tgoop.com/waaldaa/1266
Last Update:
በሆሳዕና በ፩ ቀን ለበረከት 100 ቆርቆሮ
ትኩረት ለገጠር ቅዱስ ሩፋኤል ቤ/ያን
ትኩረት ለገጠር ምዕመናን
ትኩረት ለገጠር ቋንቋ ስብከት
ትኩረት ለገጠር ህንጻ ቤተክርስቲያን
ትኩረት ለገጠር አገልጋዮች
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ የኮላይቴ ቅዱስ ሩፋኤል ህንጻ ቤተክርስቲያን እየተሰራ ይገኛል።
በጥቂት ምዕመናን የተጀመረው የኮላይቴ ቅዱስ ሩፋኤል ህንጻ ቤተክርስቲያን ዛሬ ላይ በአቅም ማነስ የተነሣ ህንጻው ያለበት ሁኔታ በጣም ያሳዝናል።
የኮላይቴ ቅዱስ ሩፋኤል ህንጻ ቤተክርስቲያን ከ1988 ዓ/ም ገደማ የተጀመረ ሲሆን ምዕመናንን ቤተክርስቲያን ለመሳለም ከ2:00 ሰዓት ይፈጅባቸዋል።
በገጠር እየኖሩ ለቤተክርስቲያን ትልቅ ናፍቆትና ፍቅር ያላቸውን ምዕመናን ማየት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ቢሆንም ቅሉ በሌላ በኩል ደግሞ አቅም አጥተው ተስፋ በመቁረጥ በመናፍቃን መከበብ ምንኛ ከባድ መሆኑ መረዳት ተገቢ ነው።
ጌታችንን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ያዳነበት ይደንቃል።
ክርስቲያኖች የክርስቶስን መከራ ለእኛ የከፈለውን ዋጋ የምናስብበት ሲሆን በተለይም ጌታችን ለእኛ ያደረገው በሚገባ በመረዳት ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን የፈሰሰውን ደም የተቆረሰውን ሥጋ በመገንዘብ ሊሆን ይገባል።
=ካህን ይናፍቃሉ ንሰሐ ለመግባት
= ቤተክርስቲያን ይናፍቃሉ ለመሳለም
= የክርስቶስ ሥጋና ደም ይናፍቃሉ ህይወት ለማግኘት
=ልጆቻቸውን ለማጥመቅ ይጨነቃሉ በዓመት ያጠምቃሉ
=ክርስቲያን ቢሞት በእርሻ ይቀበራል ፍትሐት አያገኝም
=ወጣቶች ከቤተክርስቲያን ሥርዓት ውጭ ያገባሉ
= በቋንቋ ቃሉን መማር ይፈልጋሉ ግን አያገኙም
ታዲያ በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ምዕመናንን በማሰብ ሰማያዊ በረከት ለማግኘት በገጠር ለሚገኙ ምዕመናን ትኩረት መስጠት ይገባናል።
ስለሆነም በአንድ ቀን ለኮላይቴ ቅዱስ ሩፋኤል ህንጻ ቤተክርስቲያን ማጠናከር የድርሻችንን በመወጣት የበረከት ተካፋይ እንሁን!!!
ቡና ባንክ 2459501001298
BY ማህበር ሐዋርያት ቢሊዳ ማርያም
Share with your friend now:
tgoop.com/waaldaa/1266