tgoop.com/yisakgizaw/6898
Last Update:
ሰዓቱን አየ፤ከቤተመንግሥት አንጋች ላይ የመነተፈው ነው፡፡
የተገላበጠ ሆዱን ለማስከን አንድ ሁለት ሲኒ ቡና ለመጠጣት የሚበቃ
ጊዜ ስላለው ወደ ቡና ቤት ሄደ፡፡
ቡናውን ፉት ሲል ልብ የምትሰርቅ ሴት ወደ ቡና ቤቱ ዘው አለች።
ያማረ ልብስ ለብሳለች፡ እድሜዋ ወደ ሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገመት
በመሆኑ ከሄሪ አስር አመት ብትበልጥም አየት ስታደርገው ፈገግ አለ፡፡
ሴትዬዋ ከሄሪ ቀጥሎ የሚገኝ ጠረጴዛ ይዛ ቁጭ አለች። ባለ ነጠብጣቡ
ልብስ እንዴት ሰውነቷ ላይ ልክክ እንዳለ አስተዋለ፡ ፈዘዝ ያለ ብጫ ጫማ
የተጫማች ሲሆን የሰሌን ባርኔጣ አናትዋ ላይ ደፍታለች፡ ጠረጴዛው ላይ
ትንሽ ቦርሳ አስቀምጣለች፡፡
ወዲያው ጃኬት የለበሰች ሰው መጥቶ አጠገቧ ተቀመጠ፡፡ ሲነጋገሩ ሰማና
ሴትየዋ እንግሊዛዊት ሰውየው አሜሪካዊ መሆናቸውን አወቀ፡፡ የሴትየዋ ስም ዳያና የሰውየው ደግሞ ማርክ እንደሆነ አረጋገጠ ሰውየው ክንዷን ሲደባብስ
ደረቱ ላይ ልጥፍ አለች። በፍቅር ስለታወሩ ለማንም ቁብ የላቸውም፡፡ ቡና
ቤቱ ለእነሱ ማንም የለበትም፡
ሄሪ በቅናት ተንጨረጨረ፡፡
ሄሪ ፊቱን አዞረ፡ ሆዱ አሁንም በፍርሃት እየታወከ ነው: አትላንቲክን በሙሉ በአየር ሊያቋርጥ ነው፡፡ ከስር ምንም መሬት ሳያዩ ረጅም ጉዞ ማድረግ ሲታሰብ ያስጨንቃል፡፡ ሄሪ የአየር ጉዞ ሳይንስ አይገባውም፡፡የአይሮፕላኑ ሞተሮች ይሽከረከራሉ፤ ታዲያ አይሮፕላኑ ወደ ሰማይ የሚመነጠቀው እንዴት ነው?!
ማርክና ዳያና የሚነጋገሩትን እያዳመጠ የተረጋጋ ለመምሰል ጣረ፡ ሌሎቹ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪዎች መጨነቁን እንዲያውቁበት አልፈለገም
‹እኔ ቫንዴርፖስት ነኝ ሲል አሰበ፡፡ አውሮፓ ጦርነት ስለሆነ ወደአሜሪካ የሚመለስ ወጣት አሜሪካዊ ነኝ አሁን ስራ ባይኖረኝም አንድ ገገር መስራት አለብኝ አባቴ ኢንቬስተር ሲሆን እናቴ ነፍሷን ይማረው እንግሊዛዊት ናት ዩኒቨርሲቲ አልገባሁም፧ እንግሊዝ አገር ብዙ ስለቆየሁ የአካባቢው ቋንቋ ተዋህዶኛል፡፡ ጥቂት ጊዜ በአይሮፕላን ሄጃለሁ አተላንቲክ አቋራጭ
የመጀመሪያዬ ነው፡፡ ጉዞዬን
በጉጉት እየተጠባበቅሁ ነው፡›
ቡና ጠጥቶ ሲጨርስ ፍርሃቱ ውልቅ ብሎ ሄደለት፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኤዲ ዲኪን ስልኩን ዘጋና ዙሪያውን ቃኘ፡፡ የተነጋገረውን ማንም የሰማ የለም ችግር ውስጥ የከተተው ስልክ ላይ አፈጠጠ፡ ጠላው፡፡ የቀን ቅዠቱን የሚያጠፋለት ይመስል ስልኩን ሊሰባብረው ተመኘ፡፡ ከዚያም ቀስ ብሎ ዞሮ ሄደ፡፡
