tgoop.com/yekidst_hager777/2491
Last Update:
የአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግስት
ክፍል-ሁለት፦
✍አፄ ዮሐንስ 1ኛ በተለያዩ አገሮች ለጦርነትም፣ለሌላም ጉዳይ በሚጓዙበት ጊዜ በየደረሱበት አገር ሁሉ የሕዝቡን መሻት እየጠየቁ፣ህዝቡ የፈለገውን ነገር እየሰሩ፣ችግራችን ነው ያሉትን ነገር ሁሉ መፍትሔ እየሰጡ ነበረ የሚጓዙት።በርካታ ስራቸውም ዛሬ ድረስ እንደ ቅርስነት ተቀምጦ ሲገኝ፣የገነቧቸው ግንባታዎችም እስከ አሁን ተጠብቀው ለህዝብና ለምዕመኑ ግልጋሎት እየሰጡ ይገኛሉ።ከእነዚህ ውስጥም ከአገው ምድር የአገው ግምጃ ቤት ማርያምንና ሌሎች አብያተክርስቲያናትንም አስገንብተዋል።
✍እኒህ ንጉሠ ነገስት በጦር ሜዳ ውሎ ስኬትን፣በደግ ተግባራቸው በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅነትን፣በመንፈሳዊ ስራቸው ፅድቅን እንደገበዩ ይነገርላቸዋል።በተለይም መንፈሳዊነታቸው"ወደር የለሽ"የተባለለት ነበር።ሌሎችን ትተን አንዱን እንይላቸው።
ባለቤታቸው እቴጌ ሠብለወንጌል ከንስሐ አባታቸው(አንዳንድ መፅሐፍት ከመልከኛው ምግብ አብሳያቸው ጋር ነው ይላሉ)ፍቅር እንደጀመሩ በሰፊው ይነገር ነበር። አፄ ዮሐንስም ጉዳዩን በደንብ አውቀውታል።ከእለታት አንድ ቀን ንስሃ አባታቸው፣እቴጌ ሠብለ ወንጌልና አፄ ዮሐንስ 1ኛ በአንድ ማዕድ ቀርበው የተጠበሰ ዓሳ ይመገባሉ።አፄ ዮሀንስ ቤተ መንግስታቸው ውስጥ በሚገኘው የመኖሪያ ክፍላቸው በር ላይ እንደ ጠቢቡ ሰለሞን ሰው ሰራሽ ባህር አስበጅተው፣በባህሩም ውስጥ ዓሳ አስረብተው፣ከዚህም ዓሳ ውስጥ ተመርጦ እየተሰራ ለምግብነት ይውል ነበር።አሁንም ይሄ ሊበላ የቀረበው ዓሳ ከዚሁ ባህር የተገኘ ነው።እናም በዚህ ጊዜ ንጉሡ "ሶስታችን እውነት በንናገር ይህ የተጠበሰበ ዓሳ በህያውነት ተነስቶ እባህሩ ውስጥ ይገባ ነበር"ብለው ተናገሩ።ከዚህ በኋላ እቴጌይቱ "ቄሱን አግብቼ ብኖር እወዳለሁ"ብለው በግልፅ ተናገሩ።ቄሱም"እቴጌን አግብቼ ብኖር አመርጣለሁ " ሲሉ ንጉሱ ግን "ይችን ከንቱ አለም ንቄ ብመንን እወዳለሁ" ብለው ሶስቱም እውነት ተናግረው የየፍላጎታቸውን ተግባር እንደፈፀሙት በርካታ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።ባሉት መሠረትም የተጠበሰው ዓሳ ነብስ ዘርቶ ወደ ባህሩ ገባ ይባላል።
ይቀጥላል
BY ታሪክ ዘ ኢትዮጵያ
Share with your friend now:
tgoop.com/yekidst_hager777/2491