጀ ጥያቄ ይጠይቃሉ፥ እኛም ስልመልስ ባይብል ስለ ሰይፍ የሚናገረውን ጠንቅቆ ካለማንበብ የሚመጣ ጥያቄ ነው በማለት እንመልሳለን። በባይብል የእግዚአብሔር መላእክት የተመዘዘ ሰይፍ በእጃቸው እንደሚይዙ ብዙ ቦታ ይናገራል፦
ዘኍልቍ 22፥23 አህያይቱም የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤
ዘኍልቍ 22፥31 የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደቀ።
ኢያሱ 5፥13 የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር"*።
1ኛ ዜና 21፥16 *"ዳዊትም ዓይኖቹን አነሣ፤ የእግዚአብሔር መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ"*።
ይህ ሰይፍ አንባሻ ቆርሰው የሚያበሉበት ሳይሆን የሰው አንገት የሚቀሉበት ነው፥ በአንድ ወቅት የእግዚአብሔርም መልአክ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደሎ ነበር፦
ኢሳይያስ 37፥36 *"የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ"*።
ድርሳነ ዑራኤል ላይ መልአኩ ዑራኤል ሰይፍ ይዞ አንድ ሰውን፦ "ከሁለት ቦታ እቆርጥሃለው" ሲለው ይደመጣል፦
ድርሳነ ዑራኤል ዘሚያዚያ ገፅ 174 ቁጥር 11 *"ቅዱስ ዑራኤል በሚያስፈራ ግርማ የተሳለ ሰይፉን ይዞ፦ "አንተ የነገርኩህን ነገር ለምን አቦዘንከው? አሁንስ ከሁለት ቦታ እቆርጥሃለው" አለው"*።

በተመሳሳይ ወደ ሰዎች ስንመጣ የያዕቆብ ልጆች ስምዖን እና ሌዊ እኅታቸው ዲና በመደፈሯ ሰይፋቸውን ይዘው ወንዱንም ሁሉ ገደለው እና ኤሞርንና ልጁን ሴኬምንም በሰይፍ ገደሉ፦
ዘፍጥረት 34፥25-26 *"የዲና ወንድሞች የያዕቆብ ልጆች ስምዖን እና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ሳይፈሩ ወደ ከተማ ገቡ፥ ወንዱንም ሁሉ ገደሉ። ኤሞርንና ልጁን ሴኬምንም በሰይፍ ገደሉ"*።
ፈጣሪ ለያዕቆብ ልጆች፦ "የዚያችን ከተማ ሰዎች በሰይፍ ስለት ፈጽሞ ትመታቸዋለህ፣ ከተማይቱን በእርስዋም ያለውን ሁሉ፣ እንስሳውንም በሰይፍ ስለት ታጠፋቸዋለህ" ብሏቸዋል፥ እነርሱም በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፣ ወንዱንና ሴቱን፣ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፣ በሬውንም በጉንም አህያውንም በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ፦
ዘዳግም 13፥15 *"የዚያችን ከተማ ሰዎች በሰይፍ ስለት ፈጽሞ ትመታቸዋለህ፤ ከተማይቱን፥ በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ እንስሳውንም በሰይፍ ስለት ታጠፋቸዋለህ"*።
ኢያሱ 6፥21 በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፥ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም በጉንም አህያውንም፥ በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።
ይህንን የሰይፍ መጽሐፍ ስናብራራ ሚሽነሪዎች፦ "ይህ እኮ በብሉይ ኪዳን እንጂ በአዲስ ኪዳን ስለ ሰይፍ አያወራም" በማለት ባይብሉን ቀጋና አልጋ ለማድረግ ይፈልጋሉ፥ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ፦ "ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ" ብሎ አዘዘዘ፦
ሉቃስ 22፥36 *"እርሱም፦ አሁን ግን ኮረጆ ያለው ከእርሱ ጋር ይውሰድ፥ ከረጢትም ያለው እንዲሁ፤ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ"*።
ይህ ለመከላከል የተደረገ የጦር ስልት ሲሆን ከሐዋርያቱ አንዱ በመቸኮል ወደ ማጥቃት ገብቶ እጁን ዘርግቶ ሰይፉን መዘዘ እና የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቈረጠው፦
ማቴዎስ 26፥51 *"እነሆም ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ዘርግቶ ሰይፉን መዘዘ እና የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቈረጠው"*።
በሙሴ ሸሪዓህ የገደለ ይገደል የሚል ነውና ኢየሱስም፦ "ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ" አለው፦
ማቴዎስ 26፥52 ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ።
"ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ" ማለት ሰይፍን አንስቶ በሰይፍ ያለ አግባብ የሚገድል እራሱ በሰይፍ ይገደላል ማለት ነው፦
ራእይ 13፥10 *"በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል"*።
ልብ አድርግ ራእይ 1፥1-2 ላይ ራእዩ ከእግዚአብሔር ለኢየሱስ ከኢየሱስ ለመልአኩ ከመልአኩ ወደ ዮሐንስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ይናገራል፥ ይህ "በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል" የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ላይ ያለ ቃል ነው። ማንበብ ሙሉ ሰው ያረጋልና አንብቡ! አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://www.tgoop.com/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም

Audio
ሙስሊም ለመኾን መስፈርቱ ምንድን ነው?
