Telegram Web
በፍፁም የማይቀርበት ፰ኛው ዙር የንግሥ ጉዞ ወደ አስደናቂዎቹ ገዳማት ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ እና ማኅበረ ሥላሴ በአክሱም ጽዮን ልዩ ዙር
→ መነሻ የካቲት 23 መመለሻ መጋቢት 7
→ የጉዞ ዋጋ ማረፊያን ጨምሮ 12000 ብር
* ለበለጠ መረጃ፦ 0911289877 / 0901070707

★ ይህ ልዩ የጉዞ መርሐ ግብር፦
→ እምነቱ በቅዱሳን መላእክት ከገነት የሚመጣበት ድንቅ ቦታ፤
→ በከባዱ መከራ ዘመን ክርስቲያኖች የሚጠለሉበት የዘመናችን ሐመረ ኖኅ፤
→ በርካታ ኅቡዓን አበው የከተሙበትና ፈቃደ እግዚአብሔር ለሆነላቸው ሁሉ እየተገለጡ የሚባርኩበት መካነ ግኁሣን፤
→ ዘመንዎና ሕይወትዎ ብሩክ ይሆን ዘንድ ሰው ሆነው እንደ መላእክት ከሚኖሩ ከእውነተኞቹ መናኒያንን በርከክ ብለው ቡራኬ ተቀብለው የሚመለሱበት የበረከት ምድር፤
→ ትምህርት ለማይገባው ሁሉ በኃይለ እግዚአብሔር በቅዱስ ያሬድ ቃልኪዳን አእምሮውን ለብዎውን ባርኮ አስተዋይና ጠቢብ የሚያደርግ ፈዋሽ ጠበሉን ተጠምቀውና ጠጥተው የሚመለሱበት፤
→ ጃንደረባው ባኮስ፣ ሊቁ ቅዱስ ያሬድና ሌሎች በርካታ ቅዱሳን በተሰወሩበት ደብረ ሐዊ ገዳም የቃልኪዳናቸውን በረከት የሚያፍሱበት፤
→ ለብዙ ዘመናት ወንበር ተክለው ጉባዔ ዘርግተው ምሥጢር እያደላደሉ በርካታ ሊቃውንተ ቤተከርስቲያንን ከሚያፈሩ መምህራነ ጉባዔያት ጋር ተገናኝተው ለጥያቄዎቻችሁ ሁሉ መልስ የምታገኙበት፤
→ በጸሎት ተጋድሏቸው ከተጠቀሙ ንዑዳን ክቡራን አበው ጸሎትና ቡራኬ የምትቀበሉበት፤
→ እጅግ በርካታ ጥንታዊ ገዳማትና አድባራትን የምንሳለምበት እና ታሪካዊ ቦታዎችን የምንጎበኝበት የ15 ቀናት ልዩ ጉዞ ነው።

❖ ውስን ወንበሮች ብቻ ስለቀሩን ይህንን ቅዱስ ቦታ ለመሳለም የምትሹ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሁሉ ደውሉልንና አብረን እንጓዝ! ለበለጠ መረጃ፦
👉 0901070707 / 0911289877
#ማኅበረ_ቅዱስ_ፊልጶስ_ወአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ

❖ በዚህ ታሪካዊ የንግሥ ጉዟችን የምንሳለማቸው ጥንታዊ ገዳማትና የምንጎበኛቸው መካነ ቅርሶች፦
👉🏿 ደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ (፲ሩ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት)፣
👉🏿 ቅዱስ ነአኩቶ ለአብና ቅ.ገብረ ማርያም፣
👉🏿 ሎሜ ዱር ቅ.አርሴማ የእናቶች ገዳም፣
👉🏿 ጣራ ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ወአቡነ ገላውዴዎስ የአባቶች ገዳም፣
👉🏿 ጣራ ቅ.ማርያም የእናቶች ገዳም፣
👉🏿 አስደናቂው ወይን ዋሻ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣
👉🏿 ራስደጀን ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ፣
👉🏿 መንታበር ቅዱስ ገብርኤል እና አቡነ አረጋዊ፣
👉🏿 ላይ ጣና - ጥጉና ቅ.ኪዳነ ምሕረት፣
👉🏿 ወርቅ አበባ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት፣
👉🏿 ደባርቅ መድኃኔዓለም፣
👉🏿 አይከል አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን፣
👉🏿 ጥንታዊው ማኅበረ ሥላሴ፣
👉🏿 ደብረ አጥገባ አቡነ ጰንጠሌዎን፣
👉🏿 ደብረ ቆናጽል አቡነ ሊቃኖስ፣
👉🏿 ደብረ መደራ አቡነ ገሪማ፣
👉🏿 ደብረ ሐተታ አቡነ ጽሕማ፣
👉🏿 ደብረ የሐ አቡነ አፍፄ፣
👉🏿 ደብረ ዳሞ (ደብረ ሃሌሉያ) አቡነ አረጋዊ፣
👉🏿 ጻድቋ ቅ.ዕድና ተጋድሎ ያረገችባት ቅ.ኪዳነ ምሕረት፣
👉🏿 ደብረ ጎሕ አቡነ ይምዓታ፣
👉🏿 ጎሕ ቅ.ሥላሴ፣
👉🏿 ጥንታዊው ውቕሮ ቂርቆስ፣
👉🏿 ገርዓልታ አብርሃ ወአጽብሃ፣
👉🏿 ርእሰ ገዳማት ወአድባራት አክሱም ጽዮን ማርያም፣
👉🏿 ማይኪራሕ ቅዱስ ያሬድ፣
👉🏿 አክሱም ኢየሱስ፣ አርባዕቱ እንስሳ፣ አባ ሊባኖስ፣...
👉🏿 ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣
👉🏿 ዋልድባ ደብረ ዓባይ አቡነ ሳሙኤል፣
👉🏿 ማይወይኒ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣
👉🏿 ሰቋር ዋልድባ ኪዳነ ምሕረት ወመድኃኔዓለም፣
👉🏿 ዓዲ አርቃይ አስጋዲት ቅ.ማርያም፣
👉🏿 ማይበራዝዮ አቡነ አላኒቆስ፣
👉🏿 ደብረ ዓሣ አቡነ ዮሐኒ ወአባ አሞኒ፣
👉🏿 አስደናቂው አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን፣
👉🏿 መቐለ ደብረ ሰላም ቅ.ሚካኤል፣
👉🏿 ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
👉🏿 ታሪካዊው ደሴ መድኃኔዓለም፣
👉🏿 ታሪካዊው ደብረ ብርሃን ሥላሴና ሌሎችም...
👉🏿 ከ1450 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያለው ራስ ደጀን ሆጨው ቤተ ጉባዔ [ቅዱስ ያሬድ ወንበር ተክሎ ጉባዔ ዘርግቶ ለ40 ዓመታት ያስተማረበትና እነ ቅዱስ ባኮስ የተሰወሩበት የስውሩ መቅደስ ጉልላት]፣
👉🏿 ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበትና ለተገባው በየጊዜው የሚገለጥበት ደብረ ሐዊ ቅ/ያሬድ ወቅ/ክርስቶስ ሠምራ የዋሻ ገዳም፣
👉🏿 ራሱ ቅ/ያሬድ በኪደተ እግሩ ከልሎ የገደመውና በቅዱሱ ሐይቅ በጣና ስም የሚጠራው መካነ ኅቡዓን ጣና ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም፣
👉🏿 ጃንደረባው ባኮስ የተሰወረበትን ደብረ ራስ ደጀን፣
👉🏿 ትምህርት ለማይገባው ሁሉ በቃልኪዳኑ አምነው ቢጠጡት አእምሮን የሚከፍት ጥበብና ማስተዋልን የሚያድል ተአምረኛ ጠበሉን ይጠመቃሉ፤ ይጠጣሉም።
👉🏿 ተአምረኛው ባለልብስ ጠበል የሚገኝበት ጥንታዊው መካነ ኅቡዓን ጨነቅ መድኃኔዓለም ገዳም፣
👉🏿 ታሪካዊዎቹ የጎንደር አድባራት (በተለይ በአቡነ ዓምደ ሥላሴ የተመሠረቱት፦ ጥንታዊው ደብረ ብርሃን ቅ/ሥላሴ፣ መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም፣ አጣጣሚ ቅ/ሚካኤል፣ ርእሰ አድባራት አደባባይ ኢየሱስ፣ ፊት ቅ/ሚካኤል፣ ታሪካዊቷ ግምጃቤት ማርያም፣ እንዲሁም ታሪካዊቷ የእቴጌ ምንትዋብ ደብር ቅ/ቁስቋም፣ ተአምረኛዋ በዓታ ለማርያም፣ ቅ/ሩፋኤል ወአቡነ ሐራ ድንግል፣ አደባባይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ፊት በር አደባባይ ቅ/ጊዮርጊስ፣ ታሪካዊው ጎንደር ቅ/ዮሐንስ መጥምቅ፣... ወዘተ እንሳለማለን፤ በጎንደር ፋሲለደስ ጊቢ የሚገኙትን ታሪካዊዎቹን አብያተ መንግሥታት እንጎበኛለን

❖ ማሳሰቢያ፦ ጊዜያችንን በአግባቡ ከተጠቀምን በሕይወታችሁ የማትረሷቸውና ግሩም በረከት የምታገኙባቸው ሌሎች ገዳማትም ሰርፕራይዝ ይኖራሉ።
→ መነሻ የካቲት 23 መመለሻ መጋቢት 7
→ የጉዞ ዋጋ ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 12000 ብር

👉 በተለያዩ ምክንያቶች በዚህ ጉዞ መሳተፍ ያልቻላችሁ ወገኖቻችን መክፈል የማይችሉ ወንድምና እህቶቻችንን በማገዝ ከበረከቱ ተሳተፉ።

✞❖✞ በማኅበራችን የጉዞ መርሐ ግብራት መሳተፍ ከፈለጉ ሳያመነቱ ይደውሉልንና አብረውን ይጓዙ!!!
▶️ የመሄድ አሳብ ካሎትና ከወሰኑ ቀድመው  ይመዝገቡ!
👉 0911289877 / 0901070707

