Telegram Web
Channel photo updated
.................አድዋ..............

✍🏽.አጤ ዮሐንስ ካረፋ በኋላ ግዛታቸውን እያስፋፉ ውጫሌው በተባለው ስፍራ ላይ ሰፍረው ሳለ ሚያዚያ 25 ቀን 1881 ከኢጣሊያ መንግስት ጋር 20 አንቀፆችን ተዋዋሉ ውሉም "የውጫሌው ውል" ተባለ።ይሄንንም ሲፈርሙ ገና አልነገሱም ነበር።ከእነዚህም 20 አንቀፆች ውስጥ በአንቀፅ 17 አለመስማማት ተፈጠረ።ይህም አንቀፅ በሁለት ግልባጭ የተፃፈ ነበር በአማርኛ እና በጣሊያነኛ።
1.በአማርኛ የተፃፈው "የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ከውጭ ሀገር መንግስታት ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት 'ፈቃዱ ከሆነ' በኢጣሊያ መንግስት በኩል ሊያደርግ ይቻለዋል"
2.ነገር ግን በኢጣሊ "የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ ሀገር መንግስታት ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግስት አማካኝነት ማድረግ ይገባዋል"የሚል ነበር።
✍🏽.አጤ ምኒሊክ እንደዚህ ተብሎ መተርጎሙን ያወቁት ንጉሠ ነገሥት ከሆኑ በኋላ የደስታ መልዕክታቸውን ለአውሮፓ መንግስት ሊልኩ ሲል አይ ደብዳቤ ቢሆንም በእኛ በኩል ነው ማለፍ ያለበት ባሉ ጊዜ ነው።
✍🏽.ጣልያኖችም በዮሐንስ ጊዜ ሲያደርጉት እንደነበረው አሁንም የተለያዩ መኳንቶች ከእነ ራስ አሉላ ጋር ተጣልተው ወደ እነሱ እንዲመጡ አደረጉ የጣሊያን ጦር በእነዚህ መኳንት እየተመራ ብዙ ቦታዎችን ተቆጣጠረ
✍🏽.አጤ ምኒሊክም ለቀው እንዲወጡ ቢያስጠነቅቁም አሻፈረኝ አሉ።አጤ ምኒሊክም አዋጅ አሰነገሩ አዋጁም"የሐገሬ ሰው ከአሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም።አንተም እስከ አሁን አላስቀየምከኝም።አሁንም ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ጉልበትየሌለህ ለልጅህ:ለሚስትህ:ለሀይማኖትህ እና ለሐገርህ ስትል በሐዘንህ እርዳኝ ።የወሰለትክ እንደሆነ ግን ትጣላኛለህ አልተውህም ።እግዝዕትነ ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም ዘመቻዬም በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ"ብለው የክተት አዋጅ መስከረም 7 ቀን 1988 ዓ.ም አወጁ።
✍🏽."እኔ ሴት ነኝ ጦርነት አልወድም ግን እንዲህ መሳዩን ውል አልቀበልም እኛ የናንተን የበላይነት አንፈልግም አንፈራችሁም።"እቴጌ ጣይቱ ብርሐን ዘኢትዮጵያ የውጫሌውን ውል በተመለከተ የተናገሩት።
-ጥቅምት 2 ቀን 1888 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ሲነሱ እቴጌ ጣይቱ አብረው ተነሱ ።ራስ መኮንን የጦር አበጋዝ ሆነው ራስ ወሌን :ራስ ሚካኤልን:ራስ መንገሻን ወ.ዘ.ተ ይዘው ጣሊያኖች በመሸጉት አምባላጌ ተራራ ላይ ሠፈሩ።
-ህዳር 28 አምባላጌ ላይ የተደረገው ጦርነት 2 ሰዓት ፈጅቶ ራስ መኮንን በመሩት ጦር የኢጣሊያ ጦር ወደ መቀሌ ሸሸ።ራስ መኮንን እየገሰገሱ ወደ መቀሌ ከተጓዙ በኋላ መቀሌ ላይ የተካሄደው ጦርነት ብዙ ሰዓት ከፈጀ በኋላ የውሃ ጥም ተጨምሮባቸው ብዙ መሳሪያዎችን አስረክበው ሸሹ።
-ከእነዚህ ጦርነቶች በኋላ ዋና የጦር አዝማቹ ባራቴሪ የቀረውን ጦር በ4 አቅጣጫ ከፍሎ አሰለፉ።
1.ጄ/ል አርሞንዲ
2.ጄ/ል ዳቦርሚዳን
3.ጄ:ል አልበርቶኒ
4.ጄ/ል ኤሌና የጦር ካርታ አዘጋጅቶ አሰለፋቸው።አጠቃላይ የኢጣሊ ጦር ከ20 ሺህ የበለጠ እና በዘመናዊ የጦር መሳሪያ የተሞላ እና 60 መድፎችን ታጥቀው ቀረቡ።
-የኢትዮጵያ ሰራዊት ደግሞ በ10 ጀነራሎች የተዋቀረ ነበር።
1.ምኒሊክ ከአድዋ አጠገብ ከ30,000 ሰራዊት ጋር
2.ጣይቱ በዚሁ ስፍራ ከ3000 ወታደር ጋር
3.ተክለ ሐይማኖት በዚሁ ስፍራ ከ3000 ወታደር ጋር
4.ፊት አውራሪ ገበየው ገቦ ከአሰም ወንዝ ተሻግሮ ከ6000 ወታደር ጋር
5.ንጉስ ሚካኤል ከ8000 ወታደር ጋር
6.ራስ መኮንን ከ8000 ወታደር ጋር
7.ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ አሉላ እና ከራስ ሐጎስ ጋር ከ3000 ወታደር
8.ዋግስዩም ከ6000 ወታደር ጋር
9.ራስ ወሌ ከ3000 ወታደር ጋር
10.ራስ መንገሻ አቲከም ከ3000 ወታደር ጋር በድምሩ 73,000 የኢትዮጵያ ሰራዊት ለውጊያ ተሰልፎ ነበር በዚህ ሰዓት የጊወርጊስ ዕለት ስለነበር ታቦቱን ይዘው እንደ ተሰለፉ ይተረካል።በጦርነቱ ጊዜም ቅዱስ ጊዎርጊስም ወርዶ ተዋግቷል ይባላል።ጦርነቱም ከተጀመረ በኋላ በሁለቱም ወገን ብዙ እልቂት ደረሰ።ጦርነቱም አንድ ሙሉ ቀን ወሰደ።
-ከኢጣሊ ወገን 5000 ነጭ:2000 ከኤርትራ የተመለመሉ ወታደሮች ሲሞቱ:2400 የሚሆኑት ከ60 መድፍ እና ከብዙ መሳሪያዎች ጋር ተማርከዋል።
-በኢትዮጵያ በኩል ህዝቡ ተኝቶ መታኮስ የፈሪ ነው እያለ ቆሞ በጀግንነት ሲዋጋ ስለነበር ለጥይት የተጋለጠ ስለነበር ብዙ ሰው አልቋል።በአጠቃላይ 10,000 እንደነበር ብዙዎች ይስማማሉ።
-ከ4ቱ መሪዎች 2ቱ ጄ/ል ዳቦር እና አርሞንዲን ተገደሉ።ጄ/ል አሌና ቆሰለ :አልበርቶኒ ተማረከ።በዚህም ጦርነት ትልቁን ድርሻ ባሻይ አውኣሎም በስለላ ተወጧል።
✍🏽.ጦርነቱም በባሻይ አውኣሎም ብልሀትነት:በምኒሊክ የጦር አደረጃጀት:በጣይቱ የተለየ ዘዴ እና በእነ ራስ መኮንን የጦር መሪነት እንዲሁም በኢትዮጵያ ህዝብ ወኔ እና ጀግንነት ጦርነቱን በድል አጠናቀቀች።
✍🏽.የዓለም ህዝብም ጉድ አለ።ኢጣሊ አንገተቷን ደፋች መላው የአፍሪካ ህዝብ አንገት ደግሞ ቀና አለ በዚሁም በወቅቱ የነበረው የኢጣሊ ጠ/ሚ ፍራንቺስኮ ክርስፒ ከስልጣናቸው ወረዱ።ለመላው አፍሪካዊያን ደግሞ የብርሃን ጮራ ብቅ አለች።ከድሉም በኋላ
"ምኒሊክ ተወልዶ በያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ ሐበሻ" እየተባለ ተዘመረለት።



