tgoop.com/yebezigetmoch/1251
Last Update:
🍃🍃ተስፋ 🌱🌱🌱
ደራሲ 📖ቤዛዊት የሴትልጅ🖊
❤️ክፍል ሰባት❤
.
.
.
.
.
ሀዘኔን ደስታዬ ያካፈልኳት ህይወቴን የሰጠኋት ሰናይት ዛሬ የኔ አይደለችም ጭራሽ የውሸት ድራማ ውስጥ በእሷ አለም ላይ ተገኝቻለሁ። ባያት ብዬ ስናፍቅ የኖርኩ እኔ ከንቱ አፍቅሪ ከፊቴ ሳያት እጅጉን ዘገነነኝ። መኪናውን አቁሜ ወደ ዮዳሄ ጋር ገባሁ።
ሁለተኛ ፎቅ ላይ ካለው የውበት ሳሎን በሩን በርግጄ ገባሁ ሁሉም አፈጠጠ። ሴቶቹ በእሳት ይለበለባሉ ሌሎቹ ፊታቸውን እጅ እና እግራቸው ይታሻሉ። በአይኔ ሳማትር ዮዳሄ ጆሮዋ ላይ ኤርፎን አድርጋ ከሰው መሃል ተነጥላ ተልይታለች እና አላየችኝም። እኔም ሄጄ እጇን ያዝኩት በርግጋ ከዓለሟ ወጣች። "ምንድነው አንተ ደነዝ" አለች ቃል ሳይወጣኝ ጎትቻት ወደ መኪናው ወሰድኳት በጣም ደንግጣለች መደንገጧ እኔን ሊያረጋጋኝ አልቻለም። "ስሚ ህይወቴን እንዳልኖር ነው የመጣሽው ወይስ እንድሞት ነው ማነሽ....ከእኔ ምንድነው የምትፈልጉት" እንደ ክረምት መብረቅ አምባረቁባት። "አትጩህብኝ ምንድነው የምትዘላብደው ማነህ እና ነው ከአንተ የምፈልገው" ከእኔ ድምፅ በላይ ድምጿ ገነነ ፊቷ እያየሁት ጉበት መስሏል። "ሰናይት" ጠራኋት። "ምን ትሁን " አልተረጋጋችም። "ትሰሚኛለሽ ድሮም ስትቅለሰለሺ መጠርጠር ነበረብኝ የዋህ መስለሽ ነው የሰራሽልኝ ደግሞ ሰናይት ጓደኛዬ....." ተበሳጭቼ በቆመችበት ጥያት ሄድኩ።
ያንን ጊዜ እያሰብኩ ስንከፍ ከእናት አባቴ ቤት ደረስኩ የወትሮ ብስጭቴ ከፊቴ ላይ ያነበቡት ቤተሰቦቼ ዝምታን መርጠዋል እኔም ክፍሌ ገብቼ ከወንድነቴ ጋር እየታገልኩ ወደ ውስጤ አለቀስኩ። ስልኬ በተደጋጋሚ ይደወላል ዮዳሄ ናት። እንዴት ነው የተዋወቅነው አውቃ ነው የመጣችው ግራ ገብቶኛል። የፅሁፍ መልእክት ገባልኝ ከፈትኩት .."ለእኔ ጥሩ ነገር አይገባኝም አውቃለሁ። ላደረክልኝ ነገር አመሰግናለሁ አንተ ደነዝ።ልትሰማኝ ከፈለክ ወይ ልታወራኝ ከፈለክ ለአንተ ዝግጁ ነኝ" ይላል። ውስጤ የሆነ ነገር ተጎምዶ የወደቀ መሰለኝ የረሳሁት ነገር ያለ ይመስል ንዴቴ ተኖ ስለ ዮዳሄ ማሰብ ጀመርኩ። ደወልኩላት...... "ደነዝ እወነት የሰው ንዴት እኔ ላይ ትወጣለህ" አለችኝ። የኔን ቃል ሳትጠብቅ ፈገግ አልኩኝ ወደ ልቤ ደም እያዘራሁ "ተንኮልሽ ነው ቀድመሽ ብትነግሪኝ ደስ ባለኝ።ለእኔም ጥሩ ነገር አይገባኝም ግን ይሄም አይገባኝም።" አልኳት ድጋሜ ህመሜ አገርሽቶ።"የምትለው እኮ አልገባኝም ሰናይት ማናት" አለችኝ። ክው አልኩ እንዴት እንግዳዋን አታውቅም አልኩኝ። "እባክህ እናውራ ያለህበት እኔ እመጣለሁ" አለችኝ። ያለ መጠን ዝቅ ማለቷ የሌለባትን ትህትና ብታሳይ ይበልጥ ከልቤ ጠረጠርኳት መልሴን ሳልሰጣት ስልኩን ዘጋሁት። የዮዳሄ ግራ መጋባት እኔንም አወዛግቦኛል። ሰናይት ለእሷ የወንድሟ ሚስት ለእኔ ደግሞ የህልሜ እመቤት ነበረች ብቸኛዋ የልቤ ንግስት ህይወትን መኖርን ያወኩባት ሰው አድርጋኝ አውሬ ያደረገችኝ ከሰውተራ ቀላቅላ ከሀዘን መጋዘን የከተተችኝ ብቸኛዋ ህመሜ ናት። ቀኑን የምናፍቃት ለሊቱን የማለቅስላት የኔዋ ሰናይት የሌላ ናት የኔዋ ህልሜ የሌላ እውን ናት። እንባዬ በጉንጬ ቦይ ሰርቶ ይዘረገፋል ድጋሜ መልእክት ገባልኝ ዮዳሄ ናት "እባክህን ለዛሬ ብቻ ከጉድ አውጣኝ አንተን ነው ቤተሰቤ የሚጠብቀው ከቅዠት አለም አትክተተኝ አታሳፍረኝ እከፍላለሁ" ብላ ነበር። አሰብኩት የምወዳት የአይኗ የብርሃኑ ፍላፃ ጨለማዬን የሚያበራው ዛሬ ሊያጨልምብኝ በአንድ ገበታ የተቋደስን ተለያይተን ልንቀርብ። ምን አማረሽ ብዬ ላቀማጥላት የምሻ አፍቃሪዋ ተመልካች ልሆን አልሄድም ብዬ ስልኬን ዘጋሁ። መከፋቴ አይደለም ወደአለሜ መምጣቷ ማዕበሉን አስጀመረው። ድጋሜ መልእክቱ ገባልኝ "እናቴ አይኖቿ ከበሩ ላይ ነው አንተ መድሃኒቴ ወይም በሽታዬ ነህ ምርጫው የአንተ ነው" ይላል ደነገጥኩ። ግን ደግሞ አልሄድም አልችልማ ተነስቼ ወደ መስኮቱ ተጠግቼ ቆምኩኝ .....መድሃኒት እና በሽታ ሁለት ምርጫ አለኝ ምንም አለመምረጥም መብቴ ነው።
🫀🫀🫀ይቀጥላል....🫀🫀🫀
🍃🍃🍃🍃🍃ተስፋ🍃🍃🍃🍃🍃
💑አዲስ ተከታታይ ድርሰት👫
በቤዛዊት የሴትልጅ💛
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
BY የግጥም መንደር
Share with your friend now:
tgoop.com/yebezigetmoch/1251