‹‹እነማን ናቸው? ካሮል አንን የት ነው የወሰዷት? ምንድነው ከሱ
የሚፈልጉት?›› ልክ ደንበጃን ውስጥ እንደገባ ዝምብ ጥያቄዎቹ አእምሮ ውስጥ ጥዝዝ አሉ፡ ለማስታወስም ሞከረ፡ በአንድ ጊዜ አንድ ጥያቄ ብቻ ማተኮር ፈለገ፡፡
«ማናቸው? እንዲያው እብዶች ናቸው? አይደሉም: የተደራጁ ናቸው
ኤዲ የት እንደሚሆን አውቀው ካሮል አንን አግተው ይዘው በተገቢ
ሰዓት ከሚስቱ ጋ እንዲነጋገር ለማድረግ በጥንቃቄ አቅደዋል፡ ሰዎቹ ቀላል ሰዎች አይደሉም፡፡ ለዚህ ደግሞ ህግ ለመጣስ ዝግጁ ናቸው፡፡ ከወሮበሎች ጋር እንደተጋፈጠ ተረድቷል፡፡
ካሮል አንን የት ነው የወሰዷት? ቤት ውስጥ ነው ያገቱኝ› ብላለች።
የአንዱ አፋኝ ቤት ይሆናል፤ ወይም ቤት ተከራይተው ይሆናል፡ አሊያ
ሰው የሌለበት ቦታ ወስደዋታል፡፡
ካሮል እንዳለችው ያገቷት ከሁለት ሰዓት በፊት ነው፡፡ ከባንጎር ከሰላሳ
ወይም ከሰባ ማይል አይርቅም፡፡
«ለምን አገቷት? አንድ ነገር ከሱ ፈልገዋል በፈቃደኝነት
የማይሰጣቸው ነገር ለገንዘብ ሲል የማያደርገውን አንድ ነገር፡፡ ገንንዘብ የለውም፡፡ ምንም የሚያውቀው ምስጢር የለም፡ በእሱ ቁጥጥር ስር ሰው የለም፡፡ ስለዚህ ጉዳያቸው ባህር ላይ እሚያርፈው አይሮፕላን "
የተያያዘ መሆን አለበት፡፡
መመሪያ ቶም ሉተር ከሚባል አይሮፕላኑ ላይ ከተሳፈረ
እንደሚሰጠው ተነግሮታል፡፡ ሉተር ስለ አይሮፕላን አንቀሳቃሽ ክፍሎች
በሚያውቅ ሰው የተቀጠረ ሰው ይሆናል፡ ሌላ በዚህ አይሮፕላን ላይ
ሊኖረው የሚችለው የአየር መንገድ መስሪያ ቤት ምናልባትም የውጭ አገር መስሪያ ቤት ይሆናል፡፡ ነገር ግን የዲዛይኑን ኮፒ ማግኘት የሚችሉበት ቀላል መንገድ አለ፤ እንደዚህ አይነቱን ሰነድ ብዙ ሰው ሊሰጣቸው ይችላል! የፓን
አሜሪካን አየር መንገድ ሰራተኞች፣ የቦይንግ ኩባንያ ሰራተኞች፣ እዚህ
ያሉት የኢምፔሪያል አየር መንገድ መካኒኮች፡፡ የቴክኒክ ዝርዝሮች ደግሞ በየመጽሔቱ ላይ ይወጣል፡፡ ሰው ማገት አያስፈልግም ነበር።
ወይስ አንድ ሰው አይሮፕላኑን ከነነፍሱ ሊወስደው ያስባል፡
ሌላ ሊሆን የሚችለው ምክንያት ኤዲ አንድ ሰው ወደ አሜሪካ
ለማስገባት እንዲያግዛቸው ነው፡:
ለጊዜው ሊገምት የቻለው እነዚህን ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ ምንድነው ማድረግ ያለበት?
