tgoop.com/yemariyam2121/1171
Create:
Last Update:
Last Update:
✞ኢትዮጵያ እጅሽን ዘርጊ✞
ኢትዮጵያ እጅሽን ዘርጊ ወደ አምላክ ወደ አዶናይ
ሕዝብሽን ከሞት የሚያድን ይውጣልሽ የምኅረት ፀሐይ
ሕፃናት ወላጆች አጥተው በሜዳ ሲበታተኑ
ንስሮችሽ ወጣቶች አልቀው የአፈር ሲሳይ ሲሆኑ
የሞት መልአክ ተልኮብሽ መሬትሽ አጣ ጸጥታ
ቁጣውን እንዲመልሰው ለምኚ ለሰማይ ጌታ
አዝ= = = = =
ታማሚው እያጣጣረ ጤነኛው ቆሞ ሲፈራ
አምላክሽ ይቅር ይበልሽ ይለፍሽ ይህን መከራ
አበውን ይዘሽ ተነሽ ጸሎትሽን ቆመሽ አድርሽ
ያብርደው እሳት ንዳዱን በምልጃሽ በልመናሽ
አዝ= = = = =
ልጆችሽ ቅጣት ቀጥቶአቸው እንዲያዩ ወደ አምላካቸው
መከራው ትምህርት ሆኖአቸው ይመለስ ታካች ልባቸው
የበደልነውን ታግሶ ቁጣውን እርሱ መልሶ
ይማረን ይቅር ይበለን ምኅረቱን አስታውሶ
አዝ= = = = =
አሕዛብ ተነጋገሩ አምላክሽን ረሳሽ ብለው
ልጆችሽ ሞት ሲፈጃቸው እያዩ እጅግ ተገርመው
ጉልበትሽ እንዳይሰበር ምርኩዝሽ እርሱ ነውና
ደዌ ቸነፈሩን ያርቅ አቅርቢ ጽኑ ልመና
በሊቀ መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
"ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።"
BY 💎የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች
Share with your friend now:
tgoop.com/yemariyam2121/1171