Telegram Web
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጀነራል ካውንስል አባላት የ2018 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገመገሙ::


(መስከረም 28/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጀነራል ካውንስል አባላት የ2018 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት የቁልፍና አበይት ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ የጋራ ውይይት አካሂደዋል::


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ ቀደም ሲል በየሥራ ክፍሉ ፣ በየዘርፉና በስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ግምገማ የተካሄደ መሆኑን ገልፀው ሪፖርቱ የዝግጅት ምዕራፍ ስራው በተቀመጠው እቅድ መሰረት በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑን ያሳያል ብለዋል::


እቅድ አፈፃፀም ግምገማዎች ለቀጣይ ሥራ ግብዓት የሚሆኑ ነጥቦች የምናገኝበት ነው ያሉት ቢሮ ኃላፊው በግምገማችን መሰረት ለላቀ ውጤታማነት ተናቦ መስራት ይገባል ብለዋል::


አክለውም በጋራ ውይይቱ የተነሱ ሀሳቦች ተካተው በቀጣይ የቢሮው ጠቅላላ ሰራተኞች በሚገኙበት ለውይይት የሚቀርብ መሆኑን ተናግረዋል::


በውይይቱ የቢሮው ጠቅላላ ካውንስል አባላት የተገኙ ሲሆን የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ በሩብ አመቱ የተከናወኑ ቁልፍና አበይት ተግባራት እቅድ አፈፃፀም እንዲሁም ሥራዎቹ ሲከናወኑ የነበሩ ጥንካሬዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎችን የያዘ የሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
57👏4👍3
በ25/75 ፕሮግራም የተደራጁ ቤት ፈላጊ መምህራንን ወደ ስራ ለማስገባት እንዲቻል የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ እስካሁን ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።


(መስከረም 29/2018 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላትን ጨምሮ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ፣ የመሬት አስተዳደር ቢሮ እና የህብረት ስራ ኮሚሽን አመራሮች እንዲሁም የመምህራን ማህበር ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የቴክኒክ ኮሚቴው የመምህራንን አቅም ታሳቢ በማድረግ በቀረቡ የዲዛይን አማራጮች ላይ ቤት ለመስራት በማህበር የተደራጁ መምህራን በፍጥነት ወደ ግንባታ እንዲገቡ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል። በስራው ላይም የግንዛቤ ማስፈፀሚያ ስራዎች መስራት እደሚገባ ገልፀዋል። እንዲሁም የመደራጀት ፍላጎት እያላቸው ያልተደራጅ መምህራን በፍጥነት መደራጀት እደሚገባቸው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።


የቤት ባለቤት ለመሆን በማህበር የተደራጅ መምህራን በማህበራቸው የመረጣቸው የማህበሩ ኮሚቴዎች ቶሎ ወደ ቤት ግንባታው ለመግባት እንዲቻል በትኩረት መሰራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።



ሀላፊው አክለውም ወደ ግንባታ መግባት እንዲቻል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተሰጣቸው ኃላፊነት መሰረት በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
50👍10🙏7🏆3🤝3🆒3👎2🥰1👏1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከስፕላሽ ኢንተርናሽናል ጋር ውይይት አካሄደ፡፡


(መስከረም 29/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከስፕላሽ ኢንተርናሽናል ከመጡ ልኡካን ቡድን አባላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ ላይ እንዳሉት የትምህርት ጥራትና ምቹ የመማሪያ አካባቢን ለመፍጠር ቢሮው እያከናወነ ያለውን ስራ የሚደግፍ በርካታ ስራዎች በስፕላሽ ኢንተርናሽናል በኩል ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡


በውይይቱ ቢሮው ከስፕላሽ ኢንተርናሽናል ጋር በጋራ ሲሰሩ የቆዩ ስራዎች ላይ ግምገማ ያካሄደ ሲሆን ቀጣይ ስራዎችን በጋራ ለመፈጸም የሚያስችሉ ዋና ዋና ተግባራት ላይ የጋራ ውይይት አካሂደዋል፡፡



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
22
2025/10/15 18:54:35
Back to Top
HTML Embed Code: