tgoop.com/yebirihan_lijoch/9938
Last Update:
#እንዲህም ይፃፋል 👏👏👏👏👏👏
#ምድብ_B
ነብሱን እስከ መስጠት እኛን የወደደን
የዘላለም ወጃጅ ኢየሱስ አለልን
አለው እኔ በኔ ሳይሆን በርሱ ምርጫ
የመኖረ ምክንያት ሆኖልኝ ፀጋው ብቻ
ይሄ ነው አምላኬ እንድሁ የወደደኝ
በአንድያው ልጁ መርጦ ያጸደቀኝ
በቃሉ ተጠርታ የተፈጠረች ምድር
ሰሪዎ ሲወለድ መች ቻለች ማሳደር
በግጥም በመዝሙር በእጄም ሆነ ባፌ
ለሱ ልቀኝለት በሱ ነው ማረፌ
ይቅርታ ይቅርታ ልድገመው ይቅርታ
እንደውም ያንሰኛል ጠዋት እና ማታ
እንደ ጥላቴ እቅድ ቢሆን ኖሮ
አልኖርም ነበር ዘንድሮ
ሲጠጉ ወዳንተ ወደ ደረትክ
በነው ይጠፋሉ ሀሳብና ጭንቀት
እርሱ ብርሃን ነው ላሉ በሞት ጥላ
የሀጥያጥያተኞች ወዳጅ ጠበቃ ከለላ
እርሱ ለሰላሙ ፍፃሜ የለውም
እርሱ ፃዲቅ አምላክ እንከን አያውቀውም
ሌላ ህይወት በፍፁም አይሆንም
ሰወች እንመነው ያለሱ አይሆንም
እርሱ ከወደደን ከነ በደላችን
ለምን እንራቀው አይሂድ ከደጃችን
ዝም በይ ብሉኝ ዝም የማልልው
ውለታው ብዙ አለብኝ ቆጥረ የማልጨርሰው
መች ሳላዉቅ ቀርቼ የተደረገልኝ
ቃላት አጣሁ እንጂ የልቤን ሚገልፅልኝ
እና ምን እላለሁ ከማመስገን በቀር
ቢወራ አያልቅም ቢዘመር ቢዘመር
ተናግሬው አያልቅ የጌታዬ ፍቅር
በሞትህ ሞተን ገለህ ህይወትን የሰጠሄኝ
እርግማነን ሽረህ ፅድቅን ያለበስከኝ
አቦ ልክ ብለሃል እግዚአብሔር ይባርክህ
ጸጋውን አብዝቶ ፊቱንም ያብራልህ
የኔ አምላክ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
ዘለዓለምን ፈጠራ በወዘላለም የምትኖር
እስኪ ልንገራችሁ አንደ ስሙኝማ
ዘመኑን እንዋጀው ሕይወት ሳንቀማ
አንተ ያልሰማክ ስማ ይሄ ቃል ላንተ ነው
ሳይረፍድ አስገባው ጌታ በደጅህ ነው
በሩ ሳይዘጋ ሙሽራውም መቶ
ፋኖሱ ይሞላ ጋዙ ተዘጋጅቶ
በሩም ቶሎ ይከፈት ሙሽራችን ሳይሄድ
እሱ ነው ብርሃን እውነት እና መንገድ
በሉ ተዘጋጁ አለም ጊዜዋ አልቋል
ውዱ ሙሽራችን እየሱስ ይመጣል
#ምድብ_B
BY የብርሃን ☀️☀️ ልጆች
Share with your friend now:
tgoop.com/yebirihan_lijoch/9938