Telegram Web
ማስታወቂያ!


(መስከረም 28/2018 ዓ.ም)


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
27👍8👎3👏1
የቀጠለ….

ማስታወቂያ!


(መስከረም 28/2018 ዓ.ም)


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
57👍10👎3
የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት በትምህርት ተቋማት ድጋፍና ክትትል ለሚያካሂዱ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጠ፡፡

(መስከረም 28/2018 ዓ.ም) ድጋፍና ክትትሉ በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶችና በተመረጡ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአንደኛ ሩብ አመት በመምህራን ልማት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ የሚካሄድ ሲሆን በዛሬው እለት ድጋፍና ክትትሉን ለሚያካሂዱ የቢሮ ሱፐርቫይዘሮችና ለክፍለከተማ የመምህራን ልማት ባለሙያዎች አረንቴሽን ተሰቱዋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ ድጋፍና ክትትሉ በዋናነት በ2018 ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት በክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እና በተመረጡ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመምህራን ልማት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት አድርጎ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው በትምህርት ቤቶች የመምህራን ምደባን ጨምሮ የእቅድ ዝግጅትና አተገባበር ምንደረጃ ላይ እንደሚገኝ በቼክሊስቱ መካተቱን አስታውቀዋል፡፡


ዳይሬክተሩ አያይዘውም ቢሮው ከ2017 ዓ.ም የክረምት ወቅት ጀምሮ በርካታ መምህራንን በዝውውርና በቅጥር በየትምህርት ቤቱ ሲመድብ መቆየቱን በማስታወስ መምህራኑ በተቋማቱ በአግባቡ መመደባቸውን የማረጋገጥ ስራ እንደመሰራ ጠቁመው የድጋፍና ክትትሉን ግብረመልስ መሰረት በማድረግ ፍረጃ ተሰርቶ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንደሚደረግ አመላክተዋል፡፡


የዳይሬክቶሬቱ የመምህራን ልማት ባለሙያ ወይዘሮ ፍሬህይወት አሰፋ በበኩላቸው የቢሮው ሱፐርቫይዘሮች በክፍለከተማ ትምህርትጽህፈት ቤቶች እንዲሁም የክፍለከተማ የመምህራን ልማት ባለሙያዎች ደግሞ በትምህርት ቤቶች ድጋፍና ክትትሉን የሚያካሂዱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
50
2025/10/15 05:50:50
Back to Top
HTML Embed Code: