tgoop.com/yefkrtarik/5875
Last Update:
♥️ተማሪዋ♥️
🌹...ክፍል 22...🌹
ሁኔታዎቿ ያወዛገቡኝም ያንን ማረጋገጥ ባለመቻሌ ነው አይገባህም እንዴ ኪያ?"
"ገብቶኛል ኤፊ አንተ ያልገባህ ግን ያንን የምታረጋግጥበት መንገድ አንዱ እፍታውን መውሰድ መሆኑ ነው። ቆይ እንዲህ ምድር ሰማዩ እስኪዞርብህ ያፈቀርካት ጡት እንድታጠባህ ነው እንዴ ወደድክም ጠላህም የትዳርም የፍቅርም ምሶሶው የሚተከለው ካንሶላው ስር ነው ።
ይልቅ ፍጠን፣ ከወንድ ጋር አየኋት አላየኋት እኔ የምፈልጋት ለ ዘላቂ ሂወት ነው ቅብርጥሴ እያልክ አሁን ስርስሯ ለሚሄደው ልጅ እፍታውን ታስረክብና ዘላቂ የለ አብረቅራቂ የለ ሁሉንም አጥተህ እጅና እግርህን አጣጥፈህ ትቀመጣለህ ።
እፍታውን ካስረከበችው አንተ የምታጣው እፍታውን ብቻ እንዳይመስልህ ከነአካቴው እሷንም ታጣታለህ ፣ ዘወር ብላ አታይህም!"አለኝ።
"በቃ ኪያ ከዚህ የተሻለ ምክር የለህም?" አልኩት።
"እንግዲህ ከዚህ በላይ ምክር ከፈለክ የፍቅር እና የትዳር አማካሪ ባለሞያዎች ጋር ሂድ እኔ ያቅሜን መክሬሀለሁ!" እያለኝ ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ በሩ ተጠጋና በሩን ከፈት አድርጎ ቆም አለ።
"ምነው የት ልትሄድ ነው ?"
"እንዲህ በፍቅር ተዝረክርከህ ወጥ በወጥ መሆንህን ለመክሊት አለመንገር አልችልም በቃ ካሁኑ አፌን እየበላላኝ ነው ፣ ሆድ ቁርጠትም ጀምሮኛል ኤፊዬ ሆዴንም ከሚያመኝ አፌንም ከሚበላኝ ደውዬ ልንገራት ባክህ !"
አለኝ ።
ባዶ የቢራ ጠርሙስ ብድግ ሰደርግ እየሳቀ በሩን ከፍቶ ወጣ "የጨነቀ ለት አለ ሰውየው እኔነኝ ባለጌው ሰው ነህ ብዬ ካንተ ጋር ማውራቴ አንተ ስለመፍቻ እንጂ ስለፍቅር ምን ታውቃለህ ድሮስ" አልኩት ጬክ ብዬ።
ኪያ ግቢ ውስጥ ቆሞ በዛ ሰሞን በተደጋጋሚ እየከፈትኩ ስሰማው የነበረውን የቴዲ አፍሮን ዘፈን
"ለይምሰል አይደለም ልቤ የሚወዳት
አይ ልቤ
እስከመቼም ቢሆን ምን ግዜም አይከዳት
አይ ልቤ
ተኩላ ተኩላ ስትሄድ እያየሁዋት
አይ ልቤ
መልኳን ይዛው ወጥታ. ታድያ እንዴት ልመናት
•••• •••• እያለ ጬክ ብሎ ሲዘፍን ሰማሁት••••
ትንሽ ቆይቶ ተመለሰ።
" እ ደውለህ ነገርካት ሆድህንስ ተሻለህ ? ለመክሊት ለመደወል ነው አደል የወጣኸው? እኔ ለፍቅር እጅ መስጠቴን ስታውቅ ደስ አላት? ለዚህ አቃጣሪነትህ በምላሹ ምን ልትሰጥት ተስማማች?"
"አቦ መስመር አትለፋ አንተ ደሞ ቀልድ አይገባህም እንዴ ኤፊ ሙት አልደወልኩም"
"ይሄን ግዜ ስልክ አላነሳ ብላህ ነው"
"ሀይ አልደወልኩም አልኩህ እኮ ምን አስቸኮለኝ ነገ አይደርስም እንዴ?"
"ይደርሳል ነገ ንገራት እሺ ፣ እኔ እሷ ሰማች አልሰማች የሚያስጨንቀኝ መስሎህ አትጃጃል፣ ደንታ የለኝም።
እኔ ቃልዬን ማፍቀሬን አለም ሁሉ ቢያውቅልኝ ደስታዬ ነው።እሷን በማፍቀሬ ደስተኛ ነኝ። ለማፍቀር ባትታደልም ማፍቀር መታደል ነው ሲባል ሰምተሀል መቸስ"
"ሃሃሃሃ መታደል የሚሆነው ግን ሙሉ ሲሆን ነዋ ወሬ ማሳመርማ ማን ብሎህ ኤፊ አንተና የኢትዬጲያ ብሄራዊ ቡድን ግን አንድ እንደሆናችሁ ታውቃለህ?"
"አላውቅም እንዴት ? ምን ለማለት ፈልገህ ነው?"
"በቃኣ የኢትዮጲያ ብሄራዊ ቡድን በጫዋታ ከማን ያንሳል ጫወታውን ለጉድ ይጫወተው የለ እንዴ፣ ትልቁ ችግሩ ምንድን ነው? ጎል ማግባት አደል እንዴ?"
"አዎ ነው የነሱ ተጫውተው ጎል አለማግባት ከኔ ጋር ምን ያገናኘዋል?"
"ካካካካ እስካሁን አልገባህም ኤፊዬ በደንብ ነው እንጂ የሚገናኘው ፣ አንተስ ሴት ልጅ ቀርበህ ጫወታ መች ተቸግረህ ታውቃለህ? ለጉድ ትጫወተው የለ እንዴ፣ ካንተ ጋር የተወሰነ ደቂቃ አውርታ ሶስት አራቴ ከልቧ ሳትስቅ የቀረች ሴት አለች እንዴ? እኔ እስከማውቀው የለችም።
" አየህ ይህንን የምታውቀው እኮ እኔ ከምቀርባቸው ሴቶች ስር ስለማትጠፋ ነው ።
ሁሉም ሰው ደካማ ጎን አይጠፋውም ያንተ ደካማ ጎን ግን ያስጠላል"
"ሃሃሃ ኤፊ ያንተ ደካማ ጎን ደሞ ከቤህራዊ ቡድኑ ጋር መመሳሰሉ ይገርማል።
እንዴልኩህ እነሱ ተጫውተው ጎል አያገቡም ያንተም ትልቁ ችግር አስቀህ አሳስቀህ በጎል ወይም በውጤት ማሳረጉ ላይ ነው ፣ ሹፌሩ እስከሚመጣ ሞተር የሚያሟሙቅ የከባድ መኪና ረዳት ይመስል ሞተር አሙቀህ ሳትነዳ መውረድ አመልህ ነው።
ሞተር አሟሙቀህ ሳትነዳ የማትወርደው ከባጃጅህ ላይ ብቻ ነው ካካካ•••"
"ክፍታፍ ነገር ነህ ባክህ ፣ የምትናገረው ነገር የቱንም ያህል እውነትነት ቢኖረው እንኳን አንተ ለማብሸቅና ለመሳቅ እንጂ ድክመቴን እንዳስተካክል አስበህ እንዳልሆነ ስለሚገባኝ ምንም ብትል አይዋጥልኝም"
"ካካካካ መስሎህ ነው ባክህ የግድ በትዛዝ መልክ መናገር የለብኝም ድክመቱን ማስተካከል የፈለገ በቀልድም መልክ ተነገረው በቁምነገር ዋናው ድክመቱን አምኖ ለመስተካከል ያለው ፍላጎት ነው" አለኝ።
" ስማ ኪያ አንዳንድ ሀሳቦች ትክክል የሚሆኑበት ቦታ አለ ያ ማለት ትክክል የማይሆኑበት ቦታና ሁኔታ የለም ማለት አይደለም።
አንድ ሀሳ ልክ ሊሆንም ላይሆንም የሚችለው ሀሳቡ ልክ ስላልሆነ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን እንአውዱ እንደሁኔታው ስለሚወሰንም ጭምር ነው።
ስለዚህ ላንተ ትክክልየመሰለህን ነገር ሁሉ ከማውራትህ በፊት እኔ ያለሁበትን ሁኔታ በደንብ ለመረዳትና አንተ በምታስበው እና እኔ ባለሁበት እውነት መካከል ያለውን ልዩነት ለመረዳት ሞክር!"