🎙 ኡስታዝ ኢልያህ ማሕሙድ
⭕️ በእስልምና ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶቻችን።
➩ Join channel @Islamhasanswer
ሼር☞ ሼር☞ http://www.tgoop.com/hidayaislam
http://www.tgoop.com/abuhyder
@Mahdi_Quran_Recitation
@slmatawahi
@Islamhasanswer

Forwarded from የሰለምቴዎች ቻናል
Watch "እናትህን ጓደኛ አድርጋት በወንድም አህመድ ሪድዋን" on YouTube
https://youtu.be/UJnE_0uuX2s
https://youtu.be/UJnE_0uuX2s
YouTube
እናትህን ጓደኛ አድርጋት በወንድም አህመድ ሪድዋን
#ibn_rediwan
Forwarded from የሰለምቴዎች ቻናል
أَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فَلَهُمْ جَنَّاتُ الْمَأْوَىٰ نُزُلًا بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሰሩማ ለእነርሱ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት መስተንግዶ ሲሆኑ መኖሪያ ገነቶች አሏቸው፡፡
تلاوات خاشعة خالد الجليل
- أفمن كان مؤمناً كمن كان فاسقا
ሼር☞ ሼር☞ http://www.tgoop.com/hidayaislam
http://www.tgoop.com/abuhyder
@Mahdi_Quran_Recitation
@slmatawahi
@Islamhasanswer
እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሰሩማ ለእነርሱ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት መስተንግዶ ሲሆኑ መኖሪያ ገነቶች አሏቸው፡፡
تلاوات خاشعة خالد الجليل
- أفمن كان مؤمناً كمن كان فاسقا
ሼር☞ ሼር☞ http://www.tgoop.com/hidayaislam
http://www.tgoop.com/abuhyder
@Mahdi_Quran_Recitation
@slmatawahi
@Islamhasanswer
Forwarded from ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
የሴት ደረጃ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
39፥34 “ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አለላቸው፡፡ ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው”፡፡ لَهُم مَّا يَشَاءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ۚ ذَٰلِكَ جَزَاءُ الْمُحْسِنِينَ
“ፈድል” فَضْل የሚለው ቃል “ፈዶለ” فَضَّلَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ስጦታ” “ችሮታ” “ጸጋ”Bounty” ማለት ነው፥ ሴትነት እና ወንድነት በተፈጥሮ ከአሏህ የተሰጠን ጸጋ ነው፦
4፥32 *”አላህም ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በእርሱ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ! ለወንዶች ከሠሩት ሥራ እድል አላቸው፥ ለሴቶችም ከሠሩት ሥራ ዕድል አላቸው፡፡ وَلَا تَتَمَنَّوْا مَا فَضَّلَ اللَّهُ بِهِ بَعْضَكُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ لِّلرِّجَالِ نَصِيبٌ مِّمَّا اكْتَسَبُوا ۖ وَلِلنِّسَاءِ نَصِيبٌ مِّمَّا اكْتَسَبْنَ
እዚህ አንቀጽ ላይ “ያበለጠ” ለሚለው ቃል የገባው “ፈዶለ” فَضَّلَ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል! ወንድነት ለወንድ የተሰጠ ጸጋ ነው፥ ለወንዶች ከሠሩት ሥራ እድል አላቸው። ሴትነት ለሴት የተሰጠ ጸጋ ነው፥ ለሴቶችም ከሠሩት ሥራ ዕድል አላቸው። ለወንድ የተሰጠውን ጸጋ ሴት መመኘት የለባትም! ለሴት የተሰጠ ጸጋ ወንድ መመኘት የለበትም፥ ወንድ በሴት ላይ ሴት በወንድ ላይ የሚበላለጡት ጸጋ አለ እንጂ ወንድ ሴት አይደለም እንዲሁ ሴት ወንድ አይደለችም፦
3፥36 “ወንድም እንደ ሴት አይደለም”፡፡ وَلَيْسَ الذَّكَرُ كَالْأُنثَىٰ
አንድ ተባእት አምኖ መልካም ከሠራ መልካም ኑሮን በሚኖርበት መጠን አንድ እንስትም አምና መልካም ከሠራች መልካም ኑሮን ትኖራለች፦
16፥97 ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሠራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً
አንድ ተባእት አምኖ መልካም ከሠራ ጀነት እንደሚገባ ሁሉ አንድ እንስትም አምና መልካም ከሠራች ጀነት ትገባለች፦
4፥124 ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ
40፥40 “እርሱ ምእመን ኾኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎን የሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በእርሷ ውስጥ ያለ ቁጥጥር ይመገባሉ”፡፡ وَمَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ يُرْزَقُونَ فِيهَا بِغَيْرِ حِسَابٍ
9፥72 “አላህ ምእምናንን እና ምእምናትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በመኖሪያ ገነቶችም ውስጥ መልካም መኖሪያ ቤቶችን ቃል ገብቶላቸዋል”፡፡ وَعَدَ اللَّهُ الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَمَسَاكِنَ طَيِّبَةً فِي جَنَّاتِ عَدْنٍ ۚ وَرِضْوَانٌ مِّنَ اللَّهِ أَكْبَرُ
ወንድ አማኞች “ሙእሚኒን” مُؤْمِنِين ሲባሉ ሴት አማኞች “ሙእሚናት” مُؤْمِنَات ይባላሉ፥ በጀነት ውስጥ ወንድ አማኞች እና ሴት አማኞችም የሚፈልጉት ነገር ሁሉ አለላቸው፦
25፥16 ለእነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ኾነው የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው፡፡ ይህም ተስፋ ከጌታህ ተለማኝ ተስፋ ነው፡፡ لَّهُمْ فِيهَا مَا يَشَاءُونَ خَالِدِينَ ۚ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ وَعْدًا مَّسْئُولًا

43፥71 “በእርሷም ውስጥ ነፍሶች የሚከጅሉት እና ዓይኖችም የሚደሰቱበት ሁሉ አለ፥ እናንተም በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናችሁ፡፡ وَفِيهَا مَا تَشْتَهِيهِ الْأَنفُسُ وَتَلَذُّ الْأَعْيُنُ ۖ وَأَنتُمْ فِيهَا خَالِدُونَ
41፥31 ለእናንተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አለላችሁ፡፡ ለእናንተም በእርሷ ውስጥ የምትፈልጉት ሁሉ አለላችሁ”፡፡ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَشْتَهِي أَنفُسُكُمْ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَدَّعُونَ
16፥31 “ለእነርሱም በወስጧ የሚሹት ሁሉ አላቸው፡፡ እንደዚሁ አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል”፡፡ لَهُمْ فِيهَا مَا يَشَاءُونَ ۚ كَذَٰلِكَ يَجْزِي اللَّهُ الْمُتَّقِينَ

“ተቅዋእ” تَقْوَى ማለት “አሏህ መፍራት” ማለት ሲሆን አሏህን የሚፈሩ ወንድ እና ሴት “ሙተቂን” مُتَّقِين ይባላሉ፥ ለሙተቂን በጀነት ውስጥ ከአሏህ የኾነ ውዴታ ጥንዶች አላቸው፦
3፥15 «ከዚህ ሁሉ ነገር የሚበልጥን ልንገራችሁን» በላቸው፡፡ እርሱም፦ «ለእነዚያ ለተጠነቀቁት ሰዎች በጌታቸው ዘንድ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲኾኑ ንጹሕ የተደረጉ አዝዋጅ ከአላህም የኾነ ውዴታ አላቸው» قُلْ أَؤُنَبِّئُكُم بِخَيْرٍ مِّن ذَٰلِكُمْ ۚ لِلَّذِينَ اتَّقَوْا عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَأَزْوَاجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَرِضْوَانٌ مِّنَ اللَّهِ
“ዘውጅ” زَوْج የሚለው ቃል “ዘወጀ” زَوَّجَ ማለትም “ተጠናዳ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጥንድ” “ባል” “ሚስት” ማለት ነው፥ 58፥1 ላይ “ባልዋ” ለሚለው የገባው ቃል “ዘውጂሃ” زَوْجِهَا ሲሆን 7፥19 ላይ “ሚስትህ” ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ “ዘውጁከ” َزَوْجُكَ ነው። የዘውጅ ብዙ ቁጥር ደግሞ “አዝዋጅ” أَزْوَاج ሲሆን “ጥንዶች” ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ በግስ መደብ “ዘወጅናሁም” زَوَّجْنَاهُم ማለትም “እናጠናዳቸዋለን” ብሎ ቃል ገብቷል፦
44፥54 ነገሩ እንደዚሁ ነው፥ ሁር ዒን እናጠናዳቸዋለን፡፡ كَذَٰلِكَ وَزَوَّجْنَاهُم بِحُورٍ عِينٍ
“አሕወር” أَحْوَر ማለት “ውብ” ማለት ሲሆን ተባታይ መደብ ነው፥ “ሐውራእ” حَوْرَاء ማለት ደግሞ “ውቢት” ማለት ሲሆን አንስታይ መደብ ነው። “ሑር” حُور ማለት የሁለቱም ጾታ ብዜት ነው፥ “ዒን” عِين ማለት “ዓይናማ” ” ማለት ነው። “ሑረል ዒን” حُور العِين ማለት በጥቅሉ “ውብ ዓይናማ” ማለት ነው። በጀነት “ነፍሶች የሚከጅሉት እና ዓይኖችም የሚደሰቱበት ሁሉ አለ” እንደተባለው “ሑረል ዒን” አምላካችን አሏህ ለወንድ እና ለሴት ሙተቂን ባሮቹ ያዘጋቻቸው ናቸው፥ አምላካችን አሏህ ጥንድን ያጠናዳው ምድር ከምታበቅለው፣ ከራሳችን እና ከማናውቀው ነገር ነው፦
36፥36 ያ ምድር ከምታበቅለው፣ ከራሳቸውም እና “ከማያውቁትም ነገር" ጥንዶችን ሁሏንም የፈጠረ ጥራት ይገባው፡፡ سُبْحَانَ الَّذِي خَلَقَ الْأَزْوَاجَ كُلَّهَا مِمَّا تُنبِتُ الْأَرْضُ وَمِنْ أَنفُسِهِمْ وَمِمَّا لَا يَعْلَمُونَ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 36፥36 "ከዚያም አለ፦ "ያ ምድር ከምታበቅለው ጥንዶችን ሁሏንም የፈጠረ ጥራት ይገባው" ማለት ሰብልን፣ ፍራፍሬን እና አታክልትን ማለት ነው። "ከራሳቸውም" ማለት ከወንድ እና ከሴት አደረገላቸው ማለት ነው። "ከማያውቁትም ነገር" ማለት የማይታወቁ የተለያዩ ፍጥረት ማለት ነው።
ثم قال : ( سبحان الذي خلق الأزواج كلها مما تنبت الأرض ) أي : من زروع وثمار ونبات . ( ومن أنفسهم ) فجعلهم ذكرا وأنثى ، ( ومما لا يعلمون ) أي : من مخلوقات شتى لا يعرفونها.
፨ አንደኛ "ምድር ከምታበቅለው" ማለት ከምድር ውስጧ ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው፦
13፥3 እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችን እና ወንዞችን ያደረገ በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ
፨ ሁለተኛ "ከራሳቸውም" ማለት ከራሳችሁ ጥንዶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ ያደረገ ነው፦
30፥21 ለእናንተም ከራሳችሁ ጥንዶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً
፨ ሦስተኛ "ከማያውቁትም ነገር" ማለት ሑረል ዒን አዲስ ፍጥረት አድርጎ ለሙተቂን ከዓይኖች መርጊያ የተደበቀላቸውን ጸጋ ሲሆን ይህንን ጸጋ አሁን ላይ ማንኛይቱም ነፍስ ዐታውቅም፥ በጀነት ውስጥ ያለው ጸጋ ዓይን ዓይቶት የማያውቅ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ እና በሰው ልብ ውልብ ብሎ የማያውቅ ነው፦
56፥35 እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን ለእነርሱ ፈጠርናቸው፡፡ إِنَّا أَنشَأْنَاهُنَّ إِنشَاءً
32፥17 ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ ዐታውቅም፡፡ فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 302
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የላቀው አሏህም እንዲህ አለ፦ “እኔ ለደጋግ ባሮቼ ዓይን ዓይቶት የማያውቅ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ እና በሰው ልብ ውልብ ብሎ የማያውቅ ጸጋን አዘጋጅቻለው”። ከዚያም እርሳቸው፦ “ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ ዐታውቅም” የሚለውን አንቀጽ አነበቡ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم ” يَقُولُ اللَّهُ تَعَالَى أَعْدَدْتُ لِعِبَادِي الصَّالِحِينَ مَا لاَ عَيْنٌ رَأَتْ، وَلاَ أُذُنٌ سَمِعَتْ، وَلاَ خَطَرَ عَلَى قَلْبِ بَشَرٍ، ذُخْرًا، بَلْهَ مَا أُطْلِعْتُمْ عَلَيْهِ ”. ثُمَّ قَرَأَ {فَلاَ تَعْلَمُ نَفْسٌ مَا أُخْفِيَ لَهُمْ مِنْ قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ}
በተረፈ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 238 ላይ ወይም ጃሚዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 46 ላይ አሊያም ጃሚዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 38, ሐዲስ 2760 ላይ “ሰባ ሁለት አዝዋጅ” የሚለውን ሙሐዲስ ሸይኽ አል-አልባኒይ ረሒመሁል ሏህ “ደረጃቸው ዶዒፍ ናቸው” ብለዋቸዋል፥ ዶዒፍ ደግሞ መቅቡል ሳይሆን መርዱድ ነው።
አሏህ በጀነት ያዘጋጀልንን ጸጋ ይወፍቀን! አሚን።

ስለ ኣላህ (ሱብሐነህ) ለምን አትመራመሩ ተባለ?
🎙 ኡስታዝ ኢልያህ ማሕሙድ
🌀 በእስልምና ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶቻችን።
➩ Join channel @Islamhasanswer
ሼር☞ ሼር☞ http://www.tgoop.com/hidayaislam
http://www.tgoop.com/abuhyder
@Mahdi_Quran_Recitatio
🎙 ኡስታዝ ኢልያህ ማሕሙድ
🌀 በእስልምና ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶቻችን።
➩ Join channel @Islamhasanswer
ሼር☞ ሼር☞ http://www.tgoop.com/hidayaislam
http://www.tgoop.com/abuhyder
@Mahdi_Quran_Recitatio
Forwarded from የሰለምቴዎች ቻናል
YouTube
quran
Forwarded from የሰለምቴዎች ቻናል
فَسَبِّحْ بِاسْمِ رَبِّكَ الْعَظِيمِ
የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡
🍂አል ዋቂአህ🍂
القارئ أنس جلهوم
ሼር☞ ሼር☞ http://www.tgoop.com/hidayaislam
http://www.tgoop.com/abuhyder
@Mahdi_Quran_Recitation
@slmatawahi
@Islamhasanswer
የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡
🍂አል ዋቂአህ🍂
القارئ أنس جلهوم
ሼር☞ ሼር☞ http://www.tgoop.com/hidayaislam
http://www.tgoop.com/abuhyder
@Mahdi_Quran_Recitation
@slmatawahi
@Islamhasanswer
Forwarded from ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
ተስዊር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡
23፥14 *ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ*፡፡ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ
“ሙሶዊር” مُصَوِّر ማለት “ቀራፅ” “ሰዓሊ” “ሠሪ” “ፈጣሪ” ማለት ነው፥ የሙሶዊር ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሙሶዊሩን” مُصَوِّرُون ወይም “ሙሶዊሪን” مُصَوِّرِين ሲሆን “ቀራፆች” “ሰዓሊዎች” ማለት ነው፦

“ሰዓሊዎች” ለሚለው ቃል የገባው “ኻሊቂን” خَالِقِين ሲሆን “ሙሶዊሪን” مُصَوِّرِين ማለት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37, ሐዲስ 150
ዐብደላህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በትንሳኤ ቀን ከሰዎች በጣም ተቀጪ ሰዓሊዎች ናቸው”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ إِنَّ أَشَدَّ النَّاسِ عَذَابًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ الْمُصَوِّرُونَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 182
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የስዕላት ባለቤት በትንሳኤ ቀን ይቀጣሉ፥ ለእነርሱም፦ “የፈጠራችሁትን ሕያው አድርጉ” ይባላሉ”*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ “ إِنَّ أَصْحَابَ هَذِهِ الصُّوَرِ يُعَذَّبُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَيُقَالُ لَهُمْ أَحْيُوا مَا خَلَقْتُمْ
ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ ነው። ነቢያችን”ﷺ” በቁርኣን ከተሰጣቸው አንዱ አንድ ቃላት ሰፊ ትርጉም ነው፥ ይህም “ጀዋሚዓል ከሊም” ነው። “ጀዋሚዓል ከሊም” جَوَامِعَ الْكَلِم ማለት “አንድ ቃል ሆኖ ብዛት ትርጉም ያለው” ማለት ነው። “ሱራህ” صُورَة ማለት ብዙ አውራ ትርጉም ያለው ሲሆን “ስዕል” “ቅርፅ” “መልክ” “ፎቶ” ማለት ነው፥ “ሱወር” صُوَر ደግሞ የሱራህ ብዙ ቁጥር ሲሆን “ስዕላት” “ቅርፃት” ማለት ነው። “የፈጠራችሁትን” ለሚለው የገባው ቃል “ኸለቅቱም” خَلَقْتُمْ ሲሆን ስዕሉን ስለሳሉት እና ቅርፁን ስለቀረፁት እንጂ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተውት አይደለም፥ ይህ “ኢሕቲራዕ” اِخْتِرَاع ማለትም “ፈጠራ” ነው። በእጃቸው የፈጠሩትን ላይ እንደ አላህ ሩሕ ማድረግ አይችሉም፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 77, ሐዲስ 179
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *”በዚህ ዓለም ቅርፅ የቀረፀ በትንሳኤ ቀን በውስጡ ሩሕ እንዲነፋበት ይጠየቃል፥ ግን መንፋት አይችልም”*። فَقَالَ سَمِعْتُ مُحَمَّدًا صلى الله عليه وسلم يَقُولُ “ مَنْ صَوَّرَ صُورَةً فِي الدُّنْيَا كُلِّفَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَنْ يَنْفُخَ فِيهَا الرُّوحَ، وَلَيْسَ بِنَافِخٍ
እዚህ ሐዲስ “ሶወረ” صَوَّرَ ማለት “ቀረፀ” “ሳለ” “ሠራ” ማለት ነው። “ኸልቅ” خَلْق የሚለው ቃል “ተስዊር” تَصْوِير ለሚለው ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ እንደገባ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ ይህ የቋንቋ ሙግት ታሳቢ ያደረገ ነው። ነቢያችን”ﷺ” ባልደረቦቻቸውን ወደ ሐበሻህ ሲልኳቸው ከሔዱት መካከል በአክሱም ቤተክርስቲያን ውስጥ ስዕላትን አይተዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 77
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ *”ኡሙ ሐቢባህ እና ኡሙ ሠለማህ በሐበሻህ ስላዩአት በውስጧ ስዕሎች ስለነበሩባት ቤተክርስቲያን ዘክረዋል፥ ስለዚህ ለነቢዩም”ﷺ”ዘክረዋል። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ “በእነዚያ ሰዎች መካከል የትኛውም ሷሊሕ ሰው ቢሞት በመቃብሩ ላይ የአምልኮ ስፍራ ቢገነቡ እና እነዚህን ስዕላት ቢያደርጉ፥ በትንሳኤ ቀን በአላህ ዘንድ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው”*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ أُمَّ حَبِيبَةَ، وَأُمَّ سَلَمَةَ ذَكَرَتَا كَنِيسَةً رَأَيْنَهَا بِالْحَبَشَةِ فِيهَا تَصَاوِيرُ، فَذَكَرَتَا لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ “ إِنَّ أُولَئِكَ إِذَا كَانَ فِيهِمُ الرَّجُلُ الصَّالِحُ فَمَاتَ بَنَوْا عَلَى قَبْرِهِ مَسْجِدًا، وَصَوَّرُوا فِيهِ تِلْكَ الصُّوَرَ، فَأُولَئِكَ شِرَارُ الْخَلْقِ عِنْدَ اللَّهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ
“ተስዊራህ” تَصْوِيرَة ማለት “ስዕል” ማለት ነው፥ የተስዊራህ ብዙ ቁጥር “ተሷዊር” تَصَاوِير ማለት ሲሆን “ስዕላት” ማለት ነው። ስዕል በአምልኮ ውስጥ ምንም ሚና መኖር የለበትም፥ የሥላሴ፣ የኢየሱስ፣ የማርያም፣ የመላእክት እና የቅዱሳን ሰዎች ስዕል ስሎ በፊታቸው መለማመን ባዕድ አምልኮ ነው። በተመሳሳይ ቁረይሾች የአላህ ቤት ውስጥ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በእጆቻቸው አዝላም የያዙ አስመስለው ስዕላት ስለው ነበር፥ “አዝላም” أَزْلاَم ማለት “የጥንቆላ ቀስት” ማለት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 32
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” በአላህ ቤት ስዕላት በተመለከቱ ጊዜ ባልደረቦቻቸው እንዲያጠፉ እንኪያዙ ድረስ ወደ እዚያ አልገቡም። ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል”ሠላም በእነርሱ ላይ ይሁን! በእጆቻቸው አዝላም የያዙ ስዕላት ነበሩ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ “አላህ ይርገማቸው(ቁረይሾችን)! ወሏሂ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በአዝላም አይለማመዱም”*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم لَمَّا رَأَى الصُّوَرَ فِي الْبَيْتِ لَمْ يَدْخُلْ، حَتَّى أَمَرَ بِهَا فَمُحِيَتْ، وَرَأَى إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ ـ عَلَيْهِمَا السَّلاَمُ ـ بِأَيْدِيهِمَا الأَزْلاَمُ فَقَالَ “ قَاتَلَهُمُ اللَّهُ، وَاللَّهِ إِنِ اسْتَقْسَمَا بِالأَزْلاَمِ قَطُّ
የኢብራሂም አባት እና የኢብራሂም ሕዝቦች ቅርጻ ቅርጽ የሆነ አስናምን ያመልኩ ነበር፥ “አስናም” أَصْنَام ማለት ከእንጨት፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከወርቅ ተሠርተው አምልኮ የሚቀርብላቸው ናቸው፦

26፥70 *ለአባቱና ለሕዝቦቹ «ምንን ታመልካላችሁ?*» ባለ ጊዜ፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَا تَعْبُدُونَ
26፥71 *አስናምን እናመልካለን፥ እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን*» አሉ፡፡ قَالُوا۟ نَعْبُدُ أَصْنَامًۭا فَنَظَلُّ لَهَا عَٰكِفِينَ
21፥52 ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ «ይህቺ *”ቅርጻ ቅርጽ”* ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የኾናችሁት ምንድን ናት?» ባለ ጊዜ መራነው፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ مَا هَـٰذِهِ التَّمَاثِيلُ الَّتِي أَنتُمْ لَهَا عَاكِفُونَ
“ቲምሳል” تِمْثَال ማለት “ምስል” “ቅርጽ” ማለት ነው፥ የቲምሳል ብዙ ቁጥር ደግሞ “ተማሲል” تَمَاثِيل ሲሆን “ምስሎች” “ቅርጻ ቅርጽ” ማለት ነው። የአምልኮ ይዘት ያላቸው ማንኛውም ምስል ሆነ ስዕል ያለበት ቤት መላእክት አይገቡም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37, ሐዲስ 156
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ምስሎች ወይም ስዕሎች ያለበት ቤት አይገቡም”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ لاَ تَدْخُلُ الْمَلاَئِكَةُ بَيْتًا فِيهِ تَمَاثِيلُ أَوْ تَصَاوِيرُ
ስለ ሱራህ በመስኩ ምሁራን ዘንድ ያለው እይታ በአራት ይከፈላሉ፥ እነርሱም፦
1ኛ. ለምንም ነገር ሱራህ መጠቀም ሐራም ነው፣
2ኛ. በእጅ የተሠራ እንጂ ልክ እንደ መስታዎት እራሳችንን የሚያሳዩ በካሜራ እና በፊልም የሚታዩ ነገሮች ችግር የላቸውም፣
3ኛ. ለፓስፓርት፣ ለመታወቂያ እና ለሰርተፍኬት ብቻ መጠቀም ይቻላል፣
4ኛ. ለአምልኮ አንጠቀም እንጂ ስዕል እና ቅርጻ ቅርጽ በራሱ ሥነ-ጥበብ”art” ነው” የሚሉ ናቸው። ለምሳሌ “ፊደል” የሚለው ቃል “ፈደለ” ማለትም “ቀረፀ” ወይም “ጻፈ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ቅርፅ” ወይም “ጽሑፍ” ማለት ነው፥ ፊደል የቃላት ቅርፅ ናቸው። “ሐርፍ” حَرْف የሚለው ቃል እራሱ “ሐረፈ” حَرَفَ ማለትም “ጻፈ” ወይም “ቀረፀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ቅርፅ” ወይም “ጽሑፍ” በሚል ይመጣል፥ ቃል በጽሑፍ ወይም በቅርፅ ማስቀመጥን ያመለክታል። አራተኛውን እይታ ለማስደገፍ፦ “ሡለይማን በቤተ-መንግሥቱ ምስሎች አድርጓል፥ እነዚህ ምስሎች ስዕሎች ነበሩ” ይላሉ፦
34፥13 *ከምኩራቦች፣ “ከምስሎችም”፣ እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል*፡፡ يَعْمَلُونَ لَهُ مَا يَشَاءُ مِن مَّحَارِيبَ وَتَمَاثِيلَ وَجِفَانٍ كَالْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَاتٍ ۚ اعْمَلُوا آلَ دَاوُودَ شُكْرًا ۚ وَقَلِيلٌ مِّنْ عِبَادِيَ الشَّكُورُ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 34፥13
ወሱዲይ ከወድሐክን፣ ዐጢይል ዐውፊይ አለ ብሎ እንደተናገረው፦ *”ምስሎች ማለት ስዕሎች ናቸው”*። فقال عطية العوفي ، والضحاك والسدي : التماثيل : الصور
“ዒሣ የወፍ ቅርፅ እንዲሠራ መፈቀዱ በራሱ “ቅርፅ መቅረፅ በራሱ ችግር የለውም” የሚል አቋም አላቸው። በሱራህ እሳቤ ዙሪያ “አንጡራ መረጃ አላገኘንም” ካላችሁ በአካባቢያችሁ ወደሚገኙት ምሁራን እና ሊሒቃን ጎራ ብላችሁ ጠይቁ! አሏሁ አዕለም።
✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ

ቁርኣን ከኣላህ ለመኾኑ ማስረጃው ምንድን ነው?