በቴሌግራም ይቀላቀሉን 👇
👉🏿 @waldiba
@negeretewahido
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከ50 በላይ ጥንታዊ ገዳማትና አድባራትን የሚሳለሙበት ልዩ የዙር ጉዞ ወደ አስደናቂዎቹ ገዳማት
👉🏿 ጥንታዊው ማኅበረ ሥላሴ፣
👉🏿 ምሣጢራዊው ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ፣
👉🏿 ደብረ ሮሃ አስደናቂዎቹ ቅዱስ ላሊበላ 10 ውቅር አብያተ መቃድስ፣
👉🏿 ርእሰ ገዳማት ወአድባራት አክሱም ጽዮን ማርያም፣
👉🏿 የቆላ ተንቤኑ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን፣
👉🏿 የተስዓቱ ቅዱሳን ገዳማት
👉🏿 ዋልድባ ደብረ ዓባይ እና ሰቋር፣
👉🏿 በወሎ፣ በጎንደርና በትግራይ የሚገኙ በርካታ ቅዱሳት መካናት፣
→ መነሻ የካቲት 23 መመለሻ መጋቢት 7
→ የጉዞ ዋጋ ማረፊያን ጨምሮ 12000 ብር

❖ ውስን ወንበሮች ብቻ ስለቀሩን ይህንን ቅዱስ ቦታ ለመሳለም የምትሹ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሁሉ ደውሉልንና አብረን እንጓዝ! ለበለጠ መረጃ፦
👉  0901070707 / 0911289877
አዘጋጅ፦ ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

👉 በተለያዩ ምክንያቶች በዚህ ጉዞ መሳተፍ ያልቻላችሁ ወገኖቻችን መክፈል የማይችሉ ወንድምና እህቶቻችንን በማገዝ ከበረከቱ ተሳተፉ።
መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ምሥጢራዊው መንዝ እመጓ ቅዱስ ዑራኤል
* መነሻ የካቲት 21
* መመለሻ የካቲት 23
* የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 2800 ብር
ለበለጠ መረጃ፦ 0901070707 / 0911289877

አስተውሉ! ጌታችን በቦታው ላይ፦
“ስፍራውን የረገጠ ወንድ የ40ቀን ሴት የ80ቀን ንጹሕ አደርገዋለሁ፤
እስከ ዕለተ ምጽዓት ቦታው በከሃዲያን አይጠፋም፤
የማልምረውን ስፍራውን አላስረግጠውም፤
በዚህ ሥፍራ የለመነኝን አልነሳውም የጠየቀኝን አልከለክለውም፤
በሞተ ጊዜ ሲዖልን አያያትም፤ በደረቴ አቅፌ ባሕረ እሳትን አሻግረዋለው።” ብሎ ለቅ/ዑራኤል ቃልኪዳን ሰጥቶበታል።

ጌታችን በወንጌል፦ “የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው። እውነት እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።” ማቴ ፲፫፥ ፲፮- ፲፯ እንዳለ እነዚህን ቅዱሳት መካናት በመሳለም ለመባረክ የታደለ ማን ነው?

#እመጓ_ዑራኤል ( #እመ_እጓል )
እመጓ ደብረ ቆጵሮስ ኢየሱስ ወቅ/ዑራኤል ገዳም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ስር በመንዝ ማማምድር ወረዳ ውስጥ ከሞላሌ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል።

፩- ድንግል ማርያም ከልጅዋ ጋር በተሰደደች ግዜ የተቀመጠችበት ቦታ ነው፡፡

፪- ቦታውን በአረማይክ ቋንቋ እመጓ - የእኔና የአንች (የእናትና የልጅ) ሀገር ስም እራሱ ጌታችን ነው እመጓ ብሎ በአረማይክ ቋንቋ የሰየመው። እመእጓል ሲለው / ብሎታል።

፫- በቦታው 2 ተራራዎች አሉ።
1- ገሊላ (ክሊና) ተራራ፦ ይህ ተራራ እመቤታችን የተቀመጠችበትና ጌታችን ኢትዮጵያን አስራት ሀገር ትሁንሽ ብሎ ያረገበት ቦታ ሲሆን በተራራው ላይ በአየር ላይ የቆመ ድንጋይ ይታያል፤ በድንጋዩ ላይ ተወጥቶ 3 ግዜ ይዞራል።
2- ቆጵሮስ ተራራ፦ ይህ ተራራ ቅ/ዑራኤል የጌታን ደም የረጨበትን የብርሃን ጽዋ የሰወረበት፣ ቅዱስ መስቀሉ ወደ ግሸን ሲሄድ 14 ቀን የተቀመጠበት ቅዱስ ተራራ ነው።

፬- በዚህ ቦታ ጌታችን ለቅ/ጊዮርጊስ ኢትዮጵያን አስራት ሀገርህ ትሁን ብሎ ቃልኪዳን እንደሰጠው የቦታው አባቶች ይናገራሉ።

፭- አፄ ይኩኖ አምላክ በአሳነፁት የቅዱስ ዑራኤል ቤተ መቅደስ ታቦተ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስን አስገብተው ቅዳሴ ቤቱን ያከበሩት ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ናቸው፤ በቦታውም ላይ “የበረረ ወፍ የሰገረ ቆቅ አይገደልብሽ ሸሽቶ” ብለው በምሥጢር ገዝተዋል።

፮- ሊቁ አባታችን ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ ዐምደ ሃይማኖት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ቦታውን ባርኮ ማሕሌት ቆሞ ቀድሶ ቃልኪዳን ተቀብሎባታል።

፯- ደጋጎቹ ነገሥታት አጼ በዕደ ማርያም፣ አፄ ናዖድና አፄ ይኩኖ አምላክ በቦታው ሱባኤ ገብተው ጸሎታቸው ተሰምቶላቸው እጅ መንሻቸውን አበርክተውለታል።

፰- በአንድ ወቅት ፬ ቅዱሳን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም መጥተው ሦስቱ በታሪካዊው ሰደድኩላ ቅዱስ ሚካኤል፣ በቀስታት ቅ/ሚካኤልና በአደሌ ቅ/ሚካኤል ሲጸልዩ አንደኛው ጻድቅ ግን በእመጓ ቆላ በምትገኘው ምስአለ ማርያም ነው ተጋድሎውን ያደረገው።

፱- ቅዱስ መስቀሉን ወደ ኢትዮጵያ ያመጡት ፲ሩ ቅዱሳን ከነደቀመዛሙርቶቻቸው ከመስቀሉ ጋር ባመጡት በታቦተ ሚካኤል እየቀደሱ ለ14 ቀን ቆይተውበታል።

፲- በቦታው ላይ ዋሻዎች አሉ።
በዋሻው ውስጥ፦ (የድንግል ማርያም የእጅዋ አሻራ በድንጋይ ታትሞ) ይታያል።
- ያልፈረሰ፣ ያልበሰበሰ ክንፍ ያላቸው አፅመ ቅድሳን አጽም ይታያል
- የድንግልና የልጅዋ ልብስ እንዳለ ይነገራል።

፲፩- በዚሁ አካባቢ በስእለት ሰሚዋ ቀጭን አምባ ማርያም ገዳም ውስጥ ቅ/ዑራኤል በክንፉ በጠረገው ቦታ ላይ የእመቤታችን ቤተክርስቲያን ታንፆበታል፤ በዚች ቤተ ክርስቲያን አጼ ናዖድና ሌሎችም አበው ስዕለታቸው ስለሰመረላቸው ገዳሟ ምስዓለ ማርያም እየተባለችም ትጠራለች።

☞ የቦታው ቃልኪዳን፦ ጌታችን "አስቀድሜ በታላቁ ዐምደ ወርቅ ስሙን ያልጻፍኩትን ሰው ይህንን ደጅ አላስረግጠውም! ይህንን ቅዱስ ቦታ የረገጠና ያየ ትውልደ ዘሩን እባርከዋለሁ እምረዋለሁም፤ የጠየቀውን የሀሳቡን እሰጠዋለሁ።" ብሎ ቃል እንደገባበት ልብ ይሏል!

• በጉዟችን የምንሳለማቸው ቅዱሳት መካናት፦
→ ታሪካዊው ዳግማዊ ቤተልሔም አፍሮ አይገባም መድኃኔዓለም ወአቡነ ዘርዓ ብሩክ ገዳም፣
→ ምሥጢራዊው እመጓ ቅ/ዑራኤል፤
→ ጻድቃኔ ማርያም፤
→ ዘብር ቅ/ገብርኤል፤
→ ስዕለት ሰሚዋ ቀጭን አምባ ምስዓለ ማርያም፣
→ እመ እጓል ቅ/እግዚአብሔር አብ፣
→ እመቤታችን በስደቷ ጊዜ በኪደተ እግሯ የባረከቺው የኅቡዓን በዓት ደብረ ክሊና /ገሊላ፣
→ ቅ/ዑራኤል ደመ መለኮትን ለዓለም ሁሉ የረጨበት ብርሃናዊው ቅዱስ ጽዋ የተቀመጠበትና ቅዱስ መስቀሉ ወደ ግሸን ሲሄድ ለ14 ቀናት ያረፈበት ደብረ ቆጵሮስ፤
→ ታሪካዊው ሰላድንጋይ ቅ/ማርቆስ፣

★ ወደዚህ ቅዱስ ስፍራ ታላቅ የበረከት ጉዞ ተዘጋጅቷል፤ መኪናው ሊሞላ ጥቂት ወንበሮች ብቻ ናቸው የቀሩን።
* መነሻ የካቲት 21 ከሌሊቱ 11:00
* መመለሻ የካቲት 23
* የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 2800 ብር
* ለበለጠ መረጃ፦
📞 0901070707
📞 0911289877
#ማኅበረ_ቅዱስ_ፊልጶስ_ወአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ

መነሻ ቦታዎች፦ አራዳ ጊዮርጊስ፣ መገናኛ እና ጣፎ አደባባይ
የዓቢይ ፆም የማኅበራችን የጉዞ ፕሮግራም!