🙏🏾.ክብር አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍሰው ይቺን ሀገር ላቆሙ የኢትዮጵያ ነገስታት እና ህዝቦች

.ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

@yekidst_hager777
@yekidst_hager777
@yekidst_hager777
† 7ቱ ኪዳናት †

=>'ተካየደ' ማለት 'ተስማማ: ተማማለ' እንደ ማለት ሲሆን 'ኪዳን' በቁሙ 'ውል: ስምምነት' እንደ ማለት ነው:: ይኸውም እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር: ሰዎችም ከሰዎች ጋር የሚያደርጉት ሊሆን ይችላል:: ልዩነቱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቅዱስና የማይለወጥ መሆኑ ነው::

+እግዚአብሔር አምላክ ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ በየጊዜው ከብዙ ወዳጆቹ ጋር ኪዳንን አድርጉዋል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እነዚህን ኪዳናት ጥቅልል አድርጋ 7 እንደ ሆኑ ታስተምራለች:: ስለዚህም ዛሬ ፈጣሪ ቢረዳን እነዚሁን 7 ኪዳናት በጥቂቱ እንመለከታለን::

"ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ"
"ከመረጥኩዋቸው ጋር ቃል ኪዳንን አደረግሁ" (መዝ. 88:3)

1. +" ኪዳነ አዳም "+

=>አዳም ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረት: የፍጡራን አስተዳዳሪ: ነቢይ: ካህንና ንጉሥ ነው:: እግዚአብሔር ከአዳም ጋር አስቀድሞ በእጸ በለስ አማካኝነት ቃል ኪዳን ነበራቸው:: ነገር ግን አባታችን በዲያብሎስ ሴራ በመረታቱ ኪዳኑ ፈረሰ:: (ዘፍ. 3:1)

+አዳምና ሔዋን ተጸጽተው ቢያለቅሱ ግን አዲስ የኪዳን ተስፋ: "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ኪዳንን ተቀበሉ:: (ቀሌምንጦስ: ገላ. 4:4)

2. +" ኪዳነ ኖኅ "+

=>ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ባሉት 10 ትውልድ ዓለም በዓመፃ ተሞላች:: ቅዱስ ኖኅ በደግነቱ መርከብ ሠርቶ ቤተሰቡን ሲያተርፍ ዓለም በማየ ሥራዌ ጠፋች:: ከመርከቡ ከወጣ በሁዋላ ኖኅና እግዚአብሔር በቀስተ ደመና ምልክትነት ቃል ኪዳን ተጋቡ:: "ኢያማስና ለምድር ዳግመ በማየ አይኅ" እንዲል:: (ዘፍ. 9:12)

3. +" ኪዳነ መልከ ጼዴቅ "+

=>መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር ካህኑ: የክርስቶስም ምሳሌው የሆነ የሳሌም ንጉሥ ነው:: በ15 ዓመቱ መንኖ: አጽመ አዳምን ይዞ: በቀራንዮ በሕብስትና በወይን ያስታኩት ነበር::

+እግዚአብሔር ለመልከ ጼዴቅ: በሐዲስ ኪዳን ለምትሠራው ክህነትና ምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ አድርጐ በቃል ኪዳን አትሞታል:: በዚህም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ ሞትን እስካሁን አልቀመሰም:: ይህም ካህኑ መልከ ጼዴቅ ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት ጊዜ ተገልጧል:: (ዘፍ. 14:17, ዕብ. 7:1)

4. +" ኪዳነ አብርሃም "+

=>ቅዱስ አብርሃም የሕዝብና የአሕዛብ አባት: ሥርወ ሃይማኖት: የጽድቅም አበጋዝ ነው:: ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲል ከርስቱና ከወገኖቹ ተለይቶ በቅድስና ኑሯልና እግዚአብሔር "በዘርሕ አሕዛብ ይባረካሉ" አለው:: (ዘፍ. 12:1) የቃል ኪዳን ምልክትም ይሆነው ዘንድ ግዝረትን ሰጠው:: (ዘፍ. 17:1-14)

