Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/tgoop/post.php on line 37

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/xobya/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/tgoop/post.php on line 50
ኢት-ዮጵ@xobya P.1186
XOBYA Telegram 1186
ሰባት ቍጥር እና ጥንተ ተፈጥሮ

ሰው ራሱ 7 ቁጥር ነው፡፡ ጥንታውያን የኢትዮጵያ ተመራማሪና ተፈላሳፊ ሊቃውንት፣ የጥናትና የምርምር ማዕቀፋቸው የሚያተኩረው ሰው ላይ ነበር፡፡ አንድን መንጋ ንብ ለመያዝ እያንዳንዱ ሠራተኛ ንብ ላይ መልፋት ሳይኾን
አዋጪው ብልሀት፣ አውራውን መያዝ ነው የሚለው ንጽጽር፣ ሰው ከተሠራ ሌላውን ማለትም መንፈሳዊውንና ዓለማዊውን ነገር ኹሉ ሰው ራሱ ይሠረዋል፤ ከሚል መነሻነት እንደኾነ ብዙ ምሁራን ይስማማሉ፡፡ ‹ያልተገነባ ጭንቅላት የተገነባ ከተማን ያፈርሳል!›› እንዲሉ ባልተሠራ ሰው መኃል ሕንጻ ቢገነባ፤ ባቢሎን ቢሠራ፣ መንገድ ቢጥመለመል፣ ሀገር በሚመኝዋት ልክ ካርታ ላይ ብትሣል… የተሳለችበትን የካርታ ወረቀት ኾና ትቀራለች፡፡ ሕግ ቢረቀቅ፣ ለኅትመት የዋለውን ወረቀት ያክል ዋጋ እንኳን ሳይኖረው የአቧራ መደበቻ ኾኖ ይቀራል… ወዘተ. ወዘተ. በሚል መነሻነት የሰው ልጅ ግንባታ ላይ ለፍተዋል፡፡በመልካም ሥነ ምግባር የተገነባ ሰው፣ እንኳንስ የተገነባ ሀገር አግኝቶ ይቅርና እንደ ሕዝበ እስራኤል የተበታተነች ሀገር
ቢያስረክቡትም መልሶ መገንባት ይችላል፡፡
‹‹እስመ ኁልቈ ፯ቱ በኀበ ዕብራውያን ፍጹም ውእቱ፡፡›› ሰው ማለት በዕብራውያን ዘንድ ሰባት/ሳብእ ፍጹም ቁጥር ማለት ነው፡፡›› እንዲል መጽሐፈ አቡሻኽር ፡፡ሰው፣ ሰው የሚሆነው የሰባቱ ድምር ውጤት ማለትም አራቱ ባሕርያተ ሥጋና ሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ ያሉበት ሲኾን ነው፡፡
ሰው ባሕርያተ ሥጋው ሲያሰንፈው ባሕርያተ ነፍሱ ያነቃዋል፡፡ በሥጋው ይተኛል፤ በነፍሱ ደግሞ ይነቃል፡፡ ሥጋው ዕረፍትን ሲይሻ ነፍሱ ትጋትን ታለብሰዋለች፤ ታጎናጽፈዋለችም፡፡ በዚህ ምክንያት ተቃራኒ ነገሮች ሲፈራረቁበት የሚኖር ፍጡር ኾኖ እናገኘዋል፡፡ ለዚህ ነው እስስታዊ ፀባይ ያላቸውን ሰዎች “አንዴ ሰው አንዴ
አፈር ያደርገዋል” የምንላቸው፡፡ ይህ ወደ ተለዋዋጭ የሰዎችን ጠባይ ለመግለጥ
የምንጠቀምበት አባባል ነውና የሰውን ልጅ ከግብራቱ መካከል አንዱ የኾነውን
ጠባዩን ያሳየናል፡፡ አንድን ሰው “እንዴት እንደዚህ ይለኛል!? እንዴት እንደዚህ ያደርጋል!?” የምንለው ይኖራል፡፡ ሊያሸማግለን የሚሞክር ሰው ደግሞ፥ ‹መቼስ ሰው አይደል!? ሰው እኮ ደካማ ነው፤ ሥጋ ለባሽ ነው፡፡›› ይለናል፡፡ሥጋ
ለባሽ ነው ሲለን፣ ሥጋ የለበሰው ምንድነው? ስንል ነፍስ የሚል መልስ ይሰጠናል፡፡ ለዚህ ነው ሰው ነፍስና ሥጋ ነው፡፡ ሥጋው አራት ባሕርያት ሲኖሩት ነፍሱ ደግሞ ሦስት ባሕርያት ይዘው በድምሩ ሰባቱ ባሕርያት ናቸው ሰው ያደረጉት፡፡ በመኾኑም ሰው ሰባት ቍጥር ነው፤ ፍጹም ሰባት ነው የሚለውን የዕብራውያኑን አባባል መሠረት አድርጎ መጽሐፈ አቡሻኽር የተነተነው፡፡ [ሰባት ቁጥር እና ሕይወት ይባቤ አዳነ ገጽ -72]

tgoop.com/xobya/1186
Create:
Last Update:

BY ኢት-ዮጵ

Share with your friend now:
tgoop.com/xobya/1186

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

A vandalised bank during the 2019 protest. File photo: May James/HKFP. Add the logo from your device. Adjust the visible area of your image. Congratulations! Now your Telegram channel has a face Click “Save”.! To upload a logo, click the Menu icon and select “Manage Channel.” In a new window, hit the Camera icon. Find your optimal posting schedule and stick to it. The peak posting times include 8 am, 6 pm, and 8 pm on social media. Try to publish serious stuff in the morning and leave less demanding content later in the day. “[The defendant] could not shift his criminal liability,” Hui said.
from us

Telegram ኢት-ዮጵ
FROM American