1ኛ ሳምንት ዘወረደ፦ ሰሚነሽ ኪዳነ ምሕረት
👉 የካቲት 16 ደርሶመልስ
👉 የጉዞ ዋጋ ምሳን ጨምሮ 900 ብር

2ኛ ሳምንት ቅድስት፦ እመጓ ቅዱስ ዑራኤል
መነሻ የካቲት 21
መመለሻ የካቲት 23
የጉዞ ዋጋ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 2800 ብር

★ ወደ አስደናቂዎቹ ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድና ማኅበረ ሥላሴ ገዳማት
☞ በአክሱም ጽዮንና በቅዱስ ላሊበላ ዙር ከ50 በላይ ገዳማትን የምንሳለምበት የ15 ቀናት ታሪካዊ የንግሥ ጉዞ
☞ መነሻ የካቲት 23
☞ መመለሻ መጋቢት 7
☞ የጉዞ ዋጋ ማረፊያን ጨምሮ 12000 ብር

3ኛ ሳምንት ምኩራብ፦ እመ ምሕረት ቅድስት ኪዳነምሕረት
→ መነሻ የካቲት 29
→ መመለሻ የካቲት 30

እመጓ ቅዱስ ዑራኤል
መነሻ የካቲት 28
መመለሻ የካቲት 30
የጉዞ ዋጋ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 2800 ብር

4ኛ ሳምንት መፃጉዕ፦ ምድረከብድ አቦ
• መነሻ መጋቢት 4
• መመለሻ መጋቢት 5 ከንግሥ በኋላ
የዝዋይ ሐይቅ ገዳማት መጋቢት 7 ደርሶ መልስ

በዓለ መስቀሉን በመስቀሉ ሥፍራ ግሸን ደብረ ከርቤ
* መነሻ መጋቢት 8
* መመለሻ መጋቢት 12

5ኛ ሳምንት ደብረ ዘይት፦ ምሁር ኢየሱስ ገዳም
👉 መነሻ መጋቢት 13
👉 መመለሻ መጋቢት 14 ከንግሥ በኋላ
👉 ምቾት ባለው ልዩ ባስና በመደበኛው ደረጃ 1 አውቶቡስ

6ኛ ሳምንት ገብርሔር፦ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
መነሻ መጋቢት 19
መመለሻ መጋቢት 21
የጉዞ ዋጋ 4500 ብር

★ ዋልድባ አብረንታንት ገዳም
👉🏿 መነሻ መጋቢት 22
👉🏿 መመለሻ ሚያዚያ 3

7ኛ ሳምንት ኒቆዲሞስ፦ እመጓ ቅዱስ ዑራኤል
👉 መነሻ መጋቢት 26
👉 መመለሻ መጋቢት 28
👉 የጉዞ ዋጋ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 2800 ብር

8ኛ ሳምንት ሆሣዕና፦ ሆሣዕናን በሆሣዕና ማርያም
መነሻ ሚያዚያ 4
መመለሻ ሚያዚያ 5
የጉዞ ዋጋ 1500 ብር

* መነሻ ቦታ ለሁሉም ጉዞዎች፦ አራዳ ጊዮርጊስና መገናኛ

* ለበለጠ መረጃ፦
👉🏿 0901070707
👉🏿 0911289877
አዘጋጅ፦ ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

የዚህ ፆም የጉዞ ፕሮግራማችን ይህንን ይመስላል። በየመሀሉ እየተጨመሩ የምንሳለማቸው ብዙ ገዳማት ስለሚኖሩ አብረውን ተጉዘው የበረከቱ ተሳታፊ ይሁኑ ዘንድ ግሩፑን በደንብ ይከታተሉ!

👉🏿 @waldiba
@negeretewahido
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ገዳመ_ወንያት_አቡነ_ሐራ_ድንግል_አንድነት_ገዳም
☞ በ1574 ዓ.ም በኢትዮጵያዊው ጻድቅ በአቡነ ሐራ ድንግል የተመሠረተ ታላቅ ገዳም ነው። በዚህ ቦታ ጻድቁ ወንጌልን እያስተማሩ፣ እጅግ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን እያደረጉ፣ ሙት እያሠነሡ፣ ድውያንን እየፈወሡ እግዚአብሔርን በንጽሕና በማገልገል ለ50 ዓመታት ተጋድሎ አድርገውበታል።

☞ ጻድቁ እመቤታችንን አብዝተው ይወዷት ስለነበር ምስጋናዋን ሲያደርሱ 3 ክንድ ከመሬት ከፍ ይሉ እንደነበር ዜና ሕይወታቸው ይገልጣል። ጻድቁን ዘወትር እየረዳ ለፍጻሜ ክብር ለቅድስና ያበቃቸው መጋቤ ሐዲስ መጽንዔ ኃይል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነው።

☞ አቡነ ሐራን ድንግል የትውልድ ቦታቸው በምዕራብ ጎጃም ዞን ባሕርዳር ዙሪያ ወረዳ ላጉና ቀበሌ ሲሆን የተወለዱት ጥቅምት 19 ቀን 1534 ዓ.ም ነው። አባታቸው ሊቀ ካህናት ዮሐንስና እናታቸው ብፅዕት ወለተ ጊዮርጊስ በሕገ እግዚአብሔር ጸንተው የሚኖሩ ደጋግ ቅዱሳን ነበሩና ልጃቸውን በሃይማኖትና በምግባር አሳድገዋቸዋል።

☞ አባታችን ዓለምን ንቀው በአባ ኖብ ድንግል ወደተመሠረተውና በርካታ ቅዱሳን ለፍጻሜ ወደ በቁበት ሬማ መድኃኔዓለም ገዳም ከአባታቸው ጋር እያገለገሉ ሲኖሩ እናታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ አቡነ ሐራ ድንግልም
ከሐዘናቸው በእግዚአብሔር ተጽናንተው በፆም በጸሎት ተወስነው ፈጣሪያቸውን ሲያገለግሉ ቆይተው 30 ዓመት ሲሞላቸው ከሬማው ቆሞስ ከአባ መዓዛ ድንግል ምንኩስና ተቀበሉ። ጻድቁ ምንኩስና እንደተቀበሉ ከገዳሙ ሳይወጡ በአጽንዖ በዓት ተወስነው ለ14 ዓመት ቆይተዋል፡፡

☞ ጻድቁ ጥር 11 ቀን 1624 ዓ.ም በክብር ሲያርፉ በመቃብራቸው ላይ ለ40 ቀን ብርሃን ሲወርድ በገሐድ ታይቷል፡፡ ቅዱስ አፅማቸውም በስማቸው በተሰራው ቤተክርስቲያን ውስጥ በክብር አርፎ ይገኛል።
የአራዳ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ህንፃ ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ እድሳት ለማድረግ: ታቦታተ ህጉ በመቃረቢያ  መቃኞ ይገኛል። ስለሆነም የህንፃ ቤተ ክርስቲያኑን እድሳት ለማከናወን በተከፈተው የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1423 አቅማችን የፈቀደውን የበረከት ስራ በመስራት ሁላችንም ከሰማዕቱ በረከት ረድኤት እንሳተፍ::
ወራሪ ጠላታችንን ድል ከነሳልን የሀገር ባለውለታና ጠባቂ ቅዱስ ሰማዕት በረከት ሌሎችም እንዲሳተፉ : ይህን መልዕክት ለሁሉም በማጋራት ታሪካዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ:: እግዚአብሔር ይስጥልን!!!
የሊቃውንት ጉባኤ '' ዝክረ ኒቅያ» በሚል መሪ ሐሳብ ሀገር አቀፍ የጉባኤ ቤት መምህራንና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የምክክር ጉባኤ ከሚያዝያ 20 -25 ቀን 2017 ዓ .ም እንደሚከናወን ሊቃውንት ጉባኤ አስታወቀ።
የጉባኤው ዐላማ:- ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ የጉባኤ ቤት መምህራንና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ተሰባስበው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው ለቅዱስ ሲኖዶስ ምክረ ሐሳብ እንደምያቀርቡም በመግለጫው ተጠቅሷል ።

የመግለጫ ሙሉ መልእክት ከዚህ በታች ቀርቧል ።
ዘጋቢ ሰላም አምባዬ

«ዝክረ ኒቅያ» በሚል መሪ ሐሳብ ሊደረግ ስለታቀደው ሀገር አቀፍ የጉባኤ ቤት መምህራንና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የምክክር ጉባኤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከሊቃውንት ጉባኤ የተሰጠ መግለጫ።

«እስመ ብዝኀ ጠበብት መድኀኒተ ዓለም ውእቱ የሊቃውንት ብዛት ለዓለም መድኀኒት ነው።»

የሊቃውንት ጉባኤ በቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው ኀላፊነት መሠረት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት፣ ሥርዐተ አምልኮ፣ ታሪክና ትውፊት፣ ልሳነ መጻሕፍትና የዕውቀት ሀብታት፣ ጥበባተ አበውና ባህለ ሃይማኖትን መጠበቅና ማስጠበቅ፣ ማስፋፋትና በአግባቡ እንዲተረጐሙ ማድረግ፣ ዐቂበ እምነትን ማጠናከር፣ በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ልዕልና፣ ህልውና፣ የትምህርቷን ጥራትና ርትዐት መጠበቅ ዋንኛ የሥራ ድርሻው ነው፡፡

በቀድሞ ዘመን መናፍቅና ከሓዲ ሲነሣ፣ ሃይማኖትና ሥርዐት ሲጣስ፣ ዐላውያን የሐሰት ትምህርትን በዐውደ ጉባኤ ሲያሠራጩ፡ ሊቃውንት ከየአሉበት ተሰብስበው ዘርዐ ኑፋቄን አርመው፣ ኀይለ ክሕደትን አድክመው ርትዕት ሃይማኖትን አቆይተዋል። በእኛም ዘመን በርካታ ውይይትና ምክክር የሚያስፈልጋቸው ዐበይት ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ጥያቄዎች በመኖራቸው፤ ያለፈውን ለማጽናት፣ የሚመጣውን ለማቅናት የሊቃውንት መሰባሰብ እጅግ ተገቢ ሆኖ ይገኛል።

በመሆኑም ቀደም ሲል ሲደረግ እንደነበረው ሁሉ፤ በአሁኑ ሰዓት “ዝክረ ኒቅያ ሀገር ዐቀፍ ጉባኤ ሊቃውንት" ማድረግ የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት በአስተማማኝ ደረጃ ለመጠበቅና ኅልውናዋን ለማስቀጠል እንደሚያስችል በመታመኑ፣ ጉባኤው በጥር ወር 2017 ዓ.ም. እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፤ በተለያዩ አሳማኝ ምክንያቶች :-

1ኛ) ጉባኤው በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የጉባኤ ቤት መምህራንና ሊቃውንት የሚታደሙበት እንደመሆኑ፥ በተለይ በጠረፉ የሀገራችን ክፍል የሚገኙ መምህራንን በበቂ ቊጥር ለማካተት እንዲቻል፥ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ተጨማሪ ጊዜ በማስፈለጉ፤

2ኛ) በጥር ወር በርካታ ሀገራዊ ክንውኖችና ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት በየአካባቢው የሚካሄዱ በመሆናቸው የጉባኤው መካሄጃ ጊዜ እንዲስተካከል ከአንዳንድ አህጉረ ስብከት በተደጋጋሚ አስተያየት በመሰጠቱ፤

3ኛ) ጉባኤው ከዘመናት ቆይታ በኋላ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድና በቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ዙሪያ ጠቃሚ ውይይቶችን በማካሄድ፥ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሚጠቅም የውሳኔ ሐሳብና አስተያየት የሚያቀርብ፥ አልፎም የአቋም መግለጫ የሚያወጣ በመሆኑ ከሚያዝያ 20-22 ቀን 2017 ዓ.ም. እንዲካሄድ የሊቃውንት ጉባኤ / መወሰኑን በቤተ
ክርስቲያኒቱ የቴሌቪዥን ሥርጭትና በሕዝብ ግንኙነት ማኅበራዊ ሚድያ መገለጹ ይታወቃል።

ስለ ጉባኤው ጥቂት መረጃዎችን ለመስጠት ያህል፦

ሀ) የጉባኤው ዝግጅት፤

«ዝክረ ኒቅያ ሀገር ዐቀፍ ጉባኤ» በቋሚ ሲኖዶስና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በተፈቀደው መሠረት ከርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በፊት የሚካሄድ ሲሆን፤ ከመላው ሀገራችን ከተቻለም ከውጭው ዓለም የሚመጡ የጉባኤ ቤት መምህራንና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጭምር የሚታደሙበት ይሆናል፡፡

ለ) የጉባኤው ዐላማ፤

ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ ዐይናማ የጉባኤ ቤት መምህራንና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ተሰባስበው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው ለቅዱስ ሲኖዶስ ምክረ ሐሳብ እንዲያቀርቡ ማድረግ ነው፡፡

ሐ) ከጉባኤው የሚጠበቁ ውጤቶች

በዚህም ጉባኤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እርስ በርስ እንዲተዋወቁ፣ ከሊቃውንት የሚጠበቀውን የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ አገልግሎት ዘመኑን የሚመጥን፣ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና የሚያስጠብቅ እንዲሆን፣ ሊቃውንት ግልጽ ውይይትና ምክክር በማድረግ፣ የጐበጠውን እንዲያቀኑ፣ የጐደለውን እንዲሞሉ፣ ወቅታዊ ምላሽ ለሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ተገቢውን ሐሳብና ምላሽ እንዲያቀርቡ ለማስቻል ነው::

በጉባኤው ላይ በተለያዩ ርእሶች ዙሪያ የሚያተኩሩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ሰፊና ጥልቅ ውይይት የሚካሄድና በመጨረሻም የአቋም

መግለጫ የሚቀርብ ሲሆን፤ ከምክክሩ የሚገኙ ፍሬያማ ውጤቶች ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በግብአትነት የሚቀርቡ ይሆናሉ።

ዝክረ ኒቅያ ሀገር ጉባኤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፥ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፥ የጉባኤ ቤት መምህራንና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፥ የመምሪያና የድርጅት ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት ከሚያዝያ 20-22 ቀን 2017 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሚካሄድ ይሆናል።

በዚህ ጉባኤ ሀገረ ስብከታችሁን ወክላችሁ የምትመጡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፥ ጉባኤው ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ጉዳዮች የሚነሡበት እንደመሆኑ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉና ለጉባኤው ስኬት የጎላ አስተዋጽኦ እንድታበረክቱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም ከወዲሁ እናሳስባለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሊቃውንት ጉባኤ

የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ተመስገን!
ረዲኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገን ወደ ታላቁ ማኅበረ ሥላሴ ገዳም ያደረግነውን የ16 ቀናት ልዩ መንፈሳዊ የንግሥ ጉዞ አምላከ አበው በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሁሉ ጠብቆ አሳልፎን በርካታ ቅዱሳት መካናትን ተሳልመን በሰላም ተመለስን።

👉 ከአዲስ አበባ የካቲት 23 ቀን ተነስተን ደብረ ብርሃን ሥላሴን ተሳልመን በታሪካዊው ደሴ መድኃኔዓለም አደርን።
👉 በኩልመስክ አድርገን ቅዱስ ነአኩቶ ለአብና ቅ/ኪዳነ ምሕረትን ተሳልመን ደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገብተን ቤተ ጊዮርጊስን ተሳልመን አደርን፤
👉 10ሩንም ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከተሳለምን በኋላ ወደ መቄት አመራንና ጥንታዊውን ጨጨሆ (ዝንጀሮ አስጨብጭብ) መድኃኔዓለምን ተሳልመን በታሪካዊው ጣራ ገዳም አደርን።

👉 በጣራ ቅ/ማርያም ኪዳን አድርሰን አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ወአቡነ ገላውዴዎስ እና ዋሻ እንድርያስን ተሳልመን ተአምረኛው ወይን ዋሻ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ፈዋሽ ጸበሉን ተጠምቀን መኪናችንን ሲያዩት «እባካችሁ ምክሆን ለምዕመናን የሆነውንና እንኳን ሰው ከ3000 የሚበልጡት ከብቶቹ በሰው ቋንቋ ተረድተው በሥርዓት የሚኖሩበትን የሺዎች ቅዱሳን ማኅበር ታላቁን ማኅበረ ሥላሴ ገዳምን እና ምሥጢራዊው የኅቡዓን በዓት ራስ ደጀን ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ ገዳምን አሳዩን» ብለው ግድ ያሉንን መነኮሳት ከገዳሙ ፈቃድ ወስደው ይዘናቸው ወደ ደረቅ ዓባይ አመራን፤
👉 ከደረቅ ዓባይ ወደ ገዳሙ የሚያስገባው ኮረኮንች መንገድ በትላልቅ ዛፎች የተከበበና ወጣ ገባ ስለሆነ አውቶቡስ መኪናችን አቁመን በገዳሙ የጭነት ሲኖትራክ ጉዟችንን እስከ ግዝት በሩ ቀጠልን፤ አብርሃ ወአጽብሃ የወርቅ ጫማቸውን ካወለቁበት የገዳሙ ግዝት በር ጀምረን ወንዶቹ ጫማችንን አውልቀን በባዶ እግራችን 40 ደቂቃ በመጓዝ ሺዎች ባሕታዊያን ለፍፃሜ የበቁበትን የቅዱሳን ከተማ ገባን፤ የሥላሴን ቤተክርስቲያን ተሳልመን የገዳሙን ቤተ እግዚአብሔር በረከት መኮሬታውን በሰሊጥ አፈላሎ በልተን የኑግ ጭልቃውን ጠጥተን በዓሉ ወደሚከበርበት የገዳሙ መዘከሪያው ወረድን፤
👉 የጻድቁ አቡነ ዓምደ ሥላሴን በዓለ ልደትና ዕረፍት አክብረን አስቀደስን ከመካከላችን የተዘጋጁት ቆረቡ፤ ከምሳ በኋላ የያዝነውን መባ አስረክበን ከአበው ጸሎተ ማርያም ተቀበልን፤ የመናኒያኑን ሠርከ ሕብስት መኮሬታ በአፈላሎ ከኑግ ጭልቃ ጋር ራት በልተን አደርን።

👉 በሌሊት ተነስተን የጭነት መኪናው እስከ መኪናችን ተጉዘን ምንጣፍና የሌሊት ልብሳችንን ጭነን ወደ ጭልጋ አርሴማ ከአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ገዳም አመራን፤ ጥንታዊዎቹን የጎንደር አድባራት እቴጌ ምንትዋብ የመሠረተቻትን ቁስቋም ማርያምን፣ በ1674 የተመሠረተውን ደብረ ብርሃን ሥላሴን፣ ጻድቁ አቡነ ዓምደ ብርሃን ባርከው ከመሠረቷቸው አደባባይ ኢየሱስ፣ እልፍኝ ጊዮርጊስ፣ ፊት ሚካኤል፣ መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለምና ግምጃ ቤት ማርያም በተጨማሪ ሌሎችንም ታሪካዊ አድባራት ተሳልመን የፋሲል ግንብን ጎብኝተን በግምጃ ቤት አደርን፤
👉 በጧት ተነስተን ጭሮለባ ኪዳነ ምህረትን ተሳልመን የደብሩ ካህናትና ሕዝቡ ያዘጋጁልንን ምሳ በልተን ጠላ ጠጥተን ተመራርቀን ጸሎተ ማርያም ተቀብለን መንታ በር ገብርኤል ደርሰን አደርን፤
👉 በጧት ተነስተን ከደብሩ አበው ጸሎተ ማርያም ተቀብለን የባሕታዊያን በዓት የነበረውን አቡነ አረጋዊን ተሳልመን ምጢራዊውን ራስደጀን ተራራ በ4 ምዕራፍ ወጥተን ሆጨው ደረሰን በቦታው ጸሎታችንን አደርሰን በቀንድ የሚቀዳውን እጅግ ተአምረኛ ፈዋሽ ጠበሉን ተጠምቀንና ጠጥተን ለድካመ ሥጋ ጥቂት ቴምርና ቆሎ ቀምሰን በባሕታዊያኑ መንደር አድርገን ከተጠቀሙት አበው ጸሎትና ቡራኬ ተቀብለን ጻድቁ የተሰወረበትን ዋሻ ተሳልመን በታችኛው ገዳሙ አደርን፤