5. +" ኪዳነ ሙሴ "+

=>ቅዱስ ሙሴ የነቢያት አለቃ: የእሥራኤል እረኛ: የእግዚአብሔር ሰው እና ፍጹም ትሑት (የዋህ) ሰው ነው:: በፈጣሪው ትዕዛዝ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አውጥቶ ለ40 ዘመናት በበርሃ ሲመራቸው ከእግዚአብሔር የኪዳንን ጽላትና አሠርቱን ትዕዛዛት ተቀብሏል:: (ዘጸ. 20:1, 31:18)

6. +" ኪዳነ ዳዊት "+

=>ቅዱስ ዳዊት ሥርወ ነገሥት: ጻድቅ: የዋህና ቡሩክ የሆነ አባት ነው:: እግዚአብሔር ከእረኝነት ጠርቶ ንጉሥ አድርጐ ሹሞት "ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አኖራለሁ" (መዝ. 131:11) ሲል ምሎለታል:: አክሎም ሰፊ ቃል ኪዳን ሰጥቶ "አልዋሰሽህም" ብሎ ሲምልለት እንመለከታለን:: (መዝ. 88:35)

7. +" ኪዳነ ምሕረት "+

=>በብሉይ ኪዳን የነበሩ 6ቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲዖል ማዳን ግን አልቻሉም:: ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን ያስፈልግ ነበር:: ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል ማርያም ማሕጸን አደረ::

+በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ: አድጎ: ተጠምቆ: አስተምሮ: ሙቶ: ተነስቶና ዐርጐ ሥጋ ማርያምን በዘባነ ኪሩብ አስቀመጠው:: ኪዳነ ምሕረት (የምሕረት ኪዳን) የምንለው አንዱ ታዲያ ይሔው ነው::

+የጌታችን መጸነሱ: መወለዱ: መሰደዱ: መጠመቁ: ማስተማሩ: ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ: መሰቀሉ: መሞቱና መነሳቱ: ማረጉና መንፈስ ቅዱስን መላኩ በአንድ ላይ ኪዳነ ምሕረት ይባላል:: ታዲያ ይህ ሁሉ የተደረገው በሥጋ ማርያም ነውና የኪዳኑ ባለቤት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት::

+የእርሷ ኪዳን 6ቱን አበው ኪዳናት ፍጹም በማድረጉ የኪዳናት ማሕተም ይባላል:: የድንግል ማርያም ኪዳኗ ከሲዖልና ከገሃነም ሊታደገን አቅሙ አለውና:: መድኃኒታችን ክርስቶስ ለድንግል እናቱ ቃል ኪዳኑን ያጸናላት ደግሞ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ ጐልጐታ ላይ ነው::

+እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ ሆይ! በስምሽ ያመነውን: በቃል ኪዳንሽ የተማጸነውን እምርልሻለሁ" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና:: ይሔው በእመ ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን ምዕመናን ከመቅሰፍትና ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ 2ሺ ዓመታት ሆኑ:: ዛሬም እኛ ኃጥአን ልጆቿ ከእሳት እንደምታድነን አምነን በጥላዋ ሥር እንኖራለን::

*" ኢትዝክሪ ብነ አበሳነ: ኃጢአተነ: ወጌጋየነ:
ማርያም እሙ ለእግዚእነ:
በኪዳንኪ: ወበስደትኪ ድንግል ተማሕጸነ::"

"ድንግል ሆይ! ኃጢአታችን: አበሳችንና በደላችንን አታስቢብን ዘንድ በስደትሽና በኪዳንሽ ተማጽነናል::"

=>የአርያም ንግሥት: የሰማያውያንና ምድራውያን ኁሉ እመቤት: የአምላክ እናት: ቅድስት: ስብሕት: ክብርት: ልዕልት: ቡርክት: ፍስሕትና ጥዕምት የሆነች ድንግል ማርያም የድኅነታችን መሠረት: ላመኑባት አንገት የማታስደፋ እውነተኛ አማላጅ ናት::

+በዚህች ዕለት የካቲት 16 ስለ ወገኖቿ የሰው ልጆች ፍቅር በእንባ ያቀረበችውን ልመና የባሕርይ አምላክ የሆነ ልጁዋ ተቀብሎ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ገብቶላታል:: በስምሽ ያመነ በቃል ኪዳንሽ የተማመነ እሳት አያይም ብሏታል::

=>ቸሩ ልጇ ከበረከተ ኪዳኗ አይለየን:: በዓሉንም የሰላም: የፍቅርና የበረከት ያድርግልን::

@yekidst_hager777
@yekidst_hager777
@yekidst_hager777
የጋላ(ኦሮሚያ) ግስ ነው።ጋላ ሲባል ስድብ አይደለም ታሪክን መርምሩ🚶🏾

ሀሳብ አስተያየት @Redii1028
የአፄ ዮሐንስ 1ኛ ዘመነ መንግስት
ከ1659-1674 ዓ.ም


ክፍል አንድ:-

✍🏽.አፄ ዮሐንስ በሚለው መጠሪያ ስም ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የነገሱት እኒሁ የአፄ ፋሲል ልጅ የሆኑት ናቸው። የአፄ ፋሲል እረፍት ለሕዝብ ሳይወጣ እስከ ልጃቸው ንግስና ድረስ ተደብቆ ነበር። ይኸውም በዙፋን ምክንያት አመፅ እንዳይቀሰቀስ ተሰግቶ የተደረገ ነበር። ያኔ የነገስታቱ ዘር ታጉረው ከሚኖሩበት አምባ ዮሐንስን በማስመጣት እንዲነግሱ አደረጓቸው።
✍🏽.አፄ ዮሐንስ 1ኛ በ1659 ዓ.ም የንግስና ስማቸውን "አእላፍ ሠገድ" አሰኝተው የአባታቸውን መንግስት ይዘው ስራቸውን ማካሄድ ጀመሩ።
✍🏽የመጀመሪያ ስራቸው ያደረጉት የነገስታቱ ልጆች ብቻ በወህኒ አምባ እንደከዚህ ቀደሙ ባሉበት እንዲቆዩ አድርገው፣ለቀሪው መላው እስረኛ ሁሉ ሙሉ ምህረት ማድረግን ነበር።
አፄ ዮሐንስ 1ኛ ለንግስና የተመረጡበት ምክንያት ከልጅነታቸው ጀምረው መንፈሳዊ ት/ት ላይ ያተኮሩና ለደሀ አዛኝ መሆናቸውን በደንብ ይታወቅ ስለነበር ነው።በወህኒ አምባ በለመዱት ስራቸው ሰሌን እየሰሩ ለድሆች በነፃ ይሰጣሉ።እጅግ ደግ ከመሆናቸው የተነሳም"ፃድቁ ዮሃንስ"በሚል መጠሪያቸው ነበር የሚታወቁት፤በዘመናቸው ከፈፀሟቸው ተግባራት ውስጥም የተለያዩ ነገዶችን ለየግላቸው መንደራቸውን ለይተው በየራሳቸው ባህል፣ወግ እና ልማድ እንዲኖሩ ማድረጋቸው ይጠቀሳል።የውጪ ሀገር ዜጎችን በተመለከተም በኢትዮጵያውያን ወግ እና ባህል፣እንዲሁም ሀይማኖት ስር ሆነው መኖር የሚፈልጉትን በነፃነት መኖር እንዲችሉ በመግለፅና በዚህ ካልተስማሙ ግን ወደየመጡበት አገራቸው እንዲመለሱ አውጀዋል፤ይህን መሰሉ አዋጅ ሲታወጅ በኢትዮጵያ ምድር የነበሩ የውጭ ዜጎች በአሪንጎ ሰፍረው ይኖሩ ነበር።ወደ ሀገራቸው ሳይሄዱ በያሉበት የነበሩትም ይገድሉናል ብለው ፈርተው ነበር።ወዲያው "ሊይዙን የመጡ እንደሆነ ሳንዋጋ እጃችንን አንሰጥም ብለዋል" የሚል ወሬ በቤተ መንግስቱ ተሰማ።ስለዚህ ንግግር አዋቂና የዲፕሎማሲ ሰው ግራዝማች ሚካኤል ነው፤ተባለና ተመርጦ ፈረንጆቹ ወዳሉበት ሄዶ"በቆላ ወይም በደጋ በፈለጋችሁት በኩል ወደ አገራችሁ እንድትመለሱ ታዛችኋል"ሲባሉ እነሱም"በቆላ በኩል አድርገን በስናር በኩል ተጉዘን ወደ አገራችን እንገባለን" አሉ።ከዛም ግራ አዝማች ከአሪንጎ ወደ ጎንደር ተመለሱ።
✍🏽ከአፄ ፋሲልና ከእቴጌ እህተክርስቶስ የተወለዱት አፄ ዮሐንስ 1ኛ በዘመናቸው በአባታቸው ጊዜ ይሸፍቱ የነበሩትን የሻንቅላ፣የሀንጋዝ፣የባንጋ፣የዋጅራት ነገዶችን አመፅ አስተናግደዋል።በየክፍሉ እንደራሴያቸውን መልዓከ ክርስቶስን፣የጦር አለቃቸውን ብላቴን ጌታ ገብረልዑልን፣ሹማምንቶቻቸውን እና ደጃዝማች ዘማሪያምን ልከው እያዋጉ፣እራሳቸውም እነ አቤቶ ዮስጦስን፣እነ ፊትአውራሪ ወልደ ብሩክን እያስከተሉ ሄደው ከአገር ወደ አገር እየተዘዋወሩ ሲያዋጉና ሲዋጉ ቆይተው፣የየግዛቱን አመፆች አርግበው በድል አድራጊነት ወደ ጎንደር ለመመለስ ችለዋል።ከጦር ሜዳ መልስም "ከሕዝብ ከፍተኛ ቀረጥና ግብር አልወስድም"በማለት ራሳቸው በሚሰሩት ሰሌን ይተዳደሩ ጀመር።የተረፈውንም ለድሆች በመመፅወት ይኖሩ ነበር እንጂ የተንደላቀቀ ህይወትን ንቀውት ነበር ጊዜያቸውን ያሳለፉት።ሆኖም ሰፊ የሰላም ጊዜ እንዳይኖራቸው የሀገር ውስጥ አመፅ መበራከት አገዳቸው።በ1667 ዓ.ም በአገው ምድር ያመፁትን ተዋግተው ያስገብሯቸው ዘንድ ጉዞ ጀመሩ።
✍🏽በዚያ ወቅት ደግሞ በአገዎች ዘንድ ብዙ ተላላፊ በሽታዎች በርክተው ህዝቡ ማለቅ ጀምሮ ነበር።ንጉሡ እንደደረሱም ሠባቱ የአገው ምድር ነዋሪዎች የሸፈቱት ሁሉ ለንጉሠ ነገስቱ ሰገዱላቸው።ሳጥናቸውንም እየከፈቱ ወርቅ ብርና የዝሆን ጥርስ እጅ መንሺያና ይቅርታ መጠየቂያ ሠጡዋቸው።ውጊያውም ቀርቶ ሁኔታው በሠላም ተፈታ።
.
.
.
ይቀጥላል
ጨረቃና የወር አበባ

✍🏾የሴት ልጅ የወር አበባ ዑደት በአማካይ 28 ቀናትን ይወስዳል።የዚኽ ዑደት ከጨረቃ አንድ ዙር የጉዝ ዕድሜ ጋር ይገጥማል።ይኸውም በሴት ልጅ ማህፀን ውስጥ ስለሚያኮርተው እንቁላል ነው።

🌗.እንቁላሉ በመጀመሪያ ሳምንት እንደ ለጋ ጨረቃ ያለ ቅርፅ ይኖረዋል።

🌕.በ፪ኛው ሳምንት ደግሞ የሙሉ ጨረቃን ቅርፅ ይይዝና በወንዱ የዘር ፍሬ ፅንስን ለመጀመር ዝግጁ ይሆናል።ይህን ዕድል ካላገኘ ደግሞ፦

🌓.በ፫ተኛው ሳምንት መጉደልና መተርሸት ይጀምራል።

🌑.በ፬ኛው ሳምንት ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ይተረሽና በወር አበባ መልክ ይወገዳል።ይኽም የጨረቃ አራተኛ ሳምንት የጨለማ ደረጃ ጋር ይመሳሰላል።

🌕.ወርኅ ማለት ጨረቃ ማለት ነው የሰላሳ ቀን ቆይታን ወር የምንለውን የዝኽ ተነስተን ነው።የወር አበባም በወር አንዴ የሚከሰት የተፈጥሮ ዑደት ነው።ስያሜውም የጨረቃ አበባ ማለት ይሆናል።

ማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ ካላቹ በዚ ልታገኙኝ ትችላላቹ @Redii1028
የአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግስት

ክፍል-ሁለት፦

አፄ ዮሐንስ 1ኛ በተለያዩ አገሮች ለጦርነትም፣ለሌላም ጉዳይ በሚጓዙበት ጊዜ በየደረሱበት አገር ሁሉ የሕዝቡን መሻት እየጠየቁ፣ህዝቡ የፈለገውን ነገር እየሰሩ፣ችግራችን ነው ያሉትን ነገር ሁሉ መፍትሔ እየሰጡ ነበረ የሚጓዙት።በርካታ ስራቸውም ዛሬ ድረስ እንደ ቅርስነት ተቀምጦ ሲገኝ፣የገነቧቸው ግንባታዎችም እስከ አሁን ተጠብቀው ለህዝብና ለምዕመኑ ግልጋሎት እየሰጡ ይገኛሉ።ከእነዚህ ውስጥም ከአገው ምድር የአገው ግምጃ ቤት ማርያምንና ሌሎች አብያተክርስቲያናትንም አስገንብተዋል።
እኒህ ንጉሠ ነገስት በጦር ሜዳ ውሎ ስኬትን፣በደግ ተግባራቸው በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅነትን፣በመንፈሳዊ ስራቸው ፅድቅን እንደገበዩ ይነገርላቸዋል።በተለይም መንፈሳዊነታቸው"ወደር የለሽ"የተባለለት ነበር።ሌሎችን ትተን አንዱን እንይላቸው።
ባለቤታቸው እቴጌ ሠብለወንጌል ከንስሐ አባታቸው(አንዳንድ መፅሐፍት ከመልከኛው ምግብ አብሳያቸው ጋር ነው ይላሉ)ፍቅር እንደጀመሩ በሰፊው ይነገር ነበር። አፄ ዮሐንስም ጉዳዩን በደንብ አውቀውታል።ከእለታት አንድ ቀን ንስሃ አባታቸው፣እቴጌ ሠብለ ወንጌልና አፄ ዮሐንስ 1ኛ በአንድ ማዕድ ቀርበው የተጠበሰ ዓሳ ይመገባሉ።አፄ ዮሀንስ ቤተ መንግስታቸው ውስጥ በሚገኘው የመኖሪያ ክፍላቸው በር ላይ እንደ ጠቢቡ ሰለሞን ሰው ሰራሽ ባህር አስበጅተው፣በባህሩም ውስጥ ዓሳ አስረብተው፣ከዚህም ዓሳ ውስጥ ተመርጦ እየተሰራ ለምግብነት ይውል ነበር።አሁንም ይሄ ሊበላ የቀረበው ዓሳ ከዚሁ ባህር የተገኘ ነው።እናም በዚህ ጊዜ ንጉሡ "ሶስታችን እውነት በንናገር ይህ የተጠበሰበ ዓሳ በህያውነት ተነስቶ እባህሩ ውስጥ ይገባ ነበር"ብለው ተናገሩ።ከዚህ በኋላ እቴጌይቱ "ቄሱን አግብቼ ብኖር እወዳለሁ"ብለው በግልፅ ተናገሩ።ቄሱም"እቴጌን አግብቼ ብኖር አመርጣለሁ " ሲሉ ንጉሱ ግን "ይችን ከንቱ አለም ንቄ ብመንን እወዳለሁ" ብለው ሶስቱም እውነት ተናግረው የየፍላጎታቸውን ተግባር እንደፈፀሙት በርካታ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።ባሉት መሠረትም የተጠበሰው ዓሳ ነብስ ዘርቶ ወደ ባህሩ ገባ ይባላል።


ይቀጥላል
የአፄ ዮሐንስ 1ኛ ዘመነ መንግስት
ክፍል-3፦
.....ቀዳማዊ አፄ ዮሐንስ ቀደም ሲል በመንፈሳዊነታቸው እና በጸሎታቸው ይታወቁ የነበሩትን የመደባይን ባላባት የገብረመስቀል ጃታማን ልጅ ሠብለወንጌልን አግብተው ይኖሩ በነበረበት ጊዜ አቤቶ ዮስጦሰን፣አቤቶ እያሱን፣ልዕልት ኢሌኒን፣አቤቶሁን ቴዎፍሎስንና አቤቶ ቆላዥን ወልደው ነበር።ስለሆነም አፄ ዮሐንስ 1ኛ አእላፍ ሰገድ ንጉሠነገስት ዘኢትዮጵያ ተብለው በነገሱ በ15ኛ አመታቸው የዚያን ዓለም ደስታ ትተው ልጃቸውን አቤቶ ኢያሱን ለትምህርት ከተላከበት ገዳም አስመጥተው በመመረቅ ብላቴን ጌታ ገብረቃል፣ብላቴን ጌታ አካለክርስቶስ፣ፀሃፌ ትዕዛዝ ወልደሐይማኖት እንዲሁም ሌሎች ባሉበት በ15ኛ አመተ መንግስታቸው ልጃቸውን አዲያም ሠገድ ኢያሱን ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ አሠኝተው በመሾም መነኑ።
ከዚህም በኃላ የፃድቁ ዮሐንስ መመነን ለማንም እንዳይነገር ራሳቸው ስለከለከሉና ስላወገዟቸው አቤቶ ቴዎፍሎስንና አቤቶ ቆላዥን ወደ ወህኒ አምባ አስወስደው ስርዓተ ንግሡን አስፈፅመው ደጃዝማች አስጦንጣንዮስ "ንጉሳችን አፄ ዮሐንስ አርፈዋልና ልጃቸውን አዲያም ሰገድ እያሡን ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ ብለን አንግሰናል" ብለው አሳወጁ።
ከዚያ በኃላም ፃድቁ ዮሐንስ በ1674ዓ.ም ሐምሌ 15ቀን በዕለተ እሁድ ሞተው ቀደም ሲል ባሠሩት በጠዳ እግዚአብሔር አብ ቤ/ያን ተቀበሩ።ቆይቶም ቅሪተ አካላቸው ተቆፍሮ ወጥቶ በጣና ደሴት በፅርሀ ፅዮን ገዳም እንዲቀመጥ ተደረገ።አፄ ዮሐንስ በዘመናቸው ምንም አይነት 'የባዕድ' ወረራና ውጊያ ሳይነካቸው ነበር የግዛት ዘመናቸው የተጠናቀቀው።
ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም

በዛሬዋ_ዕለት

ከ 93 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንግሥ በዓል ዋዜማ ፤ የንጉሠ ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለበዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ የተመረቀበት ዕለት ነበር።

የዳግማዊ አጤ ምኒልክ መታሰቢያ ሀውልት የቆመው/የተተከለው ከዛሬ 93 ዓመታት በፊት ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም ነበር፡፡

ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ የአባታቸውን የዳግማዊ አጤ ምኒልክን ስራና ውለታ ቀጣዩ ትውልድ ያስበውና ይዘክረው ዘንድ … ማስታወሻ የሚሆን የመታሰቢያ ሐውልት ለማሰራት አሰቡ፡፡

ሐውልቱንም በጀርመናዊው መሃንዲስ ሙሴ ሄንትል አማካኝነት አስጠንተው፤ ከጀርመን ተቀርፆ እንዲመጣ አዘዙ፡፡ ሀውልቱ የተመደበለት ቦታ ተደልድሎ ከተዘጋጀ በኋላ ገና ሳይተከል/ሳይቆም ንግሥቲቱ መጋቢት 22 ቀን 1922 ዓ.ም አረፉ፡፡

በመሆኑም የንግሥቲቱን እረፍት ተከትሎ ንጉሰ ነገሥት ለመሆን እየተዘጋጁ የነበሩት አልጋ ወራሽ ንጉሥ ተፈሪ መኮንን፣ ከዛሬ 93 ዓመታት በፊት (ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም) ሐውልቱ በታላቅ ክብረ በዓል እንዲተከል አደረጉ፡፡

በሐውልቱ ላይ አፄ ምኒልክ ካባ እንደለበሱ አንባር አጥልቀው በእጃቸው ጣምራ ጦር ይዘው በፈረሳቸው በ‹አባ ዳኘው› ላይ ተቀምጠው በግርማ ሞገስ ይታያሉ፡፡ የሐውልቱ ቁመት ከተፈጥሮ አካላዊ መጠን በላይ ሲሆን ‹አባ ዳኘው› ፊቱን ወደ ሰሜን መልሶ በኋላ እግሮቹ ቆሞ፣ የፊት እግሮቹን ወደላይ አንስቶ ይታያል፡፡ ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት በ 1929 ዓ.ም ወድቆ/ፈርሶ ነበር፡፡

ብርሃኑ ድንቄ ‹‹የአምስቱ የመከራ ዓመታት አጭር ታሪክ›› በሚለው መጽሐፋቸው ጣሊያኖች የአፄ ምኒልክን ሐውልት እንዴት እንዳፈረሱት እንደሚከተለው ገልፀውታል፡፡ ‹‹ … በቅድሚያ ሐውልቱ ያለበትን አካባቢ ረጅም እንጨት እየማገሩ በቆርቆሮ ሲያጥሩ ሰነበቱ …. ይህንን ያየው የአዲስ አበባ ሕዝብ ‹‹ሊያፈርሱት ነው›› ብሎ እርስ በእርሱ በሐዘን መነጋገሩን ቢሰሙ ‹‹ልናድስ›› ነው ብለው አስወሩ፡፡ ሁሉንም ነገር ካመቻቹ በኋላ ግን በየበሩ በታንክ ጭምር ጥበቃ አጠናክረው … ወደ ማታ የአራዳን አካባቢ በታንክ አጥረው በባውዛ ሌሊቱን ከተማውን እየተቆጣጠሩ በሌላ ኃይል ደግሞ ሐውልቱን ሲያፈርሱ አድረው ሲነጋጋ ወደ አልታወቀ ቦታ ወስደው ቀበሩት፡፡ ሕዝቡ እድሜና ፆታ ሳያግደው ሐዘኑን ይገልጽ እንደነበር አዛውንቶች ይመሰክራሉ …

በጊዜው የአዲስ አበባ ነዋሪ የነበረው የሃንጋሪው ዶክተር ላዲ ስላስ ላቫ እንደፃፈው፣ ሐውልቱ ከፈረሰበት ቦታ ቆመው ያለቅሱ የነበሩትን ሰዎች የጣሊያን ወታደሮች በኃይል ይበትኑ እንደነበር ገልጿል፡፡

በሌላ ዘገባ ደግሞ አንድ ሕፃን ልጅ ሲያለቅስ ጣሊያኖች ደርሰው ለምን እንደሚያለቅስ ቢጠይቁት ‹‹የንጉሱን ምልክት ስላወረዳችሁ ነው›› ብሎ እንደመለሰላቸውና ጣሊያኖችም ከሙሶሊኒ ሌላ ንጉሥ እንደሌለው በመንገር ልጁን ገርፈው እንዳባረሩት ተገልጿል፡፡ ጣሊያኖች ሐውልቱን ካፈረሱ በኋላ ሰው ሳያይ ሸፍነው በመውሰድ በታላቁ ቤተ-መንግሥት አዳራሽ ጀርባ ቀበሩት …››

የፋሺስት ወራሪ ኃይል ከኢትዮጵያ ከተባረረ በኋላም፣ ሐውልቱ ከተቀበረበት ቦታ ወጥቶ እንደገና ታድሶና ተጠግኖ ሚያዝያ 27 ቀን 1934 ዓ.ም ቀድሞ በነበረበት ቦታ እንዲቆም ተደረገ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ በ1988 ዓ.ም የአድዋ ድል መቶኛ ዓመት ሲከበር ሐውልቱ ጥገና ተደርጎለት እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

#ታሪክን_ወደኋላ
የዛሬ 93 ዓመት ልክ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም አልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪ መኰንን፤ አጼ ኃይለሥላሴ (ቀኃሥ) ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተሰኝተው በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የንግሥና ዘውዳቸውን የደፉበት ቀን ነው
#አምላካችን_ጌታችን_ቅዱስ_አማኑኤል
ጥቅምት ሀያ ስምንት በዚህች ዕለት ይቅርታው ቸርነቱ ለሁላችን ይደረግልንና ዓመታዊ በዓሉ ታስቦ የሚውለው አምላካችን ቅዱስ አማኑኤል ለንጉሥ ሣህለ ሥላሴ በሱዳን በኩል የመጣውን አንበጣ በማጥፋት ተአምር ያደረገበት መታሰቢያ በዓሉ ነው።የጥቅምት አማኑኤል በዓል አከባበር ጅማሮው እንዲህ ነው፤ በንጉሥ ሳህለ ሥላሴ አማካይነት አዲሱ ቤተክርስትያን በገባ በአምስተኛው ወር ጥቅምት 27 ቀን በ1827 ዓ.ም ብዛቱ ከወትሮው የተለየ የፀሐይ ብርሃንን መጋረድ የቻለ የአንበጣ መንጋ መላ የኢትዮጵያን ሀገራት ሸፈነ፡፡ንጉሥ ሳህለ ሥላሴም በተፈጠረው ክስተት በማዘን ለቅዱስ አማኑኤል ስዕለት በማድረግ ከወትሮው ልማዳቸው በመለየት ከዙፋናቸውም በመውረድና ልብስ መንግሥታቸውን በማውለቅ አመድ ነስንሰው ማቅ ለብሰው መዝሙረ ዳዊት እየደገሙ ፀልየዋል፡፡ በጥቅምት 27 ለጥቅምት 28 አጥቢያ ሌሊቱን ሰፍሮ ያደረው የአንበጣው መንጋ ከአደረበት ከመላው ኢትዮጵያ መሬት ለቆ በመሻገር የመን አደረ ይባላል፡፡በልማድ አንበጣ በቀን እንጂ በሌሊት ሄዶ አያውቅም፡፡ሆኖም መንጋው በሌሊት ከመሬት ለቆ በንፋስ ኃይል እየተገፋ ወደ ላይ ከወጣ በኋላ ጎህ ሲቀድ ለዓይን አልታየም፡፡ አንበጣው ወዴት እንደሄደ ሲጠየቅ የነበረውም ህዝብ "መጠቀ" ወጣ ወይም ከሀገራችን ወጣ የሚል መልስ በማግኘቱ ምክንያት "በመጠቀ" ምትክ ሚጣቅ ተብሎ አካባቢው ተሰይሟል ሌላው ሚጣቅ የተባለበት ምክንያት ደግሞ አጋንንትን ገና ከመንገድ ሳሉ መንጥቆ በማውጣት በቅፅረ ገዳሙ መግቢያ እንደደረሱ እንዲሁም በጸበሉ ፈጽሞ ከሰው ልጆች ዘንድ ያስወግዳቸዋልና ‹፣መንጥቅ አማኑኤል›› ሲሉ እንደሰየሙት አባቶች ይናገራሉ፡፡ይህ ገዳም በብዙ ስውራን አባቶች የተሞላ ነው።
📜.አቡሻኽርን የተረጎሙ ፱ኙ ሊቃውንት

፩.ሰዒድ ወልደ በጥሪቅ
፪.ማኀቡብ መንበጋዊ
፫.ሰዒዳዊያን አይሁድ
፬.ዮሐንስ አፈወርቅ
፭.ቄርሎስ
፮.ኤጲፋንዮስ
፯.ዮሐንስ ዘደማስቆ
፰.ማርቆስ ወልደ ቀንበር
፱.ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ
አቡሻክር 1.pdf
16.9 MB
አቡሻክር 2.pdf
18.7 MB
#የአለባበስ #ሥርዓት

በነገራችን ላይ ለምን እንደምትለብሱ አስባችሁት ታውቃላችሁ? ብዙ ምክንያቶች አሉት። አንደኛው ራስን ከፀሐይ፣ ከውርጭ እና ከመሳሰሉት ራስን ለመከላከል ነው። ነገር ግን የአለባበስ ሥርዓት ላይ የምናጠብቅበት ዋናው ፍሬ ምክንያት ከዝሙት ጋር የተያያዘ ስለሆነ ነው። በአለባበስ ዙሪያ ቅዱስ መጽሐፍ በተለያዩ ቦታዎች ተናግሯል። የካህናት አለባበስ፣ የሴቶች አለባበስ ተገልጿል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሴቶች ግን ራሳቸውን ይከናነቡ ለምን አለ? ሙሴስ ሴት የወንድን ወንድ የሴትን ልብስ አይልበስ ለምን አለ። የወንድ ልብስ ምንድን ነው? የሴት ልብስስ ምንድን ነው? የሚለውን እንመልከት።
                           ።
በማየት የሚመጣ ፍትወት ከሴት ይልቅ በወንድ ይጸናል። በመስማት የሚመጣ ፍትወት ደግሞ ከወንድ ይልቅ በሴት ይጸናል። ወንድ ልጅ የሴትን ገላ ካየ ፍትወት ይነሳበታል። ፍትወት ከተነሳበት ደግሞ "ወደ ሴት አይቶ የተመኘ አመነዘረ" የሚለውን የፈጣሪ ሕግ ይሽራል። ሕግ ከሻረ ደግሞ መንግሥተ ሰማያት አይገባም። በነገራችን ላይ ይህን ሰው መንግሥተ ሰማያት እንዳይገባ መሠናክል የሆነችው ሴትም መሰናክል ስለሆነች መንግሥተ ሰማያት አትገባም። ከታናናሾቹ ያሰናከለ ወዮለት ብሎ ጌታ የተናገረው ለዚያ ነው። ስለዚህ ብፁዕ ጳውሎስ ሴቶች ራሳቸውን ይከናነቡ አለ። ከዚህ ላይ ሴቶች የወንዶችን ልብስ አይልበሱ ሲል ሴቶች ሊለብሱት የሚገባ ልብስ ተብሎ የተዘረዘረ ነገር የለም። ነገር ግን ከሐዋርያው ጳውሎስ ንግግር እንደተረዳነው ተገልብቦ "መከናነብ" ራስን ላለማሳየት ነው። ስለዚህ ሴቶች በየትኛውም መስፈርት አካላቸውን የሚያንጸባርቅ ልብስ መልበስ የለባቸውም። ሰፋ ያለ ከአካላቸው ያልተጠበቀ ልብስ ሊለብሱ ይገባል። ወንድ ልጅም እንዲሁ ሴቶችን ለፍትወት የማይጋብዝ ልብስ ሊለብስ ይገባል። ልብስ የምንለብሰው እንዲያምርብን እና ሌሎችን በፍትወት ለመሳብ ብለን ከሆነ ልብሱ ምንም ይሁን ምን ሥርዓት አልባ አለባበስ ይባላል። በዋናነት ልብሱን የለበስንበትን ምክንያት እንመርምረው።
                            ።
ሌላው የወንድ ልብስ እና የሴት ልብስ የሚለውን በትውፊት እናውቀዋለን። እንደ ኢትዮጵያ ባህል ሴት ልጅ ዘረፍረፍ ያለ ሰፋ ያለ ቀሚስ ነው የምትለብስ "ቀሚስ በመልበሷም የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስን ቃል ትፈጽማለች"። በነገራችን ላይ ጥብቅ ያለ ቀሚስም ያው ሥርዓት አልባ አለባበስ ነው። ምክንያቱም የአካልን ቅርጽ ያሳያልና። ሌላው የካህናት አለባበስ በኦሪት ዘሌዋውያን በሰፊው ተገልጿል። ካህናት ጠምጥመው ልዩ ልብስ የሚለብሱት ስለ ክብረ ወንጌል ነው። እንጂ ካህናትም ይህንን አለባበሳቸውን ለተርእዮ ካዋሉት እንዲለብሱ አይፈቀድም። ቅዱስ መጽሐፍ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ይላልና። በእኛ አለባበስ ምክንያት በሌላው ፈተና ከሆንን ሌላውንም ራሳችንንም ወደ ገሐነም የምንልክ ስለምንሆን ወዮልን። ኢትዮጵያዊ መጽሐፋዊ ትውፊታዊ አለባበስ ይኑረን። የባዕድ ሀገር አለባበስ ተገዥ አንሁን። የእኛ ባህል አብዛኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ።ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከጉልበቱ በላይ ጸምር ወይም አጎዛ ብቻ ይለብስ ነበር።እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በዚህ ምድር ስትኖር ሁለት ቀሚስ ልብስ ብቻ ነው የነበራት። ዮሐንስ ወንጌላዊውን ስታርፍ በአንዱ ቀሚሴ ገንዘኝ።አንዱን ቀሚሴን ደግሞ ለአንዲት ድሃ ሥጥልኝ ብለዋለች። ልብስ ለከዲነ ዕርቃን ነው። ታላላቁ ቅዱሳንም መንገድ ላይ የሆነ ልብስ ይጥሉና ሰው ንቆ ከተወው አንስተው ይለብሱታል። አንስቶ ይዞት ከሄደ ግን ለሰው ይማርካል ማለት ነው ስለዚህ ፈጣሪየ ከመልበስ አዳነኝ ብለው ይደሰቱ ነበር። ሥለዚህ ዕርቃናችንን የሚሸፍን ጥብቅ ያላለ ሰፋ ያለ ልብስ እንልበስ።ይህ ነው ኢትዮጵያዊው አለባበስ።
የካቲት ፲፪ - የአካፋው ሚካኤል

የካቲት ፲፪ በሃገራችን ታሪክ የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን በቤተክርስቲያን ደግሞ በተለምዶ የአካፋው ሚካኤል ተብሎ ይታወቃል ።

በሁለተኛው የኢጣሊያ ወረራ ወቅት በኢትዮጵያ የፋሽስት ሹም የነበረውን ግራዚያኒን ለመግደል እነ አብርሃም ደበጭና ሞገስ አስገዶም በጣሉት አደጋ ምክንያት የተቆጣው የኢጣሊያ ጦር እንደ ግራዚያኒ ቁስለኛ የሆኑበትን የአመራሮቹንና የሞቱበትን ጥቂት ወታደሮች ደም ለመበቀል በቦታው ለምፅዋት ከተሰበሰቡት ሰዎች አንስቶ በአዲስ አበባና አካባቢዋ ያሉ እስከ ፴ ሺ የሚደርሱ ዜጎችን በዘግናኝ ሁኔታ በአካፋ ሳይቀር ያገኙትን መሳሪያ ሁሉ እየተጠቀሙ ጨፈጨፏቸው።

በየአብየተ ክርስቲያኑ ደጃፍ የቅዱስ ሚካኤልን ወርኃዊ የበዓል መታሰቢያውን ለማድረግ በጠዋት የወጡ ምዕመናን ሬሳቸው እንደቅጠል ረገፈ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ በመቶዎች የሚቆሩ የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት አርበኞችን ደብቃችኋል ተብለው በገዳማቸው ተረሸኑ።

ፋሺስት ጣሊያን ሕዝቡን ለመጨፍጨፍ አካፈን ተጠቅማ ስለነበርና በየሜዳው የወደቀውን አስከሬን በአካፋ እየተሰበሰበ በጅምላ ስለተቀበረ ቀኑ የአካፋው ሚካኤል ተባለ።

እነሆ ዛሬ ይህ ታሪክ ፹፯ ዓመታት ሞልቶታል።ቤተ ክርስቲያን ከነፃነት ማግስት ጀምሮ በየዓመቱ አጽማቸው ተሰብስቦ በክብር ባረፈበት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ውስጥ ባሉት ሁለት ሐውልቶቻቸው ዙሪያ በጸሎተ ፍትኃት ታስባቸዋለች።
2025/01/04 00:11:46
Back to Top
HTML Embed Code: