tgoop.com/youthkiper/11384
Last Update:
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሥራውን ለመጀመር ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ
ሀዋሳ፡ መስከረም 28/2013 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሥራውን ለመጀመር ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ከትምህርት ሚኒስቴር የመጣው ግብረ ሀይል የዩኒቨርሲቲውን ቅድመ ዝግጅት ተመልክቶ ግብረ መልስ ሰጥቷል፡፡
ከ2012 አጋማሽ ጀምሮ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት የመማር ማስተማር ሥራው በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መቋረጡ ይታወሳል፡፡
በዘንደሮ የትምህርት ዘመን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማር ሥራቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ከትምህርት ሚኒስቴር በወረደው መመሪያ መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ይነገራል፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲም ከሣይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከመጣው ግብረ ሀይል ጋር ቅድመ ዝግጅቱ ያለበትን ደረጃ ተመልክቷል፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ ዩኒቨርሲቲው ከጥቅምት 20 ጀምሮ 4571 ተመራቂ ተማሪዎችን ተቀብሎ በሁለት ወራት ውስጥ ቀሪ ሥራዎችን በማጠናቀቅ እንደሚያስመርቅ ገልፀዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የመማሪያ፣ የመኝታና የመመገቢያ እንዲሁም ከግቢው ውጭ የሚደረጉ የተማሪዎች እንቅስቃሴዎች ለኮሮና በማያጋልጥ መልኩ መሆን እንዳለበት ከመግባባት ላይ መደረሱን ዶ/ር ዳምጣው ጠቀመዋል፡፡
@youthkiper
BY ወጣቱ ና ሙዱ
Share with your friend now:
tgoop.com/youthkiper/11384