👉 ከገዳሙ አርእስተ አበው ጸሎተ ማርያም ተቀብለን ጥገና ኪዳነ ምሕረትን ተሳልመን በምካና ኢየሱስና አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አብያተ ክርስቲያናት በኩል አድርገን ጭሮለባ ኪዳነ ምሕረት ገብተን አደርን፤ የደብሩ ካህናትና ምዕመናንን መስተንግዶ ለመግለጽ ቃላት የለኝም።
👉 ታሪካዊው ጨነቅ መድኃኔዓለምን ተሳልመን እጅግ ተአምረኛውን ባለ ልብስ ፈዋሽ ጸበሉን ተጠምቀን ጸሎተ ማርያም ተቀብለን ሰቋር ዋልድባ ገብተን መካነ ሕርመቷን ኪዳነ ምሕረትን፣ የገዳሙ አርእስተ አበው የማይጠፉበትን መድኃኔዓለምን የእመው መነኮሳይያትን ገዳም ቅ/ጊዮርጊስን ተሳልመን በእናቶች ገዳም ራት በማር ብርዝ በልተን አደርን።
👉 በጧት ተነስተን በአባቶች ቤተ እግዚአብሔር ከሊቀ አበው ሦስቱ በየስማችን ጸሎተ ማርያም ሰጥተውን ጸሎት አስደርጉልን ያሉንንና የቤተሰባችንን ክርስትና ስም መዝግበን ሰጥተናቸው መንገዳችንን ቀጠልን፤ እነ አባ ወ/ትንሣኤ እስከ 180 ዓመት ኖረው ለፍፃሜ የበቁበትን ማይወይኒ (ግዝግዛ) አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ተሳልመን ፈዋሽ ጸበሉን ተጠምቀን ጠጥተን ሽረ እንዳ ሥላሴ ምሳ በልተን ፈለገ አበው ደብረ በንኮን አቡነ መድኃኒነ እግዚእ እና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳምን ተሳልመን አዳራችን አክሱምጊቢ ውስጥ ሆነ፤

👉 በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ለቅዱስ ያሬድ ዜማ ከእግዚአብሔር መገለጥን ለማረጋገጥ በአፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት ከኅዳር 1-7 አማኒያን ሁሉ የገቡትን ሱባኤ ባለማቋረጥ እስካሁን ድረስ የየወሩን መጀመሪያ ሳምንት ከሌሊቱ 9:00 ጀምሮ ታቦት ወጥቶ ምሕላ ስለሚደረግ በምሕላው ተሳትፈን አክሱምን ጽዮንን፣ አርባዕቱ እንስሳን፣ በቅዱሳት ሥዕላት ያሸበረቀውን አክሱም ኢየሱስን፣ አባ ሊባኖስ ወቅት/ሩፋኤልን፣ ደብረ መዊዕ ቅ/ሚካኤልን፣ ማይኪራሕ ቅዱስ ያሬድን፣ ደብረ ቆናጽል አባ ሊቃኖስን፣ ደብረ አጥገባ አቡነ ጰንጠሌዎንና መቅደላዊት ማርያምን ተሳልመን ሊጎበኙ የሚገባቸውን ታሪካዊ መካናት ሁሉ ጎብኝተን ጸሎተ ማርያም ተቀብለን ወደ ዓድዋ አመራን፤ ደብረ አደራ አቡነ ገሪማንና ደብረ የሃ አቡነ አፍፄን ተሳልመን እንትጮ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የደብረ ዳሞ ገዳም አዲስ ሕንፃ አደርን፤
👉 በኩረ ገዳማት ደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ገዳምን ተሳልመን ገፃቸው ከሚያስፈራው ባለ አስኬማዎቹ አበው ጸሎተ ማርያምና ቡራኬ ተቀብለን ፈዋሽ ጸበሉን ተጠምቀን ገዳሙን ጎብኝተን የጻድቁ ወላጅ እናት ቅ/እድና ተጋድሎዋን ፈጽማ ያረፈችባት ቅ/ኪዳነ ምሕረትን ተሳልመን ወደ ገርዓልታ አመራን፤ መጋብ ሥላሴንና አስደናቂውን አቡነ ይምዓታ ገዳምን ተሳልመን መቐለ ጀብሩክ ቅ/ሚካኤል ገብተን አደርን።

👉 ወለደ አዕላፍ አባ ኢየሱስ ሞዓ ግሩም ተጋድሎ የፈጸሙበትንና 800 ቅዱሳንን አስተምረው በንቡረ ዕድ ማዕረግ የመረቁበትን ፯ቱ ቅዱሳን እንደ መሶብ ከፍ አድርገው ባስባረኩት ሐይቅ ቅ/እስጢፋኖስን ተሳልመን አደርን፤
👉 ወንዶቹ በቅ/እስጢፋኖስ ሴቶቹ በቅ/ኪዳነ ምሕረት ኪዳን አድርሰን ጸበሉን ተጠምቀን መንገዳችንን ቀጠልን፤ ቀይት ስንደርስ መኪና ስለተበላሸብን እዛው አድረን በማግሥቱ ደብረ ብርሃን ሥላሴን ተሳልመን ጸሎተ ማርያም ተቀብለን በ16ኛ ቀናችን አዲስ አበባ በሰላም ገባን።
የማኅበራችን ቀጣይ የንግሥ ጉዞዎች ወደ፦
1⃣ ለበዓለ ደብረ ዘይት (እኩለ ጾም) ምሁር ኢየሱስ
መነሻ መጋቢት 13 ቅዳሜ ጠዋት 11:00
መመለሻ መጋቢት 14 ከንግሥ በኋላ
የጉዞ ዋጋ፦ ምቾት ባላቸው ልዩ ባሶች 2000 ብር
በመደበኛ አገር አቋራጭ አውቶቡሶች 1600 ብር

2⃣ ምሥጢራዊው መንዝ እመጓ ቅ/ዑራኤል
👉 መነሻ መጋቢት 19 ዓርብ ከሌሊቱ 10:30 - 11:00
👉 መመለሻ መጋቢት 21
👉 የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 2800 ብር

3⃣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም
በጉዟችን ላይ ደብረ ጎል አባ በጸሎተ ሚካኤልን፣ አባ ጽጌ ድንግልን፣ በልበሊት ኢየሱስን እንሳለማለን
መነሻ መጋቢት 19 ዓርብ 11:00
መመለሻ መጋቢት 21
የጉዞ ዋጋ 4500 ብር

4⃣ ዋልድባ አብረንታንት ገዳም
👉🏿 በአክሱም ጽዮን ማርያም ስለምንሄድ የተስዓቱ ቅዱሳንን ጨምሮ በርካታ የትግራይ ገዳማትን እንሳለማለን።
👉🏿 መነሻ መጋቢት 23 ከሌሊቱ 11:00
👉🏿 መመለሻ ሚያዚያ 3
👉🏿 የጉዞ ዋጋ ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 10000 ብር

5⃣ ምሥጢራዊው መንዝ እመጓ ቅ/ዑራኤል
መነሻ መጋቢት 26 ዓርብ ከሌሊቱ 10:30 - 11:00
መመለሻ መጋቢት 28
የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 2800 ብር

6⃣ ሆሣዕናን በሆሣዕና ማርያም
👉 መነሻ ሚያዚያ 4
👉 መመለሻ ሚያዚያ 5
👉 የጉዞ ዋጋ 1500 ብር

* መነሻ ቦታ ለሁሉም ጉዞዎች፦ አራዳ ጊዮርጊስና መገናኛ

* ለበለጠ መረጃ፦
👉🏿 0901070707
👉🏿 0911289877
አዘጋጅ፦ ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለገብርኄር ወደ አስደናቂው፦
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም
በጉዟችን ላይ ደብረ ጎል አባ በጸሎተ ሚካኤልን፣ አባ ጽጌ ድንግልን፣ በልበሊት ኢየሱስን እንሳለማለን።
መቅደሱ ብርሃን እንዲያስገባ ቅዱስ ሚካኤል በሰይፉ ስለሸነቆረው ክፍት ቢሆንም ዝናብ ግን አያስገባም።
መነሻ መጋቢት 19 ዓርብ 11:00
መመለሻ መጋቢት 21
የጉዞ ዋጋ 4500 ብር

እና ወደ መንዝ እመጓ ቅ/ዑራኤል
👉 መነሻ መጋቢት 19 ዓርብ ከሌሊቱ 10:30 - 11:00
👉 መመለሻ መጋቢት 21
👉 የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 2800 ብር
*******

ቢቀሩ የሚቆጩበት የንግሥ ጉዞ ወደ
ዋልድባ አብረንታንት ገዳም
👉🏿 በአክሱም ጽዮን ማርያም ስለምንሄድ የተስዓቱ ቅዱሳንን ጨምሮ በርካታ የትግራይ ገዳማትን እንሳለማለን።
👉🏿 መነሻ መጋቢት 23 ከሌሊቱ 11:00
👉🏿 መመለሻ ሚያዚያ 3
👉🏿 የጉዞ ዋጋ ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 10000 ብር

ለኒቆድሞስ ወደ መንዝ እመጓ ቅ/ዑራኤል
መነሻ መጋቢት 26 ዓርብ ከሌሊቱ 10:30 - 11:00
መመለሻ መጋቢት 28
የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 2800 ብር

ሆሣዕናን በሆሣዕና ማርያም
👉 መነሻ ሚያዚያ 4
👉 መመለሻ ሚያዚያ 5
👉 የጉዞ ዋጋ 1500 ብር

* መነሻ ቦታ ለሁሉም ጉዞዎች፦ አራዳ ጊዮርጊስና መገናኛ

* ለበለጠ መረጃ፦
👉🏿 0901070707
👉🏿 0911289877
አዘጋጅ፦ ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቢቀሩ የሚቆጩበት የንግሥ ጉዞ ወደ
ዋልድባ አብረንታንት ገዳም
👉🏿 በአክሱም ጽዮን ማርያም ስለምንሄድ የተስዓቱ ቅዱሳንን ጨምሮ በርካታ የትግራይ ገዳማትን እንሳለማለን።
👉🏿 መነሻ መጋቢት 23 ከሌሊቱ 11:00
👉🏿 መመለሻ ሚያዚያ 3
👉🏿 የጉዞ ዋጋ ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 10000 ብር

ለኒቆድሞስ ወደ መንዝ እመጓ ቅ/ዑራኤል
መነሻ መጋቢት 26 ዓርብ ከሌሊቱ 10:30 - 11:00
መመለሻ መጋቢት 28
የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 2800 ብር

ሆሣዕናን በሆሣዕና ማርያም
👉 መነሻ ሚያዚያ 4
👉 መመለሻ ሚያዚያ 5
👉 የጉዞ ዋጋ 1500 ብር

✥ መነሻ ቦታ ለሁሉም ጉዞዎች፦ አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ እና መገናኛ

• የጉዞ ትኬት ለመቁረጥ (ለምዝገባ)፦
👉 ባላችሁበት አካባቢ በሚከተሉት የመ/ር አንተነህ ውብሸት የባንክ አካውንቶች በካሽ (በሞባይል ባንኪንግ) አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
☞ የኢት.ንግድ ባንክ 1000099794899
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
Swift Code: ABYSETAA
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ ዓባይ ባንክ 1931019728607012
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0911289877

★ ውስን ወንበሮች ብቻ ስለቀሩን ቅዱሳት መካናትን መሳለም የምትፈልጉ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሁሉ ቀድማችሁ ደውሉልንና አብረን ተጉዘን በረከት እናግኝ!
* ለበለጠ መረጃ፦
👉🏿 0901070707
👉🏿 0911289877
ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

❖ የገዳማትን የቃልኪዳን በረከት እንዲያገኙ ለሌሎች ምክንያት መሆንም ልዩ በረከት ያሰጣልና ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።
የሰሙነ_ሕማማት_ዕለታት_ስያሜዎች

ሰኞ፤ መርገመ በለስና አንጽሖተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት
ማክሰኞ፤ የጥያቄና የትምህርት ቀን።
ረቡዕ፤ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን።
ሐሙስ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ እግር፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ።
ዐርብ፤ ስቅለት
† ቅዳሜ፦ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ፡፡

በሰሙነ_ሕማማት_የሚፈጸሙ_ሥርዓቶች

፩. ስግደት፦
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል። እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ በተገረፈው ግርፋት ልክ በዚህ ሳምንት በጠቅላላው 6666 ስግደት ይሰገዳል።

፪. ጸሎት፦
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ። እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት፣ 3 ሰዓት፣ 6 ሰዓት፣ 9 ሰዓት፣ 11 ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት፣ 3 ሰዓት፣ 6 ሰዓት፣ 9 ሰዓት፣ 11 ሰዓት ናቸው።
በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።

፫. ጾም፦
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ 1፡00 እንድንጾም ይኸውም ቆሎ፣ ዳቦ፣ ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

፬. አለመሳሳም፦
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ ፫፥ ፲፫ ማቴ ፲፥ ፴፰ ማቴ ፳፮፥ ፳፱

፭. አክፍሎት፦
እመቤታችን ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።

፮. ጉልባን፦
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።

፯. ጥብጠባ፦
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።

፰. ቄጠማ፦
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።
#ዝክረ_ኒቅያ ከሙሉ በክፍሉ ነገሩ ይሄው ነው።
(ከታች መምህሬ የኔታ ኃይለ ማርያም ገልጸውታል)

#4ቱ_የዝክረ_ኒቅያ_ሕፀፆች
”የምነቅፍብህም ነገር አለኝ።” ራእ ፪፥ ፬
★ ዝክረ ኒቅያ መልካም የሆኑ ነገሮች እንደነበሩት ሕፀፆችም አሉት ለቀጣይ እንዳይደገሙ። እንዲህ ቃኝተናቸዋል፦
👉 በመጀመሪያ አመራርጡ የቤቱ አሸርጋጆችን ማዕከል ያደረገ ነው።
👉 ፪ኛ፦ ምንም ሴራው የማይገባቸውን መሠረት ያደረገ ነው።
👉 ፫ኛ፦ ትቂት ጉዳዩ የገባቸውን እጅ ሲያወጡ እንኳን እንዳይናገሩ አፍነው ነው የጨረሱት።
👉 ፬ኛ፦ የተወያዩበትን ሳይሆን የሚፈልጉትን እንዲነገር የተደረገበት ነው።
👉 ፭ኛ፦ በራሱ ጊዜ የጥፋት መልእክተኛ ሁኖ ከቅቡልነት የወረደውን አህጉረ ስብከት ስም መመለሻ ነው።
👉 ፮ኛ፦ የኒቅያ ጉባኤ ዓለም አቀፋዊ ነው ይሄ ግን ትግራይ ያሉ ሊቃውንትን እንኳን ያላካተተ ነው።
👉 ፯ኛ፦ የቤተ ክርስቲያንን ህልውናዊ ጉዳይ የረሳ የጳጳሳቱ የክብር መጠበቂያ ጉባኤ ነው።
👉 ፰ኛ፦ የጉባኤው ማሠሪያ የለውም። የጥፋት መሠረቱን ለመጠበቅ ቃል እንገባለን ተባብለው ነው የተበተኑት።
አንዳችም የቤተ ክርስቲያን ህልውናዊ ጉዳይ እንዳይነገር  ቁጭ ብለው ሲጠብቁት ሰነበቱ እንጂ በነጻነት ውይይት ማድረግ ያልቻለበት ጉባኤ ነው።

በተጨማሪም በጥልቅ ጉዳዮች  ውይይት እንዳይደረግባቸው ጊዜው ያጠረ ነው። በዚህ ማፋዘዣ ሥርዓቱም ድርሻ አለው ብየ አምናለሁ። በተጨማሪም “በእኔ የሥራ አስኪያጅነት ዘመን ይሄ ተደረገ...” ለማለት የቀረበም ጭምር ነው።

ለመሆኑ ሊቃውንቱ ወስነው ተግብረው የተለያዩት ምንድን ነው? ምንም! ብቻ ቤተ ክህነቱን ለመጠበቅ ቃል እንገባለን አስብለው አስምለዋቸዋል።
"ቀኖናው እንዳይሻር መጠበቅ አለባችሁ?" ሲባል ነበር። ለመሆኑ ማን ነው የሻረው? ከማንስ ነው የሚጠበቀው?
→ የገዳማቱ ውድመት፣
→ የምእመናን እልቂት፣
→ የአብነተ ተማሪዎች ጅምላ መሞት፣
→ በየገዳማቱ የንዋየ ቅድሳቱ ስርቆት፣
→ የምእመናን ረሀብ እና ስደት፣
→ በመከፋፈላችን ምክንያት የደረሰው ችግር፣
→ የትግራይ አባቶች አንድነት ጉዳይ፣... ለምንድን ነው ያልተነሣው?
★ ሊቃውንቱ ይሄ ሁሉ አይመለከታቸውም? ...
ጎበዝ መረር ደፈር ብለን ካልመከርን ምስለኔዎች በቁማችን እየቀበሩን ነው።

https://youtu.be/ke3D1UDu3UU?si=yLrizA_y8bGhWxlH
የንግሥ ጉዞ ወደ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም
👉 በየዓመቱ ግንቦት 21 ቀን የሚከበረውን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ንግሥ ምክንያት በማድረግ አንጋፋው ማኅበራችን አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ወደመሠረቷት ጥንታዊቷ ደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ቅ/ማርያም ገዳም የአዳር ጉዞ አዘጋጅቷል።
* በጉዟችን ላይ ተአምረኛዎቹ አጃና ቅዱስ ሚካኤልና ሽብሻቦ ማርያም ገዳማትን እንሳለማለን።
* የጉዞ ዋጋ ማረፊያ ቤትና መስተንግዶን ጨምሮ 1500 ብር

❖ ለበዓለ ዕርገት የንግሥ ጉዞ ወደ ምሥጢራዊው መንዝ እመጓ ቅዱስ ዑራኤል
→ መነሻ ግንቦት 19
→ መመለሻ ግንቦት 22
→ የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 3000 ብር

★ በ2ቱም ጉዞዎቻችን ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድመው ይመዝገቡ!!!
👉 ለበለጠ መረጃ፦
📞 +251901070707
📞 +251911289877
አዘጋጅ፦ ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

❖☞ ቢቀሩ የሚቆጩባቸው ሌሎች ጉዞዎቻችን፦
፩ኛ) መንዝ እመጓ ቅዱስ ዑራኤልና የመንዝ ገዳማት
→ በየ15 ቀኑ ዓርብ ቅዳሜ እሑድ

፪ኛ) ሐመር ቡስካ ጽዮን ማርያም ወአቡነ ሙሴ ጸሊም ገዳም፣ ብርብር ማርያም እስከ ኬንያና ሱዳን ድንበር ድረስ ያሉ የደቡብ ኦሞ ገዳማትና አድባራት
→ መነሻ ሰኔ 18 መመለሻ ሰኔ 27

፫ኛ) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም
→ አባ ጽጌ ማርያም፣ አባ በጸሎተ ሚካኤል፣ በልበሊት ኢየሱስ እና አቡነ መልከ ጼዴቅ ገዳማትን እንሳለማለን።
→ መነሻ ሐምሌ 4
→ መመለሻ ሐምሌ 9

፬ኛ) ጥንታዊው ማኅበረ ሥላሴ እና የምዕራብ ጎንደር ገዳማት
→ የጣና ገዳማትን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳት መካናትን የምንሳለምበት እና ታሪካዊ ቦታዎችን የምንጎበኝበት የ9 ቀናት ልዩ የንግሥ ጉዞ ነው።
→ በጉዟችን እመቤታችን በየቀኑ በጣና ቂርቆስ ገዳም እየተገለጸች የምትባርከውን ባለ ልብ ቅርጹን የጣና ሐይቅን በዘመናዊ ጀልባ እየቀዘፍን በቅዱሱ ሐይቅ ላይ የሚገኙ በርካታ ቅዱሳት መካናትን እንሳለማለን።
→ መነሻ ሐምሌ 4 መመለሻ ሐምሌ 12

፭ኛ) አሰቦት ቅድስት ሥላሴ ገዳም
[መካነ ኅቡዓን የቅዱሳን መነኃሪያ]
መነሻ ሐምሌ 6
መመለሻ ሐምሌ 8

፮ኛ) ስእለት ሰሚው ቁልቢ ቅ/ገብርኤል በሐረርና ድሬዳዋ የሚገኙ ገዳማትና አድባራትን ጨምሮ
→ መነሻ ሐምሌ 16
→ መመለሻ ሐምሌ 20
@negeretewahido

👉 #መነሻ_ቦታዎች፦ አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ፣ መስቀል አደባባይ ቅ/እስጢፋኖስ እና መገናኛ

#ለምዝገባ (ትኬት ለመቁረጥ)፦
👉 ባላችሁበት አካባቢበሚከተሉት የመምህር አንተነህ ውብሸት የባንክ አካውንቶች በካሽ (በሞባይል ባንኪንግ) አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
☞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ ዓባይ ባንክ 1931019728607012
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0911289877

→ ከሃገር ውጪ ሆናችሁ ለቤተሰቦቻችሁ መክፈል ለምትፈልጉ Swift Code: CBETETAA

❖ የዩቲዩብ ቻናላችንን « መኮሬታ Mekoreta Tube »ን በሚከተለው ሊንክ ከፍተው Subscribe, Like, Share, Comment & Copy Link በማድረግ ያግዙን☞ https://youtube.com/@mekoreta
«ዕድሜህን ይበሉበሀል።»
✍🏻 መምህር ኤፍሬም ተስፋ

#ጠላትህን_ማሳደድ

ብዙ ወንድሞችና እህቶች እንደጀብደኘነት ይቆጥሩታል ።

ብዙዎቹ ደግሞ የጀግንነታቸው ምሥጢር አድርገው ይመኩበታል።

ብዙዎቹም አይነኬ ለመምሰል የውሸት ጉራ ይነዙበታል።

ነገር ግን ጠላትን እያሳደዱ ማጥቃት የጀግንነት መገለጫ ይሆናልን?*

ጥሬ ሐቁ መራራ ስንፍና ነው።

ጠላትን በፈሊጥ መከላከል የመኖርህ ግዴታ ቢሆንም።

ጠላትን ማሳደድ ግን የአእምሮ ስንፍና ነው።

ጠላትን ስታሳድድ የምታወጣው ኀይል የምታባክነው ጊዜ የምትናደደው ንዴት አለ።

ይህን ጉልበት ከጠላትህ ለማምለጥ ብትሮጥበት እርሱ የማይደርስበህ የጠላትህ ሰማይ መሆን ትችላለህ ።

ያኔ ጠላትህ ቀና ብሎ ለማየት ይጣጣራል እንጅ ወዳንተ ድንጋይ አይወረውርም። የሚወረውረው ድንጋይ ተመልሶ ከርሱ ራስ ላይ ያርፋልና።

ሰማይን ይገረሙበታል እንጅ አይመቱትም።

በረዶውን ቢያዘንበው፣ መብረቁን ቢያጮኸው፣ ዐውሎ ነፋሱ ከሰማይ ቢመጣ ዐመቱን ሙሉ በፀሐይ ድርቅ ቢያቃጥል፣ ቀና ብለን ከማየት ውጭ የምናደርገው አንዳች ጉልበት የለንም።

ሰማይ ራሱን ያስከበረው ከፍ በማለቱ ነው።

እንደመሬት ዝቅ ቢል ኖሮ አራሹ፣ተኳሹ፣ ነጋሹ፣ እግረኛው እረኛው ዳንሰኛው ሙደኛው ደገኛው ቆለኛው ሁሉ ሲጠቀጠቀው የሚኖር መከራ ተሸካሚ ነበር።

አንተም እንደሰማይ ከፍ ለማለት ፍጠን እንጅ እንደመሬት ለመውደቅ አትታገል።

በራስህ እቅድ ተጓዝ በምቀኞችህ ትእዛዝ አትመራ።

ጠላቶችህን ስታባርር ለአድመኝነታቸው አድማ ስታከማች ለጉልበታቸው ጉልበት ስታዘጋጅ የምትውል ከሆነ ለራስህ ያለ አንዳች ጊዜ ትቀራለህ።

በደጋፊዎችህ ኀይል የምትወጣ በጠላቶችህ ኀይል የምትወርድ ጠላቶችህ በሚያጠምዱለህ የድንጋይ ውርዋሮ ሜዳ ድንጋይ ስትለቅም የምትውል ከሆነ እያስፈጸምክ ያለኸው የጠላቶችን እቅድ ነውና ከግብግባቸው ራቅ።

ነገር ግን በትንሽ እውቀተትህ ከቀኑብህ ብዙ ተምረህ አናድዳቸው ደረቅ እንጀራ ከከለከሉህ እንጀራ በወጥ ለመብላት በርትተህ ሥራ።

ለጠላት እጅ መስጠት ሀገራዊ ነውር ቢሆነም ከጠላት ጋር መታገልም ግለሰባዊ እብደት ነው።

ጠላቶችህ እንዳይጥሉህ ተጠንቀቅ እንዳያገኙህም ራቅ እንዳያጠቁህ በፈሊጥ ተከላከል።

እግር በእግር ግን አትከተል።

ሁሌም ከኋላቸው ከተከተልክ ወደፊት ማለፍ አትችልምና።

ጊዜም አትስጣቸው ያለህን ይወስዱብሀል።

እየከሰስክ ሥራ አትሠራም እየተኮስክ አታመርትም እያቆሰልክ አታነብም።

እየገደልክ አትነግድምና ለጠላቶችህ ጊዜ አትስጥ ዕድሜህን ይበሉብሀል።
የሚጣቅ ቅዱስ አማኑኤል ገዳም ታሪክ

በጎል ሰከበ ደብረ መንክራት ሚጣቅ አማኑኤል ገዳም በሰሜን ሸዋ ዞን በባ/ወ/ወ/ በዋዩ አንገት መውጊያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሚጣቅ በተባለ ስፍራ ከደ/ብርሃን ከተማ በስተ ደቡብ ምስራቅ 30 ኪ.ሜ ርቅት ላይ ይገኛል፡፡ ደብረ መንክራት ቅዱስ አማኑኤል ገዳም የተመሰረተው በአምኃ ኢየሱስ ዘመነ መንግስት ማብቂያ አካባቢ በ1760 ዓ.ም እንደሆነ ታሪክ ያስረዳል፡፡ ገዳሙን በመጀመሪያ የመሰረቱት መብዓ ፅዮን የሚባሉ አባት ሲሆኑ አካባቢውና ቤተክርስቲያኑ ከፍተኛ እውቅና ያገኘው በደጉና ሩህሩሁ የሸዋው ንጉስ ሳህለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ነው፡፡ ፅላቱን መብዓ- ፅዮን ከደብረ ዳሞ ገዳም በ1760 ዓ.ም እንዳመጡት ይነገራል፡፡

ቦታው ከባህር ጠለል በላይ በ2837 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀድሞው ዘመን ጥቅጥቅ ባለ ደን የተሸፈነ ነበር፡፡ ደኑም የኃይማኖት መሪዎችና በነዋሪዎቹ ዘልማዳዊ የትውልድ የጋራ ስምምነት ህግ ይጠበቅ እንደነበር ድርሳናት ይተርካሉ፡፡ ቤተክርስቲያኑ የተሰራበት ቦታ ድልድይ ዋሻ ይባል እንደነበርና አሁን አማኑኤል ቤተክርስቲያን ካላበት በቀኝ በኩል ከገደል ስር ይገኛል፡፡

ሚጣቅ አማኑኤል ንጉስ ሳህለ ስላሴ ትልቅ የታሪክ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በቅድመ አያታቸው ዘመነ መንግስት በመብዓ ጽዮን የተሰራው ቤተክርስቲያን በዕድሜ ብዛት ተጐሳቁሎ ስላገኙት እንደገና ለመስራት ሱባኤ ገብተው እንዲሰራ ሲፈቀድላቸው ከአፋፍ በታች መሆኑ ለማደስ ስለቸገራቸው በአሁኑ ስዓት ቤተ ልሄም አለበት ቦታ ላይ ቤተክርስቲያን ሰርተው ታቦቱን ከቀድሞው ቦታው አስመጥተው አስገብተዋል፡፡

በኋላም ንጉስ ሳህለ ስለሴ ያሰሩት ቤተክርስቲያን በእድሜ ብዛት በማርጀቱ በአዲስ እንዲሰራ ወ/ሮ ወሰንየለሽ የተባሉ ግለሰብ ለንግስት ዘውዲቱ አቤቱታ አቀረቡ ንግስቲቱ በመፍቀዳቸው ወ/ሮ ወሰንየለሽ የህንፃ ቤተክርስቲያኑን በ1913 ዓ.ም አስመሰረቱ፡፡ ይህን ቤተክርስቲያን ለማሰራት ወ/ሮ ወሰንየለሽ 16000 ማርትሬዛ ተኮናትረዋል፡፡ ቤተክርስቲያኑ ሲሰራ ለእንጨት ስራ ከመንግስት ደን ከሙገሬ ዛላና ወፍ ዋሻ ከሚባሉ ቦታዎች ዛፍ ተፈቅዷል፡፡ ከነዚህ ቦታዎች በተገኘ እንጨት የጣሪያው እንጨት አምደ ወርቁ፣ በሮቹና መስኮቶቹ ሌሎችም ቅርፃ ቅርፅ ተሰርተዋል፡፡ ጣርያውንም በከብት ቆዳ በጠፍር ተማግሮ በሳር ክዳን ተከድኖ ነበር፡፡

ህንፃ ቤትክርስቲያኑ የተገነባው በተለየ ድንጋይና በኖራ ሲሆን ግንበኞቹም ኢጣሊያኖች ነበሩ፡፡ ዋና መሃንዲሶችም ኒኮላና ኮስታ የሚባሉ ጣሊያኖች ነበሩ፡፡

የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ በድል ከተቀለበሰ በኋላ በገዳሙ የሚኖሩ አባቶች የቤተክርስቲያኑ ጣሪያ ከሳር ወደ ቆርቆሮ እንዲዛወር ለንጉስ ሳህለ ስላሴ አመልክተው ተቀይሯል፡፡ በዚሁ ቤተክርስቲያን በአገልግሎት ላይ የሚገኘው ደውል ከብር ከነሃስና ከተለያዩ ማዕድናት በማሰራት ያበረከቱት አፄ ምኒሊክ እንደሆኑ ታሪክ ያወሳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በገዳሙ ከ300 በላይ እድሜ ጠገብ ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን በሳይንሳዊ መንገድ የመመዝገብና የመጠበቅ ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

