Telegram Web
🌾አብሳሪ ሁን!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿علّموا ويسّروا ولا تعسّروا، وبشّروا ولا تنفّروا﴾

“አስተምሩ፣ አግራሩ፣ አታወሳስቡ፣ አበስሩ፣ አታስደንብሩ።”
@ychanut
🌾አልሃምዱሊላህ❤️

ከ464 የግፍ ቀናት በኃላ የጋዛ ንጹሀን ሰላማዊ ሌሊትን በአላህ ፍቃድ ዛሬ ምሽት ያሳልፋሉ። ሰማዕቶቻችሁን አላህ ይቀበል፣ ቅዋችሁንም የበለጠ ኃያል ያድርገው..!
@ychanut
🌾ነቲን ያሆ 2023

" ሐ/ማ*ስ ከዚህ በኋላ ጋዛ ውስጥ ህልውና የለውም።"

ዘንድሮ 2025 ያው ምላስ

"እኛ የቀረበውን ሰነድ ተስማምተን እየጠበቅን ያለነው ሐ/ማ*ስን ነው።"

አቡ/ዑበይዳ ገና ያኔ ከ O⁷ 2023 ያስቀመጥንላችሁን መስፈርት ተከትላችሁ የማትደራደሩ ከሆነ በጉልበታችሁ ትንበረከኳታላችሁ ብሎ ነበር።

ነስር ወይም ድል ማውደም ከሆነ ወራሪዋ አሸንፋለለች። ድል ማለት ጠላትን መፈናፈኛ ማሳጣትና ፍልሚያውን ማሸነፍ ከሆነ ግን ወራሪዋ ጎምዛዛ ሽንፈትን ተጎንጭታለች።

سلام عليكم بما صبرتم
@ychanut
🌾 የውስጡን መግለፅ አቅቶት ያ ረቢ ብሎ ባለቀሰ ሁሉ ላይ የአላህ እዝነት ይስፈንበት ።
@ychanut
🌾"... ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ::"
(አልኢምራን:102)
@ychanut
🌾ድክመትህን አላህ ፊት ብቻ ግለጠው። ዓለም ጉልበትህን ብቻ ይመልከት!…

ማንም ድክመትህን እንዳያይ! በመስታወት የሚያዩህ ዓይኖችህ እንኳን የጨፈገገና የተከፋ ፊትህን አይመልከቱ!

ደስታህ ሰዎች በሚዘረጉልህ የእዝነት እጅ ወይም በሚያሳዩህ ፊት ላይ አይቋጠር!…

የሰዎች እገዛም ሆነ ጫና ደስታህን ከፍም ሆነ ዝቅ አያድርጉብህ! የሰዎች መልካም ትድድር ተጨማሪ ነገር ሆኖ የደስታህና የእረፍትህ ምንጭ ቀልብህ ይሁን!
ህይወት ለደካሞች ጠባብ ናት!
@ychanut
🌾በዉስጡ መቅረት እንደማትችሉ እያወቃችሁ የሰዉን ልብ አታጥምዱ፡፡ ሰዉን ሳትፈልጉም የፈለጋችሁ አትምሰሉ፡፡ ጓዝህን ጠቅልለህ እንደምትሄድ እያወቅክ ሰው ዉስጥህ ገብቶ እስኪደላደል ድረስ አታመቻች፡፡  ሆነብላችሁ ቅርበታችሁን ከፍ ካደረጋችሁ በኋላ ኡ .. እኔኮ እንደዚያ አላሰብኩም ማለት ላግጣ ነው፡፡ ወድቆ አንሳኝ ያለህን የተዘረጋን እጅ መመለስ ከባድ ነው፡፡
ሆነብላችሁ የሰው ልብ እንዲንጠለጠልባችሁ አታድርጉ፡፡ በሌሎች ስሜት መቀለድ አቁሙ፡፡ ሰው ሲያለቅስ አትሳቁ፡፡ ሰው እያመመው አትዝናኑ፡፡ በሰው ስቃይ አትደሰቱ፡፡
የሰዉን የመጀመርያ ኒያ እና ሙሉ የዉስጥ ሀሳቡን አላህ ያውቃል፡፡ እንደኒያችሁም ይሠጣችኋል፡፡ ዛሬ የሠራችሁት በደል ነገ ዞሮ እንደሚመጣ አትጠራጠሩ፡፡ ያኔ በናንተ ሲደርስ ብቻ ህመሙ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ይገባችኋል፡፡
@ychanut
🌾የሙናፊቅን ትርጉም ለማወቅ እሩቅ አትሂድ። ሙናፊቅ ማለት ሰው መሃል የሚያወድስህ ዞር ሲል ደግሞ የሚያንኳስስህ ሁለት መልክ ያለው ነው።
@ychanut
🌾ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿وَاللَّهِ لَوْ تَعْلَمُونَ مَا أَعْلَمُ لَضَحِكْتُمْ قَلِيلًا وَلَبَكَيْتُمْ كَثِيرًا﴾

“ወላሂ! እኔ ማውቀውን ብታውቁ ኖሮ፣ ጥቂት ስቃችሁ ብዙ ባለቀሳችሁ ነበር።”
@ychanut
🌾የቱንም ያህል ውሃ ቢጠማህ መጠየቅ የሌለብህ ሰዎች አሉ። ምክንያቱም...
@ychanut
🌾ለሰው ብላችሁ ምንም ነገር አታድርጉ፣ ሁሉንም ነገር ታጣላችሁ።
@ychanut
🌾ለወንድምህ ዱዓእ አድርግለት!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿دُعاءُ الأخِ لأخِيهِ بِظَهرِ الغيْبِ لا يُرَدُّ﴾

“ወንድም ለወንድሙ በሌለበት የሚያደርገው ዱዓ አይመለስም። (ተቀባይነት አለው)።” በዱኣችሁ🙏
@ychanut
🌾አንድ የ ሴንጋፑር ዜጋን "እኛ ኢትዬጵያዊያን የ3ሺ አመት የነጻነት ታሪክ አለን" ብትለውና ቢያይህ ሊታመምብህ ይችላል። እነሱ ነጻ የወጡት እንደፈረንጆቹ በ1960 ነው። የሰሩት ግን ከ3 ሺ አመት በላይ የሆነን ነገር ነው። ወዳጄ እኛ ገና ውግያ ላይ፣ ህጻናትን ደፍሮ መግደል ላይ፣ ሀኪምን የሚያህል ነገር የጥይት ኢላማ ማድረግ ላይ ነን! እስኪ ስለ ሴንጋፑር እያነበብን!
@ychanut
🌾የአላህ ዉዴታ ያሳሰበው አንድ ደረሴ "ሸይኻችን ሆይ አላህ ከሚወዳቸው መካከል መሆኔን እንዴት ላውቅ እችላለሁ?" አላቸው።

"ልጄ ባይወድህማ ኖሮ ስለ ዉዴታው አያሳስብህም ነበር።" አሉት።

ሰላማችሁ ይብዛ
@ychanut
🌾የጊዜ ጉዳይ እንጂ አላህ ዘንድ ጉዳዩ አልቆ ተወስኖ ሊሰጠን የተዘጋጀ መልካም ነገር አለ አብሽሩ
@ychanut
🌾ህመምን መደበቅ ጥበብ ነው። ምን ልል ፈልጌ መሰላችሁ ሁሉም ጋር ጥበብ አለ ግና አብሽሩ🙏
@ychanut
🌾ማንኛዉም ሪዝቅ ከቆየባችሁ ኢስቲግፋር አብዙ ተብሏል።
@ychanut
🌾የቂያም ቀን እጅግ ከሚያሳዝኑ ነገሮች አንዱ በጣም ለምትወደው ሰው አንዲት ሐሰና መስጠት አትችልም። ነገር ግን ጠልተኸው ላማኸውና ለበደልከው ሰው መልካም ሥራህን(ሀሰናህን) አሳልፈህ ትሰጣለህ አልያም ወንጀሉን ትሸከማለህ ።
@ychanut
🌾ሰዎች ተስፋ ሲቆርጡ የሚመርጡህ አይነት ሰው አትሁን!
@ychanut
🌾አላህን ያገኘ ምን አጣ ? አላህን ያጣስ ምን አገኘ ? ምንም
@ychanut
2025/02/25 12:00:19
Back to Top
HTML Embed Code: