tgoop.com/yeabderiyderesoch/3364
Last Update:
#ገንዘብና_ጀነት/#ጀነትና_ገንዘብ
ዘመኑ በኑሮ ውድነት ህዝቡን እያተረማመሰ ያለ ቢሆንም፤ በሌላ በኩል እራስን፣ እምነትን፣ ባህልን፣ ወግን፣ ሃገርን በመሸጥ(በመለወጥ) ተቆጥሮ የማያልቅ ገንዘብ ያፍሳሉ። አንዱ ወገን ቁርስ ላይ በተመገበው ወደ መኝታው ሲያመራ ሌላኛው ገንዘብን ተንተርሶ ይተኛል። በመሃለቸው ያለው ልዩነት መስፋት የሚያስከትለው የኑሮ ግሽፈት ቀላል ሚባል አይደለም።
አሁን ላይ ጀነት በገንዘብ እየተለወጠ ነው ማለት የምንችለበት ሁኔታዎች ላይ ነን ብንል የሚቃወም ያለ አይመስለኝም። ብዙ ነገሮችም ይህንን እውነታ ያረጋግጣሉም።
አንድ ስራ ሲጀመር ግቡ ገንዘብ ማግኘት ከሆነና ገንዘብን ከጀነት ካስቀደመ፤ ጀነትን በገንዘብ ይለውጠዋል፤ ነገር ግን ከገንዘብ ጀነትን ካስቀደመ ባንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ የሚባለውን ተግባራዊ ያደርጋል። በነዚህ ሁለት ጽንሰ ሃሳቦች መካከል ያለው ለውጥ ብዙም ቦታ ላንሰጠው እንችላለን ነገር ግን በውጤቱ ላይ የሚያሳድረው ተጽኖ የገዘፈ ነው። ጀነትን አልሞ የተነሳና ገንዘብን ኢላማው አድርጎ የተንቀሳቀሰ ሰው ጋር አንድ አድርገን ልንወስዳቸው ይቅርና ባንድ ሜዳ ማሰለፍኳ የማይሆን ነገር ነው።
ገንዘብ ወደ ጀነት የሚወስደን ቁሳዊ ነገር ነው እንጂ ጀነት ለመግባት መስፈርት አይደለም። ጀነትን አስበህ የምትንቀሳቀስ ከሆነ ግን ትርፍህ የጎላ ነው። ስራው አድካሚ ቢሆንም ህልምህ ጀነት ነውና ለድካምህ ቦታ ትነፍገዋለህ፣ ተስፋህን የሚያጨልም ነገር ቢያጋጥምህም ተስፋ አትቆርጥም፣ ወኔህ አይሟሽሽም። ነገር ግን ግብህ ገንዘብ ከሆነ በብልጭልጭ አለም በመታለል አኼራን በመርሳት ከሸሪዓ ውጪ በሆኑ ተግባራት ላይ እንድትሰማራ ያስገድድሃል።
ስለሆነም ህይወትህን በምን መልክ መምራት እንደሚገባህ ለአለም ብርሃን ከሆኑትና ከከዋክብቶቹ የህይወት አቅጣጫ መውሰድ ይኖርብሃል። ገንዘብን ሳይሆን ጀነትን ማስቀደም ብልህነት ነው፤ ከዚህ ባሻገር የማይተካ ሚና እንዳለውም ልትገነዘብ ግድ ይላል።
አኼራህን ከሚያስረሳ፣ አላህ ፊት ከሚያዋርድህ፣ የአላህን ህግጋት ከሚያስጥስህ፣ የነብዩን አስተምህሮት ከሚቃረን፣ የሶሃቦችን ተግባር ከሚነቅፍ ተግባር እራስህን ልትጠብቅ ይገባል።
አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን
:
. ❥❥__ #ሰናይ_ጊዜ __❥❥
@wahdinn
@wahdinn
@wahdinn
⚖ ┈┈┈••●💎የፍትሕ መንገድ 💎●••┈┈┈⚖
BY የዐብደሪይ ደረሶች
Share with your friend now:
tgoop.com/yeabderiyderesoch/3364