ለአብነትም 182 ዓመት ያስቆጠረ ጋን እና ሌሎች የጠፍር አልጋዎች ይጠቀሳሉ፡፡ በገዳሙ በዓመት በአማካኝ ከ10000 በላይ የእምነት ተጓዦች የሚጐርፋበት ሲሆን ይህም ለጥቅምት 28 እና ግንቦት 28 ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የሚጣቅ አማኑኤል ጠበል በአገራችን ታዋቂ ከሆኑ ፈዋሽ ጠበሎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህን ጠበል ባርከው አገልግሎት እንዲሰጥ ያደረጉት አባ ወልደ እየሱስ የሚባሉ አባት ሲሆኑ ከአባ እየሱስ ሞዓ ገዳም ከሃይቅ እስጢፋኖስ እንደመጡ ይነገራል፡፡ አባ ወልደ እየሱስ ሳህለ ስላሴና ታምር ከተደረገለት ደጃዝማች ጋር በተገናኙ ወቅት የዚችን ቦታ ክብርና ተአምር ተገልፆልኝ አማኑኤል በፍቃዱ ወደ ዚህ ቦታ እንድመጣ አድርጐኛል፡፡ አሁንም ንጉስ ሆይ ፈቃድዎ ይሁንና ቦታው ደብር መባሉ ቀርቶ ይገዳም ዘንድ እጠይቅዎታለሁ ብለዋቸው ንጉሱም ፈቃዳቸው ሆኖ ሊገደም ችሏል፡፡ መምህር አባ ወልደ እየሱስም ፀበሉን ባርከው በደዌ ቁራኛ የተያዙ ምዕመናንን በመፈወስ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ጠበል ቦታ ከተደረጉ ታምራት መካከል ዋና ዋናዎቹ ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡

• ሁለት አይናቸው የታወረ አንድ ደጅ አዝማች ፊታቸውን በውሃ በታጠቡ ወቅት አይናቸው ስለበራላቸው ለንጉስ ሳህለ ስላሴ በዚህ ውና ታጥቤ አይኔ በራ ብለው ተናግረው ለአባ ወልደ እየሱስ በመመስከር የአሁኑ ፀበል እንዲከበር ተደርጓል፡፡

• አቶ ወልደ ትንሳኤ ለማ እና እማሆይ አስካለማርያም የተባሉ ሰዎች ከካንሰር ተፈውሰዋል፡፡

• ደጀዝማች የማነ ሃሰን የተባሉ ምዕመናን ሰውነታቸው እግራቸውና እጃቸው ለመንቀሳቀስ ባለመቻሉ በአልጋ ወደ ጠበሉ እንዲመጡ ተደርጐ ድነዋል፡፡

• ወ/ሮ በቀለች ይልማ የተባሉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ቀኝ እጃቸው ፓራላይዝ ሆኖባቸው በተለያዩ የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገር ሃኪም ቤት ቢታከሙ ሳይድኑ በዚሁ ፀበል ድነዋል፡፡

• ወ/ሮ አመዘነች የተባሉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ማየት የተሳናቸው ሲሆኑ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ህክምና ቢከታተሉም መዳን ሳይችሉ ቀርተው በአማኑኤል ጠበል የዳኑ በመሆናቸው ወደ ጠበሉ የሚወስደውን አስቸጋሪ መንገድ በ92 ደረጃ በጥርብ ድንግጋይ አሰርተዋል፡፡

በአጠቃላይ በሚጣቅ አማኑኤል በርካታ ታሪኮች የተተገበሩ ሲሆኑ የጥቅምት አማኑኤል በዓል አከባበር ጅማሮ ልዩ ግርምትን ያጭራል፡፡ በንጉስ ሳህለ ስላሴ አማካይነት አዲሱ ቤትክርስትያን በገባ በአምስተኛው ወር ጥቅምት 27 ቀን በ1827 ዓ.ም ብዛቱ ከወትሮው የተለየ የፀሐይ ብርሃንን መጋረድ የቻለ የአንበጣ መንጋ መላ ሃገራቱን ሸፈነ፡፡ ንጉስ ሳህለ ስላሴም በተፈጠረው ክስተት በማዘን ለቅዱስ አማኑኤል ስእለት በማድረግ ከወትሮው ልማዳቸው በመለየት ከዙፋናቸውም በመውረድና ልብስ መንግስታቸውን በማውለቅ አመድ ነስንሰው ማቅ ለብሰው መዝሙረ ዳዊት እየደገሙ ፀልየዋል፡፡

በጥቅምት 27 ለጥቅምት 28 አጥቢያ ሌሊቱን ሰፍሮ ያደረው የአንበጣው መንጋ ከአደረበት ከመላው ኢትዮጱያ መሬት ለቆ በመሻገር የመን አደረ ይባላል፡፡ በልማድ አንበጣ በቀን እንጂ በሌሊት ሄዶ አያውቅም፡፡ ሆኖም መንጋው በሌሊት ከመሬት ለቆ በንፋስ ኃይል እየተገፋ ወደ ላይ ከወጣ በኋላ ጐህ ሲቀድ ለአይን አልታየም፡፡ አንበጣው ወዴት እንደሄደ ሲጠየቅ የነበረውም ህዝብ "መጠቀ" ወጣ ወይም ከሃገራችን ወጣ የሚል መልስ በማግኘቱ ምክንያት "በመጠቀ" ምትክ ሚጣቅ ተብሎ አካባቢው ተሰይሟል፡፡

ምንጭ፡- የባሶና ወራና ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት
መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ምሥጢራዊው መንዝ እመጓ ቅዱስ ዑራኤል
* መነሻ ሰኔ 6
* መመለሻ ሰኔ 8
* የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 3000 ብር
* ለበለጠ መረጃ፦ 0901070707 / 0911289877

☞ የቦታው ቃልኪዳን
ጌታችን ለቅዱስ ዑራኤል፦ "አስቀድሜ በታላቁ ዐምደ ወርቅ ስሙን ያልጻፍኩትን ሰው ይህንን ደጅ አላስረግጠውም! ይህንን ቅዱስ ቦታ የረገጠና ያየ ትውልደ ዘሩን እባርከዋለሁ እምረዋለሁም፤ የጠየቀውን የሀሳቡን እሰጠዋለሁ።" ብሎ ቃል እንደገባበት ልብ ይሏል!

• በጉዟችን የምንሳለማቸው ቅዱሳት መካናት፦
→ ታሪካዊው ዳግማዊ ቤተልሔም አፍሮ አይገባም መድኃኔዓለም ወአቡነ ዘርዓ ብሩክ ገዳም፣
→ ምሥጢራዊው እመጓ ቅ/ዑራኤል፤
→ ጻድቃኔ ማርያም፤
→ ዘብር ቅ/ገብርኤል፤
→ ስዕለት ሰሚዋ ቀጭን አምባ ምስዓለ ማርያም፣
→ እመ እጓል ቅ/እግዚአብሔር አብ፣
→ እመቤታችን በስደቷ ጊዜ በኪደተ እግሯ የባረከቺው የኅቡዓን በዓት ደብረ ክሊና /ገሊላ፣
→ ቅ/ዑራኤል ደመ መለኮትን ለዓለም ሁሉ የረጨበት ብርሃናዊው ቅዱስ ጽዋ የተቀመጠበትና ቅዱስ መስቀሉ ወደ ግሸን ሲሄድ ለ14 ቀናት ያረፈበት ደብረ ቆጵሮስ፤
→ ታሪካዊው ሰላድንጋይ ቅ/ማርቆስ፣

★ ወደዚህ ቅዱስ ስፍራ ታላቅ የበረከት ጉዞ ተዘጋጅቷል፤ መኪናው ሊሞላ ጥቂት ወንበሮች ብቻ ናቸው የቀሩን።
* መነሻ ሰኔ 6 ከሌሊቱ 11:00
* መመለሻ ሰኔ 8
* የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 3000 ብር

* ለበለጠ መረጃ፦
📞 0901070707
📞 0911289877
#ማኅበረ_ቅዱስ_ፊልጶስ_ወአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ
መነሻ ቦታዎች፦ አራዳ ጊዮርጊስ፣ መገናኛ እና ጣፎ አደባባይ

• የጉዞ ትኬት ለመቁረጥ (ለምዝገባ)፦
👉 ባላችሁበት አካባቢ በሚከተሉት የመ/ር አንተነህ ውብሸት የባንክ አካውንቶች በካሽ (በሞባይል ባንኪንግ) አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
☞ የኢት.ንግድ ባንክ 1000099794899
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
Swift Code: ABYSETAA
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ ዓባይ ባንክ 1931019728607012
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0911289877
የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሆይ፦ ጥንታዊ ቅዱሳት መካናትን እና አስደናቂ ታሪካዊ ቦታዎችን ለምዕመናን የማስተዋውቅበትን የTiktok አካውንት ለማዘጋት Report ስላረጉብኝ
👉🏾 Repost, Copy Link & Share አድርጉልኝ

https://vm.tiktok.com/ZMSDtDGAe/
የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሆይ፦ ጥንታዊ ቅዱሳት መካናትን እና አስደናቂ ታሪካዊ ቦታዎችን ለምዕመናን የማስተዋውቅበትን የTiktok አካውንት ለማዘጋት Report ስላረጉብኝ
👉🏾 Repost, Copy Link & Share አድርጉልኝ

https://www.tiktok.com/@betewali/video/7514320321965542661?_r=1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ምሥጢራዊው መንዝ እመጓ ቅዱስ ዑራኤል
* መነሻ ሰኔ 6
* መመለሻ ሰኔ 8
* የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 3000 ብር
* ለበለጠ መረጃ፦ 0901070707 / 0911289877

☞ የቦታው ቃልኪዳን
ጌታችን ለቅዱስ ዑራኤል፦ "አስቀድሜ በታላቁ ዐምደ ወርቅ ስሙን ያልጻፍኩትን ሰው ይህንን ደጅ አላስረግጠውም! ይህንን ቅዱስ ቦታ የረገጠና ያየ ትውልደ ዘሩን እባርከዋለሁ እምረዋለሁም፤ የጠየቀውን የሀሳቡን እሰጠዋለሁ።" ብሎ ቃል እንደገባበት ልብ ይሏል!

• መነሻ ሰኔ 6 ዓርብ ከሌሊቱ፦
10፡30 አራዳ ጊዮርጊስ፣
11፡00 መገናኛ ማራቶን ሕንፃ፣
12፡00 ጣፎ አደባባይ

• መኪናችን ሊሞላ የቀሩን ጥቂት ወንበሮች ብቻ ናቸው።

• የጉዞ ትኬት ለመቁረጥ (ለምዝገባ)፦
👉 ባላችሁበት አካባቢ በሚከተሉት የመ/ር አንተነህ ውብሸት የባንክ አካውንቶች በካሽ (በሞባይል ባንኪንግ) አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
☞ የኢት.ንግድ ባንክ 1000099794899
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
Swift Code: ABYSETAA
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ ዓባይ ባንክ 1931019728607012
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0911289877
2025/06/11 09:11:03
Back to Top
HTML Embed Code: