tgoop.com/yeberhanljoche/2021
Last Update:
ራስን መግዛት እንዴት ?
መንፈሳዊው ሰው ካሉት ብቃቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ራስን መግዛት ነው፡፡ እርሱ ራሱን ለሥጋ ምኞትና ለፍላጎቶቹ አሳልፎ አይሰጥም፡፡ ሕሊናው የኃጢአትን ምኞት ሲናፍቅ ይህን አሳቡን በመቃወም መንፈሱ እንድትመራው በማድረግ ራሱን አጥብቆ ይገዛል:: መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:- «በመንፈሱ ላይ የሚገዛ (መንፈሱን የሚገዛ) ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል፡፡» ምሳ. 16፥32
እንደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ራሱን የሚገዛ ወይም የሚመራ ማለት ሥጋው የጠየቀውን ሁሉ የማይሰጥ ይልቁኑ የሚቃወም ማለት ነው:: «ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፤ነፍሱን በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል፡፡» ዮሐ. 12፥25።
ራስን መግዛት በውስጡ የተለያዩ ክፍሎች እንዳሉት እርግጥ ነው፡፡ እነርሱም፤-
1. #ምላስን_መግዛት፡፡
2. #አሳብን_መግዛት::
3. #ልብን_መግዛት፡፡ (ፍላጎትንና ምኞትን በመግዛት)
4. #ስሜትን_መግዛት::
5. #ሆድን_መግዛት (ምግብን በተመለከተ) ናቸው፡፡
ራሱን የሚመራ ሰው እርሱነቱን ለእሴትና ለዓላማ እንዲሁም ለሕግና ደንብ ያስገዛል፡፡ ራሱን መምራት የማይችል ሰው ግን በእርግጥ እርሱነቱን ለጥፋት ይጋብዛል፡፡ ራሱን የሚገዛ ሰው ነፍሱን በእውነተኛ ፍቅር ይወዳታል:: ራሱን የሚያቀናጣ ግን ነፍሱን ከማጣቱም በላይ ሌሎችም ከእርሱ ጋር አብረው እንዲጠፉ ያደርጋል፡፡ ራሱን አጥብቆ የሚጠብቀው በትጋቱ ነፍሱን ስለሚጠብቃትና በመልካም ሁኔታ ስለሚይዛት ያድናታል፡፡ አልፎ ተርፎም ሌሎችን ለማዳን ምክንያት ይሆናል፡፡ የራሱን አመለካከትና ግንኙነት በቅደም ተከተል ያደራጃል፡፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ያስቀድማል፤ በመቀጠል ሰዎችን ያስከትላል፤ በመጨረሻም ራሱን።👉
#ምላስን_መግዛ፡
መንፈሳዊው ሰው ቃላት ወይም አሳቦች ያቀበሉትን ወደ አእምሮው የመጡትን ሁሉ በአንደበቱ አይናገራቸውም፡፡ እያንዳንዱን ቃል ከአንደበቱ ከማውጣቱ በፊት ይመዝናል:: የእርሱ ሚዛን የሚለካው የቃሉን ፍሬ ነገር ብቻ ሳይሆን ትክክል መሆኑንና አለመሆኑንም ጭምር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የእርሱ ዋና ዓላማው ቃሉ በሌሎች ሰዎች ላይ የሚያመጣውን ተጽዕኖ፣አፀፋና ውጤቱን ጭምር ነው::
የምላስ ወይም የአንደበት ስህተት ውጤት ሥጋን ማሳደፉንና የፍጥረትንም ሩጫ ማቃጠሉን የሚያውቅ ሰው ከመናገሩ በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል:: ያዕ. 3፥5-6:: ከነቢዩ ከዳዊት ጋር ሆኖም:- «አቤቱ ለአፌ ጠባቂ አኑር፤ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ፡፡» ይላል፡፡ እርሱ አንዴ ከአፉ የወጣው ቃል ተመልሶ ሊገባ እንደማይችል ያውቃል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ከአፉ የወጣው ቃል አድማጮቹ ጆሮ ከደረሰ በኋላ የተናገረውን መልሶ ሊውጠው፣ ወይም ይቅርታ ሊያገኝበት እንደማይችል አስቀድሞ ያውቃል:: ከዚህ በኋላ ስህተቱን ለማስተካከል ቢጥርም ጥፋቱ በእርሱ ላይ ዕዳ ሆኖ እንደሚቆጠር አጥብቆ ይረዳል፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ ጌታ እንደተናገረው እንደሚኮነንበት ያውቃል፡ . . . ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና፤ ከቃልህም የተነሣ ትኮነናለህ፡፡» ማቴ. 12፥37::
(#በብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#መንፈሳዊ_ሰው_መጽሐፍ ገጽ 122-128
#በአያሌው_ዘኢየሱስ_የተተረጎመ
@yeberehanljoche
BY ውሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤ/ት(ጫንጮ)
Share with your friend now:
tgoop.com/yeberhanljoche/2021