tgoop.com/yebirihan_lijoch/9946
Last Update:
ታማኙ አማካሪ
በአንድ ዘመን ይኖር የነበረ ንጉስ 10 አማካሪዎች ነበሩት ። ታማኝነታቸውን እና ከእነርሱ ውስጥ የቅርቤ የሚለውን አንድ ሰው ሊያውቅ ፈለገና እያንዳንዳቸውን ለየብቻቸው ጠርቶ የተለያየ ነገር ነገራቸው እና ሚስጥር እንደሆነ አስጠንቅቆ ይነግራቸዋል እነርሱ ግን ሁሉም እጅግ የጠበቀ ግንኙነት ስለነበራቸው የነገራቸውን የእያንዳንዱን ወሬ እርስ በእርስ ይነጋገራሉ በህብረት በሚሰበሰቡበት ግዜ በድንገት አመለጣቸውና ለአንዱ ብቻ የተነገረውን ሀሳብ ሁሉም አወሩ ንጉሱ አማካሪዎቹ አለመታመን ይበሳጫል።
ይሄ ነው እምነታችሁ ብሎ ሲጠይቃቸው ሁሉም ተካክደው የራሳቸውን ንፁህነት ብቻ ለማስረዳት ለፈለፉ እኔ ታማኝ ነኝ እገሌ ነው የተናገረው እየተባባሉ ተካሰሱ ንጉሱ እርስ በእርስ መካካዳቸውን ሲያይ ይበልጥ ተበሳጨ
ከእነርሱ የቅርቤ የሚለው ሰው እንደማያገኝ ይረዳና ያዝናል ሁሉም መበሳጨቱን አይተው ቁጣው እስኪበርድ በሚል ትተውት ወጡ ። ሚስቱ ሀዘኑን አይታ ለምን ትንሽ ጭንቀትህን ትረሳ ዘንድ በግዞት ቤት ያሉትን እስረኞች አትጎበኝም የሚል ሀሳብ አቀረበችለት ።
ሳያንገራግር በግዞት ወደ ታሰሩት እስረኞች አመራ እያንዳንዳቸውን እየዞረ ምን አጥፍተው እንደሆነ ይጠይቅ ጀመር አብዛኞቹ ራርቶ እንዲያስፈታቸው ያለጥፋታቸው መታሰራቸውን ነገሩት እየተገረመ ጉብኝቱን ቀጠለ አንደኛው እስረኛ ንጉሱን ከሎሌዎቹ ጋር ሲያይ ሊደበቅ ዳዳው ንጉሡም ምን አጥፍቶ እንደታሰረ ጥያቄ አቀረበለት ። ሞት የሚገባው ወንጀለኛ መሆኑን ለንጉሱ እያነባ ተናገረ ወዳጁን ባለመግባባት ሲጣሉ እንደ ገደለው አሁን ግን ፀፀት ሰላሙን እንደነሳው መኖር እንደማይፈልግ ለንጉሡ ነገረው ።
ንጉሱ ተደንቆ ለምን መኖር አትፈልግም አለው ወንጀለኛ ነኝ ወዳጄን ስለገደልኩ እኔም መኖር አያስፈልገኝም ብሎ ምርር ብሎ አለቀሰ ንጉሱ ጠባቂዎቹን እንዲፈቱት አዘዘ ወደ ቤተ መንግስት ከእርሱ ጋር ይዞት ሄደ ወንጀለኛው በሞት ፍርድ ሊቀጣ እንደሆነ ገምቶ ነበር ልብሱን ቀየሩለት ከንጉሱ አማካሪዎች ጋር በማዕድ ተቀመጠ ሁሉም ግራ ተጋቡ ንጉሱም እንዲህ አላቸው በግዞት ቤት ሁሉንም እስረኞች ጥፋታቸውን ጠየኩአቸው ነፃ ለመውጣት ሲሉ ሌባውም ነብሰ ገዳዩም ያለጥፋታቸው መታሰራቸውን ነገሩኝ ይሄ እውነተኛ ሰው ግን ከልቡ ተፀፅቶ ወንጀሉን ተናዘዘ እውነተኛ ነው አልዋሸኝም ለዚህም ከእናንተ የተሻለ ታማኝ አገልጋዬ ይሆነኛል ብዬ ከእኔ ጋር አምጥቼዋለሁ አላቸው ሁሉም ተናደዱ አንደኛው ተነሳና ንጉስ ሆይ ይህ ሰው ዕውቀት አለውን? የንጉስ አማካሪ ለመሆን የመኳንንት ቤተሰብ ነውን?
አለ ሁሉም ሳቁ ንጉሱ ከፍ ባለ ድም መቼም ዕውቀት አለን የመኳንንት ቤተሰብ ነን ከምትሉ ከእናንተ በታማኝነት 100 እጥፍ ይበልጣል እኔ ደግሞ የምፈልገው ያንን ነው ጨርሼአለሁ አላቸው ። ያሰውም ይምረው ዘንድ በአምላኩ ፊት በንሰሀና በለቅሶ ቀረበ ንጉሡንም በታማኝነት ያገለግለው ጀመር ንጉሡም ሚስጥሩን ሁሉ ሀሳቡን ሁሉ ያካፍለው ነበር።
እና ወዳጆች ምን ልላችሁ ነው እግዚአብሔርም ሀሳቡን የሚያወራው የቅርቡ ሰው ይፈልጋል በሰዎች ላይ የሚመፀዳደቅ ሳይሆን በፊቱ የተራቆተን ሰው ሰው እንኳን ሚስጥሩን ለማውራት የቅርብ ጓደኛውን ወይ ቤተሰቡን ይመርጣል ጌታም ሀሳቡን ሊያካፍለን ዕለት ዕለት እንድንቀርበው እንድናውቀው ይፈልጋል ። ልክ ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር አውርቶ ሲመለስ የፊቱ መልክ ይለወጥ እንደነበር ለምን ሲባል የእግዘብሔርን ድምፅ ስለሰማ ከእግዚአብሔር ጋር ስላወራ ጌታ የሚያወራው ሰው ይፈልጋል የልቡን ሀሳብ የሚጋራው ታማኝ ሰው ይፈልጋል የጌታ የቅርብ መሆን እኮ መታደል ነው ዕድል ነው ። ልናማክረው አይደለም እርሱን ማንም አያማክረውም ሀሳቡን ፈቃዱን ሰምተን እንድናደርግ እንድንኖርለት ። በፀሎት ፊቱን እንድንፈልግ ይፈልጋል እንፀልይ እንፀልይ እንፀልይ .......
ሉቃስ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥
² እንዲህ ሲል፦ በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ።
³ በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች፦ ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር።
⁴ አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ፦ ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥
⁵ ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ።
⁶ ጌታም አለ፦ ዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ።
⁷ እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?
⁸ እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?
ሳይታክቱ ይፀልዩ ዘንድ ......
✍️ Aksan Adane
TEBAREKU 🙏
BY የብርሃን ☀️☀️ ልጆች
Share with your friend now:
tgoop.com/yebirihan_lijoch/9946