🎙 ኡስታዝ ኢልያህ ማሕሙድ
🌀 በእስልምና ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶቻችን።
➩ Join channel @Islamhasanswer
ሼር☞ ሼር☞ http://www.tgoop.com/hidayaislam
http://www.tgoop.com/abuhyder
@Mahdi_Quran_Recitation
@slmatawahi
@Islamhasanswer
🎙 ኡስታዝ ኢልያህ ማሕሙድ
🌀 በእስልምና ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶቻችን።
➩ Join channel @Islamhasanswer
ሼር☞ ሼር☞ http://www.tgoop.com/hidayaislam
http://www.tgoop.com/abuhyder
@Mahdi_Quran_Recitation
@slmatawahi
@Islamhasanswer
Forwarded from የሰለምቴዎች ቻናል
كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَنَبْلُوكُم بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً ۖ وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ
ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፡፡ ወደኛም ትመለሳላችሁ፡፡
@Mahdi_Only_Quran
القارئ سعد الغامدي |تلاوة خاشعة🍁
ሼር☞ ሼር☞ http://www.tgoop.com/hidayaislam
http://www.tgoop.com/abuhyder
@Mahdi_Quran_Recitation
@slmatawahi
@Islamhasanswer
ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፡፡ ወደኛም ትመለሳላችሁ፡፡
@Mahdi_Only_Quran
القارئ سعد الغامدي |تلاوة خاشعة🍁
ሼር☞ ሼር☞ http://www.tgoop.com/hidayaislam
http://www.tgoop.com/abuhyder
@Mahdi_Quran_Recitation
@slmatawahi
@Islamhasanswer
Forwarded from የሰለምቴዎች ቻናል
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
📜እንኳን ደስ አላችሁ📜
ኑር የቁርአን ማእከል
✒️በተከበረው ሰላምታችን አስላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
✒️የአላህን ቃል ለማወቅ በተከበረው ቁርአን ለመድመቅ ሽንፈትን ዑዝር ሊያሳጣ እነሆ ኑር የቁርአን ንባብ እና ኢሰላማዊ ጥናት ማእከል ብቅ አለ
✒️በየትኛወም አገር ለምትገኙ እህት ወንድሞች ከፈጅር ጀምሮ እስከ ምሽቱ 5 ስአት ድረስ በዓይነቱ ለየት ባለ zoom application በመጠቀም አገልገሎት የሚሰጠው ማእከላችን ከ ቃዓዳ ጀምሮ እስከ ሂፍዝ ድረስ ቂርዓት ለምትፈልጉ እነሆ በሩን ከፍቶ እየጠበቃቹ ይገኛል
ስለማእከሉ የትኛወንም መረጃ ለማወቅ ከፈለጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ሥ-ቁ 002519 73 10 10 05
002519 62 15 05 02
ኑር የቁርዓን ንባብ ኢስላማዊ ጥናት ማእከል
ኑር የቁርአን ማእከል
✒️በተከበረው ሰላምታችን አስላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
✒️የአላህን ቃል ለማወቅ በተከበረው ቁርአን ለመድመቅ ሽንፈትን ዑዝር ሊያሳጣ እነሆ ኑር የቁርአን ንባብ እና ኢሰላማዊ ጥናት ማእከል ብቅ አለ
✒️በየትኛወም አገር ለምትገኙ እህት ወንድሞች ከፈጅር ጀምሮ እስከ ምሽቱ 5 ስአት ድረስ በዓይነቱ ለየት ባለ zoom application በመጠቀም አገልገሎት የሚሰጠው ማእከላችን ከ ቃዓዳ ጀምሮ እስከ ሂፍዝ ድረስ ቂርዓት ለምትፈልጉ እነሆ በሩን ከፍቶ እየጠበቃቹ ይገኛል
ስለማእከሉ የትኛወንም መረጃ ለማወቅ ከፈለጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ሥ-ቁ 002519 73 10 10 05
002519 62 15 05 02
ኑር የቁርዓን ንባብ ኢስላማዊ ጥናት ማእከል
Forwarded from ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
ዐቅመ-ጋብቻ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
65፥4 *"እነዚያም ከሴቶቻቸው ከዐደፍ ያቋረጡት በዒዳቸው ሕግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እነዚያም ገና ዐደፍ ያላዩት ዒዳቸው እንደዚሁ ነው፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው"*፡፡ وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِن نِّسَائِكُمْ إِنِ ارْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَاثَةُ أَشْهُرٍ وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ ۚ وَأُولَاتُ الْأَحْمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ
"ዐቅመ-ጋብቻ" ማለት አንድ ተባእት ለዐቅመ-አደም ሲደርስ እና አንዲት እንስት ለዐቅመ-ሐዋህ ስትደርስ ማለት ነው። ለምሳሌ “የቲም” يَتِيم ስንል አጠቃላይ “ወላጅ-አልባ” ማለትም “እናትና አባቱ” ወይም “አባቱን በልጅነቱ በሞት የተነጠቀ ሕፃን” ማለት ነው። የቲሞች እራሳቸው ይችሉ ወይም አይችሉ እንደሆነ ይፈተናሉ፥ ይህም ፈተና ለጋብቻ እስከሚደርሱበት ድረስ ነው፦
4፥6 *"የቲሞችንም ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ ድረስ ፈትኑዋቸው"*፡፡ وَابْتَلُوا الْيَتَامَىٰ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغُوا النِّكَاحَ
"ኢዛ" إِذَا ማለት "ጊዜ" ማለት ሲሆን የጊዜ ተውሳከ-ግስ ነው። ጋብቻ የራሱ የሆነ ጊዜ እንዳለው አመላካች ነው፥ ይህም ጊዜ ለማመልከት "ጋብቻን እስከደረሱ" ድረስ በማለት ይናገራል። "በለጉ" بَلَغُوا ማለት "ለጋብቻ በሰሉ" ማለት ነው፥ "በለገ" بَلَغَ ማለት "ለጋብቻ በሰለ" ማለት ሲሆን "በለገት" بَلَغَت ማለት ደግሞ "ለጋብቻ በሰለች" ማለት ነው። "ባሊግ" بَٰلِغ ማለት እራሱ "ዐቅመ-ጋብቻ"Puberty" ማለት ነው፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 4፥6
*"ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ" የሚለውን ሙጃሂድ፦ "ለዐቅመ-ጋብቻ ነው" ብሏል፥ ዐበይት ምሁራን፦ "ለዐቅመ-ጋብቻ" ለጋዎች ኢሕቲላም ሲኖራቸው ነው" ብለዋል። አቢ ዳውድ በሡናው እንደዘገበው፥ ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ከዐቅመ-ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም"*።
( حتى إذا بلغوا النكاح ) قال مجاهد : يعني : الحلم . قال الجمهور من العلماء : البلوغ في الغلام تارة يكون بالحلم ، وهو أن يرى في منامه ما ينزل به الماء الدافق الذي يكون منه الولد . وقد روى أبو داود في سننه عن أمير المؤمنين علي بن أبي طالب ، رضي الله عنه ، قال : حفظت من رسول الله صلى الله عليه وسلم : " لا يتم بعد احتلام
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 18, ሐዲስ 12
ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ እንደተረከው፦ "የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ከዐቅመ-ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም"*። قَالَ عَلِيُّ بْنُ أَبِي طَالِبٍ حَفِظْتُ عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " لاَ يُتْمَ بَعْدَ احْتِلاَمٍ
"ዐቅመ-ጋብቻ" አካል ተራክቦ ለማድረግ ሲበስል ነው፥ ከዐቅመ-ጋብቻ በኃላ የቲምነት ስለሌለ የቲሞች እራሳቸው እንዲችሉ ይፈተናሉ። "ኢሕቲላም" احْتِلاَم ማለት አንድ ልጅ ወይም አንዲት ልጂት ተራክቦ ለማድረግ የሚኖራቸው ፈሳሽ ነው። ይህ ፈሳሽ እስኪመጣ ድረስ ለዐቅመ-ጋብቻ ስላልደረሱ የሚሠሩት ሥራ አይመዘገብም፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 48
ዓኢሻህ "ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ብዕር ከሦስት ሰዎች ተነስቷል። እነርሱም፦ የተኛ ሰው እስኪነሳ ድረስ፣ ዕብደ ወደ ዐቅሉ እስኪመለስ ድረስ፣ ልጅ እስኪጎሎብት ድረስ"*። عَنْ عَائِشَةَ، رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " رُفِعَ الْقَلَمُ عَنْ ثَلاَثَةٍ عَنِ النَّائِمِ حَتَّى يَسْتَيْقِظَ وَعَنِ الْمُبْتَلَى حَتَّى يَبْرَأَ وَعَنِ الصَّبِيِّ حَتَّى يَكْبَرَ

በእንቅልፍ ልብ፣ በዕብደት እና በእንጭጭነት የሚደረግ ሥራ መላእክት አይመዘግቡትም። አንድ ሕጻን ለዐቅመ-አደም ከደረሰ የሰው ቤት ዘው ብሎ አይገባም፥ ከዚያ ይልቅ አንኳክቶ ያስፈቅዳል፦
24፥59 *"ከእናንተም ሕፃናቶቹ አቅመ አዳምን በደረሱ ጊዜ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት እንዳስፈቀዱ ያስፈቅዱ"*፡፡ وَإِذَا بَلَغَ الْأَطْفَالُ مِنكُمُ الْحُلُمَ فَلْيَسْتَأْذِنُوا كَمَا اسْتَأْذَنَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ
አሁን እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢዛ" إِذَا የሚለው የጊዜ ተውሳከ-ግስ የዐቅመ-ጋብቻ ጊዜ አመላካች ነው፥ ይህንን ዐቅመ-ጋብቻ ለማመልከት "በለገ" بَلَغَ የሚል የግስ መደብ ይጠቀማል። አንዲት እንስት ለዐቅመ-ሐዋህ የመድረሷ የመጀመሪያው እና ዐቢይ ምልክት አድሬን-አርክ"adrenarche" አካሏ ለተራክቦ ዝግጁ ሲሆን እንዲሁ ጡቷ ሲያጎጠጉጥ ቴል-አርክ"thelarche" እና ብብቷና ብልቷ አካባቢ ጸጉር መብቀል ፑብ-አርክ"Pubarche" ሲጀምር የምታመነጨው ፈሳሽ"Vaginal lubrication" እንጂ የወር አበባ አይደለም፥ የወር አበባ ማየት አንዲት ሴት ለዐቅመ-ሐዋህ መድረሷን ከሚያሳዩ ሁለተኛ እና ንዑስ ምልክት ዕንቁላል ማምረት ጎናድ-አርክ"gonadarche" እንዲሁ የወር አበባ ደም ሜን-አርክ"menarche" ነው። አንዲት ሴት ስታርጥ የወር አበባ ይቋረጣል፥ ያኔ የምታመነጨው ፈሳሽ ያለ የወር አበባ ተራክቦ ማድረግ ትችላለች። ምክንያቱም ተራክቦ ለማድረግ የወር አበባ ብቻውን መስፈት አይደለም፥ የወር አበባ ለፅንስ እንጂ ለተራክቦ መስፈት አይደለም፦
65፥4 *"እነዚያም ከሴቶቻቸው ከዐደፍ ያቋረጡት በዒዳቸው ሕግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እነዚያም ገና ዐደፍ ያላዩት ዒዳቸው እንደዚሁ ነው፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው"*፡፡ وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِن نِّسَائِكُمْ إِنِ ارْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَاثَةُ أَشْهُرٍ وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ ۚ وَأُولَاتُ الْأَحْمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ
“ዒዳህ” عِدَّة ማለት ሁለት ጥንዶች ከተጋቡ በኃላ ተራክቦ አድርገው ከዚያም አለመግባባት ቢፈጠር ፍቺ ለማድረግ ቢያስቡ ቅድሚያ ነፍሰ-ጡር መሆኗን ለማረጋገጥ የሚቆይበት የሦስት ወር ጊዜ ቆይታ ነው። "ዐደፍ" ለሚለው የገባው ቃል "መሒድ" مَحِيض ሲሆን "የወር አበባ" ማለት ነው። አንድ ወንድ ከዐደፍ ያቋረጠች ማለትም ያረጠች ሴት ለመፍታት ምናልባት አርጣለች ተብሎ እግዝና ስለሚከሰት የሦስት ወር ጊዜ ይኖራታል። አንዲት ሴት ልጅ ለዐቅመ-ሐዋህ ስደርስ ግንኙነትን ሲታሰብ ወይም ሲፈለግ የሚወጣ ያዝ የሚያደርግና የሚያጣብቅ ቀለም አልባ እና ሽታ አልባ ቀጭን ፈሳሽ"nocturnal emission" አላት፥ ነገር ግን ይህ ፈሳሽ ኖሮ የወር አበባዋ ሳይመጣ ብዙ ጊዜ ሊቆይ ይችላል። ይህንን የወር አበባ ያላዩ ሴቶች መሃል ላይ እንቁላል ማምረት ችለው እርግዝና ሊከሰት ስለሚችል ሦስት ወር ባል የማይፈታበት ጊዜ አለ፦
2፥235 *የተጻፈውም ዒዳህ ጊዜውን እስከሚደርስ ድረስ ጋብቻን ለመዋዋል ቁርጥ አሳብ አታድርጉ፡፡ አላህም በነፍሶቻችሁ ያለውን ነገር የሚያውቅ መኾኑን ዕወቁ፤ ተጠንቀቁትም፡፡ አላህም መሓሪ ታጋሽ መኾኑን ዕወቁ"*፡፡ وَلَا تَعْزِمُوا۟ عُقْدَةَ ٱلنِّكَاحِ حَتَّىٰ يَبْلُغَ ٱلْكِتَٰبُ أَجَلَهُۥ ۚ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِىٓ أَنفُسِكُمْ فَٱحْذَرُوهُ ۚ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌۭ
እንግዲህ ዐቅመ-ሐዋህ ጅማሬው አካላዊ ሽግግር"physical transition" የሆኑት ጡቷ ማጎጥጎጥ፣ ብብትና ብልት አካባቢ ጸጉር ማብቀል፣ የተራክቦ ፈሳሽ ማመንጨት ሲሆን ቀጣዩ የእንቁላል እድገት"ovarian development" ልጅ ለመፅነስ መደላድል ነው፥ እንቁላሉ የወንድ የዘር ሕዋስ ካላገኘ የወር አበባ ሆኖ ይወጣል። ይህንን በቅጡ ያልተረዱ ሚሽነሪዎች ዐይናቸውን በማንሸዋረር "የወር አበባ ያላየች ሴት" የሚለውን "ለዐቅመ-ሐዋህ ያልደረሰች" ብለው በማውረግረግ ኢሥላምን ሊዘልፉ ይፈልጋሉ፥ ይህ የደፈረሰ መረዳት ከላይ ያለውን ተስተምህሮት ጥልልና ጥንፍፍ አድርጎ ካለማየት የመጣ የተሳከረ መረዳት ነው። በኢሥላም ምንም ነገር መጉዳት አይፈቀድም፥ ጉዳትም ካለ በቂሷስ ይፈረዳል እንጂ ጉዳት አይመለስም፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 13, ሐዲስ 34
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ *"መጉዳት የለም፥ ጉዳትንም መመለስ የለም"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ لاَ ضَرَرَ وَلاَ ضِرَارَ ” .

ሼር☞ ሼር☞ @Mahdi_Quran_Recitation
@slmatawahi
@Islamhasanswer
🎙 ኡስታዝ ኢልያህ ማሕሙድ
🌀 በእስልምና ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶቻችን።
➩ Join channel @Islamhasanswer
ሼር☞ ሼር☞ @Mahdi_Quran_Recitation
@slmatawahi
@Islamhasanswer
Forwarded from የሰለምቴዎች ቻናል
Watch "ኑር የቁርአን ማእከል" on YouTube
https://youtu.be/EavluzzN72k
https://youtu.be/EavluzzN72k
YouTube
ኑር የቁርአን ማእከል
📜እንኳን ደስ አላችሁ📜
ኑር የቁርአን ማእከል
✒️በተከበረው ሰላምታችን አስላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
✒️የአላህን ቃል ለማወቅ በተከበረው ቁርአን ለመድመቅ ሽንፈትን ዑዝር ሊያሳጣ እነሆ ኑር የቁርአን ንባብ እና ኢሰላማዊ ጥናት ማእከል ብቅ አለ
✒️በየትኛወም አገር ለምትገኙ እህት ወንድሞች ከፈጅር ጀምሮ እስከ ምሽቱ 5 ስአት ድረስ በዓይነቱ ለየት ባለ zoom…