ኤዲ ለህግ ተገዥ ሰው ነው፡፡ አሁን የወንጀል ሰለባ ሆኗል፧ እናም
ፖሊስ መጥራት ፈለገ፡፡ ነገር ግን ፈራ፡፡ በህይወቱ እንዲህ ፈርቶ
አያውቅም፡፡ በልጅነቱ አባቱንና ሰይጣንን ብቻ ነበር የሚፈራው፡፡ ከዚያ ወዲህ ግን የሚያስፈራው ነገር አልነበረም፡፡ አሁን አቅመ ቢስ ሆኗል፡፡ሰውነቱ ደነዘዘ፤ ከቆመበት መንቀሳቀስ አቃተው፡፡
እንግሊዝ ውስጥ ስላለ ለእንግሊዝ ፖሊሶች የሚያሳውቅበት ምክንያት
የለውም፡፡ ወደ አሜሪካ ፖሊስ ወይም ኤፍ ቢ አይ ስልክ ደውሎ በቅርቡ የተከራየ ገንጠል ያለ ቦታ ላይ ያለ ቤት በሙሉ እንዲያስሱ ሊነግራቸው ተመኘ።
‹‹ለፖሊስ ስልክ እንዳትደውል፤ አይረባህም›› ብሎታል በስልክ
የተንቆረቆረው ድምጽ፡ የምትደውል ከሆንክ ምን ያህል ክፉ እንደሆንኩ
እንድታውቅ፤ ሚስትህን እደፍራታለሁ!›› ብሎታል፡፡ ኤዲም አመነው ማድረጉ እንደማይቀር ከድምጹ አውቋል፡ የሆዷ ሞላ ማለትና የጡቷ መወጣጠር ካሮል አንን የምታማልል አድርጓታል፡፡ እጁን ቡጢ ጨበጠ፤ ነገር ግን ከግድግዳው በስተቀር የሚመታ ነገር የለም፡፡
ኤዲ ተራ ሰው ነው፤ የተወለደው ከባንጎር ወጣ ያለ ገጠር ውስጥ
ነው፡፡ አባቱ አርሶ አደር ሲሆኑ የበሬ ግምባር የምታክል የድንች ማሳ፣
በጣት የሚቆጠሩ ዶሮዎች፣ አንዲት ላምና የጓሮ አትክልት ነበራቸው፡ ኒው ኢንግላንድ ስቴት አሜሪካ ውስጥ በድህነት መኖር ከባድ ነው፡፡ ክረምቱ አለቅጥ ረጅም ሲሆን በጣም ይበርዳል፡ አባቱና እናቱ እግዚአብሔር ያመጣው ነው ይላሉ፡፡ የኤዲ ታናሽ እህት በሳምባ ምች ስትሞት እግዚአብሔር እኛ የማይገባን ምክንያት ስላለው ነው ብለዋል፡ በልጅነቱ ጫካ ውስጥ የተቀበረ ሃብት አገኛለሁ እያለ በቁሙ ያልም ነበር፡ ያ የገጠር
ቤታቸው ምቾት ወደ ተሞላበት እና ደስታ ወደነገሰበት ቦታ ሲለወጥ በዓይነ ህሊናው ይታየው ነበር፡ የተመኘውን ሀብት ባያገኝም በየቀኑ በእግሩ እየኳተነ የተማረበትን ዕድል አላጣም፡፡ ትምህርት ቤቱ ከቤቱ ይልቅ ይሞቅ ስለነበር ይወደው ነበር፡፡ አስተማሪው ደግሞ
መሳሪያዎች እንዴት እንደሚሰሩ ይጠይቃት ስለነበር ትወደው ነበር፡፡
ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ አናፖሊስ ባህር ኃይል ማስጠኛ ገባ
ማሰልጠኛው ለእሱ ገነት የመግባት ያህል ነበር፡፡ መኝታው የተሟላ ምግቡ ለሱ ጥሩ ነው። እንዲህ አይነት ቅንጦት በህይወቱ ሙሉ አልሞ አያውቅም የማሰልጠኛው ጥብቅ ደምብ ለእሱ ቀላል ነበር፡ በመጠኑ በትምህርት
BY 📚 Book center የመፅሐፍት ማዕከል 📚
Share with your friend now:
tgoop.com/yisakgizaw/6898