"አቦ አንተ ልጅ አሁንስ የማውቀው ኤፍሬም አልመስልህ አልከኝ እኮ ፣ መፈላሰፍ መጀመርህን ለምንድን ነው ያልነገርከኝ? ካካካካ•••አይ ፍቅር •••ፍቅር ምን የማያደርገው ነገር አለ ?የቀረህ የጥበብ ሰው መሆን ብቻ ነው ኤፊዬ ግጥም ምናምንስ መፃፍ አልጀመርክም? እስካሁን ካላፃፈክም ወደፊት መፃፍህ አይቀርም፣ አሁን ፈላስፋ አድርጎሀል፣ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ግጥም መጣጥፍ ምናም ያፅፍህና ከጥበቡ ጎራ ይቀላቅልሀል ሆሆሆሆ••••"
"ግልፍጥ ነገር ነህ ዝም ብለህ ገልፍጥ " አልኩት በገዛ እጄ ኪያ ምላስ ላይ ወድቄ እየተንጨረጨርኩ።
"ለማንኛውም ኤፊ ለመረዳት ሞክር የምትለኝ ምን እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም። ብሞክርም አሁን ከገባኝ የተለየ አዲስ ነገር አይገባኝም ።
እኔ በምለው ነገር እና አንተ ባለህበት እውነት መካከል ያለውን ልዩነቱን ምን እንደሆነ ከገባህ አንተው ንገረኝ "
"ልዩነቱማ ኪያ አንተ ለጭን እንጂ ለፍቅር ተንበርክከህ ስለማታውቅ የሁሉም ነገር መክፈቻም መዝጊያም ቁልፉ የሚገኘው ጭን ውስጥ ነው የሚመስልህ።
እኔ ደሞ እያልኩህ ያለሁት የእውነት ካፈቀርክ ከምታፈቅራት ልጅ የምትፈልገው ፍቅርን ነው ፣ ምንም ነገር ላይ አትቸኩልም፣ ምንም እንድትሆንልህ አትጫናትም እሷን ተጭነህ የምታደርገው ነገር ደስታ አይሰጥህም።
ምክንያቱም ስታፈቅር ከራስህ ደስታ በላይ የሷ ደስታ ያረካሀል፣ ከራስህ ፍትወት ይልቅ የሷ ፍላጎት ይመራሀል ስለዚህ ለራስህ ፍላጎትና ደስታ አትሽቀዳደምም።
ሁሉ ነገርህ ፣ሁሉ መሻት እና ፍላጎትህ ከሷ ፍላጎት ጋር አብሮ እንዲሄድ እንጂ ለኔ ፍላጌት ቅድሚያ ካልተሰጠው አልያም እኔ የፈለኩትን ነገር ሁሉ ለምንድን ነው አንቺም በተመሳሳይ ሁኔታና ግዜ ላይ የማትፈልጊው ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትልም።
ስለምታፈቅራት ሁሉ ነገርህን ትሰጣታለህ እንጂ እሷ ያላደረገችልኝ እሷ ያልስጠችኝ ምን አለ እያልክ እሱን አንተ በፈለክበት ግዜ ብቻ ለማግኘት ባገኘሀት ግዜ ሁሉ አትነዘንዛትም።
.
.
ከ 100 ላይክ ቡኋላ ክፍል 23 ይለቀቃል🌹
https://vm.tiktok.com/ZMh2s1nsh/
BY የፍቅር ታሪክ 🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/yefkrtarik/5875