tgoop.com/yenetube/52847
Last Update:
በአፋር ክልል ነዳጅ ጭነው ተደብቀው የቆሙ ቦቴዎች መያዛቸውን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ!
አዲስ አበባን ጨምሮ ለተለያዩ ክልሎች የሚጓጓዝን ነዳጅ ይዘው በአፋር ክልል ልዩ ቦታው ሰርዶ አድማስ በሚባል ቦታ 'በየጥሻው' የቆሙ ቦቴዎች ተደብቀው በቆሙበት መያዛቸውን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡በአፋር ክልል ንግድ ቢሮ ትብብር የፀጥታ አካል ባደረገው አሰሳ የተያዙት ተሽከርካሪዎቹ የክልሉ ንግድ ቢሮ ለተሸከርካሪዎቹ እጀባ በመስጠት ወደ የመዳረሻቸው እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል ተብሏል፡፡
ባለስልጣኑ ትናንት ባወጣው መግለጫ በወሩ መጨረሻ የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ይሠራል በሚል ያልተጨበጠ ተስፋ ነዳጁን ይዘው የተሸሸጉት እነዚህ ተሸከርካሪዎች ያለአግባባ የሚያገኙትን ትርፍ ከማሰብ ውጪ የጫኑት ነዳጅ በባህሪው በትነት የሚባክን፣ አደጋን የማስከተል አቅም ያለው መሆኑን ለማሰብ አልፈቀዱም ብሏል፡፡
ከዚህ ባለፈ በየክልል ከተሞች የነዳጅ ማደያዎችን በማድረቅ እጥረት በመፍጠር ህብረተሰቡን የማጉላላት ስራን መስራታቸውን ማመን አይፈልጉም ሲልም ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ተግባሩን በፈጸሙት ላይ መንግስት ለህብረተሰብ ተጠቃሚነት ሲል በድጎማ የከፈለበትን የነዳጅ ወጪ እንዲሸፍኑ የሚደረግ እንደሆነ እና ከምርት መሰውር ጋር በተያያዘ በሕግ ተጠያቂ የሚደረጉ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
በነዳጅ ግብይት ሂደት ውስጥ የሚፈፀሙ ሕገ-ወጥ ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መመጣታቸውን የገለጸው መግለጫው ነዳጅ የጫኑ ተሸከርካሪዎች በየቦታው እንዲዘገዩ በማድረግ ተጨማሪ ትርፍ ለማግኘት ተስፋ በማድረግ ተጠቃሚውን ህብረተሰብ የማጉላላት ተግባር ይፈጽማሉ ሲል ከሷል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
BY YeneTube
Share with your friend now:
tgoop.com/yenetube/52847