tgoop.com/waaldaa/1232
Create:
Last Update:
Last Update:
#ሰው_ነህ
ሰው እንጂ ድመት አይደለህምና በሰጡህ ቦታ አትቅር ።
ሰው እንጂ ውኃ አይደለህምና ወደ ተመቸህ አትሂድ።
ሰው እንጂ ውሻ አይደለህምና ወደ ተፋኸው አትመለስ።
ሰው እንጂ ዝንጀሮ አይደለህምና ለፍትወትህ አትኑር።
ሰው እንጂ ጦጣ አይደለህምና ብልጠት አታብዛ።
ሰው እንጂ እባብ አይደለህምና ተንኮለኛ አትሁን።
ሰው እንጂ የመስኖ ውኃ አይደለህምና
ማንም ወደ ፈለገው አይቀይስህ።
ሰው እንጂ ጎርፍ አይደለህምና በቁጣ የሠራኸውን አታፍርስ።
ሰው እንጂ ዛፍ አይደለህምና በወደቅህበት አትቅር።
ሰው እንጂ እህል አይደለህምና ዘረኛ አትሁን።
ሰው እንጂ እንስሳ አይደለህምና ማስተዋል አይራቅህ።
ሰው እንጂ እስስት አይደለህምና አሰመሳይ አትሁን።
ሰው እንጂ ሰይጣን አይደለህምና በሰው ውድቀት ጮቤ አትርገጥ።
ሰው እንጂ መስታወት አይደለህምና ከፊትህ የቆመውን ሁሉ አትምሰል።
ሰው እንጂ መኪና አይደለምህና ማንም ወደ ፈለገው አይንዳህ
ሰው እንጂ ቁስ አይደለህምና ገንዘብ አይለካህ
https://www.tgoop.com/betekrstiyan_21
BY ማህበር ሐዋርያት ቢሊዳ ማርያም
Share with your friend now:
tgoop.com/waaldaa/1232